Ayu Zehabesha-Official አዩዘሀበሻ


Гео и язык канала: Эфиопия, Английский
Категория: Новости и СМИ


ቻናላችንን Join በማድረግ በቀላሉ ፈጣን መረጃዎችን ይከታተሉ።
Inbox👉 https://t.me/ayulaw

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Английский
Категория
Новости и СМИ
Статистика
Фильтр публикаций


#MoE
የ2017 ዓ.ም የዩኒቨርሲቲ ምደባ ይፋ ሆነ‼️

በ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስደው በመደበኛው ፕሮግራም ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግሥት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ትምህርታቸውን ለመከታተል የሚያስችል የማለፊያ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች የተቋም ምደባ ይፋ ሆኗል።

ተማሪዎች ከታች በተዘረዘሩት አማራጮች ምደባቸውን ማየት እንደሚችሉ ትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል።

በድረ-ገፅ 👇
https://placement.ethernet.edu.et
በቴሌግራም 👇
https://t.me/moestudentbot

የተቋም ይቀየርልኝ ጥያቄ የማያስተናግድ መሆኑን ሚኒስቴሩ አሳውቋል።
👇👇👇
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s


ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የመምህራን ደመወዝ በመቋረጡ የትምህርት ሥራ መታጎሉ ተገለጸ‼️
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የተለያዩ ዞኖች የመምህራን ደመወዝ በመቋረጡ የተነሳ እስከ አኹን በአንዳንድ ትምሕር ቤቶች ትምሕርት አለመጀመሩን ወላጆች ገለጹ።

ከግል እና አንዳንድ የመንግሥት ትምሕርት ቤቶች ውጪ አብዛኞቹ እንዳልተከፈቱ፣ ቢከፈቱም ከሁለት በላይ መመሕራን ስለማይገቡ ትምሕርት አለመጀመሩን የተናገሩ ወላጆች፣ ስጋታቸውን አጋርተዋል።

የክልሉ መምሕራን ማኅበር በወላይታ ዞን፣ በጋሞ ዞን፣ በኮንሶ ዞን እና በጎፋ ዞኖች የሚገኙ 28 ወረዳዎች የሚገኙ በሺሕዎች የሚቆጠሩ መምህራን ደመወዝ በወቅቱ እንደማይከፈል አስታውቋል።
#ቪኦኤ
👇👇👇
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s


‼️ደብረ ብረሀን እና አዲስ አበባ ላላችሁ ብቻ‼️

🌟 ከሁለት ድንቅ ሰዓቶች በተጨማሪ ኤርፖድ በዉስጡ የያዘዉን ድንቅ  ሰዓት
በ 2199 ብር ብቻ ለእርሶ ይፈጠኑ😱😱

❇️ደብረ ብረሀን ምዝገባዉ ሊጠናቀቅ ስለሆነ ፈጥነዉ ደዉለዉ ይመዝገቡ❇️
  
አሁኑኑ ይደዉሉ👉 0967500121

  💥 አዲስ አበባ ላይ የምንሰጠዉ ነፃና ፈጣን የዴሊቨሪ አገልግሎት እንደተጠበቀ ነዉ ይደዉሉ💥

🌍 ስትቀበሉ ሙሉ የዕቃዉን አጠቃቀም ገለፃ የምንሰጣችሁ ይሆናል🌍


🎤🎤በጥቂት ጊዜያት ዉስጥ ከፍተኛ ተቀባይነት ያገኘዉ ተች ሴንሰር የተገጠመለት ተቆጥረዉ የማያልቁ አገልግሎቶችን ከስልክ ጋር ተገናኝቶ መስጠት የሚችለዉ W26 pro max ለእናንተ🙏

W26 PRO MAX Special with
Earbuds

✅ለወንድም ለሴትም የሚሆን ዘረፈ ብዙ ጥቅምች ያሉት smartwach ከ pro wireless earpode ጋር🔥

  ❄️የራሱ ቻርጀር እና power bank ያለዉ
📌 የልብ ምትዋን  ይለካል
📌 ስፖርት ስንሰራ ምን ያህል ካሎሪ እንዳቃጠልን ያሳውቃል
📌 ብዙ ሰአት ስንተኛ ይቀሰቅሰናል
📌 ስልካችን ሲጠፋ ለመፈለጊያ ያግዘናል
📌 ቴክስት መላክ እንዲሁም መቀበል የሚያስችል
📌 ከስልክ ጋ በ Bluetooth ተገናኝቶ ስልክ መደወል እንዲሁም ማናገር ያቻላል
📌  wireless charger እና በሁለት አይነት የእጅ መሳርያ የቀርበ
📌  Blood Oxygen Detection
📌 Stress & Mood Testing

