All students exams&info


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Telegram


High school &university students exams &👁️‍🗨️

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Telegram
Статистика
Фильтр публикаций


#Exit_Exam_Result

የ2017 አጋማሽ ዓመት የመውጫ ፈተና (Exit Exam) ውጤት ኦንላይን የመመልከቻ ሊንክ መስራት ጀምሯል።

https//result.ethernet.edu.et ላይ በመግባት ExitExam የሚለውን በመምረጥና የራስዎን User Name በማስገባት ውጤትዎን መመልከት ይችላሉ።

@alluexams


UU Mid 2017 Exit Exam Result.pdf
104.3Кб
#UnityUniversity

፨የዩኒቲ ዩኒቨርሲቲ የመውጫ ፈተና ውጤት ይፋ ተደርጓል

ከላይ ስማችሁ የተዘረዘረ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና ያለፋችሁ መሆኑን ዩንቨርሲቲው አሳውቋል።


@alluexams


For all tg group owners don't sell your channel to a scammers like

@Vibes1221 (deciver and scammer )


Don't sell your group for this guy👀‌‌

Translation: en-en
For all tg group owners don't sell your group to a scammers like

@Vibes1221 (deciver and scammer )


Don't sell your group for this guy👀‌‌


የድሮ የቴሌግራም ግሩፕ ያላችሁ
            . 2020
            . 2021
            . 2022
.2023 jan-may       

የተከፈተ የድሮ ግሩፕ ያላችሁ መሸጥ ትችላላችሁ
.

                  👉🏻  dm @ET_RAPPER


#exit_exam

ጅግጅጋ ዩንቨርስቲ በአመቱ አጋማሽ በተሰጠው የመውጫ ፈተና ካስፈተናቸው ተመራቂዎች መካከል 98% ተማሪዎች ማለፋቸውን ገልጾአል


@alluexams


የግል ዩንቨርሲቲዎች የመውጫ ፈተና ውጤት እዳልተለከላቸው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ዳይሬክተሩ ገልጸዋል

ለፈጣን መረጃ

@alluexams


#exit_exam

በዘንድሮው የ አመቱ አጋማሽ የመውጫ ፈተና የውሰዱ የአርባምንጭ ዩንቨርስቲ የ ዶክተር ኦፍ ሜዲስን ተመራቂዎች ውስጥ 97.6% ተፈታኞች ማለፋቸው ታውቋል
ዩንቨርሲቲው 85 የዶክተር ኦፍ ሜዲስን ተመራቂዎችን ያስፈተነ ሲሆን 83 ተፈታኞች ማለፋቸውን አሳውቋል

@alluexams


#Update
#EXITEXAM

ነገ በዩኒቨርሲቲዎቻቹህ በኩል ታያላቹህ📣


የኢትዮጵያ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ህብረት ፕሬዝዳንት የሆነው ሃየሎም ስዩም የመውጫ ፈተና ውጤት ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሬጅስትራር መላኩንና ተፈታኞችም በተቋሞቻቸው በኩል ነገ ማየት እንደሚችሉ አሳውቋል።

መልካም እድል🙏

✨ Share with your  Friends
 
   
@alluexams


በተለያዩ ዩንቨርሲቲዎች ተማሪዎች በመውጫ ፈተና ላይ ቅሬታ በማቅረብ ላይ ናቸው
በተለያ በ comprehensive nursing ,civic የተሰጠው ፈተና ለፈተና ብጋርነት ከተዘጋጀው ብሉ ፕሪንት ጋር የማይገናኝ መሆኑን ተማሪዎች በደብዳቤ ለ ዩንቨርስቲዎች በማሳወቅ ላይ መሆናቸው ታውቋል


ለEXIT EXAM ወሳጅ ተማሪዎች

ትምህርት ሚኒስቴር የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ ተግባራዊ ማድረግ ከጀመራቸው ስራዎች አንዱ የሆነ የተመራቂ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና ከዛሬ ጥር 26 ቀን 2017 ዓ/ም ይጀምራል።

ለመሆኑ በዚህ ፈተና ወቅት ከተማሪዎች እንዲሁም ከፈታኞች ምን ይጠበቃል ?

