Фильтр публикаций


የተራቡ ዜጎች በተለይም ህጻናት በአገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች መበራከት፣ግጭቶችና የኑሮ ውድነት ተዳምረው አገሪቱን አስከፊ ገጽታ ውስጥ እየከተታት ነው የሚሉ አስተያቶች መደመጣቸውን ቀጥለዋል፡፡

በሌላኛው ጫፍ ያሉ የመንግስት ተጠሪዎች ደግሞ የተራበ የለም ፣ምርቱም ሙሉ ነው የሚሉና ተያያዥነት ያላቸው አስተያየቶችን ሲሰጡ ይደመጣሉ፡፡

ለመሁኑ እየተፈጠሩ ያሉ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ቀውሶችን ለማቅለል በእርግጥስ ስራ እየተሰራ ነው? ከዚሁ ጋር ተያይዞ በቅርቡ አስደንጋጭና አነጋጋሪ መረጃ የወጣበት አካባቢና የመንግስት ባለስልጣኑን አነጋጋሪ ምላሽ አካተን በአዲስ ማለዳ ትንታኔ ተመልክተነዋል፡፡

ከዚህ በታች ያለውን ማስፈንጠሪያ በመጫን ሙሉ ዝግጅቱን ይከታተሉ፡፡
https://youtu.be/Zc1W0T3icI8


“የእሳት አደጋ ኢንሹራንስ አገልግሎት መኖሩን የሚያውቁ ዜጎች ባለመኖራቸው ብዙ ጉዳት እየደረሰ ነው”- የኢንሹራንስ ባለሙያዎች

ሰኞ ታህሳስ 21 ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ) ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየተባባሰ የመጣው የእሳት አደጋ በንብረት እና በሰዎች ላይ የሚያስከትለው ችግር ከባድ እየሆነ መጥቷል፡፡

በንብረት ላይ በሚደርስ የእሳት አደጋ ከፍተኛ የገንዘብ መጠን ያላቸው ንብረቶች መውደማቸው በመርካቶ እና በተለያዩ አካባቢዎች የደረሱት የእሳት አደጋዎች የቅርብ ጊዜ ማሳያ ናቸው፡፡

ይህን ተከትሎ አዲስ ማለዳ ያነጋገረቻቸው የኢንሹራንስ ባለሙያዎች አብዛኛውን ባለንብረት ስለእሳት አደጋ ኢንሹራንስ ይህ ነው የሚባል እውቀት የሌለው በመሆኑ ከንብረት መውደም በዘለለ ለማንሰራራት ከፍተኛ ችግር ውስጥ እንደሚገቡ አስረድተዋል፡፡

“የኢንሹራንስ ኩባንያዎችም ስለ አገልግሎቱ መረጃዎችን በግልጽ ከማስረዳት እና ከማስተዋወቅ አንጻር ክፍተት እንዳለባቸው የሚያነሱት የኒያላ ኢንሹራንስ ዋና ስራ አስፈጻሚና የኢንሹራንስ ባለሙያው ያሬድ ሞላ ይህ ደግሞ ከእሳት አደጋ ኢንሹራንስ ጋር በተገናኘ እዚህ ግባ የሚባል ግንዛቤ በመድህን ሰጪዎቹ በኩልም ባለመኖሩ እንደሆነ ጠቁመዋል ፡፡

የእሳት አደጋ መድህን አገልግሎት በኢትዮጵያ የመድህን ዘርፍ እውቅና ከተሰጣቸው ውስጥ አንዱ ቢሆንም በተገቢው ሁኔታ አገልግሎት ስላለመስጠቱ ተደጋግሞ ይጠቀሳል፡፡

ከዚሁ ጋር በተያያዘ እንደ ስራ አስፈጻሚው ገለጻ “ብዙ ሰው እንደሚያውቀው የእሳት አደጋ ኢንሹንስ የሶስተኛ ወገን የመድህን አገልግሎት ግዴታ የሚያደርግ ህግ ቢጸድቅ የተሻለ ውጤት ሊመጣ እንደሚችልም አንስተዋል፡፡

