አንዲት ሴት የተራበ ትንሽ እባብ መንገድ ላይ አገኘች።
እናም ከሚሰቃየው እራብ ልታድነው ወሰነች።
ወደ ቤቷ ወሰደችውና አስጠለለችው።እባቡም አድጎ እስኪለምዳት ድረስ መመገብ ጀመረች።
ወደ ቤት በገባችበት ቦታ ሁሉ ከኃላ ይከተላታል።
ማታ ላይ በሙቀቷ እየተደሰተ አልጋው ላይ ከጎኗ ይተኛል ።
ዓመታት አለፉ እና እባቡ አደገ።
🌼🌼🌼🌼
እናም አንድ ቀን ያቺ ሴት እባቡ ባልታወቀ ምክንያት መብላት በማቆሙ ተገረመች።
አዛኟ ሴት እባቡን እንዲበላ ለማድረግ ብዙ ሞክራለች።
እሱ እንዳይሞትና እንዳይጠፋ በመፍራት ፤ እባቡ ግን እምቢ አለ።
እና ሙከራዎቿ ሁሉ አልተሳኩም።
- እባቡ ለመመገብ ፈቃደኛ ባለመሆኑ ለብዙ ሳምንታት በዚህ ሁኔታ ውስጥ ቆየ።ነገር ግን በቀን ይከተላታል ።ማታ አልጋዋ ላይ ከጎኗ ይተኛ ነበር። ሰውነቷ ላይ በመጠምጠም ሙቀት ከሰውነቷ እየወሰደ አብሯት ይተኛል ።
- በመጨረሻም ከጥቂት ሳምንታት በኋላ ሴትየዋ ወደ የእንስሳት ሐኪም ወስዳ እንዲመረምረው ወሰነች። ምናልባት ታሞ ህክምና ያስፈልገዋል ፤ በሚል እሳቤ።
ሐኪሙ እባቡን ከመረመረ በኋላ ወደ ሴቲቱ ዞር ብሎ ጠየቃት።
🌼🌼🌼🌼
ሃኪሙ :- እባቡ ላይ የምግብ ፍላጎት ከማጣት እና ከምግብ ከመታቀብ በስተቀር ሌሎች ምልክቶችን አስተውለሻል ?
ሴትየዋ መለሰች፡- እረ የለም።
- ዶክተሩ በድጋሚ ጠየቃት: - አሁንም ለሊት ካጠገብሽ ይተኛል ?
- ሴትየዋ መለሰች:- አዎ ፡ እሱ ከእኔ ጋር በጣም ይጣበቃል። ወደ ቤት ውስጥ በሄድኩበት ሁሉ ይከተለኛል። ሁልጊዜ ማታ በአጠገቤ አልጋ ላይ ይተኛል።
- ዶክተሩ ጠየቃት፡- አንዳንድ ጊዜ ከጎንሽ ሲተኛ በሰውነትሽ ላይ እንደሚጠመጠም አላስተዋልሽም?
- ሴትየዋ በጣም ተገርማ ለሐኪሙ: - አዎ ፡ አዎ ፡ ይጠመጠምብኛል አለችው።
በቅርብ ጊዜ በህመሙ ምክንያት ሙቀት በመፈለግ እንዳዝንለት አንዳንዴ በእንቅልፍዬ ላይ እያለሁ ይጠመጠማል። ሲነቃም በአይኑ ይከተለኝና ምግብ ለሱ ለመስጠት እቸኩላለሁ። እንደ አለመታደል ሆኖ ለመብላት ፈቃደኛ አልሆነም እና በቦታው ይቀመጣል።
- ዶክተሩ ፈገግ አለና እንዲህ አላት፡ -
እመቤት ፦ ይህ እባብ አልታመመም ሊበላሽ ነው እንጂ!!!
እሱ
እባቡ አንችን ለመብላት አእስኪችል ድረስ ለመራብ እየሞከረ ነው።
እንዲሁም ከአንቺ ጋር በፍቅር ሳይሆን በሰውነትሽ ላይ የሚጠቀለለው አንቺ እንደምታስቢው ሙቀት እና ርህራሄ ፍለጋ ሳይሆን ከሆዱ መጠን ጋር የሰውነትሽ መጠን ለመለካት እየሞከረ ነው።
ይህም ሆዱ የአንቺን መጠን የሚበላ ምግብ ለማስተናገድ በትክክለኛው ጊዜ ሊያጠቃሽ እየተዘጋጀ ነው።
እመቤቴ ይህን እባብ በፍጥነት አስወግጅው። ብሎ መከራት !!
ከታሪኩ የምንማረው ፡-
- አንዳንዶች በዙሪያው ያሉትን በፍቅር፣ በደግነት ወይም በበጎ አድራጎት ሊለውጥ ይችላል ብለው ያስቡ ይሆናል።
ነገር ግን በአንዳንዶች ውስጥ በተፈጥሮ መርዝ ተሸክመው ጊዜ የሚጠብቁ ብዙ ሰዎች አሉ እናም ይጠንቀቁ ።
ፈጣሪ ከክፋታቸው ይጠብቀን ።
Bini Berhe✍
🌼🌼🌼🌼
"ማንበብ ፋሽን ነው።"
Join us
@noahbookdelivery