ATC NEWS


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Образование


#ADDIS_ABABA : ETHIOPIA
ለመልዕክት 👇🏻
@mujaabot
For Advertisement👇🏿
@atcads

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Образование
Статистика
Фильтр публикаций


የብቃት ምዘና ፈተና ለምትወስዱ ጤና ባለሙያዎች በሙሉ


ጤና ሚኒስቴር ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በ Medicine, Nursing, Public Health, Anesthesia, Pharmacy, Medical Laboratory Science, Midwifery, Dental Medicine, Medical Radiology Technology, Environmental Health, Psychiatric Nursing, Pediatric & Child Health Nursing, Emergency & Critical Care Nursing, Surgical Nursing, Physiotherapy, Optometry እና Human Nutrition ሙያዎች በመጀመሪያ ዲግሪ ተመርቃችሁ የመውጫ ፈተን ያለፋችሁ እንዲሁም በጤና ሚኒስቴር በኩል ተመዝግባችሁ የብቃት ምዘና ፈተናውን ለመውሰድ በመጠባበቅ ላይ ለምትገኙ የጤና ባለሙያዎች በመጋቢት 2017 ዓ.ም ፈተናውን ለመስጠት በዝግጅት ላይ ይገኛል፡፡

ስለሆነም የዚሁ ፈተና ምዝገባ ከየካቲት 24 - መጋቢት 7/2017 ዓ.ም የሚከናወን ስለሆነ ፈተናውን የምትወስዱ የመንግስትም ሆነ የግል ተቋማት ተመዛኞች በኦንላይን http://hple.moh.gov.et/hple ላይ በመግባት እንድትመዘገቡ እያሳሰብን ከላይ ከተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ውጪ ምንም ዓይነት የምዝገባ ጥያቄ የማናስተናግድ መሆኑን አውቃችሁ በተጠቀሱት ቀናት እንድትመዘገቡና ሲስተሙ የሚሰጣችሁን የፈተና መለያ ቁጥር (Registration No) የያዘ ስሊፕ print አድርጋችሁ በመያዝ ስትመዘገቡ በመረጣችሁት የፈተና ጣቢያ በፈተናው ወቅት እንድትገኙ እያሳሰብን ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0115186275/0115186276 መደወል የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

ማሳሰቢያ፦
- እያንዳንዱ የፈተና ጣቢያ በየሙያ መስኩ ማስተናገድ በሚችለው ከፍተኛ የተመዛኝ ቁጥር ልክ ገደብ ስለተቀመጠለት ተመዛኞች ምዝገባውን ቀድማችሁ በማጠናቀቅ ተጠቃሚ መሆን የምትችሉ መሆኑን እያሳወቅን ከፍተኛው የተመዛኝ ቁጥር በደረሰበት የፈተና ጣቢያ ላይ ተጨማሪ ምዝገባ ማከናወን የማይቻል መሆኑን እናሳስባለን።

- ማንኛውም ተመዛኝ ወደ ፈተና ጣቢያ ሲመጣ ሲስተሙ የሚሰጠውን የፈተና መለያ ቁጥር (Registration No) የያዘ ወረቀት /ስሊፕ/ print አድርጎ ካልያዘ ፈተናውን መውሰድ የማይችል መሆኑን በጥብቅ እናሳስባለን፡፡

- በጥር 30/2017 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር የተሰጠውን የመውጫ ፈተና ተፈትናቹ ያለፍችሁና በዚህ የብቃት ምዘና ፈተና ለመቀመጥ የተዘጋጃችሁ ነገር ግን ቴምፖረሪ ዲግሪ ከተቋማችሁ ያልደረሰላችሁ ተመዛኞች ከትምርት ሚኒስቴር ይህ ጉዳይ ቀጥታ ከሚመለከተው የስራ ክፍል የትብብር ደብዳቤ ማያያዝ የሚጠበቅባችሁ መሆኑን እንሳውቃለን።

