አዲስ ሪፖርተር - NEWS


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Новости и СМИ


🔖 ይህ የአዲስ ሪፖርተር የቴሌግራም ገፅ ነው !
=> በቻናሉ
📌 ፈጣን ፥
📌 ትኩስ ፥
📌 ወቅታዊ እና
📌 አዳዲስ መረጃዎች እንደወረዱ በቅፅበት ፥ በትኩሱ ይደርሳችኋል !
🔖 ይወዳጁን ፤ በእርግጥም ይወዱታል !
For promotion @Addis_reporter_bot
#ADDIS ABABA, ETHIOPIA

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Новости и СМИ
Статистика
Фильтр публикаций


መቀሌ ውጥረት ነግሷል‼️

ዛሬ ለሊቱን ጀምሮ ብዛት ያለው  ሰራዊትና መትረየስ የጫኑ ፓትሮል መኪኖች በመቀሌ ከተማ በከፍተኛ ሁኔታ  እንቅስቃሴ እያደሩጉ እንደሚገኙ ታውቋል‼️

በደብረፂዮን የሚመራው የህወሓት ቡድን በኢትዮጵያ አቆጣጠር ከሌሊቱ 8:00 ሰዓት መግለጫ ያወጣ ሲሆን ህዝባዊ ሰራዊታችን በከሃዲ ቡድን ሴራ አይፈርስም ብሏል።

ህወሓት በመግለጫው የግዚአዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንትን ጨምሮ ብሄራዊ ክህደት የፈጸሙ እና እየሰሩ ያሉ አመራሮችን በማባረር በጊዜያዊ አስተዳደር ውስጥ ያላቸውን ውክልና አንስቻለሁ ያለ ሲሆን ነገር ግን ጊዚያዊ ፕሬዝዳንቱ እና ሌሎች የቡድኑ አባላት ከህግና ስርዓት ውጪ ፀረ ህዝብ ተግባራቸውን ቀጥለዋል ብለዋል።

የህዝባችንን አንድነት በማደፍረስ የትግራይን ሁለንተናዊ አቅም በማዳከም ብሄራዊ ክህደት እየፈፀመ ያለው የቀድሞ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አሁን በትግራይ ህዝብ ላይ የታወጀውን የዘር ማጥፋት ለመፋለም የተደራጀውን የትግራይ ሰራዊት ለመበተን ድርጊቱን አጠናክሮ ቀጥሏል"ብሏል።

የቀድሞ ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ከስልጣናቸው እና ከኃላፊነታቸው ውጪ የትግራይ ጦር ግንባር አመራሮችን እና ጄኔራሎችን  አግደዋል ያለው ህወሃት፣ይህ ማዕቀብ መሠረተ ቢስ እና ተግባራዊ ሊሆን የማይችል ቢሆንም ህዝባዊ ትግሉን ከህግ እና ከስርዓት ውጭ ለማድረግ ቡድኑ ሌት ተቀን እየሰራ መሆኑን ያሳያል ማለቱን አዩዘሀበሻ ከመግለጫው ተመልክቷል።

Via : አዩዘሀበሻ

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
ሳርቤት መቻሬ ሜዳ ፊትለፊት
📲0936410003 // 0905524551
🛏️ ባለ አንድ መኝታ
                65.77 ካሬ
                 86.86 ካሬ 
                 90.37 ካሬ 

🛏️ባለ ሁለት መኝታ
              ✅97.82 ካሬ
       
              ✅114.22 ካሬ

🛏️ባለ ሶስት መኝታ
              ✅140.31ካሬ
              ✅153.11ካሬ

Few units  are left
🏠 Reality Sarbet Canada Embassy

✨ Structure? ✅ Done!
✨ Block Work? ✅ Complete!
✨ Finishing? 🚧 In Progress

With only 10% down payment and 80% of construction complete, secure your dream home now and watch it come to life with every brick laid. Don’t miss the chance to own a quality-built, beautifully designed space in the heart of Addis Ababa.