🚒 አዲስ አበባ ዉስጥ ነፃ እና ፈጣን  የዴሊቨሪ አገልግሎት እንሰጣለን።

ዋጋ  2199 ብር ብቻ
       ፈጥነዉ ይደዉሉ

📞  0967500121

ተጨማሪ እቃዎችን ለማየት
👉@Dubai_tera1 ን ይቀላቀሉ።


በ #አማራ ክልል በሶስት ወራት ውስጥ 37 ሰዎች በወባ በሽታ ምክንያት መሞታቸው ተገለጸ‼️
በአማራ ክልል በሶስት ወራት ውስጥ ብቻ 37 ሰዎች በወባ በሽታ ምክንያት መሞታቸውን የኢትዮጵያ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ገለጸ።

በክልሉ ባለው የጸጥታ ችግር የተነሳ አስፈላጊ የቁጥጥር እና የክትትል ስራዎች ባለመከናወናቸው ባለፉት ሶስት ወራት ብቻ ከ600ሺህ በላይ ሰዎች በወባ በሽታ ሲጠቁ 37 የሚሆኑት ደግሞ ለህልፈት መዳረጋቸውን በኢንስቲትዩቱ የወባ መከላከልና መቆጣጠር ፕሮግራም አስተባባሪ የሆኑትን አቶ ዳምጤ ላንከርን ጠቅሶ የአሜሪካ ድምጽ  ዘግቧል።

“የተከሰተው ወረርሽኝ ከዚህ በፊት ታይቶ አይታወቅም” ያሉት አቶ ዳምጤ አክለውም በክልሉ አሁን ላይ በሳምንት ከ64 ሺህ በላይ ሰዎች በወባ በሽታ መያዛቸውን የሚገልጹ ሪፖርቶች እንደሚደርሳቸው ተናግረዋል።

በክልሉ ወረርሽኝ ተስፋፍቶባቸዋል ከተባሉ አከባቢዎች መካከል የ #አዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን በቀዳሚነት የሚጠቀስ ሲሆን #ደቡብ_ጎንደር እና #ማዕከላዊ_ጎንደርን ጨምሮ በ40 ወረዳዎች ወረርሽኙ ተስፋፋቶ እንደሚገኝ ተጠቁሟል።
👇👇👇
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s


CROWN DOOR        ክራዉን በር

ከእንጨት ፋይበር የተሠራ በር

ዘላቂነት፡- ክራዉን ኢንጂነሪድ የእንጨት ላምኔትድ በሮች ከባህላዊ የእንጨት በሮች የበለጠ ረጅም ጊዜ እንዲቆዩ በማድረግ ከከፍተኛ እርጥበት እስከ ከፍተኛ የሙቀት ለውጥ ድረስ እንዲቋቋም ተደርገው የተነደፉ ናቸው።

የ25% ቅናሽ ዋጋ በካሬ 9850 ብር ኢንክ ቫት ጀምሮ  ለተወሰነ ጊዜ ብቻ

ባለ 800mm በር ከ16,540 ብር ኢንክ ቫት

ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥራችን ፡-

0993050914/ 0993053021

https://t.me/crowndoor

@crowndoor1

Email: crowndoor101@gmail.com

የማሳያ ሾዉ ሩም አድራሻ፡-

ብስራት ገብርኤል ቦራን ኮምፕሌክስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ አዲስ አበባ


