Фильтр публикаций


ሰበር ዜና: 1446 የረመዳን ጨረቃ በሳውዲ አረቢያ በመተየቷ ነገ ቅዳሜ የካቲት 22 የረመዳን የመጀመሪያ ቀን ይሆናል።


የቀይ ባሕር አፋር ዴሞክራሲያዊ ድርጅት...✌️🇪🇷

ይህ ከስር በፎቶ የምትመለከቱት የቀይ ባሕር አፋር ዴሞክራሲያዊ ድርጅት ሊቀመንበር ታጋይ ኢብራሂምን ሃሩን ይባላሉ።

የዛኔ በሁለቱ ወንበዴ ቡድኖች ስምምነት የተደረገው የቀይ ባህር አፋር ያገለለው ሪፈረንደም ከተረገ ጊዜ ጀምሮ የተቋቋመው የቀይ ባሕር አፋር ዴሞክራሲያዊ ድርጅት ለሁለት አስርተ አመታት የአምባገነኑ የኢሳያስ አፍወርቂ ስረዓት ለመጣል የትጥቅ ትግል እያደረገ ይገኛል።

እንደሚታወቀዉ "የቀይ ባሕር አፋር ሕዝብ በአምባገነኑ የኢሳያስ አገዛዝ ሃይለኛ ጭቆና ግፍ እየወረደበት በዚህ ምክንያት በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ የቀይባህር ስደተኞች በአፋር ክልል በተለያዩ በስደተኞች ካምፕ ይገኛሉ። እዛም ሀገሩ ውስጥ የቀሩት ብዙ ጭቆናና ግፍ እየደረሰባቸው ይገኛል ። እናም እነዚህ ጀግና ልጆቻቸው ህዝባቸውን ከአምባገነኑ ስረዓት ነፃ ለማውጣት ያደረጉት የብዙ አመታት ልፋት ፍሬ ሊያፈራና የቀይባህር አፋር ህዝብ የሰላም አየር የሚተነፍሱበት ጊዜ ቅርብ ነው። ኢንሻአላህ።

Ahmed Habib Alzarkawi


ግብጽ እና ኤርትራ መርዶ ላይ ናቸው። ፈረሶቻቸው የሚገቡበት ጎድጓድ አጥተዋል። ጀግናው የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሶማሊያ፣ ሞቃዲሾ ገብቷል።
ጠ/ሚ ዐቢይ እና ፕ/ት ሀሰን ሼክ በጋራ በሰጡት መግለጫ በሁለቱ ሀገራት ሕዝቦች መካከል ያለውን ጥልቅ ታሪካዊ ትሥሥር እና የጋራ ድንበርን ከግንዛቤ በማስገባት በተጠናከረ ዲፕሎማሲያዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ማኅበራዊ ትብብር የበለጠ ማጠናከር የሚቻልበት ሁኔታ ላይ ተወያይተዋል።
Ahmed Habib Alzarkawi


ስለ ቀይባህር ሲነሳ!!

''የኢትዮጵያን ሰንደቅ አላማ እንኳን እኛ ግመሎቻችን ያውቁታል''

ይህ የአፋር ንጉስ ቢቱወደድ ሱልጣን አሊሚራህ አላህ ይርሀማቸው ታሪካዊ ንግግር ሁሌ ስለ ቀይባህር ሲነሳ አብሮ ይነሳል ምክንያቱም ቢቱወደድ ሱልጣን አሊሚራህ ይህን አይረሴ በሁሉም ኢትዮጽያዊ ዘንድ የሚወደድለት ታሪካዊ ንግግር የተናገሩት ያኔ በሁለት ወንበዴ ቡድኖች ስምምነት የኤርትራ ህዝበ ውሳኔ ሪፈረንደም የቀይ ባህር አፋር በገለለ መልኩ ሲካሄድ። የቀይ ባህር አፋሮች ከኢትዮጵያ መነጠሉን አስመልክቶ የተናገሩት ታሪካዊ ንግግር ነው።

