Фильтр публикаций


መንገዱ የሚጀምረው አሁን ካለህበት ቦታ ነው


በሕይወትህ ውስጥ ለውጥ መደረግ እንዳለበት ካወቅክ፣ ከዓላማህ በጣም የራቅክ ወይም እንዴት እዚያ እንደምትደርስ ገና ያልገባህ ብትሆንም እንኳን ችግር የለውም፡፡

ገና እየጀመርክ ቢሆንም ችግር የለውም፡፡

ገና ከታች ብትሆንና መንገድህ በግልጽ እየታየህ ባይሆንም ችግር የለውም፡፡

ገና በተራራህ ግርጌ ያለህና፣ ለማሸነፍ በሞከርክ ቁጥር እየወደቅክ ብትሆንም ምንም አይደለም፡፡

አብዛኛው የፈውስ ጉዞ የሚጀመረው ከዝቅታ ስፍራ ነው። ይህ የሚሆነው ዝቅታ ላይ ስትሆን በድንገት ብርሃን ስለሚታይህ፤ መጥፎዎቹ ቀናት በአስማት ወደ አንድ የደስታ አይነት ስለሚለወጡ ወይም የሆነ ሰው ከራስህ እብደት ስለሚያድንህ አይደለም፡፡ ዝቅታ የለውጥ መነሻ የሚሆነው፤ ብዙ ሰዎች “እንደዚህ አይነት ስሜት እንደገና ሊሰማኝ አልፈልግም፡፡" ብለው የሚወስኑበት ቦታ ስለሆነ ነው።

✍Brianna weist
📚@Bemnet_Library


ማየት የምትችለው  ብርሃን የሚያሳየውን ብቻ ከሆነና የምትሰማውም ድምፅ የሚያሰማውን ብቻ ከሆነ በእውነቱ አንተ አታይም፣ አትሰማምም።

📓የጥበብ መንገድ
✍ካህሊል ጂብራን

📚@Bemnet_Library


"ሁሉም እንዳንቺ የማያውቀውን አባት ፍለጋ፤ የሚያውቃትን እናቱን እየረሳ፤ የሌለ በሽታ ሆነበት። ከፊት ያለውን ማየት ሲቻል፤ በእጅ ያለውን ማጥበቅ ሲቻል፤ የሄደ ትናንትን ፍለጋ ሰው እንዴት የዛሬን ይለቃል? "

📚 ርዕስ፦ አለማወቅ
✍️ ፀሃፊ፦ ዳዊት ወንድማገኝ (ዶ/ር)

🌆 ሸጋ ምሽት

📖 @Bemnet_Library

7.1k 0 11 12 142

ሰዎች የበለጠ ስልጣን ባላቸው ቁጥር ያ ቦታ እንደሚገባቸው ለማረጋገጥ ሲሉ የበለጠ ችግር ውስጥ ይገባሉ።በራሳቸው ላይ ምንም ጥርጣሬ እንዳይኖራቸው ሲሉ "ሲጠሩት አቤት ሲልኩት ወዴት" የሚባሉ አይነት ጭፍሮችን በዙሪያቸው በማሳለፍ የማያባራ ሙገሳ እና አዎንታዊ ማረጋገጫን ማየት ይሻሉ።

📓ርዕስ፦የለውጥ ጥበብ
✍️ደራሲ፦ዴል ካርኒጌ


📚 @Bemnet_Library

8.4k 0 27 9 164

እብድ ነኝ? በጭራሽ እብድ አይደለሁም! እብድ ነህ! ካላችሁኝ ግን እስቅባቹኋለሁ... ምከንያቱም እኔ እብድ አይደለሁማ... ለነገሩ እብድ ማለት እኮ ነገሮችን እኛ ማየት ባልቻልንበት መንገድ የሚመለከት! ዓለምን በራሱ የተለየ መነፅር የሚመለከት ነው፡፡

እንደውም አንድ አሪፍ አባባል ትዝ አለኝ ፡-

“ዓለም ላይ ሰውን እብድ ነው የሚል ራሱ ትልቅ እብድ ነው!"

