Ashara Media - አሻራ ሚዲያ


Гео и язык канала: Эфиопия, Английский
Категория: Telegram



Гео и язык канала
Эфиопия, Английский
Категория
Telegram
Статистика
Фильтр публикаций






የኢትዮጵያ አየር ኃይል ዋና አዛዥ ነው ያዘዙት በሚል 6 የኢትዮጵያ አየር መንገድ አመራሮች ለፋኖ በኢትዮጵያ አየር መንገድ የባህርዳር በረራ መሳሪያ ልካችኋል በሚል እንዲታሰሩ መደረጉ ተሰማዘንድሮ ከፋኖ እና ከመከላከያው ውጊያ ጋር ተያይዞ በየእስር ቤቱ በሚፈረበረከው የክስ ዓይነት የሚታሰሩ ዜጎች ጉዳይ ይገርማል ይላሉ የዘ-ሐበሻ የደህንነት ምንጮች። ስማቸው እንደ ሸዋንግዛው የመሳሰሉ ሰዎች በአዲስ አበባ ዙሪያ እንኳን ጭምር መንቀስቀስ የማይችሉና በመታወቂያቸው እየተለየ በኮማንድ ፖስቱ እንደሚታሰሩ ከዚህ ቀደም የዘገብን ሲሆን፤ ዛሬ ደግሞ የደህንነት ምንጮች ያደረሱን መረጃ ከማስገረምም አልፎ የደረስንበትን አደገኛ ሁኔታ የሚያሳይ ሆኖ አግኝተነዋል።በኢትዮጵይ አየር መንገድ በተለያየ ኃላፊነት የሚሰሩ ስድስት አመራሮች እና እንዲሁም የአየር መንገዱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው ሹፌር ከፋኖ ጋር ተጠጥርጥረው በሃሰተኛ ክስ አዋሽ 7 እና አዋሽ 40 እየማቀቁ እንደሆነ የደህንነት ምንጮች ገልጸዋል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦርድ ሊቀመንበር የሆኑት የአየር ኃይሉ አዛዥ ጀነራል ይልማ መርዳሳ ናቸው ያዘዙን በሚል የአየር መንገዱ የግሩፕ ሴክዩሪቲ ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ሄርጳ አዱኛ እና የአየር መንገዱ የሴኩሪቲ ኢንቨስቲጌሽን ማኔጀር አቶ ግርማ በኬ በብሔራቸው አማራ የሆኑ ስድስት የአየር መንገዱን የሥራ ሃላፊዎች ለፋኖ በባህርዳር በረራ የጦር መሳሪያ ልካችኋል በሚል ሃሰተኛ እና ;አስቂኝ; በተባለ ክስ አስረዋቸው አዋሽ አርባ እና አዋሽ 7 በእስር እንደሚማቅቁ የደህንነት ምንጮቹ ለዘ-ሐበሻ ገልጸዋል።የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው ሹፌር የሆነው ደምስ፣ አለበል ሁነኛው፣ የኔሰው አረጋ፣ አቤል አላምረው፣ አበራ ተገኔ፣ ስንታየሁ ደምሴ እና ሌሎችም ከታሰሩት መካከል ሲሆኑ ወ/ሮ ፋሲካ የተባለችው የደረሰች ነፍሰ ጡርም እንዲሁ በፋኖ ሰበብ ወደ ባህርዳር በኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራ ጦር መሳሪያ አዘዋውረዋል በሚል የመንግስትን የኤርፖርት ሴኪውሬቲ በሚያዋርድ መልኩ ሃሰተኛ ክስ ተመርቶባቸው መታሰራቸን የደህንነት ምንጮች ገልጸው፤ ወ/ሮ ፋሲካ ትፈታ አትፈታ ባያረጋግጡም ሌሎቹ ግን አሁንም በአዋሽ አርባ እየማቀቁ እየተሰቃዩ ይገኛሉ ብለዋል።እነዚህ በኢትዮጵያ አየር መንገድ የተለያዩ የሥራ ኃላፊዎች የቦርዱ ሊቀመንበር ጀነራል ይልማ መርዳሳ አዘውን ነው በሚል በሄርጳ አዱኛ እና በአቶ ግርማ በኬ ፋኖ ናቸው በሚል እንዲታሰሩ የተደረገው ቦታቸውን ለሌላ ለመስጠት እንጂ በድርጊቱ ተሳትፎ ኖሯቸው አይደለም የሚሉት የደህንነት ምንጮች፤ በአሁኑ ወቅት የአየር መንገዱ ሠራተኞች በሰራተኞች ላይ እየደረሰ ባለው እንዲህ ያለው ሃሰተኛ ክስ መማረር ውስጥ ወድቋል ብለዋል። በተለይም እነዚህን የታሰሩ ሰዎች የሥራ ባልደረቦቻቸው ለመጠይቅ በሄዱበት ወቅት ስማቸው ተመዝግቦ ማስፈራሪያ ጭምር እንደደረሰባቸው የሚገልጹ ሠራተኞች የአየር መንገዱን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሹፌር ያሰሩትም አቶ መስፍንን በጫና ሥራውን እንዲለቅ እነ ጀነራል ይልማ መርዳሳ ካላቸው ፍላጎት ነው ሲሉ ተናግረዋል። ጀነራል ይልማ መርዳሳ አዞናል የሚሉት ሄርጳ አዱኛ እና ግርማ በኬ በአየር መንገዱ ሃሰተኛ ክስ በመፍጠር ሰራተኞችን እያጎሳቆሉ ነው የሚሉት የደህንነት ምንጮች በተለይ የአማራ ተወላጅ የሆኑ የአየር መንገዱ ሰራተኞች ተማረው ሥራ እንዲለቁ የማይቆፍሩት ድንጋይ የለ ይላሉ። ይህም የኢትዮጵያ አየር መንገድን ከማዳከም ውጭ ሌላ ተልዕኮ ሊኖረው እንደማይችል ነው እየተገለጸ ያለው። በጉዳዩ ላይ ዘ-ሐበሻ ሄርጳ አዱኛ እና አቶ ግርማ በኬን አግኝቶ ምላሻቸውን ለማካተት ያደረገው ጥረት ስልካቸው ባለመነሳቱ አልቻለም።የታሰሩት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሠራተኞች ካለምንም ፍርድ በአዋሽ 7 እና በአዋሽ 40 በስቃይ ላይ ሲሆኑ አዳንዶቹም ህመም ላይ መሆናቸውን የደህንነት ምንጮቹ አክለዋል።