Ahmed Habib Alzarkawi

9.1k 1 4 11 107

አሰብ ወደ ባለንብረቷ ኢትዮጵያ ሉዓላዊ ግዛት በቀጥታ እስካልተመለስ ድረስ ኢትዮጵያና ኤርትራ መሀል የሚፈጠር ሽንገላ እንጂ እውነተኛ ሰላም አይኖርም ።

የኤርትራ ቀጣይ ኢኮኖሚና ደህንነት የሚረጋገጠው አሰብ ለኢትዮጵያ በሰላማዊ መንገድ በመመለስ ብቻ ነው። ያ ካልሆነ ኤርትራ ካለፈው 33ዓመታት ነፍስ አልቦነት የከፋ ሁኔታ እንጂ ያነሰ ቀጣይ Future አይኖራትም። ነገር ግን ከትክክለኛውን የሰላማዊ ርክክብ ውጭ በነ ኢሳያስ በኩል የሚመረጥ የጥፋት መንገድ ካለ መጨረሻው የ130 ሚሊየን ባህርበር የተዘጋባቸውን ኢትዮጵያዊያንን ድል ያፋጥናል።

በየትኛው መንገድ አሰብ ወደ ኢትዮጵያ መመለሱ ላይቀር ከጥፋት መንገድ እንዲቆጠብ ሻዕቢያን መምከር ከባድ ቢሆንም ኤርትራዊያንን ማስተማር ማስገንዘብ ያስፈልጋል።

ሊሰመርበት የሚገባው :- ኢትዮጵያ አሰብን በኪራይ አይደለም ምትፈልገው ፤ ወደ ሉዓላዊ ግዛቷ መመለስ እንጂ ፤ " በሊዝ በኪራይ ወዘተ.. ተጠቀሙ" አይነት ማዘናጊያ መቼም ቢሆን ተቀባይነት አይኖረውም።

#asabethiopia

9.5k 1 11 37 135

በኢትዮጵያ ፈንታሌ የተከሰተው የመሬት መናወጥ የምስራች ዜና ይዞ መጥቷል

የኢሮፒያን ሳተላያት መረጃ ይዞ በወጣው መሰረት ከሰሞኑን በፈንታሌ ሲከሰት የነበረው የመሬት ርዕደት እንደተፈራው አደጋ ሳይሆን እጅግ ባልተለመደ መልኩ ሚቴን የተሰኘውን የተፈጥሮ ጋዝ ከምድር ሆድ እቃ ውስጥ ይዞ ወጥቷል ብሏል።

በሚቴን የተፈጥሮ ጋዝ ዙሪያ የሚሰራው የካናዳው ድርጅት GHGsat እንደገለፀው በፈንታሌ ተራራ በአሁን ሰዓት በ ቀን 1,400 ቶን የሚቴን ጋዝ እየወጣ ይገኛል ። ይህንንም በንፅፅር ሲያስረዳ 1,400 ቶን ጋዝ በቀን ማለት 20ሚሊየን ኪሎ ግራም የከሰል ድንጋይ ቢቃጠል የሚገኘው ሃይል እንደ ማለት ነው ብሏል ግዝፈቱን ለማስረዳት ።

በሌላ በኩል በአሁን ሰዓት በቀን እየወጣ ያለው 1400 ቶን የሚቴን ጋዝ 8000 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ሀይል ማመንጨት የሚችል ሲሆን ይህም... ከህዳሴው ግድብ ሀይል ማመንጫ በ3ሺ ሜጋ ዋት ይልቃል ።