✍አዘርግ
📚@Bemnet_Library

9.6k 0 28 24 229

"እየውልህ ወዳጄ! ቤትን የሚያደምቀው ቀለም አይደለም። ፈገግታዋ ከቀለም በላይ የሚያበራ ቆንጆ ሚስት ፈልገህ አግባ። ትልቁና ወደር የሌለው ደማቅ ቀለም ፍቅር ነው። የፍቅር ቀለም አይደበዝዝምም በሌላም ቀለም አይጠፋም። ህያው ሆኖ የሚገኝ የፍቅር ቀለም እስኪገኝ ሰው ቀለም ሲያሳድድ ይኖራል።"

📚 ርዕስ፦ ዙበይዳ
✍️ ፀሃፊ፦ አሌክስ አብርሃም

የፍቅር ቀን ☀️
📖 @Bemnet_Library

9.5k 0 61 22 250

ወደ ልቀት የሚያደርሱ 9 ደረጃዎች


1,በሕይወት ውስጥ አላማን ጠንቅቆ ማወቅ።

2,የራስ የሆነ የህይወት ፍልስፍናን ወይም መመሪያን መያዝ

3,የቅርብ፣የመካከል እና የወደፊት እቅድ ማውጣት

4,በእያንዳንዱም እቅድና ድርጊት ግልፅና ሊደረሰበት የሚችል ግብ ማስፈር

5,ውጤቱን ለማሳካት የጋለ ስሜትን ማዳበር/እንደሚሊዮናዊ ተልእኮ ያለ/።

6,ግብቹን ለማሳካት የጊዜ መርኃ ግብር መንደፍ

7,ለማከናወን በተነሱት ድርጊት የማይናወጥ እ እምነት እና በራስ መተማመን ማጎልበት።

8,ምንጊዜም አውንታዊ ውጤትን መጠበቅ

9,ቀደም በአይነ ህሊና ውጤቱን በመመልከት ደስታን መግለፅ።

📚 @Bemnet_Library

10.8k 0 139 13 198

ብዙ ሰዎች ሌሎችን ለመውደድ በቅድሚያ ራስህን ውደድ ብለው መክረውህ ይሆናል፤ እውነታው ግን ሌሎችን መውደድ የቻለ ራሱን መውደድ ይማራል የሚለው ነው።

✍Brianna weist
📚@Bemnet_Library

10k 0 20 26 228

መጽሐፍ ልንሸልም ነው


የምንሸልማቸው መጽሐፎች አለማችን ላይ በከፍተኛ ደረጃ ተቀባይነት ያገኙና ከ90% በላይ ተወዳጅነት ያላቸውን የቢዝነስና የሳይኮሎጂ መጽሐፎችን ነው።

ለመሸለም ከእናንተ የሚጠበቀው Active view ወይም ፈጥኖ ተመልካች (ፈጥኖ ደራሽ) መሆን ብቻ ነው።እኛ የሆነ ፖስት ስንፖስቶ ቶሎ ማየትና ሪያክት ማድረግ ነው።በተለይ ቶሎ የሚፖሰቱ ነገሮችን  መመልከት ነጥቡን ከፍ ያደርገዋል።

መጽሐፉቹን የምንሸልመው በSoftcopy ሲሆን ነገር ግን ይሄ ሀሳባችን 75% ለውጥ ካመጣ ወደ "HardCopy" ሽልማት እንቀይረዋለን።በደምብ ተቀባይነት ካገኘ ደግሞ ከመጽሐፍ ውጪ እስከ 10ሺ ብር መድበን እንሸልማለን።

#ንቁ ሁኑ
#የምንፓስታቸውን ነገሮች ፈጥናችሁ ተመልከቱ
#ሪያክት አድርጉ
#ከዛ በሽልማት እናበሸብሻችኋለን።መጨረሻ ላይ መረጃው ታይቶ ንቁ ተሳታፊው የሚሸለም ይሆናል።በብዛት የምንሸልመው ታዋቂ የትርጉም መጽሐፎችን ነው።