እሳቱን ለማጥፋት በ4 ሚሊዮን ብር የተደራደሩት የእሳት አደጋ ሰራተኞች‼️
ከትናንት በስተያ በአዲስ አበባ ከተማ መርካቶ ሸማ ተራ የገበያ ማዕከል እሳት አደጋ መከሰቱን ተከትሎ የእሳት አደጋ ሰራተኞች በወቅቱ ቢደርሱም "ከማን ጋር ነው የምንደራደረው"ብለው እሳቱን ለማጥፋት በመዘግየታቸው ውድመቱን እንዳባባሰው የአካባቢው ነዋሪዎች በቂ መረጃ እንዳላቸው ተናግረዋል።
👉የአካባቢው አይን እማኞች ማንኛውም ሰው ቢመጣ መረጃ ለመስጠት ዝግጁ ነን ብለዋል።
መጀመሪያ እሳቱ ሸማ ተራ የገበያ ማዕከል የተከሰተ ሲሆን የእሳት አደጋ ሰራተኞቹ በወቅቱ ደርሰው የነበረ ሲሆን እሳቱ ሳይዛመት በቀላሉ ማጥፋት ይችሉ ነበር ብለዋል። በወቅቱ የደረሱት የእሳት አደጋ ሰራተኞች ግን " በገንዘብ ከማን ጋር ነው የምንደራደረው በማለታቸው"እሳቱን ወደ ማጥፋት ቶሎ እንዳልልገቡ ጠቁመዋል። እሳቱ ህንፃው ላይ ሲደርስ የተወሰኑ የሱቅ ባለቤቶች ሱቃቸው ውስጥ ብዙ ብር ስለነበራቸው የእሳት አደጋ ሰራተኞቹ ከባለሱቆቹ ጋር ተደራድረው እስከ 4 ሚሊዮን ብር  ከፍለው እሳቱን ወደማጥፋት እንደገቡ ታዝበናል ብለዋል።
ይህ ሂደት የተለመደ ቢሆንም የእሳት አደጋ ሰራተኞቹ ከተደራዳሪዎች ቶሎ ገንዘብ ባለመከፈሉ እሳቱ ይሄን ያህል ውድመት በማስከተሉ አዝነናል ብለዋል።
የእሳት አደጋ ሰራተኞቹ ሸማ ተራ ገበያ ማዕከሉ ላይ የተነሳውን እሳት በወቅቱ ማጥፋት ያልቻሉት ገንዘብ የሚከፍል ጠፍቶ ነው ብለዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ ከሌላ ቦታ የመጡ ሰዎች በርካታ ንብረቶችን ዘርፈው ጭነው ወስደዋል ብለዋል።
✍️አዩዘሀበሻ
👇👇👇
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s


ሽቶዎች(Perfumes) በተመጣጣኝ ዋጋ❗❤             
Chanel , Boss ,Tom ford ,Versace ,giorgio armani


