ብሒለ አበው


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Другое


የአባቶቻችን ተግሳፅና ምክር

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Другое
Статистика
Фильтр публикаций


[📲የስልካችሁን የመጨረሻ ቁጥር
ንኩ ከዛ በሚፈጠረውን ነገር ተዝናኑ።📱




ብታነቡት አንድ ሥርዓት ትፈጽማላችሁ ታቃላችሁ 👍

ጾመ ገሃድ

ገሃድ ምንድን ነው?

ገሃድ የቃሉ ትርጉም መገለጥ፣ መታየት ነው፡፡ በጥምቀት መገለጥ መባሉ ሰው የሆነው አምላክ በዓለም ሲኖር እስከ 30 ዓመት እድሜው ድረስ ሰዎችን ለማዳን የመጣ መሲህ ሰው የሆነበት፣ አምላክ ኢየሱስ ክርስቶስ እሱ መሆኑን ሳያውቁ ከኖሩ በኃላ በ 30 ዓመት እድሜው በባሕረ ዮርዳኖስ በእደ ዮሐንስ እጅ ሲጠመቅ አብ በደመና ሆኖ ‹‹የምወደው ልጄ ይህ ነው›› በማለቱ መንፈስ ቅዱስ በርግብ አምሳል በራሱ ላይ ሲያርፍ በመታየቱ ነቢያት ይወርዳል ይወለዳል ይሰቀላል ይሞታል ይነሳል ብለው የተናገሩለት መሲሕ እርሱ መሆኑ ተገልጦአልና እንዲሁም ሦስቱ አካላት በአንድ ጊዜ ታይተዋልና ምስጢረ ሥላሴ የተገለጠለት በመሆኑ ገሃድ ይባላል፡፡(ማቴ 3፡13-17)

ይህን በማሰብ የምንጾመው ጾም “የገሃድ ጾም” ይባላል፡፡

በዚህ መሠረት የአሁን የገሃድ ጾም የራሱ አዋጅ አለው

ስንክሳር ዘጥር ፲ እንዲህ ብሎ ያዛል

ወለእመ ፡ ኮነ ፡ ዕለተ ፡ በይረሙን ፡ ዘውእቱ ፡ አስተርእዮ ፡ በዕለተ እሁድ አው፡በዕለተ፡ ሰንበተ አይሁድ፡ይጹሙ፡በእለተ ፡ ዓርብ ፡እምቅድሜሁ፡እስከ፡ምሴት፡በከመ ተናገርነ፡ ቅድመ ዳዕሙ ይትዓቀቡ፡እምነ፡በሊዕ፡ጥሉላተ።

ጥምቀት እሁድ ስለዋለ አስቀድመን አርብ እስከ 12 ሰአት ይጾማል። በዋዜማው ደሞ ቅዳሜ ከቅዳሴ በኃላ ምግብ መመገብ ይቻላል። ግን ጥሉላት አይበሉም።
ለምሳሌ  ሥጋ ፣ ወተትና የወተት ተዋጽኦ......

በረከት የምናገኝበት ጾም ያድርግልን!!!
@yetewahedofera
@yetewahedofera
@yetewahedofera


ዘንድሮ ከተራ ቅዳሜ ነው የሚውለው ፤ ጥምቀት ደሞ ገሀድ ጾም አለው

ጥያቄ ዘንድሮ እንዴት ነው ገሀድ ሚጾመው?

መልሳችሁን በ coment section ላይ ይላኩ ዋና ምላሹን በኋላ ይዘን እንመጣለን
@yetewahedofera
@yetewahedofera
@yetewahedofera


➢ ምን ማስተዋወቅ ይፈልጋሉ ❓

🔔• የምንሰጣቸው የማስታወቂያ አገልግሎቶች

┣➤ የ" ቻናል ማስታወቂያ "
┣➤ የ ዩቲዩብ ቻናል ማስታወቂያ
┣➤ ትሪትመንቶች እና
┣➤ ሌሎችም ሽያጮች ማስታወቂያ ያስተዋውቁ👍

በተመጣጣኝ ዋጋ
ለማስተዋወቅ ያናግሩን።

•➤አሁኑኑ ያናግሩን 👇

📩 •➤ 𝐈𝐧𝐛𝐨𝐱 𝐌𝐞
@fikreabe


በፈተና ወድቀህ እንደሆነ ፤ የኃጢአተኝነት(የጥፍተኝነት) ስሜት ከመጸለይ እንቅፋት እንዲሆንብህ አትፍቀድለት።
ንስሓ እስክገባ ብለህ መጸለይን ካቆምክ፤ መቼም ቢሆን ንስሓ አትገባም። ጸሎት ወደ እውነተኛ ንስሐ መግቢያ በር ናትና።