መልካም ዕድል
መልካም ጊዜ

📚 @Bemnet_Library


ርጋታ ያስፈልግሻል።ምክንያቱም ካልተረጋጋሽ ወደ ውስጥሽ መግባት አልችልም።እንቅስቃሴሽ ሁሉ መወገድ አለበት።ትኩረትሽ በሙሉ እኔ ላይ ብቻ መሆን አለበት።ምክንያቱም አሁን ከአንቺ ጋር ያለሁት እኔና እኔ ብቻ ነኝ።በእምነት ወይም በእምኒ ልትይኝ ትችያለሽ።

እያንዳንዱን ማይክሮ ሰከንድ በአይኖቼ ላይ ብቻ ትኩረት አድርጊ።ከዛ አይኖችሽን በፈገግታ ሙያቸው።ነገር ግን ሌሎች አካሎችሽ በዝምታ የተሞሉ ይሁኑ።በጣም ተረጋጊ፤በጣም ዝግ በይ፤ከፈጠንሽ የምንሰራውን ነገር ሁሉ ታበላሺዋለሽ።ስለዚህ በእኔ ላይ ብቻ ትኩረት አድርጊ...

እዚህ ማንም የለም፤እኔና አንቺ ብቻ!...እዚህ ማንም አይረብሸንም፤ማንም አይጮህብንም፤ማንም አያየንም።እዚህ ያለው ታይቶም ተሰምቶም የማይታወቅ ታላቅ ትኩሳት ነው።በጣም ደስ የሚል ትኩሳት፤በጣም የሚያቃጥል ትኩሳት፤ብቻ በዚህ ትኩሳት ውስጥ ያለነው እኔና አንቺ ብቻ ነን።

ፍቅረኛ ካለሽ እርሺው፤ባል ካለሽ እርሺው።የምትወጂው ሰው ካለሽ እርሺው፤የምትሳሽለት ሰው ካለ እርሺው።ምክንያቱም አሁን ያለነው እኔና አንቺ ብቻ ነን።በዙሪያችን ደግሞ ትልቅ ፍም እሳትና ሀይለኛ አውሎንፋስ እየነፈሰ ነው።ጉዞ ወደ ተፋፋመው የስሜት እሳት......


ፀሀፊው እያበደ ነው
✍️ Bemni Alex

12.7k 0 34 42 149

ዝም ስንል ማውራት የማንችል ወይም ስለራሳችን መከራከር የማንችል ይመስላቸዋል።ዝም ስንል ፍርሃት ያለብንና ስለምንም ነገር የማንጨነቅ ይመስላቸዋል።ዝም ስንል እነሱ ብልጥ እኛ ጅላንፎ እንመስላቸዋለን።ሼም ሊያሲዙን ይሞክራሉ።ሊያሸማቅቁን ይጥራሉ።በቃ እነሱ ብቻ ንቁና በራስመተማን ያላቸው እንደሆኑ ነው የሚያስቡት....

እኔ ዝም ልል እችላላው።ትንሽ ትንሽ ነገር ላወራ እችላለው።ከተመቸኝ ደግሞ በጣም በዝምታ ውስጥ ልዋጥ እችላለው።በተለይ አንዳንድ ጊዜ በራሴ አለም ውስጥ ልጠልቅ እችላለሁ።ግን እኔ ከማስቀምጠው ገደብ ማንም ሰው ሊያልፍ አይችልም።ማንም ከፍም ዝቅም ሊያደርገኝ አይችልም።ሁላችንም የየራሳችን ገደብ አለን።

እንጫወታለን፤እንዝናናለን፤እንሳሳቃለን።ምናልባት ውስጣችን ያለውን ነገር ማወራት ካለብን እናወራለን።ነገር ግን ከዛ ውጪ ዝምትኝነትን ተገን አድርገው ክብርን መጣል ከሚፈልጉ ሰዎች ጋር ንግግር የለንም።የእነሱንም ህግ እናከብራለን፤የእኛንም ህግ ያከብራሉ እንጂ እኔን ብቻ አክብሩ የእናንተን ክብር እርሱት ከሚሉ ጋር ቀጣይነት ያለው ግንኙነት ሊኖረን አይገባም።ስለዚህ ሁላችሁም ከእንደዚህ አይነት ሰዎች የምትርቁበትን መንገድ አሁኑኑ ፈልጉ።ጊዜው በረዘመ ቁጥር በሌሎች ሰዎችም እንድትናቁ ያደርጓችኋል።