[ ከተፈታኞች የሚጠበቅ ]

👉🏾 ተፈታኞች ወደ መፈተኛ ክፍል ሲመጡ ማንኛውም አይነት ስልክ፣ ስማርት ሰዓት ፣ ታብሌት ፣ ላፕቶፕና ... ወዘተ ተመሳሳይ ኤክትሮኒክ ቁሳቁስ መያዝ በፍፁም የተከለከለ ነው።  (ይዞ የተገኘ ፈተናው /ውጤቱ ተሰርዞበት በቀጣይ ጊዜ እንዲቀመጥ ይደርጋል)

👉🏾 ፈተና ከመጀመሩ ከ30 ደቂቃ በፊት መፈተኛ ክፍል መገኘት አለባቸው ይህም ማለት ከጥዋቱ 2፡00 በፊት ፤ ከሰዓት ደግሞ ከ8፡00 በፊት ተፈታኞች መገኘት አለባቸው።

👉🏾 ተፈታኞች ለፈተና ሲመጡ ID መያዝ ያለባቸው ሲሆን User Name እና Password lower-case and upper-case ፊደላትን ለይተው በጥንቃቄ መያዝ አለባቸው።

👉🏾 ተፈታኞች ፈተና ከተጀመረ በኃላ ከ30 ደቂቃ በፊት ከፈተናው ክፍል መውጣት የለባቸውም።

👉🏾 ተፈታኞች ፤ ፈተናውን የሚያስፈትኑ መምህራን በሚያሳዩት ቦታ ብቻ መቀመጥ አለባቸው።

👉🏾 ሁሉም ተፈታኝ እንዲቀመጥ የተመደበበት የራሱ ኮምፒውተር ላይ ብቻ ተቀምጦ መክፈትና መጠቀም አለበት።

👉🏾 በፈተና ክፍል ውስጥ መነጋገር እና ከቦታ ቦታ መዘዋወር በፍፁም የተከለከለ ነው። እንዲሁም ማንኛውም ተፈታኝ ከጎኑ ያለውን ተማሪ ኮምፒውተር በፍፁም ማየት የለበትም።

👉🏾 ምንም ዓይነት ወረቀት ወደ መፈተኛ ክፍል ይዞ መምጣት አይቻልም።

👉🏾 ተፈታኞች በምንም ሁኔታ መኮርጅም ሆነ ማስኮርጅ ተግባር ላይ ቢሳተፉ እርምጃ ይወሰድባቸዋል።

👉🏾 ሁሉም ተፈታኞሽ ለፈታኝ መምህራንና ለአስተባባሪዎች  መታዘዝ ያለባቸው ሲሆን የፈተናው ደንብ እና ስርዓት ተገዢ መሆን ይጠበቅባቸዋል።

👉🏾 በድጋሚ ተፈታኞች የፈተና መግቢያ ትኬት (Exit Exam Entry Ticket) መያዝ ይጠበቅባቸዋል።

NB.  ሁሉም ተፈታኞች ወደ መፈኛ ክፍል ተፈትሸው እንዲገቡ የሚደረግ ሲሆን ማንኛውም ተፈታኝ ከፀጥታ ኃይሉ ጋር በፍተሻ ወቅት ይሁን ሥርዓት ለማስያዝ በሚደረግ እንቅስቃሴ እንቅፋት ሆኖ ከተገኘ ከመፈተኛ አከባቢ እንዲገለል ተደርጎ በቀጣዩ የመውጫ ፈተና መስጫ ወቅት እንዲቀመጥ ይፈቀድለታል።

[ ከፈታኝ መምህራን የሚጠበቅ ]


👉🏾 የተፈታኝ ተማሪዎችን ID በአግባቡ በማረጋገጥ ወደ ክፍል እንዲገቡ ማደረግ ይጠበቅባቸዋል።

👉🏾 ተፈታኝ ተማሪዎችን በሥም ዝርዝራቸው መሠረት ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል።

👉🏾 ፈታኝ መምራህን የተማሪዎችን አቴንዳንሰ ይወስዳሉ ፤ ተማሪዎችን ፊርማ ያስፈርማሉ።

👉🏾 በፈተና ክፍል ውስጥ ደምጽ እንዳይሰማ፣ ተማሪዎች ከቦታ ቦታ እንዳይዘዋወሩ ተገቢውን ቁጥጥር ማድረግ አለባቸው።

👉🏾 የፈተናው አጠቃለይ ሂደት በትኩረት መከታተል አለባቸው።

👉🏾 በህመም ምክንያት ተማሪዎች ከክፍል መውጣት ቢፈልጉ ከሱፐርቨዘር ጋር በመነጋገር አስፈላጊውን እርዳታ ያደርጋሉ።

👉🏾 ተማሪዎች በጎናቸው ያለውን ሌላ ኮምፒውተር እንዳይመለከቱ መቆጣጠር አለባቸው።

👉🏾 ተማሪዎች ፈተናው ከተጀመረ ከ30 ደቂቃ በፊት እንዳይወጡ መቆጣጠር ይጠበቅባቸዋል።

👉🏾 ሲኮርጂ ወይንም ሲያስኮርጅ የተገኘ ተማሪ ከመፈተኛ ክፍል እንዲወጣ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል።