ሰበር መግለጫ የአማራ ፋኖን ለመከፋፈል የሚሰሩ ቡድኖች | የአማራ ህዝባዊ ግንባር ሚስጥር | የፋኖ አንድነት ምክርቤት መግለጫhttps://youtu.be/9i7yUBpT_70


አሜሪካ ኢትዮጵያ ዉስጥ ለሚኖሩ ዜጎቿ የጥንቃቄ መልእክት አስተላልፋለች ።በመልእክቷ ዜጎቿ ከአዲስአበባ ዉጭ እንዳይንቀሳቀሱ እና በማንኛውም ጉዳይ ዝግጁ ሆነው በኢትዮጵያ ከሚገኘው የአሜሪካን ኢምባሲ ጋር በየጊዜው ግንኙነት እንዲያደርጉ አሳስባለች።በተመሳሳይ እንግሊዝም ለዜጎቿ የጥንቃቄ መልእክት አስተላልፋለች ።ለወቅታዊ ትኩስ እና አዳዲስ መረጃዎችን ለማግኘት አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:-#Youtube:- Ashara Tv - https://www.youtube.com/channel/UC2LZu_N0iOJipVUw3RyR4Ng#facbook:- https:www.facebook.com/asharamed4#ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedi#instagram:- https://instagram.com/asharamediaofficial?utm_source=qr;igshid=MzNlNGNkZWQ4Mg==#ዋትስአፕ :- https://whatsapp.com/channel/0029Va5CGsH2ER6bIAUd2L1T#ቲክቶክ:- @asharamedia1?is_from_webapp=1;sender_device=pc' rel='nofollow'>https://www.tiktok.com/@asharamedia1?is_from_webapp=1;sender_device=pc


