ለእግዚአብሔር የገባሁት ቃል ኪዳን የመረጋጋት እና የዝምታ ሕይወት ነበር ::እንደ ቃሌ ይህንን ሕይወት እየተለማመድኩ ሕሊናየ ከፍ ያለውን ነገር በሚመለከትበትና የሕይወት ፍልስፍናዬ ትክክል እንደሆነ እያመንኩ በመጣሁበት በዚህ ወራት ባልጠበቅኩት ጊዜና አጋጣሚ የተጫነብኝን ቀንበር ልሸከምበት የምችለውትከሻ አልነበረኝም :: ለእኔ አስፈላጊ የነበረው ነገር የስሜት ሕዋሳቶቼን በር ዘግቼ ከሥጋዊ እና ዓለማዊ ነገር ሁሉ ሸሽቼ ከራሴ ጋር ብቻ መሆንን ነው :: ከራስ ጋ ከመነጋገር የበለጠ ደስታን የሚሰጥ ምን ነገር አለና ከማውቀው ከራሴ ጋር መወሰንን ወደድኩ :: ለራሴ እና ለእግዚአብሔር ነገርን እየተናገርኩ ከሚታይ እና ከሚዳሰሱ ነገሮች ሁሉ በላይ ትልቅ የሆነ ሕይወትን መኖርን ወደድኩ በልቡናዬ ውስጥ የምጫረውን ሰማያዊ ነገር ::
ከምድራዊ ሐሳብ ጋር ሳልቀላቅል መንፈሳዊ የሆነ ነገር በውስጤ እንዲያድር ማድረግ የዘወትር ፍላጎቴ ነበር ይህ ሐሳብ ንጹሕ መስታወት የሰውን መልክ እንዲያሳይ እግዚአብሔርን እንድንመለከት የሚያደርግ የልቡና መስታወት ነው ::በብርሃን ላይ ብርሃንን የሚጨምር በእውቀት ላይ እውቀትን የሚጨምር በተስፋ የሚጠብቁት የሚደሰቱበት ከቅዱሳን መላእክት ጋር ሆነው እግዚአብሔርን የሚያመሰግኑበት ስሜት ነው ::
"ከራስ ጋ ከመነጋገር የበለጠ ደስታን የሚሰጥ ምን ነገር አለና ከማውቀው ከራሴ ጋር መወሰንን ወደድኩ ::"
(ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘእንዚናዙ ትምህርቱ እና ሕይወቱ ከገጽ 43-44 )