✍️ Bemni Alex

📚 @Bemnet_Library

14.5k 0 103 14 218

ዝምድና ባያዛምደን፣ ወዳጅነት ባያጋምደን እንኳን፣ ሰው መሆናችን ብቻ ሁላችንን ዘመድ ያደርገናል፡፡

📓ከማዕዘኑ ወዲህ
📚@Bemnet_Library


በህይወት ውስጥ እጅግ ታላቅ አስተማሪ አለ።እርሱም መሻት/መፈለግ ነው።ማናቸውም አይነት እድገት እንደዚሁም ትምህርት የመሻት ውጤቶች ናቸው።መሻታችን ጥልቅ በሆነ ጊዜ መረዳታችንም የላቀ ይሆናል።ማሰላሰላችን ሲሰፋ መተማመናችንም ጠንካራ ይሆናል።ኒውተን የፖሙ ፍሬ ለምን ወደ ምድር እንደወደቀ ለመገንዘብ መሻቱ ባይኖረው ኑሮ ዓለማችን ምንኛ ባልታደለች ነበር? እርግጥ ነው ሌላው ኒውተን ያገኘው እንደነበር ጥርጥር ባይኖረውም ነገር ግን እንደእርሱ ያለ መሻት ሊኖረው ግን የግድ ነው።

📓ርዕስ፦ራስን የማወቅ ሳይኮሎጂ
✍️ፀሀፊ፦ቃልኪዳን አምባቸው

📚 @Bemnet_Library


ፍቅረኛ አላችሁ?
Опрос
  •   አዎ ለዛውም የደስደስ ያላት/ያለው
  •   የለኝም ግን ቢኖረኝ ደስ ይለኛል።
  •   አሁን ላይ እንዲኖረኝ አልፈልግም።
  •   በእምኒ ተወኝ እስኪ ትዝታዬን አቀስቅሰው
  •   አግብቻለሁ!
2410 голосов

13.3k 0 16 55 138

ራስን ማወቅና መሆን የእውቀቶች ሁሉ መሰረት ነው

"ሶቅራጥስ"

ሰው ማን መሆኑን እስካለወቀ ድረስ ደስተኛ መሆን አይቻለውም

"ፐብሊቢያንስ ሲረስ

ሰው የአመለካከቱ ውጤት ሲሆን ማንነቱም የአመለካከቱ ነፀብራቅ ነው

ዶ/ር ኖርማን ቬሰንት ፔሲ

📚 @Bemnet_Library


አእምሮህ ጠጣር ሳይሆን ፈሳሽ ነው፤ ስለዚህ የፈለግከውን አይነት ቅርጽ ልታስይዘው ትችላለህ፡፡ ለምሳሌ አንድን ዛፍ ተመልክተህ፣ “እግዚአብሔር እኮ እዚህ ነው የሚኖረው፣ እንዴት ደስ ይላል፡፡” ልትል ትችላለህ፡፡ ወይም ዛፉን በፍርሃት መመልከትና “ምናልባት ሰይጣን እዚህ ላይ ይኖር ይሆናል፡፡” ልትል ትችላለህ፡፡ አእምሮ ማቆሚያ የለውም፤ በማንኛውም ጊዜ ማንኛውንም ነገር መሆን ትችላለህ፡፡ እንደ አለመታደል ሆኖ፣ ብዙ ሰዎች ራሳቸውን እንዴት መከራ ውስጥ እንደሚከቱ ተምረዋል፡፡ ያ ትልቅ ችግር ነው፡፡

📓የህይወት ኬሚስትሪ
📚@Bemnet_Library


...ሕዋው ላይ ልረሳው የምፈልገው ጠባሳ ተጋድሟል።በሬን ከፍቼ ከተማ የምወጣው እንደ ፀሀይ እያበራሁ ነው።የኀዘኔን ጥልቀት ለሰዎች ብናገር ሙሾና ምክር እንጂ መቼ ኮከብ ያወርዱልኛል?.....