✍️ምክረ አበው🥰


🔤🔤🔤 🔤🔤🔤🔤🔤🔤🔤🔤
⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️
Telegram Premium🚀🎁

☑️3 month✔️1900birr🎁

 
☑️6 month✔️2450birr🎁   
                                                                                                                  
   ☑️1 year✔️4100birr 🎁

✅Star⭐
⭐️50 star ✔️200 Birr🎁
⭐️100 star ✔️ 400 Birr🎁
⭐️250 star ✔️800 Birr🎁
⭐️500 star ✔️ 1500 Birr🎁
✔HAMESTER🪙
Ton🛑
✅Dogs🐶                                                             USDT🤑
📣መግዛት  እና መሸጥ  ምትፈልጉ💬 አናግሩኝ

🌀〰〰〰〰〰〰〰〰〰💰
            
ከታች ባለው ሊንክ አናግሩኝ
            ✅ @fikreabe


💠“ክርስቲያን” ተብለህ መጠራትህ ዋስትና አይኾንህም፤ ዋስትና የሚኾንህ … 💠

በመንገድ ዳር ላይ ዘርን የሚዘሩ ሰዎች ምንም የሚያገኙት ጥቅም እንደ ሌለ ኹሉ፥ እኛም ለልጅነታችን የሚገባ’ ምግባር ከሌለን ክርስቲያኖች ተብለን ከመጠራት የምናገኘው በቁዔት የለም፡፡ ይህ እንዴት ይኾናል የምትለኝ ከኾነም የጌታችን ወንድም የተባለው ያዕቆብን ምስክር አድርጌ እነግርሃለሁ፡፡ እርሱ፡- “ሥራ የሌለው እምነት ቢኖር በራሱ የሞተ ነው” ብሎአልና (ያዕ.2፡17)፡፡ ስለዚህ ለእኛ (ለክርስቲያኖች) ምግባር መያዝ ግዴታ ነው፡፡ ምግባር ከሌለን ግን “ክርስቲያን” የሚለው ስም ለእኛ የሚፈይደው ምንም ነገር የለም፡፡ በዚህ ተደነቅህን? እንኪያስ ንገረኝ ! በዓውደ ውጊያ የማይሳተፍ፣ ለሚመግበው ንጉሥም የማይዋጋ ከኾነ አንድ ወታደር ወታደር ተብሎ ቢጠራ ምን ጥቅም አለው? ለንጉሡ ክብር የማይዋጋ ከኾነስ ወታደር ተብሎ ባይጠራ ይሻለዋል፡፡ ይህ ሰው በንጉሡ የሚመገብ ኾኖ እያለ፥ ነገር ግን ንጉሡ በጠላቱ ላይ ድል እንዲያደርግ የማይዋጋ ከኾነ እንዴት ከቅጣት ሊያመልጥ ይችላል? ንጉሡን ምሳሌ አድርጌ ልናገረው የፈለግሁትስ ምንድን ነው? ልለው የፈልገሁት እግዚአብሔር በትንሹ ስለ ገዛ ነፍሳችን እንድንጠነቀቅ (ምግባር መያዝ እንድንችል) ኃይል (ዓቅም) ሰጥቶናል ነው፡፡

✍️#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ

" ወዳጆች ሆይ ፥ ይህን እየጠበቃችሁ ያለ ነውርና ያለ ነቀፋ ሆናችሁ በሰላም በእርሱ እንድትገኙ ትጉ " [፪ጴጥ.፫፥፲፬
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬            

#ቻናሉን_ይቀላቀሉ                 
   🌐🌐🌐🌐🌐🌐🌐🌐               
@behle_abew
@behle_abew


ከአባቶች አንደበት
∞∞∞∞∞✞∞∞∞∞∞
፩. ‹‹ጸሎት የማያፈቅር ሰው ብታይ ምንም ዓይነት በጎ ነገር በውስጡ እንደሌለ ትረዳለህ፣ወደ እግዚአብሔር የማይጸልይ ከሆነ በመንፈሳዊነቱ ሞቷል ህይወትም የለውም››
                   ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

፪. ‹‹ጸሎት ችላ የሚል ሰው እንዲሁም ለንስሐ የሚያበቃ ሌላ በር አለ ብሎ የሚያስብ በዲያቢሎስ ተሸንግሏል››     
                                   ማር ይስሐቅ

፫. ‹‹ጸሎት አእምሮን ወደ እግዚአብሔር ማቅረብ ነው ››
                    ማር ይስሐቅ

፬. ‹‹ጸሎት ጸጋን ይጠብቃል፣ቁጣንም ያሸንፋል ትዕቢትንም የመከላከል ዝንባሌ ያሳድርብናል››
                      ከአባቶች