የእሳት አደጋ ኢንሹራንስ እንደማንኛውም የኢንሹራንስ አገልግሎት የሚሰጥ ሲሆን አንድ ግለሰብ ኢንሹራንስ በሚገባበት የንብረት መጠን የተለያየ የክፍያ ሂደት እንደሚኖረው አመላክተዋል፡፡

በቤተልሄም ይታገሱ




የቀድሞ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ጂሚ ካርተር በ100 አመታቸው ህይወታቸው አለፈ

ሰኞ ታህሳስ 21 ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ) ከዲሞክራት ፓርቲ የወጡት ጂሚ ካርተር በ1976 አሜሪካ ምርጫ አሸንፈው ወደስልጣን መምጣታቸው ይታወሳል፡፡

በነበራቸው አንድ የስልጣን ዘመን ኢኮኖሚያዊ ቀውስ እና በኢራን ታግተው የነበሩ አሜሪካውን ጉዳይ ለአስተዳደራቸው ፈተና ከነበሩ ጉዳዮች መካከል ይጠቀሳሉ፡፡

ባለ ሁለት አሃዝ የዋጋ ግሽበት ፣ የወለድ ምጣኔ ከ 20 በመቶ መሻገር እና የጋዝ ዋጋ ማሻቀብ እንዲሁም የኢራን የእገታ ቀውስ በአሜሪካ ላይ ውርደትን ያመጡ ቀውሶች ተብለው ይታሰቡ ነበር፡፡

በሌላ በኩል ለሰብአዊ መብት መከበር በነበራቸው ጠንካራ ሙግት እንዲሁም በ1978 በካምፕ ዴቪድ ስምምነት ግብጽ እና እስራኤል ሰላም እንዲፈጥሩ በማድረግ የኖቤል ሽልማትም አግኝተዋል፡፡

በወቅቱ በጦርነት ላይ የነበሩትን የሁለቱን ሀገራት ፕሬዝዳንቶች ወደ ካምፕ ዴቪድ በመጥራት የሰላም ስምምነት እንዲፈጽሙ ካደረጉ በኋላ እስራኤል ከሲናይ በርሀ ወታደሮቿን እንድታስወጣ ሀገራቱም ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እንዲጀምሩ አድርገዋል፡፡

በኢትዮጲያም የ1997 ዓ.ም ብሄራዊ ምርጫን በታዛቢነት እንዲሁም የኢትየ-ኤርትራ ጦርነትን በማስቆም ረገድ ሚና እንደነበራቸው አይዘነጋም፡፡


7ኛው አመታዊ ኢቲ ሪል እስቴት ኤክስፖ ተከፈተ

ዓርብ ታህሳስ 18 ቀን 2017(አዲስ ማለዳ)በዛሬው እለት 7ኛው አመታዊ ኢቲ ሪል እስቴት እና የቤት ኤክስፖ በሻራተን ሆቴል የመክፈቻ ዝግጅቱን ያደረገ ሲሆን እስከ እሁድ ታህሳስ 20 ቀን 2017 ድረስ እንደሚቆይ ተገልጿል፡፡

በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ውስጥ የግሉ የቤት ልማት ዘርፍ የሚኖረውን ሚና ለማሳደግ እንዲረዳ ታስቦ መዘጋጀት የጀመረው ኢቲ ሪል ስቴት እና ሆም ኤክስፖ የሪል ስቴት አልሚዎችን ከገዥዎች፣ ከሻጮች፣ እና ከንግዱ ማህበረሰብ ጋር የሚያገናኝ ኤግዚቢሽን መሆኑ ተገልጿል።

በዝግጅቱ መክፈቻ ላይ በተደረገው ውይይት ሪል ስቴቶች በታሰበው ፍጥነት እድገት እንዳያስመዘግቡ ተግዳሮቶች መኖራቸውን እና ከእነሱም ውስጥ የፋይናንስ እጥረት እና የረጅም ጊዜ የብድር አገልግሎት ህግ አለመኖር መሆኑ ተመላክቷል፡፡