📲 Contact us:
📞 0936410003 // 0905524251


በባለሀብቶች የታሪፍ ፍራቻ የተነሳ የነዳጅ ዋጋ እየቀነሰ ነው ተባለ

ወደ አሜሪካ በሚገቡ ምርቶች ላይ የሚጣለው ታሪፍ በአለም ኢኮኖሚ እድገት እና በነዳጅ ፍላጎት ላይ የሚያሳድረው ተጽእኖ፣ እንዲሁም ከኦፔክ የነዳጅ አምራች ሀገራት የነዳጅ ምርት እየጨመረ በመምጣቱ፣ ባለሃብቶች ላይ ስጋትን አሳድራል። ያልተጣራው ድፍድፍ ነዳጅ አርብ እለት 90 ሳንቲም በ6 ሳንቲም ቀንሶ ወደ 70.30 ዶላር ዝቅ ብሏል። የዩናይትድ ስቴትስ ዌስት ቴክሳስ ገበያ ድፍድፍ በ ነዳጅ በ66.96 ዶላር በበርሚል የተሸጠ ሲሆን በስምንት ሳንቲን ቀንሷል።

ለሰባተኛ ተከታታይ ሳምንት ነዳጅ ቀንሷል፣ ይህም ከህዳር 2023 ወዲህ ረጅሙ የኪሳራ ጉዞ ተደርጎ ተወስዷል። የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በቻይና ምርቶች ላይ ግብር መጣላቸው እንዲሁን በዋና ዘይት አቅራቢዎቻቸው ላይ ካናዳ እና ሜክሲኮ የዘገየ ታሪፍ ከጣሉ በኋላ ድፍድፍ ነዳጅ ለሶስተኛ ተከታታይ ሳምንት ቀንሷል። ቻይና በአሜሪካ እና ካናዳ የግብርና ምርቶች ላይ የአፀፋ ታሪፍ መጣሏ ይታወሳል።

ትራምፕ ሞስኮ ከዩክሬን ጋር የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ መድረስ ካልቻለች ዩናይትድ ስቴትስ በሩስያ ላይ የምትጥለውን ማዕቀብ እንደምትጨምር ከተናገረች በኋላ አርብ እለት የነዳጅ ዋጋ ቀንሷል። ሩሲያ ከዩክሬን ጋር የምታደርገውን ጦርነት ለማቆም ከተስማማች ዩናይትድ ስቴትስ በሩሲያ የኃይል ማመንጫ ዘርፍ ላይ የተጣለውን ማዕቀብ ለማርገብ የሚያስችል መንገድ እያጠናች ነው ሲሉ ጉዳዩን የሚያውቁ ሁለት ምንጮች ለሮይተርስ ተናግረዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ኦፔክ ፕላስ በመባል የሚታወቀው ሩሲያን ጨምሮ የነዳጅ ላኪ ሀገራት ድርጅት እና አጋሮቹ ከሚያዝያ ወር ጀምሮ በዘይት ምርት ጭማሪ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል። የሩሲያ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አሌክሳንደር ኖቫክ እንዳሉት ኦፔክ ፕላስ የገበያ ሚዛን በሚኖርበት ጊዜ ውሳኔውን ሊቀይር ይችላል ሲሉ ተደምጠዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter




የኤሎን መስክ ማስጠንቀቂያ ለዩክሬን !

ኤሎን መስክ "እኔ ስታርሊንክን ባጠፋው የዩክሬይን የጦር ግንባር ይፈርሳል" ሲሉ ተናግረዋል፡፡

አሜሪካዊው ቢሊየነር አሎን መስክ ዛሬ ባሰፈሩት መልእክት የሳተላይት ኢንተርኔት አገልግሎት መስጫ የሆነውን ስታር ሊንክ ለዩክሬይን ጦርነት ወሳኝ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