፭. ‹‹የመንፈስ ፍሬዎችን ያለ ፀሎት ገንዘባችን ልናደርጋቸው አንችልም››
                    ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

፮. ‹‹ጸሎት የማያረጅ ትዕግስትን ገንዘብ የምናደርግበት ታላቅ የጦር መሣሪያ ነው››
                       ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

፯. ‹‹በጸሎት ጊዜ ከእግዚአብሔር ጋር እየተነጋገርክ አይደለምን??እንዴት ያለ መብት ነው!!!››
                      ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ

፰. ‹‹ጸሎትን ለማድረግ አታቅማማ፣ሥጋ ከመብል(ከምግብ) በተከለከለ መጠን ደካማ እንደሚሆን ነፍስም ከጸሎት ስትከለከል ደካማ ትሆናለች››
                       አቡነ ማቴዎስ ግብጻዊ

በማርያም ሼር አድርጉ😍🙏

@behle_abew
@behle_abew


#ናፈቀኝ ....
ዲ/ን ዳንኤል ክብረት

የማለዳ ተመስጦ ... ውዳሴ ማርያም መድገሜ
በልጅነት ልመጣልህ .. ጧት ማታ መፍገምገሜ
ዛሬ ግን ናፍቆት ሆነብኝ .. ተዘረረብኝ አቅሜ
እንቅልፌ ሰላም አጣ .... እባብ ሆነብኝ ሕልሜ ።
.
"እግዚኦ" ሲባል ሰምቼ .. ሳልነሳ ከትራሴ
ድንጋጤ ወረረኝ .. ከእግሬ ጥፍር እስከራሴ
ሰዓታቱን እየሰማሁ ... ተቀሰቀሰ መንፈሴ
ትዝዝ አለኝ ማኅሌቱ ... ስትዋብበት ነፍሴ
የእናቴ ስም ናፈቀኝ ...... የሕርያቆስ ቅዳሴ
.
እራሴንም ስላጣሁት ..... ከቤትህ በመራቄ
እንደ ሎጥ ሚስት መሰልኩኝ ፤ አደባባይ ደርቄ
.
የመዝሙረ-ዳዊት ጸሎት .. አነከተኝ በትዝታ
ነፍሴን ስላስጠማኋት ... አነባችብኝ አብዝታ
እሪሪሪ ብላ አለቀሰች ... በስጋ ወንጭፍ ተገዝታ
.
ናፈቀኝ ትምህርቱ ... የቅዱስ ያሬድ ጸጋ
ቁጥር ዜማ መጮሄ .... አንደበቴ እስኪዘጋ
ዛሬ ላለው ማንነቴ .. ምን ይሆን የ'ኔ ዋጋ ??
.
በከበሮ በጽናጽል ... መዘመሩ ማሸብሸቡ
ጃኖ ለብሶ በመሰለፍ ... ማመርገዱ መወረቡ
የትውስታ ስለት ይዘው ፤ ወደ ልቤ ሰርገው ገቡ
.
አምላኬንም ሳመሰግን .. ወደ ሰማይ አንጋጥጬ
እንዲህ ዛሬ ልቀብረው .. በልቤ ውስጥ ረግጬ
አገልግሎቴ ናፈቀኝ ... ከሁሉ በላይ አስበልጬ
ኮርስ ስማር ትዝ አለኝ ... በዛፉ ስር ተቀምጬ
.
አንገቴ ላይ የታሰረው .. ለምን ነበር ማኅተቤ
ዛሬ ለምን አታለልኩት .. በምክንያት ተንተብትቤ ?
.
ምኑ ነው የሆነብኝ .. ለቤተ መቅደስ እንቅፋት ?
ትዳር ለምን መሰለኝ .. ሜዳ ሆኖ ተዳፋት ?
ልቤ ከብዶ እስከመቼ .. እኖራለሁ በጥፋት ?
ነፍሴንስ ምንበወጣት ... በ'ሳት ጅራፍ ላስገርፋት
.
ድጓ ሲሉ ትርጓሜ ... ብዙ ጊዜ ሰምቻለሁ
ድጓ ሲሉ ትርጓሜ ... ብዙ ጊዜ ሰምቻለሁ
ሰው መስዬ ሲመግቡኝ .. ባ'ይኔ ብሌን አይቻለሁ
ታዲያ ግን ምን ዋጋ አለው .. ማንበብ እንደሁ ትቻለሁ
.
እውነት ነው አይካድም .. አውደ ምኅረት መቀመጤ
ወንጌሉንም እየሰማሁ .... ሳላስበው መመሰጤ
ትዝ ይለኛል አጀንዳዬ ... ከንፈሮቼንም መምጠጤ
.
ጽዋ ቢሉ ዝክረ ሰንበት .. እንዳያልፈን ስንጣራ
ዓርብ ጸሎት ስንሰለፍ .. ነጭ ለብሰን በጋራ
ከትንሹም ከትልቁም ... ስለድኅነት ስናወራ
"ጉዞ" ብለን በባዶ እግር .. ሳንደክም በተራራ
ነጭ ለብሰን ጧፍ ይዘን .. እንደ ኮከብ ስናበራ
አዎ! አስታውሳለሁ ... ስልሳ ፍሬ ስናፈራ
.
ጾም ጸሎቱ ትዝ ይለኛል .. በላያችን ስናጌጠው
በስግደት ተሽቀዳድመን ... ሳጥናኤን ስናመልጠው
ብዙ ነበር በንስሐው ... በቁርባኑ የሚገልጠው
.
ጌታ ሆይ!
ተመልሶ ይላክልኝ ... መንፈሳዊ ጀግንነቴ
በመቅደስህ ዋጋ ይክፈል .. የናቡቴ ልጅነቴ
"እሺ" ብሎ እንዳልሰራው .. አይሁንብኝ ማንነቴ
.
ቀራኒዮ አይረሳኝ ... ችንካር ያለው መስቀሉ
በክቡር ደም ተነክሮ .. ቀይ ሆኖ መንቀልቀሉ
.
እመ ብርሐን በልደቷ .. ትመልሰኝ ወደ ጥንቱ
የቅዱሳን ጥበቃቸው .... አይለየኝ በረከቱ
ናፈቀኝ
ሰነፍ ልቤ እየገዛኝ .. በሞት ሰይፍ በጫጨቀኝ
ይቅር በለኝ አምላኬ! ... ከመቅደስህ አታርቀኝ
በግራ መቆም መረረኝ ፤ አሰልፈኝ በልጅህ ቀኝ
አብርሃምን ላክና ... መልስህን ቶሎ አሳውቀኝ
በራሴ አይን ስደናበር.. መታዘብህ አስጨነቀኝ
የምኅረት ቃል አንደበትህ ፤ ፅኑ ፍቅርህ ናፈቀኝ።               share
@behle_abew
@behle_abew
@behle_abew                                                                                                                              