ይህ ብቻ ሳይሆን እንደማየነኛውም የተፈጥሮ ጋዝ ይህ አሁን ፈንታሌ በራሱ ግዜ በገዛ ፍቃዱ እነሆ በረከት ብሎ ብቅ ያለው ሚቴን በአግባቡ ጥቅም ላይ ከዋለ በአሁን ሰዓት እጅግ ተፈላጊ ወደ ሆነው LNG (Liquefied Natural gas ) ተቀይሮ ወደ 2 ሚሊየን ሊትር በቀን ማምረት ይቻላል ።
በዚህም አያበቃም ... ለግብርና ምርጥ ወሳኝ የሆነው የተፈጥሮ ማዳበሪያ ቢለወጥ ኢትዮጵያ በአለማችን ከፍተኛው ፖታሽ ሃብት ባለቤት እንደመሆኗ የኢትዮጵያን የማዳበሪያ ፍላጎት አሟልቶ በኤክስፖርት የሀብት ምንጭ የሚሆን ሀብት ነው ተብሏል።
በቀላሉ ለማስረዳት ኢትዮጵያ ሳይታሰብ የተፈጥሮ ጋዝ ምድሯን ፈንቅሎ ወጥቷልና አስፈላጊው ጥናትና በጀት ተይዞ ወደ ስራ ሊገባ ይገባል ።

4.9k 0 33 13 109

አፋር ልማት ላይ ነው!!

የአፋር ክልል ፕሬዝደንት ሀጅ አወል አርባ እና የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች በአፋር ክልል በፈንቲ ረሱ ዞን አውራ ወረዳ በክልሉ መንግስት እየተሰሩ የሚገኙ የጎርፍ መከላከል ስራዎችና እንዲሁም የተለያዩ የልማት ስራዎችን ጎብኝተዋል።ኘሬዝደንት ሀጅ አወል አርባ ላለፉት ቀናቶች በክልሉ በተለያዩ አከባቢዎች እየተሰሩ የሚገኙ የልማት ስራዎችን እየተዘዋወሩ እየጎበኙ ይገኛሉ።


ከ27 ዓመታት በፊት 1990 በኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ምክንያት ተዘግቶ የነበረው እና ከሰባት አመት በፊት የተከፈተው በኢትዮጵያ የኤርትራ ኤምባሲ በዛሬው እለት ዳግም የተዘጋ ሲሆን የኤምባሲው ሰራተኞችም በፍጥነት ንብረታቸውን ሸክፈው በመውጣት ላይ ይገኛሉ ተብሏል።


የአፋር ተወላጅ የሆነው የጅቡቲ ውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ማሕሙድ አሊ ይሱፍ የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሆነው ተመረጡ!!

የ59 ዓመቱ ዲፕሎማት ለሚቀጥሉት አራት ዓመታት ኮሚሽኑን እንዲመሩ የተመረጡት ዛሬ በአዲስ አበባ መካሔድ በጀመረው የአፍሪካ ኅብረት ዓመታዊ የመሪዎች ላይ ነው።
አሊ ሞሐመድ ይሱፍ ላለፉት ሥምንት ዓመታት የኮሚሽኑ ሊቀ መንበር የነበሩት ሙሳ ፋኪ ማኅማትን ይተካሉ። ይሱፍ የተመረጡት የኬንያው ጉምቱ ፖለቲከኛ ራይላ ኦዲንጋ እና የማዳጋስካር የቀድሞ የኤኮኖሚ እና የፋይናንስ ሚኒስትር ሪቻርድ ራንድሪያማንድራቶን አሸንፈው ነው።
የአፍሪካ ኅብረት 38ኛ ዓመታዊ የመሪዎች ጉባኤ በአዲስ አበባ ሲጀመር የአንጎላው ፕሬዝደንት ዮዋዎ ሎሬንሶ የዓመቱን የአፍሪካ ኅብረት ሊቀመንበርነት ከሞሪታኒያው ፕሬዝደንት ሞሐመድ ዑልድ ተረክበዋል።
የዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ቀውስ እና የሱዳን ጦርነት በጉባኤው ትልቅ ትኩረት ከሚሰጣቸው ርዕሰ ጉዳዮች መካከል እንደሚሆኑ ይጠበቃል። አሜሪካ የምትሰጠው ሰብአዊ ርዳታ መቋረጥም የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች ዓመታዊ ጉባኤን ትኩረት የሚስብ ነው።



Показано 10 последних публикаций.