✅ውጪ ሀገር ሆናችሁ ኢትዮጵያ ላሉ ወዳጅ ዘመድዎ ስጦታ መስጠት ከፈለጉ እናደርስሎታለን❗

በነፃ እናደርሳለን(Free Delivery )🏍

Adress :: ቦሌ መድሃኒዓለም
ስልክ☎📞👉  0942163022

Telegram channel Join👇 
http://t.me/perfumesellers
http://t.me/perfumesellers


የኢትዮጵያ ሠራዊት ስምሪት የአል ሻባብ እንቅስቃሴ እንዲጨምር አድርጓል’ - ሶማሊያ
ባለፉት ጊዜያት በሶማሊያ ውስጥ ለሰላም ማስከበር የተደረገው የኢትዮጵያ ሠራዊት ስምሪት የአል ሻባብ እንቅስቃሴ እንዲጨምር አድርጓል ሲል የሶማሊያ መንግሥት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ ወቀሰ።
የኢትዮጵያ ወታደሮች ከግዛቷ እንዲወጡ ስትጠይቅ የቆየችው ሶማሊያ ከጥቂት ወራት በኋላ የሚያበቃውን የሰላም አስከባሪ ተልዕኮን ተከትሎ በምትኩ በሚሰማራው ኃይል ውስጥ የየትኛው አገር ወታደሮች እንደሚሳተፉ የምትመርጠው ራሷ መሆኗን ገልጻለች።
የሶማሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያወጣው መግለጫ በአገሪቱ ወታደሮቻቸውን ካሰማሩ አምስት አገራት በተለየ የኢትዮጵያ ሠራዊት ላይ በማተኮር ተልዕኮው የአል ሻባብ እንቅስቃሴ ከፍ እንዲል ከማድረግ ባሻገር ያስገኘው ለውጥ ውስን ነው ብሏል።
በዚህም የተለያዩ ምክንያቶችን ያስቀመጠው የሶማሊያ መንግሥት በቀጣይ በተተኪነት በአገሩ የሚሠማሩትን ሰላም አስከባሪዎች ውስጥ የኢትዮጵያ ወታደሮች እንዲካተቱ እንደማይፈለግ ባወጣው መግለጫ ላይ ፍንጭ ሰጥቷል።
የሶማሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በቀጣይ በሶማሊያ ከሚሰማራው የአፍሪካ ኅብረት አረጋጊ ተልዕኮ አንጻር የሶማሊያ ሉዓላዊነት እና የኢትዮጵያ ሚና በሚል ረቡዕ አመሻሽ ባወጣው መግለጫ በሁለቱ አገራት መካከል የተፈጠረውን አለመግባባት ጠቅሷል።
በአፍሪካ ኅብረት ጥላ ስር በሶማሊያ የተሰማሩት የኢትዮጵያ ወታደሮች እንዲወጡ ባለፉት ወራት የሶማሊያ ባለሥልጣናት በተደጋጋሚ ሲጠይቁ መቆየታቸው ይታወሳል።
በመጪው ጥር የሚጠናቀቀውን የሰላም አስከባሪውን ውክልና ተከትሎ በሚተካው አዲስ ተልዕኮ ውስጥ አገራት የሚኖራቸውን ተሳትፎ በተመለከተ የሶማሊያ መንግሥት የበላይ በመሆን በአገሪቱ ሉዓላዊነት ላይ በማተኮር የተልዕኮውን ሚና እንደሚመራ አሳውቋል።
በዚህም ኢትዮጵያ በቅርቡ የተናጠል እርምጃ መውሰዷን በመጥቀስ ለአብነትም ነጻ አገርነቷን ካወጀችው ሶማሊላንድ ጋር የደረሰችው ስምምነት የሶማሊያን ሉዓላዊነት የሚቃረን ነው በማለት ዋነኛው ትኩረቱ ኢትዮጵያ ላይ መሆኑን አመልክቷል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሩ መግለጫ ኢትዮጵያ “ከሰሜናዊ ግዛት ጋር የደረሰችው ሕገወጥ ስምምነት፣ ሉዓላዊነታችንን የሚጥስ እና ለሰላም ማስከበሩ ተግባር አስፈላጊ የሆነውን መተማመን የሚሸረሽር ነው” ብሏል።
👇👇👇
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s


🌻50% ቅናሽለ10 እድለኞች
አዲስ አበባ : ኢትዮጵያ
#ከ DMC Real estate.
በመሀል ከተማ ለቡ 
  በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው  B4  ለሽያጭ አቅርበናል::

ግንባታው ሙሉ በሙሉ በ አሉሚኒየም ፎርም ወርክ በመገንባት ላይ የሚገኙ
50% ባንክ የተመቻቸላቸው

8% ብቻ በመክፈል ቤትወን ይምረጡ
ማለትም 
    
💝💝💝አንድ መኝታ
        69ካሬ  =431,918ብር
        77.6ካሬ=485,751
💝💝💝ሁለት መኝታ👇👇
            99ካሬ=>619,708ብር
             104ካሬ=651,000ብር
💝💝💝ሶስት መኝታ👇👇
    👉139ካሬ=870,000ብር
      👉147.6ካሬ=923,928ብር
ብቻ በመክፈል ቤትወን ዛሬውኑ  ይምረጡ
ለሱቅ ፈላጊወች  ከ20 ከካሬ
ለበለጠ  መረጃ  
💚በ+251918642895
@Gashawkefie


ኮረም‼️
የህወሀት ታጣቂዎች ከትላንት ጀምሮ በኮረም ከተማ ወረዳ ስር በሚገኙ ገጠር አከባቢዎች በሙሉ ህብረተሰቡን እንደአዲስ እያሰቃዩ ይገኛሉ ብለዋል።
ትናንት ጋዜጠኞችን ጨምሮ በርካታ ሰዎችን አፍነው ወስደዋቸዋል ብለዋል።
👇👇👇
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s


Attention‼️ ⚠️
በዓለም ላይ ብዙ የተወራለትና በራሱ በቴሌግራም የሚደገፈው major ፕሮጀክት ወደ ገንዘብ ሊቀየር ጥቂት ቀናት ቀርተውታል፣ያልጀመራችሁ እንዳትቆጩ፣ከስር ባለው ሊንክ ጀምሩ👇👇👇
https://t.me/major/start?startapp=473382500