Репост из: የተዋሕዶ ፍሬዎች
ተወዳጆች።

ብፁዕ አባታችን አቡነ ኤርምያስ (ዶ/ር)
#በኢንቴክስ-ፉድ-ኤይድ-ፕላስ በሰላም ዘርፍ ዕጩ ሁነዋል።

ሁላችንም በመምረጥ እኛኑ ለምነው ተጨንቀው ለጉባኤ ቤት ከሚደክሙት ባሻገር በዚህም ተሳትፈን ለዓላማቸው መሳካት መንፈሳዊ ድርሻችንን መወጣት አለብን።

ካሸነፉ #10 ሚሊዮን ብር ያገኛሉ።

9355 ላይ BIW08 ን በመላክ መምረጥ ይቻላል።


🗓 ድምጽ መስጠቱ  እስከ ሐሙስ
ታህሳስ 17 ቀን 6፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ይካሄዳል!

@yetewahedofera
@yetewahedofera
@yetewahedofera




✍️ በከንቱ እንዳንደክም መጾም እንደሚገባን እንጹም።

በመጾም እየደከምን ሳለ የጾምን አክሊል ካላገኘን፥ እንዴትና በምን ዓይነት አኳኋን ይህን ልንፈጽመው እንደሚገባው ልንረዳ ያስፈልጋል።

ፈሪሳዊዉም ጾሞ ነበር

ከዚያ በኋላ ግን ወደ ቤቱ የሄደው ባዶ እጁንና የጾሙን ፍሬ ሳያገኝ ነው።
ሉቃ.18፡12

ቀራጩ ደግሞ አልጾመም ነበር

ነገር ግን ከጾመው ፈሪሳዊ ይልቅ በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነትን ያገኘው እርሱ ነው።

ይህም የኾነበት ምክንያት

👉 ቀራጩ ባይጾምም ተጠቀመ፤ ለመጪው ሕይወቱም ጾም አላስፈለገውም ለማለት ሳይኾን ከኃጢአት ተከልክለው ካልጾሙት በቀር ጾም ብቻውን ጥቅም እንደሌለው እና ትሕትና አስፈላጊ መኾኑን ለማሳወቅ ነው።