የዩክሬይን ማናቸውም ወታደራዊ ግንኙነቶች የሚከናወኑት በእሱ ባለቤትነት በሚተዳደረው በዚሁ ስታር ሊንክ አማካኝነት እንደሆነም ገልፀዋል፡፡

መስክ በኤክስ ገፃቸው ላይ ‹‹እኔ ፑቲንን ከዩክሬይን ጋር በሚደረገው ጦርነት ፈትኜዋለሁ፡፡

እናም የእኔ ስታር ሊንክ ሲስተም ለዩክሬይን የጀርባ አጥንት ነው›› ካሉ በኋላ ስታር ሊንኩን ቢያጠፋት የዩክሬይን የጦር ግንባር ሙሉ በሙሉ እንደሚፈራርስ አስረድተዋል፡፡

ለአመታት በተደረገው በዚህ ጦርነት ዩክሬን ላታሸንፍ ነገር ይህንን በማድረጉና ሰዎች በመሞታቸው እንደሚፀፅታውም አስረድተዋል፡፡

ጨምረውም ‹‹አሁን ሁሉም የሚመለከተው ሁሉ ይህ ሰው እየበላ ያለው ጦርነት እንዲቆም ማድረግ አለበት፤ አሁን ሰላም ያስፈልጋል›› ብለዋል፡፡

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter


#BREAKING : ከስድስት ሳምንት ግምገማ በኋላ አሜሪካ 83 በመቶ የሚሆነውን የUSAID ፕሮግራሞችን መሰረዟን የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሮቢዮ በ X ገጻቸው አስታውቀዋል።

በቢሊዮን ዶላር ወጪ ይደረግባቸው የነበሩ 5200 ኮንትራቶች ተቋርጠዋል ያሉት ሚኒስትሩ እነዚህ ለብሔራዊ ጥቅማችን ምንም የማያገለግሉ አንዳንዶቹ የሚጎዱ ጭምር ናቸው ሲሉ ነው የገለጹት።

ቀሪ 18 በመቶ የሚሆኑት ፕሮግራሞች (1000 የሚጠጉ) በስቴት ዲፖርትመንቱ በአግባቡ እየተመራ የሚቀጥል ይሆናል ብለዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter


ለሕወሓት አመራሮች መከፋፈል ምክንያት የፕሪቶሪያው ስምምነት እንደሆነ ደብረ ጽዮን ገብረ ሚካኤል (ዶ/ር) ተናገሩ

አንዳንዴ ሞቅ ሌላ ጊዜ ደግሞ ረገብ እያለ የቀጠለው የሕወሓት አመራሮች ሽኩቻ መነሻው፣ በፕሪቶሪያው ስምምነት ላይ የተሳተፈው የአቶ ጌታቸው ረዳ ቡድን ምን መፈጸምና አለመፈጸም እንዳለበት በተገቢው ሁኔታ ሳይደራደር ትዕዛዝ ተቀብሎ በመምጣቱ ምክንያት መሆኑን፣ የሕወሓት አንደኛው ክንፍ ሊቀመንበር ደብረ ጽዮን ገብረ ሚካኤል (ዶ/ር) ተናገሩ።
ደብረ ጽዮን (ዶ/ር) ዘ ኒው ሂዩማኒታሪያን ከተሰኘ ሚዲያ ጋር በነበራቸው ቆይታ፣ ‹‹የፕሪቶሪያ ስምምነት አሁን በትግራይ ፖለቲካ ልሂቃን መካከል ለሚታየው መቆራቆስ ዋነኛ ምክንያት ነው፤›› በማለት ስምምነቱን ‹‹የክፍፍሉ መነሻ›› ብለውታል።
አቶ ጌታቸው ወደ ደቡብ አፍሪካ ይዘውት የተጓዙት ተደራዳሪ ቡድን በጦርነት ለደቀቀችው ትግራይ፣ ‹‹ጦርነቱን ብቻ እንዲያስቆምና ከዚያ ያለፈም ያነሰም ነገር እንዳይፈጽም ነበር ተልዕኮ የተሰጠው፤›› ያሉት ደብረ ጽዮን (ዶ/ር)፣ የክልሉን መንግሥት የሚያፈርስ ትዕዛዝ ጭምር ይዘው መጥተዋል...

