Фильтр публикаций










(ዘ-ሐበሻ ዜና) የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፖሊስ ትናንት በፃፈው ደብዳቤ ህወሀት ያካሄደውን ህዝባዊ ኮንፈረንስ ተከትሎ በኮንፈረንሱ የተላለፉ ውሳኔዎችን ለመደገፍ በሚል ዛሬ ጥር 18 ሰላማዊ ሰልፍ ለማካሄድ ጥያቄ እንደቀረበለትና ባለው ሁኔታ "የፀጥታ ሽፋን መስጠት ስለማይቻል ሰልፉን ለሌላ ጊዜ እንዲያስተላለፉት ማሳሰቢያ" ቢሰጥም፣ ሰላማዊ ሰልፉ ግን በትግራይ የተለያዩ ከተሞች ዛሬ እየተካሄዱ መሆናቸውን ከስፍራው የወጡ መረጃዎች አመልክተዋል።
ሰልፎቹ እየተካሄዱባቸው ካሉባቸው ከተሞች መካከል መቀሌና ሽሬ የሚጠቀሱ ሲሆን፣ ሰልፈኞችም የተለያዩ ጥያቄዎችን አንስተዋል።
ከነዚህም መካከል "የፕሪቶሪያ ስምምነት መፈፀም ለትግራይ እና ለአፍሪካ ቀንድ ህዝቦች የሰላም ዋስትና ነው!"፣ "ህወሀት ያካሄደውን ህዝባዊ ኮንፈረንስ፣ ድርጅታችን ህወሓት እና የትግራይ ሰራዊት ያሳለፏቸው ውሳኔዎች በአስቸኳይ ተግባራዊ መሆን አለባቸው!!"፣ "የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር በአስቸኳይ ሊስተካከል ይገባል!!"፣ "የፕሪቶሪያው ስምምነት አሁኑኑ ተግባራዊ ይደረግ"፣ " የተፈናቀሉ እና የተፈናቀሉ ወገኖቻችን በአስቸኳይ ወደ ቤታቸው ይመለሱ!!"፣ "የፓርቲያችን ሕጋዊ እውቅና በአስቸኳይ ይመለስ!!"፣ "ሰራዊታችንን የማፍረስ ሴራ አንቀበልም!!"፣ "የውጭ ጣልቃ ገብነቶችን እንቃወማለን" የሚሉና ሌሎችም መፈክሮች እየተሰሙ ነው።


እንደምን አደራችሁ !!

የአገው ምድር ፈረሰኞች 85ኛ በዓል ጥር 23 በበዓሉ እንዲታደሙ ተጠርተዋል።
💚💛❤






ባሕር ዳር ሰባር ጊዮርጊስ ዓመታዊ በዓል ነገ ይከበራል !!