የነነዌ ሰዎች ጾመዋል፤ የእግዚአብሔር ምሕረትንም አግኝተዋል።
ት.ዮና 3÷10

እስራኤላውያንም ጾመው ነበር፤ ነገር ግን እያጉረመረሙ ተመለሱ እንጂ በመጾማቸው አንዳች ጠቀሜታን አላገኙም።
ኢሳ 58÷3-7
1ኛ ቆሮ 9÷26

ስለዚህ እንዴት መጾም እንዳለብን ማወቅ ያስፈልጋል።


1️⃣9️⃣5️⃣
✝️ይበራል በክንፉ✝️

ይበራል በክንፉ ምልጃውም ፈጣን ነው
የአምላክ ስም አለበት ስሙ ሚካኤል ነው
ያሳደገኝ መልአክ ዛሬም ከኔ ጋር ነው (2)

ከፊቴ ቀደመ ደመናን ዘርግቶ
እንዳልደናቀፍ ጉድባዎቼን ሞልቶ
ዛሬ ላለሁበት ብሩቱ ጉልበት ሆነኝ
ሰው ለመባል በቃሁ ሚካኤል ደገፈኝ

    አዝ=====

በእናቴ እቅፍ ገብቼ መቅደሱ
አለሁ እስከዛሬ አጥሮኝ በመንፈሱ
የህይወቴን ሰልፎች አለፍኩ ከርሱ ጋራ
ተፅፏል በልቤ የሚካኤል ስራ

    አዝ=====

በዙሪያዬ ተክሎ የእሳት ምሰሶውን
ፅድቅ እየመገበ ኣሳደገኝ ልጁን
የአምላኬን ምስጋና ዘውትር እያስጠናኝ
እርሱ ነው ሚካኤል በመዝሙር የሞላኝ

    አዝ=====

ፊት ለፊት ተተክሎ ከታናሿ መንደር
ይስማኝ ነበረ ቅኔው ሲደረደር
ይወስደኛል ደጁ እየቀሰቀሰ
ታላቁት በረከት በውስጤ አፈሰሰ

    አዝ=====

ሴኬምን እንዳላይ ክንፎቹን ጋረደ
መራኝ ወደ ህይወት መዳኔን ወደደ
የሞአብን ቋንቋ ከአፌ ላይ አጥፍቶ
በፀጋው ቃል ቃኘኝ በበረከት ሞልቶ

♡ ㅤ  ⎙ㅤ  ⌲        ✉️   
   ˡᶦᵏᵉ    ˢᵃᵛᵉ    ˢʰᵃʳᵉ   ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ


Anyone online 👀? Check this👇👇


ናሁ ተፈጸመ ማህሌተ ጽጌ

ማህሌተ ጽጌ
ኢየኃፍር ቀዊመ ቅድመ ስእልኪ ወርኃ ጽጌረዳ አመ ኃልቀ፤ዘኢየኃልቅ ስብሐተኪ እንዘ እሴብሐኪ ጥቀ፤ተአምርኪ ማርያም ከመ አጠየቀ፤ጸውዖ ስምኪ ያነሥእ ዘወድቀ፤ኃጥአኒ ይሬሲ ጻድቀ፡፡

👉ትርጉም

እጅግ ብዙ የማያልቅ ምስጋናሽን እያመሰገንኩኝ : የጽጌረዳ ወራት ባለቀ ጊዜ በስዕልሽ ፊት መቆምን አላፍርም : ማርያም ተዓምርሽ እንዳስረዳ ስምሽን መጥራት የወደቀን ያነሳል : ኃጥኡንም ጻድቅ ያደርጋል ።

👉ምስጢር

የጽጌረዳ ወራት ባለቀ ጊዜ በሥዕልሽ ፊት መቆምን አላፍርም ማለቱ ከመስከረም 26 - ኅዳር 5 የቆየው የጽጌ ወቅት ቢያልፍም እኔ ግን ምስጋናሽን አላቋርጥም ይላል የዚህ ክፍል ጥንተ ነገሩ ዘካርያስ የሚባል ሰው የእመቤታችንን ሥዕል ያገኛል ፤ በጣም ተደሰተ ፤ የእመቤታችን ፍቅር አደረበትና ምን ላድርግላት ብሎ ተጨነቀ ።

ወቅቱ የጽጌ ነበርና እለት እለት 50 አበባ ለሥዕሏ አደርጋለሁ አለ ። እንዳለውም በየቀኑ ሀምሳ ጽጌሬዳ እየቆረጠ ለሥዕሏ ያደርግ ነበር ። በኋላ የአበባ ጊዜ ሲያልፍ አበቦችን ማግኘት ስለማይችል ምን ላድርግ ብሎ አሰበ ፤ በአበቦቹ ፈንታ ሀምሳ ጊዜ በሰላመ ቅዱስን አደርሳለሁ ብሎ ማድረስ ጀመረ ።