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter


እስራኤል በመላው ጋዛ የኤሌክትሪክ ሃይል አቅርቦት አቋረጦች

የሀገሪቱ የኢነርጂ ሚኒስትር ኢሊ ኮኸን "ታጋቾችን ለማስለቀቅ እና ሃማስ ከጦርነቱ በኋላ በጋዛ ህልውና እንዳይኖረው ለማረጋገጥ ሁሉንም አማራጮች እንጠቀማለን" ሲሉ ተናግረዋል።

ሚኒስትሩ የሰጡት ትዕዛዝ በተለይ የተጣራ የመጠጥ ውሃ ለማቅረብ የሚውሉ ማሽኖችን ከስራ ውጭ እንደሚያደርግ ተገልጿል።

የጠቅላይይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ አስተዳደር በቀጣይም ወደ ጋዛ ውሃ እንዳይገባ ሊከለክል እንደሚችል ነው የተነገረው።

እስራኤል ባለፈው ሳምንት እሁድ ማንኛውም የሰብአዊ ድጋፍ ወደ ጋዛ እንዳይገባ ማገዷ ይታወሳል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter


በቻይና አፍንጫውን መጎርጎር እንዲያቆም በሚስቱ ቢጠየቅም ፍቃደኛ ያልሆነው ወጣት ከፍተኛ የደም መፈሰስ አጋጥሞት ሆስፒታል ገባ

ሐኪሞች የተበጣጠሰ የደም ቧንቧ እንዳለ ካረጋገጡ በኋላ ጉዳቱን ለማስተካከል ድንገተኛ ቀዶ ህክምና አድርገውለታል። የሰውዬው ሚስት አፍንጫውን መጎርጎር ልማዱ እንደሆነ በማንሳት ከቀዶ ህክምና እያገገመ በነበረበት ወቅት ባጋራችው ቪዲዮ “ማር፣ ለምን አፍንጫህን ተነስተህ አትጎረጉርም? ተነሥተህ መልሰ ስጠኝ እንጂ” ስትል የቀረፀችው ምስል በርካቶች ተቀባብለውታል።

የጤና ባለሙያዎች እንደሚያስጠነቅቁት አፍንጫን መጎርጎር ከፍተኛ የሆነ የኢንፌክሽን ይፈጥራል፣ በከፋ ሁኔታ ደግሞ በአፍንጫው ክፍል ውስጥ ያሉ የደም ስሮች ወይም ቲሹዎች ይጎዳል፣ አልፎ ተርፎም ደም ወሳጅ ቧንቧን እንዲጎዳ ያደርጋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter


♨️የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ Jobs ✅
---—----------------------------     
✅ በ0 አመት  እና በልምድ

✅  የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በተለያዩ የስራ ዘርፎች ብቁ ሠራተኞችን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል፣ ስለሆነም ፍላጎት ያላችሁ ከዚህ በታች ያለዉን ማስፈንጠሪያ በመጠቀም ማመልከት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡

ብዛት: ከ20,000 በላይ
ደሞዝ ማራኪ

                How To Apply
                     👇👇👇

🟥 ፈጥነው ታች ባለው ሊንክ ይመዝገቡ

⁉️ ማሳሰቢያ:- VPN ወይም Psiphon መጠቀም ይኖርባችሗል

👇👇👇👇👇Apply Now👇👇👇👇👇👇
                        👇👇👇👇         
https://reportervacancy.com/national-election-board-of-ethiopia-jobs-2024/

--------Follow Our Website--------
                     👇👇👇👇👇👇
         https://reportervacancy.com

--------Join Our Telegram---------
                     👇👇👇👇👇
    https://t.me/reporter_vacancy


