ሰዋስው/@zsewasw


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Лингвистика


ሰዋስው

# ሰዋስው ማለት መሰላል ነው።
መሰላል የማይደርሱበት ነገር ተጠቅመው እንዲቻል እንደሚያደርጉት ሁሉ በዚህም ቻናል ችግር የሚባል ነገርን አስወግዳችሁ ወደ መልካም ነገር የምትወጡበትን ትምህርት ታገኛላችሁ።
እኔን ለማግኘት የሚፈልግ ሁሉ
+251934636523


Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Лингвистика
Статистика
Фильтр публикаций


ወዳጄ ሰላም🍒

"ጥቅም ለማግኘት ብለህ የተዋጋኸው ውጊያ በመጨረሻ ባለጠጋ እንጂ ባለ ኒሻን አያደርግህም ። ከገንዘብ ክብር እንደሚበልጥ ተረዳ ። የረዳህን እግዚአብሔር አልሰጠኝም ብሎ ማማት ነውና እያለህ ከሌላቸው ጋር አትሻማ ። የሌለህን ስትመኝ ያለህን እንደምታጣ ተገንዘብ ። ግማሽ ደግነት የክፋት ያህል ነውና ለጉዳይህ ብለህ ቸር አትሁን ። የጎደለ እንስራና ባዶ አዳራሽ ድምፅ ያበዛሉና በእውቀትና በመንፈሳዊነት ሙሉ ሁን"

ዘሰዋስው


https://t.me/ZSewasw


ወዳጄ ትዕግስት

"ጥልቁን ያላየ ምጥቀት ላይ ቢወጣ እንደ ቀላል ይቆጥረዋል። የሁሉም ነገር መነሻም ያ እየመሰለው አያመሰግንም። መጨረስ ያልቻሉትን አትውቀስ ፣ አንተ ገና አልጀመርህምና ። የሸመገሉትን አትሳደብ ፣ ትደርስበታለህና። ልጅነትህን አትውቀስ አትመለስበትምና። በጥቁር ፀጉርህ ትዝታ አትኑር ፣ ሽበቱን አታጌጥበትምና። በሚያዝኑት አትሳለቅ ፣ አንተ ትንሹ ቢደርስብህ ትወድቃለህና። በሚሰደዱት አትፍረድ ፣ አንዳንዴ አገር ከሲኦል ይከፋልና። በባዕድ አትቀየም ፣ ወገንህ እየገደለህ ነውና። ወጣቶችን ኰናኝ አትሁን የሰጠሃቸው የለምና።"

ዘሰዋስው

https://t.me/ZSewasw
ወዳጄ ሆይ !

"ሰውን በልብሱና በቤቱ ትልቅ ነው ብለህ አትለካው ። የሰዎችን ምሥጢር ለማወቅ አትጓጓ ። የተሸከመህን መሸከም ክብር ነው ። ሰውን በደንብ እስክታየው የእንስሳት ፍቅር አይገባህም ። ና ብሎ ዕዳ እንዲሉ መለወጡን ሳታይ የቀድሞ ባለጌን አትጥራ ። ወደ ኋላ ለምስጋና ፣ ወደፊት ለግብ ተመልከት ። በዓለም ላይ ሦስት ርካሽ ሰዎች አሉ ። አራተኛውን ግን መሬት አይችለውም ። ተሰጥቶአቸው የማያውቁበት ፣ የነበሩበትን የረሱ ፣ በሰው ውድቀት የሚስቁ ርካሾች ሲሆኑ አራተኛው ግን አምላኩን የካደ ነው ። ሰዓቱ አለፈ ብለህ ከንስሐ አትዘግይ ፤ በሕይወት እስካለህ የንስሐ ዕድል መሆኑን ተረዳ ። እግዚአብሔር ሲደርስ የባከኑ ዘመኖችን ይክሳል ። ሰይጣን የሚፈትንህ ትዕግሥት እንድታጣ ነው ፤ ከዚያ በኋላ የምትወድቀው አንተ ነህ ። አዳም አንድ ጊዜ በሰይጣን ተፈተነ ፣ ውድቀቱ ግን ውድቀት እየወለደ ሲንከባለል ኖረ ። እንደ ጠበቅከው አለመሆኑ ሰው የመሆንህ መገለጫ ነው።"

ዘሰዋስው
https://t.me/ZSewasw


Репост из: Now Button Bot
የአምላክ እናት ቅድስት ድግል ማርያምን ትወዳላችሁ

👇👇👇👇👇👇


በመጽሐፋቸው ሕይወትን እድናውቅ ከሚያደርጉኝ አባቶች በዚህ ቅርብ ዓመታት የነበሩት አቡነ ሽኖዳ ናቸው።
መጽሐፋቸው ሰዎች በቀጥታ መንፈሳዊ ሕይወት ላይ በልምምድ እድናድግ የሚያደርጉ ናቸው። ለዛሬ አንብቤ ብዙ ያተርፍኩበትን መጽሐፍ ጋበዝኳችሁ።
"ጉዞ ወደ እግዚአብሔር"

ከቻላችሁ መጽሐፉን ገዝታችሁ አንብቡት

ዘሰዋስው
https://t.me/ZSewasw
ወዳጄ ልብ❤

ነብዩ ዳዊት እግዚአብሔርን የለመነበት የኑዛዜ ማዕከሉ አቤቱ ንጹሕ ልቡና ፍጠርልኝ የሚል ነው።ምክኒያቱም ያለ ንጹሕ ልብ እግዚአብሔርን ማየት አይቻልም። የልብን መስታወት መወልወል የሚችል እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ብቻ ነው። " ነቢያት ልባቸውን ንጹሕ በማድረግ እግዚአብሔር አይተውታልና ፊት ከፊትም ተነጋገረውታል"ቅዳሴ ማርያም።  ስለዚህ ንጹሕ ልብን ፍጠርልኝ ትልቅ ጸሎት ነው። ንጹሕ ልብ ማግኘት ላለፈው ስርየት ነው።ንጹሕ ልብ ማግኘት ለሚመጣውም መጠበቅ ነው። ስህተቶችን ከማንድግማቸው መንግዶች ውስጥ አንዱ ንጹሕ ልብ ነው።ንጹሕ ልብ ካለን ያደረገውን ክፋት አንደግመውም ንጹሕ ልብ በሌለበት ኑዛዜ ጭቃ ላይ ተቀምቶ እንደመታጠብ ነው።
ዲን አክሊል ዘሰዋስው

https://t.me/ZSewasw
ወዳጄ ሆይ !!

“የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው፤ የዓለም ሰዎች ጅማሬያቸው ሰይጣንን መፍራት ነው። እግዚአብሔርን የሚሰማ በእርጋታ ይቀመጣል፥ ከመከራም ሥጋት ያርፋል ዓለምን የሚሰማ በመከራ ጥፊ እየተመታ ሲጮኽ ይኖራል። ክፉ በመስራት ደስ ከሚላቸው ራቅ አብረህ ስትሆን የክፉዎችን ብዛት ቁጥሩ ከፍ እንዲል አስተዋጽኦ እያደረክ ነው። ቃሏን ከምታለዝብ ሴት በቃሉ ከሚደልል ወንድ ለዝሙት ፍላጎት ካለው ሰው ራቅ/ቂ አካሄዳቸው ወደ ሞት ያዘነበለ ነውና
ዲን አክሊል ዘሰዋስው

https://t.me/ZSewasw
💥ቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ነጎድጓድ💥

እንደ እኛ አፈር ስትሆን ከመላእክት በላይ ከንፈህ ዕመቀ መለኮቱን የቀዳህ። የሃይማኖት ንሥር ሆይ እንደ ንሥር እስከ ሕዋ አልበረርክም። ወይም እንደ ከዋክብት እስከ ጠፈር ተወርውረህ አልበቃህም። ወይም እንደ ባቢል ነፋስ ሐኖስ ላይ አልቆክም። ወይም እንደ ሊቃናት በኤረር አልተወሰንክም። ወይም እንደ አርባብ በራማ ላይ አልበቃህም። ወይም እንደ ኃይላት ኢዮር ላይ አላበቃህም። ወይም እንደ ኪሩቤል መንበሩ ሥር አይኖችህን በክንፎቹ ሸፍነህ አልቀረህም። ወይም እንደ ሱራፌል አክሊልህ አውርደህ መንበሩን አጥነህ አልተመለስክም፡፡ ሰረገላ እሳቱን አልፈህ መጠቅ እንጅ! የመንበሩ ጫፍ ላይስ መች በቃህና ማንም ሊቀርበው የማይችለውን ነደ እሳት ቀረብከው። ወደ ልቡም ገባህ። በምስጢረ መለኮቱ ሰጠምክ። ያንንም የቀዳሃውን የሃይማኖት የመለኮት ምስጢር ለቤተክርስቲያን አፈሰሰክ። የተጠሙ ልጆቿም ከእርሱ ጠጥተው የመለኮት ልጆች ሆኑ፣በምስጢር ማዕበል እረኩ።
አንተ የመለኮት ምስጢር አባት ሆይ ለአንተ ወደተገለጠ ወደዚያ ምስጢር እንደርስ ዘንድ በአባታዊ ጸሎትህ አድርሰን
እንኳን አደረሳችሁ🙏
#ዲን_አክሊል_ዘሰዋስው
04-05-15 ዓም
https://t.me/ZSewasw


✔"ከንጽሕት ድንግል ማርያም በኋላ ዘመን እንደተወለደ እንደሚነግሩን ቀድሞም ከአብ እንደተወለደ እንዲሁ ከአባት ያለ እናት፤ከእናት ያለ አባት ለመወለድ መጀመሪያ እርሱ እንደሆነ ለፍጥረት ሁሉ ይነግሩናል" ሄሬኔዎስ የሐዋርያት ደቀመዝሙር

✔አይታይ የነበረው የሚታይ ሥጋን ተዋሐደ። የማይለወጥ እርሱ በሚለወጥ ሥጋ ተዳሠሠ። የማይለወጥም አደረገው።ባዕል እርሱ ከሌዊ ወገን በተወለደች በድንግል ማኅፀን አደረ።ሰማይን በደመና የሚሸፍን እርሱ በጨርቅ ተጠለለ፤ የነገሥታት ንጉሥ በበረት ተጣለ"አጢፎስ የሐዋርያት ደቀመዝሙር

አንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ።
ዘሰዋስው


ወዳጄ ሆይ!
የእምነት ማጠር እንጂ የቁመት ማጠር እግዚአብሔርን ከማየት አይከለክልም። ያለበት ድረስ መሄድ ቢያቅትህ ያለህበት ድረስ ሊፈልግህ የመጣውን አምላክ አክብር። በአፋቸው ከጸደቁ በልባቸው ክፋት ከያዙ ተጠበቅ። ጌታ ፣ ጌታ ከሚሉ በኑሮአቸው የጥላቻና የስግብግብነት አዳራሽ ከሆኑ ዘመናይ ተጠንቀቅ። የጥንቱን ኢየሱስ ዛሬ የተገኘ አስመስለው ከሚያወሩ ግብዞች ራቅ። በዋጋ የተቀበልከውን ሃይማኖትህን በነጻ አትሽጥ።

ዲን አክሊል ዘሰዋስው

https://t.me/ZSewasw

Показано 20 последних публикаций.