ከእለታት በአንዱ ቀን ወደ ሌላ ሀገር ሲሄድ መንገድ ላይ ሽፍታዎቹ አግኝተውት እርሱ በሰላመ ቅዱስ ገብርኤል መልአክ እያለ ይጸልያል ፤ እመቤታችን ለሽፍቶች ተገልጣ አንድ በሰላመ ቅዱስ ሲል አንድ አበባ ስትቀበል ይመለከታሉ ፤ ሀምሳውን ሲጨርስ ሀምሳ አበባ ።

የዚህን ጊዜ ሽፍታዎቹ በግንባራቸው ተደፍተው ሰገዱለት ፤ በኋላም አምነው መነኮሳት ሆነዋል ። እናም ይህ የጽጌ ምሥጋና ቢያልቅም የእመቤታችን ምሥጋና እንደማይቋረጥ ሲገልጽ ነው ፤ በውዳሴ ማርያም ፣ አርጋኖን ፣ ማኅሌት ፣ ሰዓታቱ ትመሰገናለችና ።

ስምሽን መጥራት የወደቀን ያነሣል ማለቱ አንድ እመቤታችን የሚወድ ሰው ነበር ፤ ከተወደደ ልጇ ጋር ሥዕሏን ስሎ በመሰላል ወጥቶ ዲያቢሎስ በሲኦል ነፍሳትን መከራ ሲያጸናባቸው እየሣለ እያለ ዲያቢሎስ ተናድዶ መሰላሉን መትቶ ሊጥለው ወደ ታች ሊወድቅ ሲሄድ ከሳላት ሥዕል የእመቤታችን እጅ ወጥቶ ይዞ አድኖታል ።

ኃጥኡንም ጻድቅ ያደርጋል ሲል በቃልኪዳኗ ልጄ ወዳጄ ማርልኝ ብላ ስትለምን ስለ እናትነቷ ይምራልና ኃጥኡንም ጻድቅ ያደርጋል ብሏል ።

ማህሌተ ጽጌ
ለንጉሠ ነገሥት ሰሎሞን ከመ ተፈሥሐ ልቡ፤በዕለተ ወፃእኪ መርዓት ለአንበሳ ትንቢት እምግቡ፤ማዕከለ ማኅበር ፍሡሓን ተአምረኪ ዘይነቡ፤እዜምር ለኪ ጽጌ ሐና ወፍኖተ ነፈርዓፅ እሌቡ፤ከመ ጣዕዋ ሐሊበ ዘይጠቡ።

ትርጉም

የሀና አበባ  ሆይ!ሐሴትን በተመሉ ( ማኅበረ ጻድቃን)ማኅበር መካከል ተአምርሽን የሚናገር የነገሥታት ንጉሥ ሰሎሞን ሙሽሪት  ከአንበሳዉ ትንቢት ዋሻ በወጣሽ ጊዜ ልቡ ሐሴት እንዳደረገ  እንደ ሚጠባ እንቦሳ የመፈርጠጫ ቦታየን አስተውላለሁ፤ እዘምርልሽም አለሁ።

ማኅሌተ ጽጌ

ኅብረ ሐመልሚል ቀይሕ ወፀዓድዒድ አርአያ ኰሰኰስ ዘብሩር ተአምርኪ ንጹሕ በአምሳለ ወርቅ ግቡር ተፈጸመ ናሁ ማኅሌተ ጽጌ ሥሙር አስምኪ ቦቱ ንግሥተ ሰማይ ወምድር ከመ በሕፅንኪ ያስምክ ፍቁር ።

ትርጉም
የሚያብረቀርቅ ቀይነ ነጭ ቀለም ያለው አርአያው የብር ዝንጉርጉር የሆነ ንጹሕ ተዓምርሽ በወርቅ አምሳል የተሰራ ነው ፤ እነሆ የተወደደ መልካም ማኅሌተ ጽጌ ተፈጸመ ፤ የሰማይና የምድር ንግሥት ማርያም ሆይ የተወደደ ልጅሽ በእቅፍሽ እንዲጠጋ (እንዲንተራስ ) በእርሱ አማጽኝ ።

ምስጢር
ቀይና ነጭ ቀለም ያለው ማለቱ ቀይ በትስብእቱ ነጭ በመለኮቱ ማለትም ፍጹም ሰው ፍጹም አምላክ ዝንጉርጉርም ያለው ሰው እና አምላክነቱን ነው  ( እንዘ ተኃቅፊዮ ላይ በሰፊው አይተናል )
ተአምርሽ በወርቅ አምሳል የተሰራ ነው ሲል ወርቅ የንጽሕና ምሳሌ ነውና እመቤታችንም ንጽሕተ ንጹሐን ናትና ። |  ኵለንታሃ ወርቅ |

ወርኀ ጽጌ አልቋል ሲል ተፈጸመ ማኅሌተ ጽጌ ስሙር አለ የሰማይና የምድር ንግሥት ( መዝ 44 )


ስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክቡር ... አሜን !