የውጊያ ውሎ መረጃዎች#ደብረታቦር;በትናንትናው ዕለት ከደብረታቦር ወደ ወረታ በሚወስደው መንገድ ላይ ከሚገኘው ከዓለምበር ካምፕ ወደ አሪንጎና አካባቢው ሲንቀሳቀስ በነበረ የፋሽስቱ መከላከያ ሠራዊት ላይ በደረሰ የደፈጣ ጥቃት በርካታ የፋሽስቱ ሠራዊት አባላት ተደምሰዋል። በዚህ ብስጭት የፋኖ አባላት ይኖሩበታል በሚል #ቄስጥሩ ተብሎ የሚጠራውን ጫካ ሲደበድብ እንዳመሸ ከአካባቢው ነዋሪዎች የተገኘው መረጃ ያመለክታል።#እብናትከእብናት ወደ ደብረታቦር በሚወስደው መንገድ ላይ በርካታ የሚሊሻና የፖሊስ አባላትን ጭኖ ሲጓዝ በነበረ መኪና ላይ #ርብወንዝ ሊይ በደረሰ የደፈጣ ጥቃት ሞትና ጉዳት መድረሱን ከአካባቢው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። ውጊያው ለ2 ሰዓታት የዘለቀም እንደነበር ተገልጿል።#ደብረወርቅ;ትላንት በጀመረው የደብረወርቁ ውጊያ ፋኖ ከፍተኛ ድል ተቀናጅቷል። በውጊያው 4 ምሽጎችን መስበር የቻለ ሲሆን ውጊያው የእጅ በእጅ የጨበጣ ውጊያ ጭምር እንደነበር ከአካባቢው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። በርካታ ሠራዊቱን ያጣው አገዛዙ ከቢቸና አቅጣጫ ተጨማሪ ኃይል ሲያመላልስ እንደዋለም ለማወቅ ችለናል።በደረሰበት ሽንፈት የተበሳጨው የጠላት ኃይል ከተማ ውስጥ ያገኛቸውን ከመርጦለማሪያም ለፀበል የመጡ 2 አባትና ልጅን ለተልዕኮ ነው የመጣችሁ በሚል ሁለቱንም ገድለዋቸዋል። አንድ አባት ከቤተክርስቲያን ወደ ቤታቸው ሲመለሱ የነበሩ መነኩሴም ገለዋቸዋል። ሌላው በጠላት የተገደለበትን ወንድሙን ሊያነሳ ሲል የነበረን አንድ ወጣትም አብረው ገድለውታል። በተጨማሪ የአዕምሮ በሽተኞች ጭምር ተገድለዋል ተብሏል። አሁንም ከተማዋን ፋኖ ዙሪያዋን ከቦ እንዳለ ከአካባቢው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።ውጊያው ሲካሄድ የነበረው የኦሆዴዱ ቅምጥ የአማራ ክልል አስተዳዳሪ የአቶ አረጋ ከበደ የትውልድ አካባቢ ላይ ነበር።#መሐል_ሳይንት;በትናንትናው ዕለት በመሐል ሳይንት ወረዳ ልዩ ስሙ #ወርቅ_ማውጫ ከተባለው ቦታ ላይ በፋኖ እና በፋሽስቱ ዐቢይ አህመድ ሠራዊት መካከል ውጊያዎች ሲደረጉ እንደነበር ከአካባቢው ነዋሪዎች ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። በጦርነቱ የአገዛዙ ወታደሮች ሙትና ቁስለኛ ሆነዋል። ከፋኖ የከፋ ጉዳት አለመድረሱን ለማወቅ ችለናል። ከሰዓታት በኋላ የጠላት ኃይል አካባቢውን ለቆ ወደ ደንሳ ከተማ ለመሸሽ እንደተገደደና ደንሳ ውስጥ አዲስ እየተሰራ ባለው ሆስፒታል ውስጥ መሽገው ይገኛሉ።#በረኸት;የበረኸት ወረዳ ፋኖዎች መተህብላ ከተማ ላይ ሰፍሮ በነበረ የጠላት ሠራዊት ላይ የተጠናበት ድንገተኛ ጥቃት ከፍተዋል። በውጊያው የአገዛዙ ሠራዊት ላይ ከፍተኛ ሰብዓዊና ቁሳዊ ኪሳራ ያደረሱበት ሲሆን ጥቃቱን መቋቋም አቅቶት ቤተክርስቲያን ውስጥ ገብቶ ለመጠለል እየሞከረ እንደሆነ ከአካባቢው ነዋሪዎች ያገኘነው መረጃ ያመለክታል። አገዛዙ አንድ የድሮን ጥቃት ያደረሰ ሲሆን ተጨማሪ የድሮን ጥቃት ለማድረስ የድሮን ቅኝት እያደረገ ይገኛል። ውጊያው እስከዚህ ሰዓት ድረስ እንደቀጠለ ነው።#ቡሬ;ትንሽ ቀደም ብሎ ከቡሬ ወደ ነቀምት በሚወስደው መንገድ ላይ 27 ኪ.ሜ ርቀት ላይ በምትገኘዉ #ቁጭ ከተማ የጠላት ኃይል ወደ ንጹሀን መድፍ እያዘነበ ነው። ቁጭ ከተማ ጤና ጣቢያው አካባቢ በተደጋጋሚ የከባድ መሳሪያ ቅንቡላ አርፏል። #ሸበል_በረንታ;ይሄ ወራዳ ፋሽስት መንግሥት ሸበል በረንታ ላይ የጁ ባይሌ ቀበሌ የፋኖ አባላት ናቸው ያላቸውን አቶ አዱኛው መንግሥት እና አቶ ይበልጣል በየነ የሚባሉ ፋኖዎችን ሚስቶቻቸውን ወስዷቸዋል።እነኚህ ፋኖዎች እጃቸውን በቶሎ ካልሰጡ በሚስቶቻቸው ላይ እርምጃ እንደሚወስድባቸው ዝቷል።ለወቅታዊ ትኩስ እና አዳዲስ መረጃዎችን ለማግኘት አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:-#Youtube:- Ashara Tv - https://www.youtube.com/channel/UC2LZu_N0iOJipVUw3RyR4Ng#facbook:- https:www.facebook.com/asharamed4#ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedi#instagram:- https://instagram.com/asharamediaofficial?utm_source=qr;igshid=MzNlNGNkZWQ4Mg==#ዋትስአፕ :- https://whatsapp.com/channel/0029Va5CGsH2ER6bIAUd2L1T#ቲክቶክ:- @asharamedia1?is_from_webapp=1;sender_device=pc' rel='nofollow'>https://www.tiktok.com/@asharamedia1?is_from_webapp=1;sender_device=pc