በመሆኑም ለውጭ ሀገር ባንኮች ገበያው ክፍት መደረጉ መልካም ለውጥ ይዞ እንደሚመጣ እና ከውጪ ባንኮች ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችል ሁኔታ እንደሚፈጠር ተስፋ መኖሩን የምጣኔ ሀብት ባለሙያ የሆኑት አቶ ዘመዴነህ ንጋቱ ገልጸዋል፡፡

የመኖሪያ ቤት የዋጋ ንረትን የሚያስከትለው ሌላኛው ነገር የጥሬ እቃ እና የግንባታ እቃዎች የዋጋ ውድነት እንደሆነ እና ሁሉንም የማህበረሰብ አቅም ያማከለ ንድፍና ዋጋ ለማቅረብ እንደሚሰራ ተገልጿል፡፡

በሌላ በኩል የተለያዩ በግንባታ ስራ ዘርፍ የተሰማሩ ድርጅቶችን በአንድ ላይ መሰብሰብ ተጠቃሚው የተሻለ አማራጮችን እንዲያገኝ እንደሚያደርግ የካዝና ግሩፕ ሊቀመንበር አዲስ አለማየሁ ጠቁመዋል፡፡

ኤግዚቢሽኑ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ የመጣውን የኢትዮጵያን የመኖሪያ ቤት ፍላጎት ለመቅረፍ ወሳኝ የሆኑ ዘላቂ የግንባታ አሰራሮችን፣ ተመጣጣኝ የቤት መፍትሄዎችን እና የፋይናንስ አማራጮችን የሚያጎላ ነው የተባለለት ሲሆን ከመንግስት ተወካዮች እና ባለድርሻ አካላት በኤግዚቢሽኑ ተገኝተዋል፡፡




የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ ከ13 ቢሊዮን ብር በላይ ያለማስያዣ ማበደሩን አስታወቀ

ዓርብ ታሕሳስ 18 ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ) የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ በሚቹ መተግበሪያ አማካኝነት ያለማስያዣ ከ13 ቢሊዮን ብር በላይ ማበደሩን አስታውቋል።

ባንኩ ከ750 ሺህ በላይ ለሆኑ የሚቹ ደንበኞች ያለምንም ማስያዣ ከ13 ቢሊዮን ብር በላይ ብድር በመስጠት ከሁሉም ባንኮች ግንባር ቀደም መሆን መሆን መቻሉንም ይፋ አድርጓል።

የህብረት ስራ ባንኩ በሚቹ የፋይናንስ አቅርቦት አማካኝነት ለጥቃቅንና አነስተኛ የንግድ ተቋማት የንግድ ፈቃድና የብድር ማስያዣ ሳያስፈልጋቸው በቀላሉ የብድር አቅርቦት በማግኘት ላይ እንደሚገኙ ገልጿል።

ባንኩ ከዚህ ባለፈም ያለማስያዣ የሚሰጠውን ብድር ተበዳሪ ተቋማትና ግለሰቦች በቀላሉና በተያዘለት ጊዜ መሠረት በመክፈል ላይ እንደሚገኙ አስታውቋል።

የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ 6ኛውን የህብረት ሥራ ማህበራት ቀን  "የኅብረት ሥራ ማህበራት፣ ለሁሉም  የተሻለ ነገ አቅኚዎች" በሚል መርህ በዛሬው እለት በአዳማ ከተማ በደማቅ ስነስርዓት በማክበር ላይ ይገኛል።


ሐሙስ ታህሳስ 17ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ) የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን አንጋፋውን የሰብዓዊ መብት ተሟጋች የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤን ማገዱ ተገልጿል፡፡

ኢሰመጉ የታገደው ከተቋቋመለት ዓላማ ውጭ ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ አድርጓል በማለት ሲሆን የመንግሥት ጸጥታ ኃይሎች በአመራሮቹና ሠራተኞቹ ላይ ማስፈራሪያና ዛቻ እንደሚፈጽሙ ለበርካታ ወራት ሲገልጽ መቆየቱ ይታወቃል፡፡

የኢሰመጉ ዋና ዳይሬክተሩ ዳን ይርጋ በዚሁ ዛቻና ማስፈራሪያ ሳቢያ ከአገር ለመሰደድ እንደተገደዱ በቅርቡ መግለጹ ማስታወሱን እና በትናንትናው እለት መታገዱን ዋዜማ ዘግቧል፡፡