ጥርን በባሕርዳር በልዩ ልዩ ሀይማኖታዊና ባህላዊ ትርኢቶች በታላቅ ድምቀት እንደቀጠለ ነው ።




በዚህ ሳምንት በከፍተኛ የሰራዊት አዛዦችን ስም የተሰጠው መግለጫ የትግራይ ሰራዊት ወይም ጊዜያዊ አስተዳደር አስተያየት እና ውሳኔ አይደለም። የትግራይ የፀጥታ ኃይል፣ የጊዜያዊ አስተዳደሩ ካቢኔ እና የትግራይ ህዝብ ፍላጎት በሰላማዊ መንገድ በመታገል የፕሪቶሪያ ስምምነትን በተሻለ ሁኔታ ተግባራዊ በማድረግ በተለያዩ ኃይሎች ሥር ሆኖ እየተሰቃየ ያለው ህዝባችን ነፃ ማውጣት፣ የተፈናቀሉ ወገኖቻችን ወደ ቀዬአቸው መመለስ፣ ሕገ መንገስታዊ የትግራይ ወሰን ወደነበረበት እንዲመለስ ማድርግ ነው። ይህ በከፍተኛ የጦር አዛዦች ስምየ ወጣው መግለጫም በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ካቢኔ በጥልቀት ተመርምሮ ውድቅ ተደርጓል። የፌደራል መንግስትም እንደ‍ኢሁ የፕሪቶሪያ ስምምነት በትክክል ተፈፃሚ እንዲሆን እና የሰላም ሂደቱን ዋስትና አስተማማኝ በማድረግ በተለያዩ ኃይሎች እየተሰቃየ ያለው ህዝባችን ነፃ እንዲወጣ፣ በግፍ የተፈናቀሉ ወገኖቻችን ወደ ቀዬአቸው እንዲመለሱ፣ የትግራይ ሕገ-መንግስታዊ ወሰን እንዲከበር፤ በአጠቃላይ የፕሪቶሪያ ስምምነት በአግባቡ እንዲፈፀም የተሟላ ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪያችንን እናቀርባለን።

መልእክት ለዓለም አቀፍ ማሕበረሰብ
የትግራይ ህዝብና ጊዜያዊ አስተዳደር ፍላጎትና ምኞት ሰላም ነው። ለዚህም ነው በፕሪቶሪያ ስምምነት አተገባበር ላይ በርካታ ችግሮችና ፈተናዎች ቢያጋጥሙንም ጥያቄዎቻችንን በሰላማዊ የፖለቲካ ትግል ለመፍታት ከኢትዮጵያ መንግስት እና ከዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ጋር ተቀራርበን እየሰራን ያለነው። አሁን ግን በወገኖቻችን ላይ እየደረሰ ያለው ስቃይ እጅግ የከፋ ከመሆኑ የተነሳ ሁኔታው ከቁጥጥራችን ውጭ ሊወጣ ይችላል። ስለሆነም የፕሪቶሪያ ስምምነት በተሻለ ሁኔታ ተግባራዊ ለማድረግ የተሟላ ድጋፍ እንዲታደርጉ ጥሪያችንን እናቀርባለን። በዚህ ሳምንት በከፍተኛ የሰራዊት አዛዦች ስም የወጣው መግለጫ የትግራይ ሰራዊትም ሆነ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር የማይወክል ውሳኔ መሆኑን በዚህ አጋጣሚ ማረጋገጥ እንሻለን። ይህ በእንዲህ እንዳለ የፕሪቶሪያ ስምምነት በተሻለ ሁኔታ ተግባራዊ እንዲሆን እና የትግራይን ሰላም አስተማማኝ ለማድረግ ሕጋዊ እና ሞራላዊ ግዴታችሁን እንዲትወጡ በድጋሚ ጥሪያችንን እናቀርባለን።