#MoH
ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://t.me/atc_news


በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ቤተ-ሙከራዎች ውስጥ የሚገኙት መጠቀሚያ ጊዜያቸው ያለፈባቸው ኬሚካሎች ቆጠራ በመካሄድ ላይ መሆኑ ተገለጸ።


በትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ የምርምርና ማህበረሰብ ጉድኝት መሪ ሥራ አስፈጽሚ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ቤተ-ሙከራዎች ውስጥ የሚገኙት መጠቀሚያ ጊዜያቸው ያለፈባቸው ኬሚካሎች ቆጠራ በመካሄድ ላይ መሆኑ ገልጿል፡፡

የምርምርና ማህበረሰብ ጉድኝት ጉዳዮች ተጠባባቂ መሪ ስራ አስፈጻሚ ሰራዊት ሃንዲሶ(ዶ/ር) በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት ሥራ ክፍሉ በ2017 ዓ.ም በአቅድ ከያዛቸው የሪፎርም ስራዎች መካከል አንዱ የምርምር ግብዓቶችንና ፋሲሊቲዎችን በማሻሻል የቤተ-ሙከራ ስታንዳርዳይዜሽንን እና አክሬዲቴሽን ስርዓትን መዘርጋት መሆኑን ገልጸዋል፡፡

አክለውም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ የሚገኙ የኢንዱስትሪ፤ የምርምር እና የላብራቶሪ ኬሚካሎች አያያዝ፤ ክምችትና የማጓጓዝ ሂደትና የመጠቀሚያ ጊዜ ያለፈባቸውን ኬሚካሎች የቆጠራ ሥራ ለመሥራት እንዲቻል ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አካዳሚክ ቴክኒካል ረዳት ባለሙያዎች ስልጠና መሰጠቱን ተናግረዋል፡፡

በተጨማሪም ይህ ሥራ የሚሰራው በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ብቻ ሳይሆን በአቅራቢያቸው በሚገኙ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ስር ባሉ ቤተ-ሙከራዎች ውስጥ የሚገኙትን ኬሚካሎች ምንጭ፣ አይነት፣ ደረጃ፣ መጠን እና ባህሪይ የማወቅ መረጃ የማሰባሰብ ሥራ እንደሚሰራም ሃላፊው ጨምረው ገልጸዋል፡፡


ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://t.me/atc_news


በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የሚገኘውና በአጭር ጊዜ 53 ቀናት ውስጥ የተገነባው ቅሊንጦ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በዛሬው ዕለት የመማር ማስተማር ስራ ጀምሯል፡፡

ትምህርት ቤቱ በአዲስ መልክ ከመገንባቱ በፊት 1555 የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ተማሪዎች በቅሊንጦ ቁጥር 2 አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ በፈረቃ ሲማሩ የቆዩ ሲሆን የዚህ G+4 የመማሪያ ክፍል ግንባታ ተማሪዎች ሙሉ በሙሉ ከፈረቃ ትምህርት እንዲወጡና ለብቻው በተከለለው ቅሊንጦ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ትምህርታቸዉን እንዲከታተሉ ያስቻለ ነው፡፡


ከዚህም በተጨማሪ በቅሊንጦ ቁጥር 2 አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ የተገነባው G+4 የመማሪያ ክፍል ማስፋፊያ ግንባታም የተጠናቀቀ ሲሆን በዛሬው ዕለት ለመማር ማስተማር ስራዉ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል፡፡


ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://t.me/atc_news


እንኳን ለመላው ጥቁር ሕዝቦች ኩራት ለሆነው 129ኛው #የአድዋ ድል በዓል በሰላም አደረሰዎ አደረሰን።


ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://t.me/atc_news


#MoE

በሰኔ 2017 ዓ.ም የሚሰጠውን የመውጫ ፈተና የሚወስዱ ዕጩ ተመራቂዎች የፋይዳ መታወቂያ ሊያወጡ ይገባል። - ትምህርት ሚኒስቴር

የካቲት 21/2017 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ተፈርሞ ለሁሉም የመንግሥት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተላከ ሰርኩላር፤ ብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ (ፋይዳ) የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተማሪ እና የሠራተኞችን መረጃ በተደራጀ መልኩ ለመያዝ ጠቀሜታ እንዳለው ይገልጻል።

