✅በአፍርካ ባለ ትልቋ ጥርስ ዝሆን "Dida'' ትናንት በምስራቁ''Tsavo'' ብሔራዊ ፓርክ ኬኒያ ውስጥ ሞታ ተገኝታለች ።
60-65 አመቷ እንደሆነላት የሚነገርላት ''Dida''በቅፅል ስሟ ''Queen of Tsavo''በመባል ትታወቃለች ፣ ከፍተኛ የቱሪስት ትኩረት የነበረችው ፣ በአፍርካ ብቻ ሳይሆን ምናልባት በአለምም ባለ ትልቋ ጥርስ ዝሆን ትሆናለች ተብሎ ይገመታል።
ህገወጥ የዝሆን ጥርስ አዟሪዎች በበዙባት አፍርካ ፣ አንድ ኪሎግራም ጥርስ በብዙ ሺ ዶላሮች ይሸጣል ፣ የአንድ ባለ ትልቅ ጥርስ ዝሆን ጥርስ አንዱ ብቻ እስከ 50 ኪሎግራም ይመዝናል። መሰል ዝሆኖች በህይወት የመቆየት እድላቸው ከባድ ስለሆነ ባለ ትልቅ ጥርስ ዝሆኖች በምስራቅ አፍርካ እየተመናመኑ ነው።
@Amazing_fact_433@Amazing_fact_433