የቀጠለ ከላይ ያለውን ንባብ መጀመሪያ ያንብቡት......
3️⃣ S-skill…ችሎታ
“A man who wants to lead the orchestra must turn his back on the crowd!”
Mad Lucadoመሪነት ራሱን የቻለ ችሎታም ነው፡፡ ከሚመሯቸው በላይ የላቀ ችሎታን ይጠይቃልና አውቶብስ መንዳት ራሱን የቻለ ችሎታ ነው፡፡ ተቋምን መሾፈርም እንደዚሁ፡፡ የትኛውን ማርሽ በየትኛው ጊዜ ላይ ወስኖ መጠቀም እንዳለበት መረዳት የሚችል፤ የትኛውን ቁልፍ መንካት እንዳለበትና እንደሌለበት ማወቅ የሚችል፤ አቅጣጫን የመረዳት ችሎታ፣ የመኪናውን ባህሪ የመረዳትና ማስተካከል የሚችል ችሎታ ያስፈልገዋል፡፡ አንድ የተቋም አመራርም በተግባር የተፈተሸ ልዩ ልዩ ችሎታዎች ያስፈልጉታል፡፡ ገንዘብ የማስተዳደር ችሎታ፣ ሰው አስተዳድሮ የማሰራት ችሎታ፣ ስሜቱን የመቆጣጠር ችሎታ፣ ውጤታማ ኢንቨስትመንት የማድረግ ችሎታ፣ ተናግሮ የማሳመን ችሎታ፣ የማቀድ ችሎታ፣ የወደፊቱን የመተንበይ ችሎታ፣ እያለ ይቀጥላል፡፡ አንድ አመራር ጥሩ ገንቢ አመለካከት ቢኖረው እንኳን ትክክለኛ ችሎታ በሌለበት ሁኔታ ያለትክክለኛ ትግበራ የሚጠበቀውን ትክክለኛ ውጤት ለማምጣት ያስቸግረዋል፡፡
4️⃣ K- Knowledge…
“It the blind lead the blind, both shall fall in the
ditch”
Jesus Christበእርግጥ ችሎታ የሚዳብረው ከማወቅ ነው፡፡ ለአመራርነት የሚያበቁ ችሎታዎችን ለማዳበር በቅድሚያ ስለችሎታዎቹ መሰረታዊ እውቀት ሊኖረው ይገባል፡፡ ሁሉም አይነት እውቀት አይደለም፣ ለትክክለኛ ቦታ የሚሆን ትክክለኛ እውቀት እንጂ፡፡ ይህ ብቻ አይደለም፣ ስለሚመራው ተቋምም ውስጣዊና ውጫዊ ሁኔታዎችን ሊያውቅ ይገባል፡፡ እንዲሁም የሚመራው አንድን የንግድ ተቋም ከሆነ ስለንግድ አሰራር መሰረታዊ እውቀት ያስፈልገዋል፡፡ ብዙውን ጊዜ በአገራችን የድርጅቱ ባለቤት ስለሆኑ ብቻ እንጂ መሰረታዊ የንግድ ‹‹ሀሁ›› እውቀት ኖሯቸው ድርጅታቸውን የሚመሩ ሰዎች ጥቂት ናቸው፡፡
አንድ ሰው የሚመራው የእግርኳስ ክለብን ከሆነ ደግሞ ስለ እግርኳስ መሰረታዊ እውቀትን ሊጨብጥ ይገባል፡፡ የፖለቲካ ፓርቲም ከሆነም ስለፖለቲካና አገራዊ አመራር ትክክለኛ እውቀት ያስፈልገዋል፡፡
ምክንያቱም እውቀቱ ችሎታውን ይወስናል፤ ችሎታውን ተግባሩን፡፡ ተግባሩ ደግሞ ባህሪውን ይቀርፃል፡፡ በመጨረሻም የግለሰቡንና የተቋሙን ውጤት፡፡
ለምሳሌ በአገራችን ያሉ መካከለኛና ከፍተኛ የሚባሉ ኢንተርፕራይዞች በቀጥታ ለመመራት ያለባቸው በቢዝነስ ሁለተኛ ዲግሪ ባላቸው ባለሙያዎች ሲሆን ብዙዎቹን ስንመለከት ግን ይህን ሚዛን አያልፉም፡፡ ለዚያም ነው የሚመሯቸው ተቋሞች ወደ ላይና ወደ ታች ሲሉ የምናያቸው፡፡ በፓርቲም ደረጃ እንዲሁ በፖለቲካል ሳይንስ በቂ ግንዛቤ ያላቸውን አመራሮች ይጠይቃል፡፡ አለበለዚያ አላዋቂ ሳሚ እንዳይሆን ራሳችንን መፈተሽ ይገባል፡፡ ለትክክለኛ ተቋምና ለትክክለኛ የአመራር ቦታ ብቁ የሚያደርግ ትክክለኛ እውቀት!!