የሀገር አቀፍ ፈተናዎችን ደህንነት ለማስጠበቅ አስፈላጊ መሆኑንም ያትታል።

በዚህም በሰኔ 2017 ዓ.ም የሚሰጠውን የመውጫ ፈተና የሚወስዱ ዕጩ ተመራቂዎች ፈተናውን ለመውሰድ የፋይዳ መታወቂያ ሊያወጡ እንደሚገባ አሳስቧል።

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://t.me/atc_news


ከማይነማር የሳይበር ማጭበርበሪያ ካምፖች የወጡ 800 ኢትዮጵያዊያን እዚያው በኹለት የአገሪቱ አማጺ ቡድኖች እጅ ውስጥ እንደሚገኙ ከኢትዮጵያዊያኑ ፍልሰተኞች መስማቱን ቢቢሲ አማርኛ ዘግቧል።

ኢትዮጵያዊያኑ በግዳጅ ከሚሠሩባቸው ካምፖች በቡድን ኾነው የወጡት ራሳቸውን ነጻ ለማውጣት እንደኾነና ከካምፖች አምጸው እንደወጡ አማጺ ቡድኖች እንደተረከቧቸው መናገራቸውን ዘገባው ጠቅሷል።

ኾኖም ኢትዮጵያዊያኑ እስካኹን መንግሥት ለምን ወደ አገራቸው ሊመልሳቸው እንዳልቸለ ሊገባቸው እንዳልቻለ ገልጸዋል ተብሏል። የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነቢያት ጌታቸው፣ መንግሥት ከካምፖች ነጻ የወጡ ኢትዮጵያዊያን ፍልሰተኞችን ለመመለስ ዝግጅት እያደረገ መኾኑን ትናንት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ተናግረው ነበር።



ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://t.me/atc_news


ጂንካ ዩኒቨርሲቲ የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና (Entrance Exam) ለሚወስዱ ተማሪዎች የማጠናከሪያ ትምህርት (Tutorial) ለመስጠት ዛሬ የካቲት 22/2017ዓ.ም የማስጀመሪያ መርሃግብር አካሄደ።

****

በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚታየውን የትምህርት ጥራት ለማሻሻል የሁሉም ባለድርሻ አካላት አስተዋፅኦ የሚፈልግ በመሆኑ ጂንካ ዩኒቨርሲቲም የራሱን ሀላፊነት ለመወጣት በጂንካ ከተማ ለሚገኙ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች የማጠናከሪያ ትምህርት ይሰጣል ሲሉ የማህበራዊ ሳይንስ ኮሌጅ ዲን መ/ር አብረሃም ዮሀንስ ገልፀዋል።

ዘንድሮ ለሚፈተኑ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎችን ውጤት ለማሻሻል ከትምህርት ቤቶቹ ጋር በመተባበር የማጠናከሪያ ትምህርት መስጠቱ ትልቅ ማነቃቂያ እንደሚፈጥር በመግለፅ የጂንካ ዩኒቨርሲቲ ማኔጅመንትም የተቻለውን ሁሉ አስተዋጽኦ ለማበርከት ቁርጠኛ መሆኑን ተጠቁሟል።


ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://t.me/atc_news


የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በሕክምና ሳይንስ ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች አስመረቀ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 22፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ በሕክምና ሳይንስ ዘርፍ ያሰለጠናቸውን 197 ተማሪዎች አስመርቋል፡፡

ከተመራቂዎች መካከል 153 በሜዲካል ዶክትሬት፣ 21 በጥርስ ሕክምና እና 23 ተማሪዎች ደግሞ በአኔስቴዥያ ዲግሪ ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩ ናቸው፡፡

በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ፣ የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) እና የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዚዳንት ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር) ተገኝተዋል፡፡

ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ተመራቂዎች ሕሙማንን ማከም ብቻ ሳይሆን የዓለምን ነባራዊ ሁኔታ በመረዳት በሕብረተሰቡ ጤና ላይ የበለጠ ምርምር ማድረግ ይጠበቅባቸዋል።

የተሻሉ ሐኪሞች ለአዳዲስ ሃሳቦች እንደሚተጉ አንስተው÷ተመራቂዎች ለታካሚዎች ሰብዓዊ ርህራሄ በመስጠት ሙያዊ ሥነ-ምግባር አክብረው እንዲሰሩም ጠይቀዋል።

ዶ/ር መቅደስ ዳባ በበኩላቸው÷የጤና ባለሙያዎች ቀጣይነት ላለው የጤና ሥርዓት ወሳኝ እንደሆኑ መናገራቸውን የዩኒቨርሲቲው መረጃ ያመላክታል፡፡


ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://t.me/atc_news


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የምረቃ ስነ-ስርዓት:
አሁን ከቢዝነስ እና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ አዳራሽ

የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የህክምና ትምህርት ቤት በቅድመ ምረቃ ያሰለጠናቸውን 179 ተማሪዎች እያስመረቀ ይገኛል።

ከተመራቂዎች መካከል 153 ተማሪዎች በሜዲካል ዶክትሬት፣ 21 ተማሪዎች በጥርስ ህክምና እና 23 ተማሪዎች ደግሞ በአኔስቴዥያ ድግሪ ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩ ናቸው።

102 ተማሪዎች ወንዶች እና 95ቱ ደግሞ ሴት ተመራቂዎች ሲሆኑ ከአጠቃላይ ተመራቂዎች መካከል 165 ያህል ተማራቂዎች የላቀ ውጤት ያስመዘገቡ ናቸው።

#AAUGraduation2025
#SchoolOfMedicine

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://t.me/atc_news


አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለደረጃ አንድ የቻይንኛ ቋንቋ ሰርተፊኬት ፕሮግራም ምዝገባ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡

150 ተመዝጋቢዎች በፕሮግራሙ ይሳተፋሉ ተብሏል፡፡

ለደረጃ ሁለት የቻይንኛ ቋንቋ ሰርተፊኬት ፕሮግራም ምዝገባ ያደረጉ አመልካቾች ትምህርት ነገ የካቲት 22/2017 ዓ.ም ይጀመራል፡፡

የምዝገባ ቦታ፦
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ኮንፊሽየስ ኢንስቲትዩት ቢሮ፥ 6 ኪሎ ዋና ግቢ፣ ፎረም ህንጻ፣ 8ኛ ፍሉር ጠዋት ከ3፡00-5፡00 ሰዓት

የስልጠናው ቦታ፦
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ 6 ኪሎ ካምፓስ

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://t.me/atc_news


#Update

የጤና ተመራቂዎች የሙያ ብቃት ምዘና (COC) አመልካቾች ምዝገባ ከነገ የካቲት 22/2017 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት ቀናት ክፍት እንደሚሆን ይጠበቃል።

የሙያ ብቃት ምዘና ለመውሰድ እየጠበቁ የሚገኙ የጤና ተመራቂዎች ምዝገባ በየካቲት መጀመሪያ ለማከናወን ዕቅድ ተይዞ የነበረ ቢሆንም በተለያዩ ምክንያቶች መዘግየት አጋጥሟል።

አሁን ላይ አጋጥመው የነበሩ ችግሮች መፍትሔ በማግኘታቸው ከነገ ቅዳሜ የካቲት 22/2017 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት ጥቂት ቀናት የአመልካቾች ምዝገባ (በድጋሜ ተፈታኞችን ጨምሮ) እንደሚደረግ ከጤና ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://t.me/atc_news