ባለሥልጣኑ በዲሞክራሲና መብቶች ዕድገት ማዕከል እና ጠበቆች ለሰብዓዊ መብቶች በተሰኙት ሲቪል ማኅበራት ላይ ባለፈው ኅዳር ወር በተመሳሳይ ምክንያት ጥሎት የነበረውን እገዳ ካነሳ በኋላ፣ ድርጅቶች የተሰጧቸውን የማስተካከያ ርምጃዎቾ ተግባራዊ አላደረጉም፤ ይልቁንም የቀድሞ ጥፋታቸውን ቀጥለውበታል በማለት በቅርቡ በድጋሚ እንዳገዳቸው አይዘነጋም።

በተመሳሳይ የመብቶች እና ዴሞክራሲ ዕድገት ማዕከል (ካርድ) ጨምሮ ሶስት የሰብዓዊ ተሟጋች ድርጅቶች ላይ እገዳ ተጥሎ እንደነበር እና ቆይቶም እገዳው የተነሳ ቢሆንም በድጋሚ እገዳው ተጥሏል የሚል መረጃዎች ሲዘዋወሩ ቆይተዋል፡፡




Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
#ማስታወቂያ




#ማስታወቂያ


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
በፈንታሌ ተራራ ፍንዳታና ጭስ የታየበት በሬክተር ስኬል 4 ነጥብ 6 የሆነ  የመሬት መንቀጥቀጥ ተከሰተ

ሰኞ ታሕሳስ 14 ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ) በአዋሽ ፈንታሌ ተራራ በሬክተር ስኬል 4 ነጥብ 6 የሆነ የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱን የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጂኦፊዚክስ፣ ሕዋ ሳይንስና አስትሮኖሚ ኢንስቲትዩት አስታውቋል።

በዩኒቨርሲቲው የጂኦ ፊዚክስ ሕዋ ሣይንስና አስትሮኖሚ ተቋም የሴስሞሎጂ ትምህርት ክፍል ኃላፊ፣ የመሬት መንቀጥቀጥ ሣይንስ መምህርና ተመራማሪ አታላይ አየለ (ፕ/ር) እንዳሉት፥በአዋሽ ፋንታሌ ወረዳና አካባቢው ከታሕሣሥ 10 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ የተለያየ መጠን ያለው የመሬት መንቀጥቀጥ እየተከሰተ ነው፡፡

በዛሬው ዕለትም ከቀኑ 9 ሰዓት አካባቢ ሰሞኑን ከተከሰቱት ከፍተኛውና በሬክተር ስኬል 4 ነጥብ 6 የሆነ የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱን ለፋና ዲጂታል ተናግረዋል።

የመሬት መንቀጥቀጡን ተከትሎም ተራራው የመሰንጠቅ እና የመደርመስ ምልክት ማሳየቱን ነው ያስረዱት፡፡

በአካባቢው የሚስተዋለው የመሬት መንቀጥቀጥ ከቀን ቀን እየጨመረ መምጣቱን ጠቁመው÷ነዋሪዎች ላይ ችግር እንዳያስከትል የቅርብ ክትትል ማድረግ እንደሚያስፈልግ አስገንዝበዋል፡፡

በአፋር ክልል የዞን 3 ዋና አስተዳዳሪ አቶ አብዶ አሊ አቡበከር በኩላቸው÷ዛሬ ከሰዓት በአዋሽ ፈንታሌ ተራራ የተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ የፍንዳታ ድምጽ ያስከተለ እና ጭስ የታየበት ነው ብለዋል፡፡

በመሬት መንቀጥቀጡ የፍንዳታ ድምጽ መሰማቱ እና ጭስ መታየቱም በአካባቢው ነዋሪዎች ዘንድ ድንጋጤ መፈጠሩን ማብራራታቸው ተገልጿል፡፡




በእስር ላይ የሚገኙት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና የአማራ ክልል ምክር ቤት አባላቱ ክርስቲያን ታደለ እና ዮሐንስ ቧያለው ህመማቸው ብሶባቸዋል ተባለ