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ካቢኔ
ጥሪ ቀን 20


ከትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ካቢኔ የተሰጠ ወቅታዊ መግለጫ

ባለፈው ሳምንት ከኮር በላይ የሆኑ የትግራይ ሰራዊት ከፍተኛ አዛዦች ስብሰባ ማድረጋቸው ይታወቃል። ከስብሰባው በኋላ መግለጫ ያወጡ ሲሆን የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ከኮር በላይ ተብሎ በቀረበው መግለጫ ላይ ለመወያየት ጥር 16 ቀን 2017 አስቸኳይ ስብሰባ ጠርቶ ሰፊ ውይይት በማድረግ ውሳኔዎችን ኣስተላልፏል።
1) በሰራዊቱ ከፍተኛ አዛዦችን ስም የቀረበና የተላለፈው የውሳኔ ሐሳብ ለአንድ ብዱን የወገነ፣ መንግስትን የሚያፈርስ፣ ሰራዊቱን የሚበታትን፣ የፕሪቶሪያ ስምምነትን የሚጥስ እና መሰረታዊ ስሕተት ያለበት በመሆኑ፤ በአስቸኳይ እንዲታረምና ወደ ታችም እንዳይወርድ ተወስነዋል።
ሀ) መግለጫው ከሰራዊቱ ተልዕኮ ያፈነገጠ እና በበርካታ ጉዳዮች ላይ ተቋማዊነትን ያልጠበቀ እንደሆነ በጥልቀት ታይቷል። ሰራዊቱ በአንድ የፖለቲካ ፓርቲ የውስጥ ጉዳይ ላይ ጣልቃ በመግባት አንዱን ቡድን በመቃወም ሌላውን ለመደገፍ የሚያስችል ተልእኮ እንደሌለው እየታወቀ “ጉበኤ ያደረገ እና ጉባኤ ያላደረገ” በሚል የተደረገ ውይይት እና ያስተላለፈው ውሳኔ ፍፁም ተቀባይነት እንደሌለው የጊዜያዊ አስተዳደር ካቢኔው አስምሮበታል። ከዚህ ባለፈም እራሱ የፓርቲ እውቅና ሰጪ፣ ስልጣን ሰጪ እና ከልካይ እንደሆነ አድርጎ ያስተላለፈው ውሳኔም ተቀባይነት የሌለው እና ስርዓት አልበኝነትን የሚያነግስ ብቻ ሳይሆን፤ ትግራይን መንግስት አልባ የሚያደርግ፣ የህዝባችንን አንድነት የሚያናጋ እንዲሁም የሰራዊታችንን ህልውና አደጋ ላይ የሚጥል ነው። እንደ ተቋምም ከኮር በላይ አመራር የሚባል ህጋዊ ኣደረጃጀት የሌለበት በመሆኑ ውሳኔዎችን የማሳለፍ ሕጋዊ ስልጣን ስልጣን የለውም።

ለ) የወረዳ፣ የከተማ/የክፍላተ ከተማ ምክር ቤቶችን በማስመልከት ያስተላለፈው ውሳኔም በተመሳሳይ መልኩ ከተልዕኮው ውጪ ነው። መዋቅሮችና ተቋማትን የማስተካከል ወይም ሕግ የማውጣት እና የመሻር የመንግስት ሥልጣን ሆኖ ሳለ፤ የአንድ የፖለቲካ ቡድን የስልጣን ጥማት ለማርካት ተብሎ የተላለፈ ውሳኔ በመሆኑ ተቀባይነት የለውም። ይህ ሆን ተብሎ መንግስት ስራውን እንዳይሰራ የሚያደርግ እና የህዝብንና የሰራዊቱን አንድነት የሚያናጋ ተግባር መሆኑን መላው ህዝባችንና ሰራዊታችን ሊገነዘቡት ይገባል። ይህ እንቅስቃሴ ሆን ተብሎ መንግስትእግር እንዳይተክል የሚያደናቅፍ ተግባር ስለሆነ በአስቸኳይ መታረም አለበት ብሏል ካቢኔው።

2) መንግስትን እንደገና ማዋቀር በተመለከተ የተላለፈው ውሳኔ ደግሞ የአንድ ቡድን ልክ የለሽ የስልጣን ጥማትን ለማርካት ሲባል የፕሪቶሪያ ስምምነትን የሚጻረር፤ ኃላፊነት የጎደለው ውሳኔ ነው። ይህ የትግራይን ህዝብ ወደ ሌላ የጦርነት አዙሪት የሚያስገባ ስክነት እና ብስለት የጎደለው ውሳኔ ስለሆነ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ሊቀበለውስ ይቅር ለአፍታም ቢሆን ሊያስበው እንደማይችል አፅንኦት ሰጥቶበታል። በመሆኑም ውሳኔው በአስቸኳይ እንዲታረም አቅጣጫ አስቀምጧል።