ከሌላ ቻናል ትማሩበት ዘንድ የተላከ
@yetewahedofera


የሰማዩን ምስክር


ጨለማን ሰባሪ_ብርሃን ወጥቶብሻል
ሞትን የሚገድል_ትንሳኤን ወልደሻል
ንጽሕ መሶበ ወርቅ_ ድንግል ተብለሻል
ለከበረው ክብርሽ_ስግደት ይገባሻል።

የሰማዩ ምስክር_ የታየው በራማ
በምድራዊው ገነት_ እነሆ ተሰማ
የመልአኩን በስራት_ኤልሳቤጥ ስትደግመው
በሆዷ ያለው ጽንስ_ ደስታ አዘለለው
መጥምቀ መለኮት_ክብሩ ከፍ ያለ ነው።

ለኛ ስለሰጠች _ የሕይወት እንጀራን
ሁሌም ለዘለአለም_ እንወዳታለን
የምስራቋ ደጃፍ_የወለደች ፀሐይ
የኤልሳዕ ማሰሮ_ የበረከት ሲሳይ።

የፍቅር የሰላም _ የምሕረት መገኛ
የምንመካብሽ _ ነይ ነይ ወደ እኛ
ኖርዶስ ቀሲመታት_ በጎ መዓዛ ነሽ
የአማኑኤል ማደሪያ_ የለም የሚመስልሽ።

ጌታዬ ከሰጠኝ_ እናቴ እልሻለው
የመንገድ ስንቄ ነሽ_ እመካብሻለው
ለጠየኩሽ ሁሉ _ መልስ የምትሰጪኝ
እንዳልነዋወጥ_ በዐለቱ ትከይኝ።

በመከራ ጊዜ _ መሸሸጊያ ሆኖን
የመከራን ባሕር_ በፍቅሩ አሻግሮን
እንደበደላችን_ ሳያጠፋን ጌታ
አቆመን በደጁ_ ሞልቶን በእልልታ።

ከኛ የበረታችሁ _ አስቡን በጸሎት
በስጋ ፈተና _ እንዳይገለን ምቾች
በሄድንበት ሁሉ_ እንዲገጥመን ሰላም
ፍፃሜአችን እንዲያምር_አማልጅን ማርያም።

የተሰቀለውን _በገና አውርዱ
መሰንቆ ክራሩን_ ከበሮ አሰናዱ
መቆሚያ ጽናጽል_ ይታደል ለሁሉም
በያሬድ ውብ ዜማ_በሚያስረሳ ዓለም
ተነሱ እንዘምር_ ለመድኃኒዓለም።

እንዲህ እናምናለን_ እንታመናለን
በተበተንበት በባዕዱ ምድር_ እንመሰክራለን
የሥላሴን ጥበብ_ ትውልድ እንዲረዳ
ይምጣና ይመገብ_ ከእናቱ ጓዳ
ኋላ ለጥያቄ _እነዳይሆን እንግዳ ትጉኃን

በዝማሬው ጣዕም_ተሞልተን ደስታ
በተዋሕዶነቷም _ ነፍሳችን ተጽናንታ
በቃሉ ምስክር _ ቀርቦልን ማዕድ
በወልድ እናት ምልጃ _በሕይወት መንገድ
ከቅድስት ምድራችን _በመጡት
በደጀ ሰላሙ አለን_ ተሰብስበን።

በመረዋ ድምጹ_ በሚስረቀረቀው
ሲሰማ አርነት_ተሰፋን በሚሰብከው
የአባቶችን ምክር_ትዕዛዝ በሚያከብረው
በረጋው አንደበት_ ከቴድሮስ ሰማነው
ኪዳነምሕረት_ በእቅፏ ታኑረው።


ከዕርስታችን ወተን_ ብንኖርም በእሩቅ
መተላለፋችን_ በስሙ እንዲፋቅ
ክብር ሞገስ ሆነን_ ስራው የሚያስደንቅ።

ሀይማኖት ከምግባር_የነፃነት በፍታ
የሚያስተምር ፍቅር_ ጠዋትና ማታ
የወንጌል አርበኛ_ የሚያስር የሚፈታ
ደጀንን ሸለመን_ የሰራዊት ጌታ።

