የሰው ህይወት አልፏል❗❗ ሼር❗
በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ቡግና ወረዳ በተከሰተ ከፍተኛ ምግብ እጥረት የእናቶች እና የህጻናት ሕይወት ማለፉ በዳሰሳ ጥናት ተረጋገጠ‼️
ካለፈው ወር ጀምሮ በወረዳው ከፍተኛ የምግብ እጥረት መከሰቱን #አዩዘሀበሻን ጨምሮ የአገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን የዘገቡ ሲሆን፤ ለዕይታ የሚረብሹ ምሥሎችም ይፋ ሆነዋል።
የአካባቢውን የምግብ እጥረት ለማረጋገጥ አጭር ዳሰሳ ያደረገው ወልዲያ ዩኒቨርስቲ ቀውሱ ከተነገረው በላይ "ከባድ ሆኖ አግኝቼዋለሁ" ብሏል።
ስድስት ባለሞያዎችን ያካተተ ቡድን በቡግና ወረዳ አራት "ቁልፍ" ቀበሌዎች ላይ ባደረገው ምልከታ ከፍተኛ የምግብ እጥረት፣ የህክምና አገልግሎት እጦት እና የውሃ ችግር ማኅበረሰቡ መጎዳቱን አመልክቷል።
ቡግና ወረዳ በድርቅ የሚታወቅ አካባቢ ከመሆኑ ባለፈ የሰሜኑ ጦርነት ጠባሳ ያረፈበት እና ባለፈው ዓመት የጎርፍ እና የበረዶ አደጋዎችን በማስተናገዱ ማኅበረሰቡ "ፍሬ" እንዳያገኝ አድርጎታል።
የወረዳውን የምግብ እጥረት እና የጤና ሁኔታን የሚዳስሰው ጥናት ከወሊድ ጋር በተያያዘ ከተመዘገቡ ሞቶች ውጪ አምስት ህፃናት እና ሁለት እናቶች በምግብ እጥረት ሕይወታቸው ማለፉን ይገልጻል።
ሦስት ህፃናት በቆብ ቀበሌ (ክላስተር) ሕይወታቸው ያለፈ ሲሆን፤ ብርቆ እና ቅዱስ ሀርቤ በተባሉ ቀበሌዎች ደግሞ በምግብ እጥረት የሁለት የህፃናት ሕይወት አልፏል።
በወረዳው ዋና ከተማ አይና ደግሞ ሁለት እናቶች በምግብ እጥረት ሕይወታቸው ማለፉን ባለሙያው ለቢቢሲ ተናግረዋል።
በአይና ከተማ በጎረቤቶቿ ቤት ለቡና በሚቀርብላት 'የቡና ቁርስ' ልጆቿን ትመግብ የነበረች አንዲት እናት "መቸገሯ ሳይታወቅ" ሕይወቷ አልፎ እንደተገኘች ማወቃቸውን ባለሙያው ተናግረዋል።
"ሰው በረሃብ እየሞተ ነው" ያሉት ባለሞያው፤ "በዚህ ዘመን ሰው በረሃብ መሞት የለበትም ብለን እናምናለን። ቡግና ላይ ግን ይሄ ተፈጥሯል" ብለዋል።
"እነዚህ [በአሃዝ የተገለፁት] በጣም ከአቅም በላይ ሆኖባቸው ተቸግረናል ብለው የሚመጡ ናቸው። ጤና ጣቢያ ሳይደርሱ የሚሞቱ በጣም ብዙ ናቸው" በማለት የተጎጂዎች አሃዝ ከዚህ ከፍ እንደሚል ይገምታሉ።"
ሌላ በዳሰሳ ጥናቱ የተሳተፉ ባለሙያም በተለይም የቡድኑ የቆይታ ጊዜ ሰፊ ቢሆን እና ያልተረደሰባቸው አካባቢዎች ላይ መድረስ ቢቻል "ከዚህ የከፋ ነገር እንደሚኖር ጥርጥር የለውም" ብለዋል።
የቡግና ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ጌታዬ ካሳው በወረዳው የሰዎች ሕይወት ማለፉን በወሬ ከመስማታቸው ውጪ "የተረጋገጠ ነገር የለም" ሲሉ በከፋ የምግብ እጥረት የሰው ሕይወት ማለፉን አለማረጋገጣቸውን ጠቅሰው የሞተ ሰው ስለመኖሩ ጥናት እየተደረገ ነው ብለዋል።
ዘገባው የቢቢሲ ነው።
=======================
💎⬇️⬇️⬇️👇👇👇👇👇
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2shttps://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s