👉🏾 ፈተናው ከጀመረ 15 ደቂቃ በኃላ የሚመጣ ተማሪ እንዲገባ ማድረግ የላባቸውም።

👉🏾 የፈተና አፈጻጸም ሪፖርት ለሱፐርቨዘር ማቅረብ


9 Conic Sections.pdf
1.7Мб
📚Entrance Examination📚
🔸Hind🔸
🔴🔴🔴Maths🔴🔴🔴🔴
🔸Conic sections🔸

🗨️ከEthiopia የትምህርት አሰጣጥ ጋር ተመሳሳይ ይዘት ያለው።

😊ለ Entrance Hub እና D_Marv Tutorials ተማሪዎች የተዘጋጀ።

🎈Entrance Examination ከድንቅ ማብራሪያ ጋር።



📚 𝑫_𝑴𝒂𝒓𝒗 𝑻𝒖𝒕𝒐𝒓𝒊𝒂𝒍𝒔 : 𝐵𝑟𝑖𝑛𝑔𝑖𝑛𝑔 𝐸𝑥𝑒𝑙𝑙𝑒𝑛𝑐𝑒 𝑡𝑜 𝑠𝑡𝑢𝑑𝑒𝑛𝑡!!
❤️Ⓙ︎Ⓞ︎Ⓘ︎Ⓝ︎:@alluexams
🔴
🔴
​🔴🅢︎🅗︎🅐︎🅡︎🅔︎ Ⓦ︎Ⓘ︎Ⓣ︎Ⓗ︎ 𝔂𝓸𝓾 𝑭𝒓𝒊𝒆𝒏𝒅𝒔❤️


" የመውጫ ምዘና ላልወሰዱ ማስረጃ እንዳትሰጡ " - ትምህርት ሚኒስቴር
የመውጫ ምዘና ላልወሰዱ መምህራን ማስረጃ እንዳይሰጥ ትምህርት ሚኒስቴር አሳሰበ፡፡
ሚኒስቴሩ ለዩኒቨርሲቲዎች እና ለክልል ትምህርት ቢሮዎች በጻፈው ደብዳቤ፥ የመውጫ ምዘና ላልወሰዱ መምህራን ማስረጃ እንዳይሰጥ አሳስቧል፡፡
በሚኒስቴሩ የመምህራን ትምህርት አመራሮች ልማት መሪ ሥራ አስፈጻሚ ሙሉቀን ንጋቱ (ዶ/ር) ከሳምንት በፊት የተጻፈው ደብዳቤ፥ " በክረምት መርሐግብር ከዲፕሎማ ወደ መጀመሪያ ዲግሪ ለመሸጋገር የትምህርት ማሻሻያ ስልጠና የሚከታተሉ መምህራን፣ ስልጠና ሳያጠናቅቁ መረጃ እየተሰጠ እንደሆነ ደርሼበታለሁ " ብሏል፡፡
በክረምት መርሐግብር ከዲፕሎማ ወደ መጀመሪያ ዲግሪ የትምህርት ደረጃ ለማሻሻል ስልጠና እየወሰዱ ያሉ መምህራን፣ የማስተማር ሙያ (PGDT) መውሰድና የመውጫ ምዘና ማጠናቀቅ እንዳለባቸው በመስከረም 2017 ዓ.ም የትምህርት ሚኒስቴር ማሳወቁን በደብዳቤው ገልጿል፡፡

ይሁን እንጂ አንዳንድ ክልሎች ከዚህ በተለየ የማስተማር ሙያ ስልጠናም ሆነ የመውጫ ምዘና ላልወሰዱ መምህራን፣ የደረጃ ዕድገት እየሰጡ መሆኑናቸውን መረዳቱን አሳውቋል፡፡

ማንኛውም ሠልጣኝ የትምህርት ማስረጃ ማግኘት የሚችለው የትምህርት ምዘና ወስዶ ማለፍ ሲችል መሆኑ እየታወቀ፣ የዲግሪ ትምህርታቸውን እንደጨረሱ በማድረግ የትምህርት ደረጃ ማሻሻያና የደረጃ ዕድገት የሚሰጡ አንዳንድ ተቋማት መኖራቸውን ሪፖርተር ያነጋገራቸው መሪ ሥራ አስፈጻሚው ተናግረዋል፡፡

