#Repost
🔂MR ቢን አጭር ታሪክ ክፍል 1🔂
✅የሳቅ ንጉስ ነው ይሉታል የልጅነት ጊዜያቸውን ያደመቀላቸው፣ ከህጻን እስከ አዋቂ በመላው አለም አድናቂዎች አሉት የሆሊውዱ ፈርጥ በአስቂኝ ድራማዎቹ ዝናን ያተረፈው ሮዋን ሴባስቲያን አትኪንሰን ወይንም ሚስተር ቢን፡፡🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹🔹
✅ሮዋን አትኪንሰን እንግሊዛዊ ተዋናይ፣ ኮሜዲያን እና ጸሐፊ ነው፡፡ ነገር ግን ዝናን ያተረፈው ሚስተር ቢን በተሰኘው ተከታታይ አስቂኝ ሲትኮም ላይ ነው።
✅
ብዙዎች ፊቱን ሲመለከቱ በሳቅ ይፍነከነካሉ፤ ለ30 ዓመታት ዓለምን በሳቅ አዝናንቷል። ነገር ግን ብዙዎች ትክክለኛ ህይወቱ ምን እንደሚመስል አያውቁም። ይህ የሮዋን አትኪንሰን ወይም በመድረክ ስሙ ሚስተር ቢን አጭር አስተማሪ ታሪክ ነው።
✅
እንደ ወሬ ነጋሪዎች ከአልበርት አንስታይን የሚበልጥ IQ እንዳለው ይነገርለታል .ሮዋን ከኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ በኢንጂነሪንግ ማስተርስ ድግሪ የተመረቀ ነው። የሚስተር ቢን መሆን ጉዞውም የተጀመረው እዚሁ ኦክስፎርድ በሚማርበትጊዜ ነው።
✅በዚያን ጊዜ እንኳን ሊያስቃቸው ይቅርና በመልኩ የተነሳ የክፍሉ ተማሪዎች 'ኤሌን ፊት' እያሉ ሙድ ይያዙበት ይዘባበቱ እና ያበሽቁት ነበር። በተደጋጋሚ ለትወና በሚያመለክትበት ጊዜ 'በአግባቡ ለመናገር ያዳግተው ስለነበር/ይንተባተብ ስለነበር' በተደጋጋሚ አይሆንም ይባላል። የእነሱ እምቢታ ግን ወጣቱን ወደህልሙ ከመገስገስ እና ከመሞከር ሊያቆመው አልቻለም።
✅ከብዙ ሙከራ በኋላ አንድ ቀን መንተባተብ በትንሹም ቢሆን አቆመ። በትክክል ማውራት ቻለ። ስለሁኔታው ሲናገር፤ "አውነቱን ለመናገር መስታውት ፊት ቆሜ ፊቴን እየቀያየርኩ እለማመድ ነበር። እራሴን ሳይሆን ገፀባህሪውን ስሆን መናገር ቀለለኝ።"
✅ያም ሆነ በመልኩ/በፊቱ/ የተነሳ ማንም ሊያሰራው የሚፈልግ አልነበረም። ብዙ ቢሞክርም ጥረት እንጂ ውጤት ሊያገኝ አልቻለም፤ በትወና ብቻ ሳይሆን ህይወቱም ከበደበት፤ ሁሉም ነገር ካሰበው ጋር የሚሄድ ነገር የለም።
✅በመጨረሻም ወደ ራድዮ ጣቢያዎች ጎራ አለ።
እ.ኤ.አ. በ1979 “The Atkinson People” የተሰኘ በ ቢቢሲ 3 የሬዲዮ ጣቢያ ላይ የተላለፈ አስቂኝ ተከታታይ የሬድዮ ድራማ ላይ በመሳተፍ ድብቁን እና እምቁን ችሎታውን ለህዝብ ማሳየት ቻለ።
✅አስር አመታትም ፊቱን ሲያሳይ በድምፅ ብቻ Mr bean የተባለውን ገፀባህሪ እየተጫወተ አሳደገው። በመጨረሻም ሚስተር ቢን በስሎ ከአስር ዓመት በኋላ ወደ ቴሌቭዠን በአካል መጣ።
✅እ.ኤ.አ በ 1979 በለንደን ዊኬንድ ቴሌቭዥን ላይ የተላለፈው Canned Laughter ወይንም የታፈነ ሳቅ የተሰኘ መጠሪያ ባለው አስቂኝ ተከታታይ ድራማ ላይ ለመሳተፍ በቃ።
እ.ኤ.አ በ1986 ለ4 ዓመታት በተላለፈው ብላክ አደር የተሰኘ አስቂኝ ተከታታይ የቴሌቭዥን ድራማ ችሎታውን ማስመስከር ችሏል። በጊዜውም ቢቢሲ ላይ ከተላለፉ እና ስኬታማ መሆን ከቻሉ ሲትኮሞች አንዱ ሆነ ይቀጥላል። 🔸🔸🔸🔸🔸🔸🔸
✅
@amazing_fact1✅
✅
@amazing_fact1✅