በሶስቱም ቅርንጫፎቻችን ( መገናኛ፣ ሜክሲኮና ጀሞ) እንዲሁም በኦንላይን በምንሰጣቸዉ  ስልጠናዎች በ Advanced level እና 90% practical በሆነ ካሪኩለም እንዲሁም ዘመኑ ያፈራቸዉን ሙሉ የላብራቶሪና የስቱዲዮ እቃዎችን በማሟላት ከሁሉም ስልጠናዎቻችን ላይ ታላቅ የዋጋ ቅናሽ አድርገናል! አሁኑኑ ይመዝገቡና ትልቅ ለዉጥ ወደሚያመጡበት ተቋም ይቀላቀሉ!

ከትምህርትና ስልጠና ጥራትና ቁጥጥር ባለስልጣን ሙሉ ዕዉቅና ካለዉ ሰርተፊኬት ጋር!

እኛጋ ለመሰልጠን ኮምፕዩተር መግዛት አያስፈልግዎትም!

የብዙ አመት ልምድ እና ብቃት ባላቸዉ አሰልጣኞች!

🎯 Graphics Design
🎯 Video Editing
🎯 Digital Marketing
🎯 Photography
🎯 Videography
🎯 Cinematography
🎯 Adobe photoshop
🎯 Fullstack Web app development 
🎯 Programming Language
🎯 Interior Design
🎯 English Language
🎯 Database
🎯 Basic Computer
🎯 Accounting Softwares
🎯 Engineering Softwares
🎯 SPSS & STATA
🎯 MS-Project
🎯  Foreign & Local Languages

አድራሻ:-
1. መገናኛ መተባበር ህንፃ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 419 (ሊፍት ይጠቀሙ)  ☎️ 0991929303

2. ሜክሲኮ ኬኬር ህንፃ 6ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 639 (ሊፍት ይጠቀሙ ሁለተኛዉን ሊፍት) ☎️ 0991929304

 3. ጀሞ 1 አንደኛ በር ካኩ ቢዝነስ ሴንተር 3ኛ ፎቅ ☎️ 0991926707

Join telegram https://t.me/topinstitutes

tiktok https://Tiktok.com/@topinstitute

Facebook https://www.facebook.com/Topinstitutes


ረመዷን ነገ ይጀምራል።

በሳውዲ አረቢያ የረመዳን ወር መግቢያ ጨረቃ በመታየቷ የረመዳን ወር ጾም ነገ ቅዳሜ ይጀምራል።


➡️ https://t.me/atc_news


" በነገው ዕለት አንድ ቡድን ወደ ስፍራው ያቀናል " - አምባሳደር ነብያት ጌታቸው

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ነብያት ጌታቸው ዛሬ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በሰጡት መግለጫ ፤ በማይናማር ታግተው የነበሩ 246 ዜጎችን በቀጣይ ሳምንት ወደ ሀገር ቤት ለመመለስ እየተሰራ መሆኑን ነው አሳውቀዋል።

" በማይናማር በከፍተኛ ችግር ውስጥ ያሉ ዜጎችን ለማስወጣት በቶኪዮ እና በኒውዴሊ ባሉ ኤምባሲዎች በኩል ሥራዎች እየተሠሩ ነው " ሲሉ ተናግረዋል።

" አሁን ላይ 246 ኢትዮጵያዊያን ከማይናማር ወጥተው ወደ ታይላንድ ደርሰዋል " ሲሉ ጠቅሰዋል።

" እነሱን ለመርዳትና የማጣራት ሥራ ለመሥራት በነገው ዕለት አንድ ቡድን ወደ ስፍራው ያቀናል " ብለዋል።

በተመሳሳይ በመካከለኛው ምስራቅ በችግር ውስጥ ያሉ ዜጎችን ለማስወጣት የሚደረገው ጥረት ቀጣይነት እንዳለውም ጠቁመዋል። #ኤፍኤምሲ

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://t.me/atc_news

Показано 14 последних публикаций.