3) ሁሉንም የጸጥታ መዋቅር ወደ አንድ ማዕከል ለመሰብሰብ የቀረበው ሐሳብም ህገ መንግስታዊ ያልሆነ እና የትግራይን ችግር ይበልጥ የሚያባብስ ነው ብሎታል። አቀናጅቶ ማሰማራት አይቻልም ባይባልም በአንድ ቋት ውስጥ ካልገቡ የሚለው ግን ፍፁም ተቀባይነት የለውም። ይሁን እንጂ ሁሉም የፀጥታ አካላት ሙያዊ ነፃነታቸውንና ሕጋዊ ኃላፊነታቸውን በመጠበቅ በቅንጅት እንዲሰሩ ለማድረግ በቀጣይነት የሚሰራበታል ይሆናል።

4) በዚህ መልኩ የቀረቡት ውሳኔዎች መሰረታዊ ስሕተቶች ያለባቸው እና ተፈጻሚነት የሌላቸው መሆናቸውን የጊዚያዊ አስተዳደሩ ካቢኔ አስታውቋል። ውሳኔዎችን ለማፍጠን ወደ ታች ለማውረድ የተደረገው ጥድፊያም በአስቸኳይ እንዲቆምና በትክክለኛ መርህ ላይ የቆሙ እና ይህን የተሳሳተ ውሳኔ የተቃወሙ የሰራዊት አመራሮች ላይ የሚተላለፍ ምንም አይነት ውሳኔ ተግባራዊ እንዳይሆንም ካቢኔው ወስኗል።

የተከበርክ በሃገር ውስጥም በውጭም ያላህ የትግራይ ህዝብ፦
በትግራይ ሰራዊት ከፍተኛ አዛዦች ስም የወጣው መግለጫ እጅግ እንዳሳዘነህና እንዳሳሰበህ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር በጥልቅ ተረድቷል። በሰራዊቱ የአመራር ስህተት ዳግም ወደ ጦርነት እንዳትገባ በጣም እንዳሳሰበህም በውል እንገነዘባለን። ሁኔታው እጅግ አሳዛኝና አሳሳቢ ቢሆንም፣የጊዜያዊ አስተዳደር ካቢኔው አስቸኳይ ስብሰባ በመጥራት ውሳኔዎቹ እንዳየተገበሩ ወስኗል። በአካባቢያችሁ ያሉትን እንቅስቃሴዎች በቅርበት እንድትከታተሉ እና ስህተቶች ከተከሰቱም ቶሎ እንዲታረሙ በጥብቅ እናሳስባለን። ከሁሉም በላይ ደግሞ ሰላማችሁን እንትጠብቁ እና የፕሪቶሪያ ስምምነትን የሚጥስ እና ወደ ጦርነት የሚመልሰን ማንኛውም ዓይነት እንቅስቃሴ በጥብቅ እንድትቃወሙ እናስገነዝባለን።



የተከበርክ የትግራይ ወጣት፦
በዚህ ሳምንት በተላለፉ የትግራይ ሰራዊት አመራር ውሳኔዎች ምክንያት በጣም እንደተገረማችሁ ይገባናል። ተስፋ ያደረጋችሁበት የለውጥ መንገድ እንዳይደናቀፍ እና ተሳትፎአችሁ እንዳይመክን ያሰደረባችሁ ስጋትም በውል እንገነዘባለን። የትግራይ ህዝብ እንደገና የአንድን ቡድን የስልጣን ጥማትን ለማርካት ተብሎ ወደለየለት ጦርነት እንዳይገባም ስጋት ገብቷችኋል። የጊዜያዊ አስተዳደር ካቢኔው ከሰራዊቱ ተልዕኮ ውጪ የተላለፈው ውሳኔ በዝርዝር ተመልክቶ ተግባራዊ እንዳይሆን እና ወደ ታችም እንዳይወርድ መወሰኑን ልናረጋግጥላችሁ እንወዳለን። እናንተም የተሳሳቱ ውሳኔዎች ተግባራዊ እንዳይሆኑ ከሕዝባችሁና ከሠራዊታችሁ ጋር በመሆን በርትታችሁ መታገል አለባችሁ። ከምንም ነገር በላይ ደግሞ ሰላማችሁን እንድትጠብቁ እና ከትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ጎን በመቆም ዳግም ጦርነት ሊያሰነሱ የሚችሉ መንገዶችን እንድትዘጉ ጥሪያችንን እናቀርባለን።