ሰኞ ታህሳስ 14 ቀን 2017(አዲስ ማለዳ) በቃሊቲ ማረሚያ ቤት እስር ላይ የሚገኙት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባሉ አቶ ክርስቲያን ታደለ እና የአማራ ክልል ምክር ቤት አባሉ አቶ ዮሐንስ ቧያለው "ለከፍተኛ ሕመም" መዳረጋቸውን የቅርብ ቤተሰቦቻቸው ገልጸዋል፡፡

የቅርብ ቤተሰብ እንደሆኑ የተገለጹት እስረኞቹ ቀዶ ሕክምና ከተደረገላቸው በኋላ "የማያቋርጥ የደም መፍሰስ እንዳጋጠማቸው" ተናግረዋል፡፡

እንዲሁም ሁለቱ ፖለቲከኞች "በተደጋጋሚ አቤቱታ" ከሁለት ሳምንት በፊት ቀዶ ሕክምና ማድረጋቸውን ጠበቃቸው አቶ ሰለሞን ገዛኸኝ ገልጸዋል፡፡

ከቀዶ ሕክምናው በኋላ ሁለቱ ግለሰቦቹ በሆስፒታል ይቆዩ ቢባልም "ያንን እምቢ ብለው በሰዓታት ልዩነት በማይመች መኪና ጭነው ወደ ማረሚያ ቤት መልሰዋቸዋል" ሲሉ ቤተሰቦቻቸው መናገራቸውን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

አንድ ክርስቲያን ታደለ የቅርብ ቤተሰብ "ቁስሉም አልደረቀም እና ደግሞ ደም እየፈሰሳቸው ነው ሐኪሞቹም ተናግረዋል፤ ደም መፍሰስ ሊያጋጥም እንደሚችል እና ይህ ሲያጋጥምም እንድታመጧቸው ብለው ነበር ነገር ግን ከቀዶ ሕክምናው በኋላ ወደ ሆስፒታል አለመወሰዳቸውን" ገልጸዋል፡፡

የፌደራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን ባለፈው ሳምንት ሰኞ ታህሳስ 7/ 2017 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ "ታራሚዎችን ከቃሊቲ ማረሚያ ቤት ገላን አካባቢ ወደ ሚገኘው እና በተለምዶ አባ ሳሙኤል ተብሎ ወደሚጠራው ማረሚያ ቤት እንደሚያዘዋውር አስታውቆ ነበር።

ይህን ተከትሎም "በአዲስ አበባ ቃሊቲ ማረሚያ ማዕከል ይሰጥ የነበረውን የታራሚ ቤተሰብ ጥየቃም ሆነ የቢሮ ስራ አገልግሎት ከታህሳስ 8 እስከ 13 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ተቋርጦ የሚቆይ" መሆኑን ጠቁሟል።

ኮሚሽኑ በዚሁ መግለጫው ካለፈው ሳምንት ማክሰኞ ጀምሮ የተቋረጠው አገልግሎት ከዛሬ ታህሳስ 14 እንደገና እንደሚጀምር በመግለጫው ገልጾ ነበር።

ነገር ግን የአቶ ክርስቲያን እና አቶ ዮሐንስ ቤተሰቦች ዛሬም ምግብ ማስገባት እና እስረኞቹን መጠየቅ እንዳልቻሉ ተናግረዋል።




የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን አዲስ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ታውቀዋል፡፡

እሁድ ታሕሳስ 13 ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ)
በ28ኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ጉባዔተኛው የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላትን መርጧል።
በእጩነት ከቀረቡት 14 ወንድ እና 12 ሴት ተመራጮች መሃል
1. አትሌት መሰረት ደፍር -18
2. ወ/ሮ ሳራ ሀሰን - 16
3. ወ/ሮ አበባ የሱፍ - 13
4. ዶ/ር ኤፍራህ መሀመድ -12
5.  አቶ ቢንያም ምሩፅ ይፍጠር- 10
6. አቶ አድማሱ ሳጅን - 10
7. ኢንጂነር ጌቱ ገረመው - 9
8. ዶ.ር ትዛዙ ሞሴ - 11
ድምጾችን በማግኘት የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ሆነው ተመርጠዋል።