ቡሬ ፣ መርሳን፥መሀል አንባና ሲሪንቃ | የፋኖዎቹ ክሳቸው ተቋረጠ |የጋዜጠኞች መኮብለልhttps://youtu.be/260hZTVT8V0


አሸባሪው አገዛዝ አርበኛ ሰፈር መለሰ፣ ዋርካው ምሬ ወዳጆ እና ሙሉጌታ አንበርብርነ ዛሬ በዋለው ችሎት ክሳቸውን አቋርጫለሁ ማለቱ ተሰምቷል።አርበኛ ሰፈር መለሰንና ሻለቃ ዋርካው ምሬ ወዳጆን ገዳይ ቡድን አሰማርቶ ለመግደል እየሰራ ባለበት ሁኔታ ክስ አቋርጫለሁ ማለቱ ከጀርባ ከባድ ሴራ እየተሴረ መሆኑ የማያጠራጥር ሀቅ ነው።ይሄ አሸባሪ አገዛዝ መያዝ ሲያቅተው በፋኖዎች ውስጥ መከፋፈል ይፈጥርኛል በሚል ይህን ሁነት ፈጥሯል፤ ክስ በማቋረጥና እስረኛ በመልቀቅ የሚለወጥ ሕዝባዊ ትግል አልጀመርነም።አሸባሪው አገዛዝ ይህን ውሳኔ የወሰነው፤ የፋኖ ከባድ በትር ባለመቋቋሙና የፋኖ ግስጋሴ ስለአስደነገጠው መሆኑ ልብ ማለት ያስፈልጋል።ይህ የሆነው ጥቅምት 15 ቀን በፋኖ ቀን መሆኑ በፋኖ የበለጠ እንድኮራ አድርጎኛል። ጥቅምት 15 ቀንን የፋኖ ቀን ሁኖ ለዘለዓለም እንዲዘከር እሰራለሁ።ፋኖ ድል አድራጊው በአሸባሪው አገዛዝ ያጓራቸውን ንጹሃን የአማራ ልጆችን ማጓሪያውን ሰብሮ ነጻ ያወጣል።ፋኖ ተወርዋሪው፤ ፋኖ ድል አድራጊው;;መልካም የፋኖ ቀን;;;ለወቅታዊ ትኩስ እና አዳዲስ መረጃዎችን ለማግኘት አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:-#Youtube:- Ashara Tv - https://www.youtube.com/channel/UC2LZu_N0iOJipVUw3RyR4Ng#facbook:- https:www.facebook.com/asharamed4#ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedi#instagram:- https://instagram.com/asharamediaofficial?utm_source=qr;igshid=MzNlNGNkZWQ4Mg==#ዋትስአፕ :- https://whatsapp.com/channel/0029Va5CGsH2ER6bIAUd2L1T#ቲክቶክ:- @asharamedia1?is_from_webapp=1;sender_device=pc' rel='nofollow'>https://www.tiktok.com/@asharamedia1?is_from_webapp=1;sender_device=pc

Показано 8 последних публикаций.