የተከበራችሁ የትግራይ የፀጥታ ኃይሎች
በዚህ ሳምንት በተላለፉ ተገቢ ያልሆኑ ውሳኔዎች እንዳዘናችሁ እና የራሳችሁ ህልውና አደጋ ላይ እንዳይወድቅ እና ትግላችን ሙሉ በሙሉ እንዳይደናቀፍ ከፍተኛ የሆነ ስጋት እንዳደረባችሁ ግልፅ ነው። በአስደናቂ ጀብዳችሁ ያስጠብቃችሁት ሰላም እንዳይደፈርስ፣ በከፈላችሁት መስዋዕትነት ያቋቋማችሁት ጊዜያዊ አስተዳደር እንዳይፈርስ እና ህዝባችሁ ወደ ሌላ ዙር ደም አፋሳሽ ጦርነት እንዳይገባ በእጅጉ እንዳሳሰባችሁም ከልብ እንረዳለን። ከምንም ነገር በላይ ደግሞ የከፈላችሁት መስዋዕትነት፣ የአካል ጉዳት እና ትግላችሁ አደጋ ላይ ወድቆ የአንድ ቡድን መሣሪያዎቸ‍እ እንደሆናችሁ ተደርጎ የቀረበው ሐሳብ በጣም እንዳሳዘናችሁ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ካቢኔ ተረድቷል። መግለጫው በጥልቀት ብመመርመርም ተቀባይነት የሌለው እና በምንም መልኩ ተግባራዊ እንደማይሆንም ወስነናል። እናንተም እነዚህ ውሳኔዎች በማንኘ‍ኣውም መልኩ ተግባራዊ እንዳይሆኑ ጠንክረችሁ እንድትታገሉ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።

መልእክት ለኢትዮጵያ መንግስት




በጦርነት ለተጎዱ 1026 ሰዎች መሬት ተሰጣቸው

በትግራይ ጦርነት የተጎዱ ሰዎች ሁሉ መኖሪያ ቤት ብቻ ሳይሆን ብዙ ይገባቸዋል ሲል የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ገለፀ።

ፕሬዝደንት ጌታቸው ረዳ በጦርነት የተጎዱ የትግራይ ተወላጆች በሙሉ መኖሪያ ቤት ብቻ ሳይሆን ብዙ ይገባቸዋል ብለዋል።

በአጠቃላይ 1,026 የጦር ሰለባዎች ለእያንዳንዳቸው 140 ካሬ ሜትር ቦታ መመደቡን የከተማው የመሬት አጠቃቀምና አስተዳደር ኦፊሰር ገ/ሚካኤል እንሁን ገልጸዋል።

የትግራይ ጦርነት ጉዳት የደረሰባቸው ማኅበር ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ጨርቆስ ወ/ማርያም መንግስት ላደረገው ድጋፍ አመስግኖ መንግስት በዚህ መልኩ መስራቱን አጠናክሮ እንዲቀጥልም ጠይቀዋል።


የምዕራብ ዓባያ ወረዳ ፍርድ ቤት የአስገድዶ መድፈር ወንጀል በተከሰሰ ግለሰብ መዝገብ ላይ ውሳኔ ሰጠ ።

የምዕራብ ዓባያ ወረዳ ፍርድ ቤት ትላንትና ጥር 16 /2017 ዓ.ም በዋለው ችሎት አስገድዶ የመድፈር ወንጀል በፈጸመ ተከሳሽ ላይ በፅኑ እስራት እንዲቀጣ ውሳኔ አስተላልፏል ።