በብሩክ ገነነ


አትሌት ስለሺ ስህን አዲሱ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት በመሆን ተመርጠዋል።

እሁድ ታሕሳስ 13 ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ) ዛሬ ቀጥሎ በተካሄደው የሁለተኛ ቀን 28ኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ አትሌት ስለሺ ስህን ለቀጣይ አራት አመታት የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽንን በፕሬዚዳንትነት እንዲመሩ አብላጫውን ድምፅ ማግኘታቸው ታውቋል።


“የትግራይ ሰራዊት በዲዲአር ስም እንዲበተን እየተደረገ ነው” - በደብረ ጽዮን ገብረሚካኤል የሚመራው ህወሓት

ቅዳሜ ታህሳስ 12 ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ) በዶክተር ደብረ ጽዮን ገብረ ሚካኤል የሚመራ የህወሓት ቡድን  የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር አመራሮች፣ ታጣቂዎችን ትጥቅ በማስፈታት እና በመልሶ ማዋሃድ ሥራ ስም፣ የትግራይ መሰረታዊ ጥያቄ ሳይመለስ የቀድሞ ተዋጊዎች እንዲበተኑ እየተደረገ ነው ሲል ክስ አሰምቷል።

የህወሓት አንዱ ክፋይ በመቐለ ከተማ፣ “የእምቢታ ዘመቻ” ብሎ የጠራው ስብሰባ ሲያጠናቅቅ፣ “ጊዜያዊ አስተዳደሩ እንዲፈፅም የተሰጠው ሥራ ሙሉ በሙሉ ወድቋል” በማለትም ገልጿል።

በሌላ በኩል የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ካቢኔ ለሦስት ቀናት ያካሔደውን ስብሰባ አስመልክቶ በአወጣው መግለጫ፣ “ክልሉን ወደ ግርግር እና የአመፅ ተግባር ለማስገባት የሚንቀሳቀሱ ላይ ጊዜያዊ አስተዳደሩ አይታገስም” ብሏል።

የሁለቱ ቡድኖች ፖለቲካዊ ሽኩቻ  አሁንም ድረስ መፍትሄ ሳያገኝ እንደዘለቀ ነው፡፡


በገበያ ላይ የሚገኙ ጥራታቸው ያልተረጋገጠ የፀረ-ወባ መድሀኒትቶች ማህበረሰቡ ከመጠቀም እንዲቆጠብ ተገለጸ

ቅዳሜ ታህሳስ 12 ቀን 2017 (አዲስ ማለዳ) የኢትዮጵያ ምግብ እና መድሀኒት ቁጥጥር ባለስልጣን በገበያ ላይ የሚገኙ አንዳንድ የፀረ -ወባ መድሀኒቶች ጥራታቸው ያልተረጋገጠ እና ለጤና ጎጂ በመሆናቸው ማህበረሰቡ ከመጠቀም አዲቆጠብ አሳስቧል፡፡

ደህንነት እና ጥራታቸው በባለስልጣኑ ያልተረጋገጡ መድሀኒቶች ለጤና ጎጂ እና የከፋ ችግር የሚያስከትሉ በመሆናቸው በምስሉ ላይ የተዘረዘሩትን መለያ ቁጥር የያዙ መድሀኒቶች ከመግዛት እንዲቆጠቡ እንዲሁም በቤት ውስጥ የሚገኝ ከሆነም ማህበረሰቡ በአፋጣኝ እንዲያሶግዱ  ባለስልጣኑ መመሪያን አስተላልፏል፡፡

መድሀኒቶቹም ማላሪያ ቤንን ጨምሮ ስምንት ያህል ሲሆኑ  ማህበረሰቡ ከመግዛትም ሆነ ከመጠቀም እንዲቆጠብ እንዲሁም የመድሀኒት መደብሮች ለገበያ እንዳይቀርቡ ነው ባለስልጣኑ የጠቆመው፡፡

Показано 20 последних публикаций.