❗️የአዲስ አበባ ባለሀብቶች ያላመኑበትን ግብርና ታክስ በተጨማሪ በሌሎች ችግሮች እየተፈተኑ እንደሚገኙ ተገለፀ

የአዲስ አበባ ባለሀብቶች ፎረም በከተማው ውስጥ የሚገኙ ባለሀብቶች ከባድ ችግሮች እያጋጠሟቸው መሆኑን ገልጿል። ፎረሙ የባለሀብቶችን ቅሬታ በሰነድ የተደገፈ መረጃ ለመቀበል ዝግጅቱን ማጠናቀቁን አስታውቋል።

የባለአብቶች ፕሬዝዳንት አቶ አሸናፊ ሙሴ አያሌው ለካፒታል እንደገለጹት፣ ባለሀብቶቹ ያላግባብ ድርጅቶቻቸው መታሸግ፣ መፍረስ፣ መነጠቅ (መቀማት)፣ ሥራ እንዲያቆሙ መደረግ፣ ያላመኑበትን ከፍተኛ ግብርና ታክስ ለማስከፈል ማስገደድ፣ የባንክ አካውንታቸው መታገድ፣ ከሀገር እንዳይወጡ ወይም እንዳይገቡ እየተደረጉ ነው ብለዋል።

ከዚህ በተጨማሪ በስልክ ዛቻና ማስፈራሪያ ማድረስ፣ የማያምኑበትን አሰልቺና ተደጋጋሚ መዋጮዎች መጠየቅ፣ እንዲሁም ተረጋግተው ሥራቸውን እንዳይከውኑ ማዋከብ፣ የብድር አገልግሎት በበቂ ሁኔታ ያለማግኘት እና የመሳሰሉት ችግሮች እየደረሱባቸው መሆኑን ሰምተናል ብለዋል።

ይህን ተከትሎ ፎረሙ ከመጋቢት 01 እስከ 27 ቀን 2024 ዓ.ም ድረስ የከተማውን ባለሀብቶች ቅሬታ በሰነድ የተደገፈ መረጃ ለመቀበል መዘጋጀቱንና ባለሀብቶችም መረጃቸውን በሰነድ በማቅረብ እንዲተባበሩ ጥሪ አቅርቧል።

የባለሀብቶቹ ቅሬታ ከተሰበሰበ በኋላ ለሚመለከተው አካል በማቅረብ ችግሮቹ እንዲፈቱ ፎረሙ እንደሚሰራ አቶ አሸናፊ ሙሴ አያሌው ተናግረዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter


የመፀዳጃ ቤት ፍሳሽ ወደ ወንዝ እንዲገባ ያደረጉ የንግድ ቤቶች 6 መቶ ሺህ ብር ተቀጡ

የመፀዳጃ ቤት ፍሳሽ ከዋና ፍሳሽ መስመር በማገናኘት ወደ ወንዝ እንዲገባ ያደረጉ የንግድ ቤቶችን 600 ሺህ ብር መቅጣቱን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን አስታውቋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ከአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ጋር በመተባበር በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 የመፀዳጃ ቤት ፍሳሽ ከዋና መስመር ትቦ ጋር ባገናኙ ሁለት የንግድ ቤቶች በደንብ ቁጥር 180/2017 መሰረት እያንዳንዳቸው 300,000/ሶስት መቶ ሺህ/ ብር  በድምሩ 600,000/ስድስት መቶ ሺህ ብር በመቅጣት ርምጃ መውሰዱን ገልጿል።

ባለስልጣኑ ህብረተሰቡ ማንኛውም አይነት ፍሳሽ ቆሻሻ ወደ ወንዝ ከመልቀቅና ደረቅ ቆሻሻ ወንዝ ውስጥ ከመጣል እንዲቆጠብ አሳስቧል።

ድርጊቱን በሚፈፅሙ ግለሰቦችና ተቋማት በደንብ ቁጥር 180/2017 መሠረት ርምጃውንም አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቋል።