የምዕራብ ዓባያ ወረዳ ፍ/ቤት ተከሳሽ አቶ ሳህለ ሻታ
ህዳር 1/2017 ዓ.ም በዛላ ባራና ቀበሌ ነዋሪ የሆነችውን የ20 ዓመት ሴት የአስገድዶ መድፈር ወንጀል በመፈጸም የቀረበበት ክስ በአንቀጽ 620 ንዑስ አንቀጽ 2 ላይ ክሱ ቀርቦ ፍርድ ቤቱ ተከሳሽ ያቀረባቸው ቤተሰብ አስተዳዳሪና ቀደም ሲል ወንጀል አልፈጸምኩም ሲል ባቀረበው የማቅለያ ሀሳቦች በእርከን 21 በብይን 620 ንዑስ አንቀጽ አንድ ጥፋተኛ ተብሏል።

በዚህ መሠረት ተከሳሽን በቀጣይ አንጾ ለማስተማርና ሌሎች ተመሳሳይ ወንጀሎች እንዳይፈጽም ያርመዋል በማለት የምዕራብ ዓባያ ወረዳ ፍ/ቤት በወንጀለኛው ላይ እጁ ከተያዘበት ጊዜ አንስት በ5 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ውሳኔ አስላልፏል ።

@ምዕራብ ዓባያ ወረዳ መ. ኮሚዩኒኬሽን


የቤተክርስቲያንን መብትና ጥቅም ለማስከበርና
የሕግ ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ በጥብቅ እየተሰራ ነው።
****************************************

ጥንታዊት፣ታሪካዊትና ዓለም አቀፋዊት የሆነችው የኢትዮጵያ ኦርቶዶከስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መንፈሳዊ አገልግሎቷን ለማስፋፋት በምታደርጋቸው እንቅስቃሴዎች ሁሉ የሌሎችን መብትና ጥቅም ባለመንካት በትዕግሥትና በማስተዋል የምትጓዝ አገራዊ ኃላፊነት የሚሰማት ሰላምን አብዝታ የምትሰብክ መንፈሳዊት ተቋም መሆኗ ይታወቃል።

ቤተክርስቲያናችን ሥርዓተ አምልኮቷን ለማስፋፋት በተጓዘችባቸው አያሌ ዓመታት አገራችን ኢትዮጵያ የራሷ ፊደላትና የራሷ የቀን አቆጣጠር ባለቤት እንድትሆን ያስቻለች፣በሊቃውንቶቿ የመጠቀ እውቀት አማካኝነት የሥነ ጥበብ፣ የሥነ ስዕል፣ የዕጽዋትና የጠፈር ምርምርና ጥናቶችን በማከናወን ተጨባጭ ውጤቶችን ለዓለም ያበረከተች ጥንታዊት ተቋም ስለመሆኗም አያሌ ማስረጃዎችን ማቅረብ ይቻላል።

ይሁን እንጂ ይህች ለአገረ መንግስት መመስረትና መጽናት፣ ለእውቀት መስፋፋት፣ ለአብሮነት መጎልበት፣ ትውልድን በሥነ ምግባር ቀርጻ ፍቅርና አንድነትን በተግባር የሰበከች እናት ቤተክርስቲያን ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ በተለያዩ አካላት መብትና ጥቅሟን የሚነኩ፣ በአስተምህሮቿ፣በዕምነቷ፣በንዋያተ ቅድሳቶቿ ላይ መሰረታቸውን ያደረጉና ትዕግስቷን የሚፈታተኑ ክብርና ሉአላዊነቷን የሚዳፈሩ እኩይ የትንኮሳ ተግባራት እየተፈጸመባት ይገኛል።