ለስልክ ሌባ መርዶ የተባለ ዜና‼️
ጎግል የተሰረቁ ሞባይል ቀፎዎች ዳግም እንዳይሰሩ የሚያደርግ ፈጠራ መተግበሩን አሳወቀ።
ኩባንያው ኤአይን በመጠቀም ስልካቸውን የተሰረቁ ሰዎች ወደ ስልኩ አምራች ተቋም ሪፖርት የሚያደርጉበት አሰራርን ዘርግቻለሁ ብሏል።
አዲሱ የጎግል አሰራር የስልክ ንጥቂያ ወንጀሎችን ሊቀንስ እንደሚችል ተገልጿል።
ሌቦች የስልክ ቀፎን ከወሰዱ በኋላ ለመደበቅ ቢሞክሩ እና ዳግም ጥቅም ላይ ለማዋል ሲሞክሩ ኤአይን በመጠቀም ለዘለቄታው ከአገልግሎት ውጪ እንዲሆን የሚያደርግም ነው፡፡

ለአንድሮይድ ስልክ የተገጠመለት ኤአይ ቴክኖሎጂ ቀፎው ላይ በተገጠመለት ሴንሰር አማካኝነት እንዳይከፈት አድርጎ መዝጋት ይችላልም ተብሏል፡፡
አልአይን
👇👇👇
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s


በአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪነት ለመመዝገብ ጥያቄ ላቀረቡ አመልካቾች አገልግሎቱ ከህዳር 1 ጀምሮ ይሰጣል-የሲቪል ምዘገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ‼️
በአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪነት ለመመዝገብ የክፍለሃገር መሸኛ አስገብተው በመጠባበቅ ላይ ያሉ ተገልጋዮች ያቀረቡትን መረጃ የማጥራት ሂደት ማጠናቀቁን የሲቪል ምዘገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ አስታውቋል፡፡

አገልግሎቱን ከህዳር 1 ጀምሮ ለመጀመር ዝግጅት መደረጉንም ኤጀንሲው ገልጿል።

በመሆኑም ከነገ ጥቅምት 14/2017ዓ.ም ጀምሮ በነዋሪነት ለመመዝገብ ያመለከቱ ተገልጋዮች የሲቪል ምዘገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት የወረዳ ጽ/ቤት እስከ ጥቅምት 22 ቀርበው ሪፖርት እንዲያደርጉ ኤጀንሲው አሳስቧል፡፡

ተገልጋዮች የፋይዳ ምዝገባ አስገዳጅና ምዝገባው በኤጀንሲው ጽ/ቤት የሚከናወን በመሆኑ የክፍለሃገር መልቀቅያ ባስገቡበት ወቅት ከጽ/ቤቱ የተሰጣቸውን ማስረጃ ይዘው እንዲቀርቡም ተጠይቋል፡፡

በዚህ የማጥራት ሂደት ያላለፈ አመልካች በነዋሪነት ተመዝግቦ አገልግሎት ማግኘት የማይችል በመሆኑ በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ዘውትር ከሰኞ እስከ እሁድ ቀርበው ሪፖርት እንዲያደርጉ የሲቪል ምዘገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት አሳስቧል፡፡
👇👇👇
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s


ሞሳድ‼️
እስራኤል አዲሱን የሂዝቦላህ መሪ ሀሽም ሳፊይዲንን መግደሏን አረጋገጠች‼️
እስራኤል በሀሰን ናስራላህ ምትክ ወደ ቡድኑ ሀላፊነት መጥቶ የነበረውን የቡድኑን መሪ ሀሽም ሳፊይዲንን መግደሏን አረጋገጣለች፡፡

የእስራኤል መከላከያ ሃይል እንዳስታወቀው÷ የቀድሞው የሂዝቦላህ መሪ ሀሰን ናስራላህ የአጎት ልጅ የሆነው ሀሽም ሳፊይዲን ከሶስት ሳምንት በፊት እስራኤል በደቡባዊ ሊባኖስ በወሰደችው የአየር ጥቃት ተገድሏል።

ከሀሽም ሳፊይዲን በተጨማሪ የሂዝቦላህ ኢንተለጀንስ ዳይሬክቶሬት ሃላፊ አሊ ሁሴን ሃዚማ እና የቡድኑ ከፍተኛ ወታደራዊ አዛዦች በጥቃቱ ተገድለዋል ተብሏል፡፡

በጉዳዩ ላይ ሂዝቦላህ የሰጠው ምላሽ አለመኖሩ ተገልጿል።

ቀደም ሲል በፈረንጆቹ ጥቅምት 8 ቀን 2024 የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታኒያሁ የእስራኤል መከላከያ ሀይል ሀሰን ሳፊይዲንን ጨምሮ በሺዎች የሚቆጠሩ የሂዝቦላህ መሪዎችና ታጣቂዎች መገደላቸውን ተናግረው ነበር።