የከተማ አስተዳደሩ  የአዲስ አበባ ወንዞች ከመጥፎ ሽታ ተላቀው የመዝናኛ ቦታዎች እንዲሆኑ የጀመረውን ስራ ዳር ለማድረስ ደንብ በማስከበር የበኩሉን ድርሻ እንደሚወጣም መግለጹን ከተቋሙ ማኅበራዊ ትስስር ገፅ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ህብረተሰቡም ደንቡን ተላልፎ የሚገኝ አካል ሲመለከት በነፃ የስልክ መስመር 9995 ጥቆማ እንዲሰጥ መልዕክት አስተላልፏል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
ሳርቤት መቻሬ ሜዳ ፊትለፊት
📲0936410003 // 0905524551
🛏️ ባለ አንድ መኝታ
                65.77 ካሬ
                 86.86 ካሬ 
                 90.37 ካሬ 

🛏️ባለ ሁለት መኝታ
              ✅97.82 ካሬ
       
              ✅114.22 ካሬ

🛏️ባለ ሶስት መኝታ
              ✅140.31ካሬ
              ✅153.11ካሬ

Few units  are left
🏠 Reality Sarbet Canada Embassy

✨ Structure? ✅ Done!
✨ Block Work? ✅ Complete!
✨ Finishing? 🚧 In Progress

With only 10% down payment and 80% of construction complete, secure your dream home now and watch it come to life with every brick laid. Don’t miss the chance to own a quality-built, beautifully designed space in the heart of Addis Ababa.

📲 Contact us:
📞 0936410003 // 0905524251


ሰሌክታ ግሩፕ በፖለቲካ አለመረጋጋት ምክንያት ከኢትዮጵያ ወጣ

በስዊዘርላንድ ዋና መስሪያ ቤቱን ያደረገው ሰሌክታ ግሩፕ በሰሜን ኢትዮጵያ ኩንዚላ የሚገኘውን የምርት ማዕከሉን በፖለቲካ አለመረጋጋት እና በወታደራዊ ሁኔታዎች ምክንያት ወደ ኬንያ እና ኡጋንዳ ማዛወሩን አስታዉቋል።

ኩባንያው የዚህ ውሳኔ ምክንያት በኢትዮጵያ ያለው ሁኔታ ለሰራተኞች ደህንነት ስጋት መፍጠሩ እና የሎጂስቲክስ ችግሮች መከሰታቸው እንደሆነ ገልጿል።

የኩባንያዉ ዋና ስራ አስፈፃሚ አንስጋር ክሌም ይህን ውሳኔ "አሳማሚ እርምጃ" ብለው የገለፁት ሲሆን፣ በኢትዮጵያ ያደረጉትን ከፍተኛ ኢንቨስትመንት እና ጥረት ከንቱ መሆኑን ተናግረዋል።

ይህ ውሳኔ በኩንዚላ አካባቢ ከ1,000 በላይ የስራ እድሎችን የሚያሳጣ ሲሆን፣ በቀጥታና በተዘዋዋሪ ወደ 10,000 የሚሆኑ ሰዎችን ይጎዳል። ኩባንያው ለአካባቢው ማህበረሰብ የኢኮኖሚ ህይወት መስመር እንደነበር እና መውጣቱ ትልቅ ጉዳት እንደሚያስከትል ገልጿል።

ካፒታል ያገኘዉ መረጃ እንደሚያመለክተዉ ሰሌክታ ግሩፕ በኬንያ እና ኡጋንዳ ያሉትን የምርት ማዕከላት በማጠናከር ለደንበኞች የምርት አቅርቦት እንዳይቋረጥ ማረጋገጡን ገልጿል። ወደፊት ሁኔታዎች ሲሻሻሉ ወደ ኢትዮጵያ ለመመለስ ተስፋ እንዳለውም አስታውቋል።

ሰሌክታ ግሩፕ በዓለም አቀፍ ደረጃ ግንባር ቀደም የሆነ የአበባ እና የጌጣጌጥ እፅዋት አምራች ኩባንያ መሆኑ ይታወቃል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter


በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል በፀደቁ ሁለት አዳዲስ አዋጆች ዙርያ ቅሬታ ያቀረቡ ፖለቲከኛ ዛሬ ጠዋት ታሰሩ 

ከሰሞኑ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በነበረ የምክር ቤት ስብሰባ ላይ ቀርቦ የፀደቀውን የየእርከኑ የምክር ቤት ተወካዮች ብዛት ለመወሰን የወጣ አዋጅ እንዲሁም የክልሉ ህገ መንግስትን እንደገና ለማሻሻል የወጣውን አዋጅ ተቃውመው ቅሬታ ያስገቡት ፖለቲከኛ ዛሬ ጠዋት ለእስር ተዳርገዋል።

መሠረት ሚድያ እንዳረጋገጠው የቦሮ ዲሞክራያዊ ፓርቲ የፖለቲካ አደረጃጀት ዘርፍ ሃላፊ እና የክልሉ የምክር ቤት ተመራጭ የሆኑን አቶ ዮሐንስ ተሰማ በፀጥታ ሀይሎች ተወስደዋል።

የቦሮ ዲሞክራያዊ ፓርቲ በውሳኔዎቹ ላይ ቅሬታ የነበረው ሲሆን ሶስቱ የምክር ቤቱ አባላት በወቅቱ ተቃውሞ አቅርበው ውሳኔውንም 'የህገ መንግስት አተረጓጎም ላይ የቀረበ ቅሬታ' በሚል ለፌዴሬሽን ምክር ቤት ከተጨማሪ ጥያቄዎች ጋር አቅርበው ነበር።

"በዚህ ሁኔታ ያቀረቡትን ጥያቄ የተለያዩ አንድምታ እየሰጡ ይባስ ብለው ዛሬ አቶ ዮሀንስን አስረውታል" ብለው የክልሉ የመረጃ ምንጫችን ለሚድያችን ተናግረዋል።

የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት ከየካቲት 10 እስከ 11 2017 ዓ/ም በአሶሳ ከተማ ባካሄደው መደበኛ ጉባዔ በስራ ላይ የሚገኘውን የክልሉን የምክር ቤት የመቀመጫ ቁጥር ከ99 ወደ 165 አሻሽሏል፡፡

የቦሮ ዲሞክራያዊ ፓርቲ ግን የህዝብና ቤቶች ቆጠራ ሳይደረግ 165ቱ የመቀመጫ ብዛት አሁን በስራ ላይ ለሚገኙ የምርጫ ክልሎች የተከፋፈለበት መንገድ የህዝብ ብዛትን ያማከለ አለመሆኑን እና ነባር የምርጫ ክልሎች የፈረሱበትና አዳዲስ ምርጫ ክልሎች የተቋቋሙበት ሂደት ህገ መንግስቱን የጣሰ በመሆኑን እንዲሁም በቂ ውይይትና ክርክር ያልተደረገበት መሆኑን በመግለፅ ቅሬታውን ገልፆ ነበር።

ምንጭ መሠረት ሚዲያ

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter




የሪፖርተር መረጃ የተሳሳተ ነው:-ተቋሙ‼️
ምንም አይነት  አዲስ ታሪፍ ጭማሪ አልተደረገም‼️

ከሚያዝያ ወር ጀምሮ አዲስ የታሪፍ ማሻሻያ ተግባራዊ ሊደረግ እንደሆነ ተደርጎ በአንዳንድ የመገናኛ ብዙሃንና የማህበራዊ ሚዲያ የትስስር ገፆች እየተሰራጨ የሚገኘው መረጃ የተሳሳተ ነው።

ተቋሙ ከመስከረም  2017 ዓ.ም ጀምሮ ለ4 ተከታታይ አመታት  በማኅበረሰቡ ላይ ጫና እንዳይፈጠር በየሩብ አመቱ ተከፍሎ ተግባራዊ እየተደረገ የሚገኘውን የታሪፍ ማስተካከያ  ከማስፈፀም ውጪ አዲስ ተግባራዊ ያደረገው የታሪፍ ማሻሻያ አለመኖሩን እንገልፃለን ብሏል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter


ኢትዮጵያ መረጃ ለመሰብሰብ፣ ለመከላከል አቅም እንዲሁም ለማጥቃት የሚውሉ ድሮኖችን ማምረት መጀመሯ ምን ተሰማችሁ?