ስለሆነም በተደጋጋሚ እየተፈጸሙባት የሚገኙትን እነዚህን እኩይ ተግባራት ከዚህ በላይ በዝምታና በትዕግስት ማለፍ መንፈሳዊ ተልዕኮዋን በአግባቡ እንዳትወጣ የሚያደርጋት ከመሆኑም በላይ መብቷን በእጅጉ የሚጋፋ፣ጥንታዊያን አባቶች ለሥርዓተ አምልኮ መፈጸሚያ ሲጠቀሙባቸው የነበሩና በትውልድ ቅብብሎሽ አሁን ያለው ትውልድ የተረከባቸው ንዋያተ ቅድሳቶቿን አደጋ ላይ የሚጥል ሁኔታ ከመፈጠሩም በላይ በሥርዓተ አምልኮዋ ላይ በማላገጥ በምዕመናን ዘንድ ቁጣ እንዲቀሰቀስ የሚያደርጉ በርካታ ተግባራት እየተፈጸሙ በመምጣታቸው ምክንያት እነዚህ እኩይና ጸብ አጫሪ ተግባራት ሕጋዊ እልባት እንዲያገኙ ማድረግ የግድ የሚልበት ደረጃ ላይ ደርሳለች።

ስለሆነም ቅድስት ቤተክርስቲያናችን ጉዳዩን በልዩ ሁኔታ ማጥናት፣መከታተልና ሕግን መሰረት ያደረገ መፍትሔ እንዲያገኙ ማድግ አስፈላጊ ሆኖ ስላገኘችው ወቅታዊ ሁኔታውን በዝርዝር በማጥናት ተቋማዊ እልባት የሚያገኝበትን መንገድ የሚያጠና ኮሚቴ ተቋቁሞ ወደ ሥራ እንዲገባ ያደረገች ሲሆን የቤተክርስ
ቲያናችን የሕግ አገልግሎት መምሪያም በሕግ አግባብ ተጠያቂነትን በማረጋገጥ ፍትሕ ማግኘት የሚቻልበትን ሁኔታ ለመፍጠር አስፈላጊውን መረጃ በማሰባሰብና በማደራጀት ክስ መመስረት የሚያስችለውን ሁኔታ በማመቻቸት ወደ ተግባር ለመለወጥ በዝግጅት ላይ ይገኛል።

ከዚህ ጎን ለጎንም ከፍ ሲል እንደተገለጸው በጠቅላይ ቤተክህነት ከሚገኙ መምሪያዎች መካከል ጉዳዩ በቀጥታ የሚመለከታቸውን መምሪያዎች በማካተት የተቋቋመው ኮሚቴም ዝርዝር ጥናቶችን በሚገባ በማጥናትና ችግሮቹን ለይቶ ከመፍትሔ ሀሳብ ጋር በአጭር ጊዜ ውስጥ በማቅረብ በቤተክርስቲያኒቱ ማዕከላዊ አስተዳደር አማካኝነት ተቋማዊ አቋም የሚወሰድበትና በቅዱስ ሲኖዶስ ደረጃ የማያዳግም መፍትሔ የሚሰጥበትን ሁኔታ ለማመቻቸት የሚያስችል ሥራ በመሥራት ላይ መሆኑን እየገለጸች በሁለቱም ዘርፎች የተገኙ ውጤቶችን በተመለከተ በተከታታይ ለሕዝበ ክርስቲያኑ እንዲገለጽ የምታደርግ መሆኑን ከወዲሁ እያስታወቀች በጉዳዩ ዙሪያ ሙያዊ ድጋፍ ለመስጠት ፈቃደኛ የሆኑ ምዕመናንና ምዕመናት በተቋቋመው ኮሚቴ አማካኝነት የሚደረግ
ላቸውን ጥሪ ተቀብለው ለቤተክርስቲያናችን መብት መከበር የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ እናት ቤተክርስቲያን ጥሪዋን ታቀርባለች።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን
መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት
አዲስአበባ -ኢትዮጵያ
ጥር ፲፯ቀን ፳፻ ፲ወ፯ ዓ.ም









Показано 20 последних публикаций.