5️⃣ E- Experience… ልምድ
“Leadership and (experience) are indispensable to each other”
John f. Kennedyከላይ ያሉት የአመራር ችሎታዎች የሚዳብሩት በልምድ እና በልምምድ ውስጥ ነው፡፡ እንዲሁም የአመራርነት ባህሪ በራሱ የልምድ ውጤት ነው፡፡ ከአሁን ቀደም አንድ ሰው ያዳበረው ልምድ ውጤት የማያመጣ ወይም የውድቀት ከሆነ ባህሪውም ይሄንኑ ነው፡፡ በእርግጥ የአመራር ችሎታዎቹም ቢሆኑ ውድቀትን የሚያላብሱ ናቸው የሚሆኑት፡፡ በሥራ ማስታወቂያዎች ላይ ‹‹በዘርፉ ይህን ያህል የሥራ ልምድ›› የሚባለውም ለዚያ ነው፡፡ የአንድን አመራር ልምድ በቀላሉ ለመረዳት ‹‹ከአሁን ቀደም ምን ያህል ድርጅቶች አቋቁመህ ወይም መርተህ ለውጤት አብቅተሃል?›› የሚለው ወሳኝ ጥያቄ ነው፡፡ አንዳንዱ ረጅም ዓመት የመምራት ልምድ ኖሮት ሊሆን ይችላል፡፡ ዋናው ነገር በቦታው ላይ መቆየቱ አይደለም፡፡ ድርጅቱን ከየት አንስቶ የት አደረሰው? የገጠሙትስ ተግዳሮቶች ምን ነበሩ? እንዴትስ በመፍታት ተቋሙን ለውጤት አበቃው? ነው ጨዋታው፡፡ አመራርነት ስልጣን አይደለም ውጤት እንጂ፡፡ ማዕረግ አይደለም፡፡ አፈፃፀም እንጂ ረጅም ዓመታት በመምራት መቆየትም አይደለም ረጅም የሚያስከነዳ ውጤትን ማስጨበጡ ላይ ነው ቁም ነገሩ፡፡
6️⃣ T- Talent… ልዩ ብቃት
“Your are your master, only you have the master key to pen the inner locks!”
Leonardo Davienchiይህ የአመራርነት የመጨረሻው ማስተሪ ይሉታል ባለሙያዎች፡፡ መሰጠት እንደማለት ነው፡፡ ታለንት በተፈጥሮ የተሰጠን ሊሆን ይችላል፡፡ በትምህርትና ልምምድም ወደ ማስተርነት የተቀየረም ሊሆን ይችላል፡፡ ከላይ ያሉት ውጤት ተኮር እውቀቶች፣ ውጤት ተኮር ችሎታዎች፣ ውጤት ተኮር አመለካከቶች፣ ውጤት ተኮር ልምዶች በየጊዜው በዳበሩ ቁጥር ግለሰቡ ለዚያ ቦታ የሚኖረው ልቀት ያለው አመራር (Leadership excellence) ወደ ፍፁም ብቃት ይሸጋገራል፡፡ ውጤታማ አመራርነት ለግለሰቡ ቋንቋው፣ ተግባሩ፣ መንፈሱ፣ መሆን ሲጀምር ሊደርሺፕ በራሱ ታለንት ወደ መሆን ተሸጋገረ እንለዋለን፡፡ ለዚህ መሰሉ ሰው ውጤታማ አመራርነትን አውቆት ወይም አስቦበት ሳይሆን ሳያውቀው ሁሉ የሚተገብረው ነው የሚሆነው (autopilot)፡፡ የሊደርሽፕ ማስተሪ ማለት ይህ ነው፡፡ ይሁን እንጂ በአመዛኙ የምናየው የትምህርት ማስተርስ እንጂ ውጤትና ለውጥ ሊያመጣ የሚችል ማስተሪ አይደለም፡፡ ይህ ምናልባት የትምህርት ተቋሞቻችን አንዱ ክፍተት ሊሆን ይችላል፡፡
እናም በየትኛውም ተቋማት ውስጥ ለምንቀጥራቸው አመራሮች እንደመመልመያ መስፈርትም ሆነ መገምገሚያነት እንዲሁም ተተኪ አመራሮችን ወደ ላይ ለማምጣት የ‹‹B ASKET›› መርህን መከተል
እንችላለን በምንመራው ተቋም ውስጥም ልንጠቀምበት እንችላለን፡፡
እንዲሁም በዚህ መርህ ተተኪ አመራሮችን በኮችንግ፣ በስልጠና እንዲሁም ከበላይ ካሉ አመራሮች ስር በመሆን እንዲሰሩ በማድረግ ማብቃት እንችላለን፡፡ በተላዩ የድርጅቱ ክፍሎችና ቅርንጫፎች ውስጥ
በማዟዟር ልዩ ልዩ እውቀትን፣ ልምድንና ችሎታን እንዲያዳብሩ ካደረግን በኋላ ወደ ላይ ማምጣት እንችላለን፡፡
መንፈሳችን ስለወደዳቸው፣ ደስ ስላለን ወይም ስለመሰለን የምነቀጥራቸው ወይም ደግሞ የምንተካው ሰዎች መኖር የለበትም፡፡ ደስ ስላለን ብቻ መኪናችን እንዲነዳልን ቁልፍ ሰጥተን በመኪናው ውስጥ ተሳፍረን የምንሄድ ስንቶቻችን ነን? አናደርገውም፡፡ ተቋምም እንዲሁ ነው፡፡
source:
Social Media