በወቅቱም ሀሰን ነስራላህን በመተካት ወደ ሂዝቦላህ መሪነት የመጣው ሀሽም ሳፊይዲን ሳይገደል እንዳልቀረ እየተነገረ ነበር።

ይሁን እንጂ በእስራኤል ጥቃት የመሪውን መገደል የእስራኤል መከላከያ ሃይል አዛዥ ሌተና ጄኔራል ሄርዚ ሃሌቪ በሰጡት መግለጫ አረጋግጠዋል።
👇👇👇
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s


‼️ደብረ ብረሀን እና አዲስ አበባ ላላችሁ ብቻ‼️

🌟 ከሁለት ድንቅ ሰዓቶች በተጨማሪ ኤርፖድ በዉስጡ የያዘዉን ድንቅ  ሰዓት
በ 2199 ብር ብቻ ለእርሶ ይፈጠኑ😱😱

❇️ደብረ ብረሀን ምዝገባዉ ሊጠናቀቅ ስለሆነ ፈጥነዉ ደዉለዉ ይመዝገቡ❇️
  
አሁኑኑ ይደዉሉ👉 0967500121

  💥 አዲስ አበባ ላይ የምንሰጠዉ ነፃና ፈጣን የዴሊቨሪ አገልግሎት እንደተጠበቀ ነዉ ይደዉሉ💥

🌍 ስትቀበሉ ሙሉ የዕቃዉን አጠቃቀም ገለፃ የምንሰጣችሁ ይሆናል🌍


🎤🎤በጥቂት ጊዜያት ዉስጥ ከፍተኛ ተቀባይነት ያገኘዉ ተች ሴንሰር የተገጠመለት ተቆጥረዉ የማያልቁ አገልግሎቶችን ከስልክ ጋር ተገናኝቶ መስጠት የሚችለዉ W26 pro max ለእናንተ🙏

W26 PRO MAX Special with
Earbuds

✅ለወንድም ለሴትም የሚሆን ዘረፈ ብዙ ጥቅምች ያሉት smartwach ከ pro wireless earpode ጋር🔥

  ❄️የራሱ ቻርጀር እና power bank ያለዉ
📌 የልብ ምትዋን  ይለካል
📌 ስፖርት ስንሰራ ምን ያህል ካሎሪ እንዳቃጠልን ያሳውቃል
📌 ብዙ ሰአት ስንተኛ ይቀሰቅሰናል
📌 ስልካችን ሲጠፋ ለመፈለጊያ ያግዘናል
📌 ቴክስት መላክ እንዲሁም መቀበል የሚያስችል
📌 ከስልክ ጋ በ Bluetooth ተገናኝቶ ስልክ መደወል እንዲሁም ማናገር ያቻላል
📌  wireless charger እና በሁለት አይነት የእጅ መሳርያ የቀርበ
📌  Blood Oxygen Detection
📌 Stress & Mood Testing

🚒 አዲስ አበባ ዉስጥ ነፃ እና ፈጣን  የዴሊቨሪ አገልግሎት እንሰጣለን።

ዋጋ  2199 ብር ብቻ
       ፈጥነዉ ይደዉሉ

📞  0967500121

ተጨማሪ እቃዎችን ለማየት
👉@Dubai_tera1 ን ይቀላቀሉ።


" ...አለመግባባት በዝቷል፤ ማኵረፍና መቀያየም ሰፍቷል ፤ ነገሩ ሁሉ ግራ የሚያጋባና የተመሰቃቀለ ሆኖ ይታያል፡፡ ችግሩ ከሕዝብ አልፎ የአምልኮ ስፍራዎችንና የአምልኮው ፈጻሚዎችን ዒላማ ያደረገ እግዚአብሔርን መዳፈር እየተለመደ መጥቷል " - ቅዱስነታቸው

የጥቅምት 2017 ዓ/ም የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ ተጀመረ።

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተወሕዶ ቤተክርስቲያን ሁለንተናዊ አገልግሎትና የስራ አፈጻጸም ላይ ለመምከርና ለመወሰን ኃላፊነት ያለው ቅዱስ ሲኖዶስ ዛሬ መደበኛና ዓመታዊ ጉባኤውን ጀምሯል።

