''60 ወታደር እና 200 መሳሪያ ሲማረክ ከ150 በላይ ሙት ሆኗል'' የአማራ ፋኖ ጎንደር ዕዝ።
3 ክፍለጦር፣ 3 ጀንበር እልፍ ድል በጎንደር ምድር !
የአማራ ፋኖ ጎንደር ዕዝ 3 ክፍለጦሮች 72 ሰዓታትን ከጠላት ጋር እያደረጉት ባለው እልህ አስጨራሽ ትንቅንቅ ከፍተኛ ድልና ጀብዱ አስመዝግበዋል።
እስካሁን ተጠናክሮ በቀጠለው ይህ ትንቅንቅ የአገዛዙን 68ኛ ክፍለጦር በጥራይናና ወገዳ ቀጣናዎች በመግጠም ከፍተኛ የመሳሪያና ወታደር ምርኮ ያገኙበትና ከፍተኛ ቁጥር ያለውን የአገዛዙን ሀይል ሙትና ቁስለኛ አድርገው ድል ያስመዘገቡበት፤ አሁንም እየተፋለሙበት ያለ ሆኗል።
የአማራ ፋኖ ጎንደር ዕዝ ድብ ጠለምት ክፍለጦር፣ ጭና ክፍለጦርና ሰሜን አምባራስ ክፍለጦሮች እያደረጉት ባለው ትንቅንቅና ድል በተጎናፀፉበት ተጋድሎ ከ200 በላይ የነፍስ ወከፍ መሳሪያና ከ 60 በላይ የአገዛዙ ወታደሮች እንደዚሁም ከፍተኛ ቁጥር ያለው የብሬንና ስናይፐር ምሮኮም በወገን ሀይል ተገኝቷል።
በትንቅንቁ እድል የቀናቸው የአገዛዙ ሀይሎች በቀላልና ከባድ ቁስለትም ውስጥ ሆነው ለሽሽት ሲበቁ ከ 150 በላይ የሚሆኑት በውጊያው ተገድለዋል ሲል የአማራ ፋኖ ጎንደር ዕዝ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ፋኖ ዮሀንስ ንጉሱ ለኢትዮ 251 ሚዲያ ገልጧል።
ይህ የመረጃ ቅብብል ቃለምልልስ እየተደረገ ባለበት ጊዜም ውጊያው በከፍተኛ ሁነት ተጠናክሮ መቀጠሉን ፋኖ ዮሀንስ አንስቷል።
ታሕሳስ 17/04/2017 ዓ.ም
አሻራ ሚዲያ
#ከ350 ሺህ በላይ ተከታይ የነበረው የአሻራ ሚዲያ የፌስቡክ ገፅ በጠላቶች ስለተዘጋ አዲሱን የአሻራ ፌስቡክ ገፅ ይወዳጁ 👇👇
https://www.facebook.com/profile.php?id=61554383356900ይሕ አዲሱ የአሻራ ሚዲያ የዩቱዩብ ቻናል ነው
በጠየቃችሁን መሰረት በዩቱዩብ መረጃወችን ለማድረስ ቻናሉን ከፍተናል አሁኑኑ ሰብስክራይብ በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://www.youtube.com/channel/UCc4BFUPttYZXRyyMZ83iGaAትኩስና አዳዲስ ሁነቶችን ለማግኘት አዲሱን የአሻራ ዩትዩብ ቻነል Subscribe ያድርጉ‼
👇👇👇👇👇👇
https://youtu.be/UH4zZz1lxmc