ለዘመኑ ሕመም_ መድኃኒት ያመርታል
የነፍስ ዶክተር ነው _ትውልድ ይፈውሳል
ብሉይን ከሐዲስ _ እያመሳጠረ
ስንቱን ሐሰተኛ_ ከቤት አባረረ።

በጠላት ተከቦ_ ሲደፈር ተራራው
እንደ ተመረጡት_ በእውነት አብበው
ወንጌልን ተጫምቶ_ በብዕር ይሻገራል
በለበሰው ሞገስ_ ሁሉን ያስደምማል

___
h>ttps://t.me/behle_abew


በዲሜጥሮስ ቀመር መሠረት አጽዋማትን በጠበቀ መልኩ ከትንሣኤ በዓል በፊት ያለው ዓርብ “ስቅለት” ተብሎ እንዲከበር አባቶቻችን ሥርዓት ሠርተዋል፡፡

መጋቢት 27 ቀን በዓቢይ ጾም ላይ ስለሚውል በዓቢይ ጾም ሐዘን እንጂ ደስታ ስለሌለ፤ ወደ ጥቅምት 27 ተዛውሮ በደስታ እንድናከብረው ቤተክርስቲያን ሥርዓት ሰርታልናለች።

ቅዳሴ ዮሐንስ አፈወርቅ

👉 ሊቃነ መላእክት በመፍራት እና በመንቀጥቀጥ ከፊቱ የሚቆሙለትን በአደባባይ አቆሙት፤
👉 ኃጢአትን ይቅር የሚለውን ኃጥእ አሉት፤
👉 በመኳንንት በሚፈርደው በርሱ ፈረዱበት፡፡
እንዳለ።

መጋቢት 27 ቀን ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ በተሰቀለ ጊዜ

👉 ፀሐይ ጨልማለች
👉 ጨረቃ ደም ሆናለች
ከዋክብት ረግፈዋል

👉 በምድር የቤተ መቅደሱ መጋረጃ ከላይ እስከ ታች ለኹለት ተቀዷል፤
👉 ምድር ተናውጣ ዐለቶች ተሠንጥቀዋል፤
👉 መቃብራት ተከፍተዋል፤ ሙታን ተነሥተዋል፡፡

ስቅለቱን በዲሜጥሮስ ቀመር አውጥተን የጌታን መከራውን አስበን በስግደት ሕማማቱን እናስባለን በዝክረ ጥንተ ስቅለቱ በጥቅምት 27 ደግሞ በመስቀል የተደረገልንን አስበን እናመሰግነዋለን፡፡

የመድኃኔዓለም ይቅርታውና ቸርነቱ ሁላችንንም ይጠብቀን!
አሜን!

እንኳን ለክብረ በዓሉ በሰላም እና በጤና አደረሳችሁ፡፡
@yetewahedofera


የኖትኮይን መስራች የሆነው #ሳሻ እና #የብሉም ምክትል Ceo ቭላድሚር ይሄ አዲሱን Paws ኤርድሮፕ ከጀመሩ ታዋቂ ሰዎች መካከል ይገኙበታል 😮‍💨🔥

Paws በብሉም በኦፊሺያል የትዊተር ገፅም በተደጋጋሚ የተተዋወቀ ሲሆን በWeb 3 የትዊተር ገፅም አዲሱ ዶግስ ይሆናል ሲሉ Paws ን ለብዙዎች አስተዋውቀዋል

Paws ላይ ያስገረሙኝ ነገሮች

1. ከቴሌግራም ድጋፍ ያለው መሆኑ
2. ከቴሌግራም ካልተደገፈ ቴሌግራም አካውንታችን የተጠቀምንበትን ቀን ማወቅ አስቸጋሪ ነው
2. ኖትኮይን የሰጠንን ቶክን ማወቁ
3. ዶግስ የሰጠንን ቶክን ማወቁ

እነዚህ ማሳያዎች የ Paws መስራቾች የሚታወቁ እና
#ከዶግስ #ከኖትኮይን እና #ብሉም በተጨማሪም #ከዱሮቭ ቴሌግራም ጋር ግንኙነት ያላቸው ሰዎች መሆናቸውን በቂ ማሳያ ነው

መጀመር ለምትፈልጉ ጊዜው ሳይሄድ በትጀምሩት አሪፍ ይመስለኛል 🫡

Link 👉


https://t.me/PAWSOG_bot/PAWS?startapp=7Mj9rR5L

Показано 20 последних публикаций.