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት የጉባኤውን መጀመረ አስመልክተው መልዕክት አስተላልፈዋል።

ከመልዕክታቸው ፦

" የሰው ልጆች በዚህ ዓለም ሲኖሩ የተሟላ ሰላምና ጣዕመ ሕይወት ሊኖራቸው የሚችለው በመንፈሳዊ ኑሮአቸው የተሻለ ነገር ስላገኙ ብቻ አይደለም፡፡

ሰዎች ከሥጋዊ ክዋኔም ጭምር የተፈጠሩ እንጂ እንደመላእክት ሥጋ የሌላቸው መንፈስ ስላይደሉ ለኑሮአቸውና ለሥጋዊ ክዋኔአቸው የሚሆን ነገር ያስፈልጋቸዋል፡፡

በዚህም ዓለማዊው አስተዳደር የተመቻቸ መደላድል ሊፈጥርላቸው ግድ ነው፤ ዓለማዊው አስተዳደርም የመለኮትን ተልእኮ ለመፈጸም የተሾመ ሹመኛ እንደመሆኑ የእግዚአብሔርን ሕዝብ በትክክል መምራት ይጠበቅበታል፡፡

ምንም ቢሆን የተቀበለው ኃላፊነት የእግዚአብሔር ነውና በሚሰራው ሁሉ በሿሚው አምላክ ከመጠየቅ አያመልጥም፡፡

እኛም በዚህ ዓለም የእግዚአብሔር ወኪሎች ስለሆንን ቢሰሙንም ባይሰሙንም ዓለማውያን ሹማምንትን የማስተማርና የመምከር ኃላፊነት አለብን፡፡

ይህ የሁለታችን ኃላፊነት እንደ እግዚብሔር ፈቃድ ስንፈጽም የሕዝብ ሰላምና በረከት፣ ፍቅርና አንድነት፣ ዕድገትና ልማት በአስተማማኝ ሁኔታ ይረጋገጣል፡፡

ነገር ግን በአሁኑ ጊዜ በሀገራችንም ሆነ በአካባቢያችን እየሆነ ያለው ይህ አይደለም፤ አለመግባባት በዝቶአል፣ ማኵረፍና መቀያየም ሰፍቶአል፤ ነገሩ ሁሉ ግራ የሚያጋባና የተመሰቃቀለ ሆኖ ይታያል፡፡

ችግሩ ከሕዝብ አልፎ የአምልኮ ስፍራዎችንና የአምልኮው ፈጻሚዎችን ዒላማ ያደረገ እግዚአብሔርን መዳፈር እየተለመደ መጥቶአል፤ ይህ ለአንድ ሀገር ወይም ሕዝብ የውድቀት ምክንያት ከሚሆን በቀር ከቶውኑም የዕድገት ምልክት ሊሆን አይችልም፡፡

ከሁሉም በላይ የሚያሳዝነው ደግሞ ይህ ክፉ ድርጊት እየተፈጸመ ያለው በእኛው ልጆች በኢትዮጵያውያን መሆኑ ነው፤ ስለሆነም በከተማም፣ በጫካም፣ በገጠርም በየትኛውም ስፍራ የምትገኙ ልጆቻችን ምንም ይሁን ምን ሀገርንና ሕዝብን ከመጉዳት ተቆጠቡ፡፡

በተለይም ከቤተ ክርስቲያንና ከሀገር እንደዚሁም ሕዝቡን ከሚያገለግሉ ካህናትና ሲቪል ሰራተኞች እባካችሁ እጃችሁን አንሡ፤ ቤተ ክርስቲያን እኮ የእናንተና የሕዝቡ ሁሉ እናት ናት፤ በእናታችሁ ላይ መጨከንን እንዴት ተለማመዳችሁት ? አሁንም ንስሐ ግቡ ያለፈው ይበቃል፡፡

ልብ በሉ ከእግዚአብሔር ጋር መጣላት አይበጅም፤ ሰውን መጉዳትና እግዚአብሔርን መዳፈር አቁሙ፤ የእግዚአብሔር ገንዘብ የሆነውን ሥርዓተ አምልኮም ያለቦታው አታውሉ፤ ጥያቄአችሁን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ዕድል ስጡ፡፡

በእግዚአብሔር ስም ለመላው ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችንና ልጆቻችን የምናስተላፈው ወቅታዊ መልእክታችን ይህ ነው፡፡ "
👇👇👇
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s

Показано 16 последних публикаций.