የትምህርት ሚኒስቴር ወጪያቸውን በመሸፈን የሚያስተምረው የበቁ መምህራንን ለማፍራት ነው ያሉት ኃላፊው፤ ማንኛውም ተቋም የመውጫ ምዘና ወስደው ላላለፉ ዕጩ መምህራን ምንም ዓይነት ማስረጃ እንዳይሰጥ በደብዳቤ ማሳወቁን አስረድተዋል፡፡
#ሪፖርተር


@alluexams


#EIXT_EXAM

የመውጫ ፈተና ከጥር 26 እስከ  ጥር 30 ይሰጣል።

የቅድመ-ምረቃ ፕሮግራሞች የመውጫ ፈተና (Exit Exam) ከጥር 26-30/2017 ዓ.ም እንደሚሰጥ ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል፡፡

የመውጫ ፈተናው ለአዲስ እና በድጋሜ ለመፈተን ላመለከቱ በሙሉ እንደሚሰጥ ሚኒስቴሩ ገልጿል።


@alluexams


ተይዘዋል‼️
በትላንትናው እለተ በኦሮቶዶክስ እምነት የቅዱስ ሚካኤል ታቦታ ሲያሾፉ ከነበሩት የአምቦ ተማሪዎች ውስጥ ሁለቱ በቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን አንደኛው ከፈተና እስከሚወጣ እየተጠበቀ ነው።
ይህ አስነዋሪ ድርጊት ከሴኩላሪዝም አንፃር ጭምር አስተማሪ እርምጃ መውሰድ ያስፈልጋል።




@alluexams


በ2017 ዓ.ም አጋማሽ የሚሰጠውን የቅድመ ምረቃ ፕሮግራሞች የመውጫ ፈተናን ዳግም ለመውሰድ ፍላጎት ያላችሁ አመልካቾች ይህንን ሊንክ https://exam.ethernet.edu.et በመጫን መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

@alluexams




#ማሳሰቢያ _12

የተፈታኝ ተማሪዎች ምዝገባ ተጠናቋል ተብሎ በተለያዩ የማሀበራዊ ሚዲያ የተለቀቁ መረጃዎች የተሳሳቱ መሆናቸውን ዛሬ በተላከ ደብዳቤ አረጋግጠናል
የመደበኛ ተፈታኞች ምዝገባ ሊጠናቀቅ 4 ቀናት መቅረቱ ሲረጋገጥ የድጋሚ ተፈታኞች ምዝገባ 14 ቀናት ይቀሩታል ።በዚህ መሠረት ምዝገባ እንድትፈጽሙ እናሳስባለን


ተማሪ መረጃ

@alluexams


ማሳሰቢያ_12

የ6ኛ፣8ኛ እና 12ኛ ክፍል የመጀመሪያው ሞዴል ፈተና ከጥር 6-8/2017 ዓ.ም የሚሰጠ ስለሆነ ከአሁኑ ዝግጅት እንድታደርጉ እናሳስባለን

የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ

@alluexams


ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስየልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን!

መልካም በዓል❤️
━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
━━━━━━✦✗✦━━━━━━━
ምርጫዎ ስለሆነ እናመሰግናለን

✦ የምንም ግዜ ተወዳጅ የሆነው
➳➳➳ ሼር ያድርጉ!! ➢➢➢
አዘጋጅ፦ @alluexams
    ➟➟➟➟➟➛➟➟➟➟➟


User Guide Private Registration.pdf
4.7Мб
User Guide Private Registration
የግል ተፈታኞች የመመዝገብያ መመሪያ ስለሆነ ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ ተከታትለዉ እንድመዘገቡ ድጋፊ እናድርግ
ማሳሰቢያ የሚናስገባዉ ስልክ ቁጥር ቴሌብር መኖር አለበት
ክፋያዉም መጠን በሚንፈተነዉ ትምህርት አይነት መጠን ነዉ
የግል መደበኛ እና የማታ የመመዝገቢያ ክፍያ   150 ብር  በትምህርት አይነት ተሰለቶ ክፍያ  100 ብር *በት/ት አይነት


ተማሪ መረጃ(ግርማዬ ታደሰ)

ለበለጠ መረጃ

@alluexams

Показано 20 последних публикаций.