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter


Ethio-Telecom Jobs 2025 ✅
---—----------------------------     
♨️ እንኳን ደስ አላችሁ ለመላው ለስራ ፈላጊ ኢትዮጲያዊያን!

✅ ከ 600- በላይ ክፍት ቦታዎች በ0 አመት  እና በልምድ

✅ Number of Positions: 600+    

✅positions 0 EXP and with Exp

🔺የትምህርት ደረጃ: በሁሉም የትምህርት ደረጃ
🔺የትምህርት አይነት: በተለያዩ ዲፓርትመንቶች
🔺ቦታ: በተለያዩ የኢትዮጲያ ከተማዎች
🔺የስራ ልምድ: በ 0 ዓመትና በልምድ
🔺 የቅጥር ሁኔታ: በቋሚ ቅጥር
🔺 ብዛት: 600+ በላይ
🔺ደሞዝ:  ማራኪ

🟥 ፈጥነው ታች ባለው ሊንክ ይመዝገቡ

⁉️ማሳሰቢያ:- VPN ወይም Psiphon መጠቀም ይኖርባችሗል

👇👇👇👇👇Apply Now👇👇👇👇👇👇
                        👇👇👇👇         
https://reportervacancy.com/ethio-telecom-vacancy-national-id-registration-agent/


--------Follow Our Website--------
                     👇👇👇👇👇👇
         https://reportervacancy.com

--------Join Our Telegram---------
                     👇👇👇👇👇
    https://t.me/reporter_Vacancy


Syria from bad to worse‼️

በሶሪያ በተቀሰቀሰው ግጭት  በሁለት ቀናት ውስጥ ከ 1000 ሺ በላይ ሰዎች መሞታቸው ተገለፀ‼️

በአዲሱ የሶሪያ የጸጥታ ሃይሎች እና በቀድሞው የበሽር አልአሳድ መንግስት ታማኝ ተዋጊዎች መካከል በተቀሰቀሰው ግጭት እና የበቀል ግድያ በሁለት ቀናት ውስጥ ከ1,000 በላይ ሰዎች መሞታቸው  ተገልጿል ።

መቀመጫውን በብሪታኒያ ያደረገው የሶሪያ የሰብአዊ መብት ታዛቢ ቡድን እንዳስታወቀው ከማቾቹ መካከል 745 የሚሆኑት ንፁሀን ዜጎች ሲሆኑ ፣125 የሶሪያ የጸጥታ ሃይሎች እና 148 የአሳድ ታማኝ ተዋጊዎች ተገድለዋል ሲል አስታውቋል።

ይህ የበርካታ ሰዎችን ህይወት የቀጠፈው ግጭት በታህሳስ ወር የሶሪያ መንግስት ሀይሎች  የአሳድ አማፂያን ካስወገዱ ወዲህ  አስከፊው ግጭት መሆኑን የሰብአዊ መብት ታዛቢ ቡድኑ ገልጿል ።

ባሳለፍነው ሀሙስ የበሽር አል አሳድ ታማኝ ሃይሎች፣ በሀገሪቱ የባህር ጠረፍ አካባቢ ላታኪያ በተባለችው ከተማ የመንግስት ጸጥታ ሀይሎች ለደህንነት ስራ እየተንቀሳቀሱ ባሉበት ድንገት በከፈቱት ጥቃት ግጭቱ  መቀስቀሱ ይታወሳል።

ዘገባው የዘጋርዲያን ነው

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter

Показано 20 последних публикаций.