📓ርዕስ፦ትዝታሽን ለእኔ|ትዝታዬ ለአንቺ
✍️ደራሲ፦እሱባለው አበራ

📚 @Bemnet_Library


የተለያዩ የፋሽን ልብሶችና ጫማዎች እንዲሁም ሌሎች ምርጥ ምርጥ ዕቃዎችን ቁጥር አንድ ተመራጭ ከሆኑት Aliexpress፤Shein፤Alibaba ትእዛዞችን እየተቀበልን ስለሆነ የምትፈልጓቸውን ዕቃዎች፦


ቦርሳ 🎒👜💼🧳

ጫማ 👟👞👡👠🥿

የወንዶች ልብስ 🥼👔🩳

የሴቶች ልብስ 👗🩱🥻

የትራስ ጨረቅና ብርድልብስ 🌫🌫

የስፖርት ቱታዎች🩳


እንዲሁም ማንኛውም የምትፈልጉትን እቃ ዌብሳይትና አፖቻቸው ላይ በመምረጥ ፎቶ በማንሳት ለእኛ መላክ ትችላላችሁ፤ከዛ ከ15 እስከ 20ቀን ውስጥ እናስመጣለን።

ለማዘዝ @Bemni_Alex

ቻናል፦👇👇

@BemnetMarket
@BemnetMarket
                          


በራስ መተማመን ሲባል እኔ ጸሐፊ እሆናለሁ፣ እኔ እሯጭ እሆናለሁ ብሎ የማውራት አይደለም። ይልቁንም ጸሐፊ ለመሆን ንባብን መደጋገም፣አሸናፊ ሯጭ ለመሆን ዘወትር
ልምምድ ማድረግ ለዛ ግብ ትናንሽ ልምዶችን ማዳበር ይጠይቃል።

📚@Bemnet_Library


ሰዎች ለማፍቀር ይሞክራሉ፤ ለመፀለይ ይሞክራሉ፤ ለመመሰጥ ይሞክራሉ። ስለሚሞክሩም ማፍቀር አይችሉም፡፡ ለማፍቀር እየሞከራችሁ እንዴት ማፍቀር ትችላላችሁ?ለመፀለይ የምትሞክሩ ከሆነ መፀለይ አትችሉም፡፡ ምክንያቱም ሀይላችሁ በመሞከር ላይ ያልቃልና፡፡ ለመመሰጥ የሚሞክርስ እንዴት መመሰጥ ይችላል? እናንተ በመሞከር አባዜ ውስጥ ናችሁ፡፡ የዜን መምህር መሀረቡን ሲጥል ተማሪው እዚያ ነበር፡፡ መምህሩ ለተማሪው እንዲህ አለው፡- “ለማንሳት ሞክርና ስጠኝ፡፡ አለው!”

ተማሪውም ወዲያውኑ መሀረቡን ከመሬት በማንሳት ለመምህሩ ሰጠው፡፡ ሆኖም መምህሩ መሀረቡን በድጋሚ መሬት ላይ በመጣል ለተማሪው እንዲህ አለው፡- “ያልኩህ ለማንሳት ሞክር ነው! ይህም ድርጊት ለስድስት ጊዜያት ያህል ቀጠለ፡፡ ተማሪውም የመምህሩ ንግግርና ድርጊት እንቆቅልሽ ሆነበት፡፡ ምን ማለቱ ይሆን ብሎ አሰበ፡፡ ወዲያውኑ ግን አንድ ሀሳብ ብልጭ አለለት፡፡ “መምህሩ ያለው ለማንሳት ሞክር ነው!” እናስ “እንዴት መሞከር እችላለሁ? አነሳሁትም አላነሳሁትም እንዴት መሞከር እችላለሁ?” ብሎ አለ፡፡

መምህሩም እንዲህ አለ፡- “ለዚህ ነው ለሶስት አመታት ለመመሰጥ ስትሞክር የነበረው፡፡ ተመሰጥክ አልተመሰጥክ እንዴት አድርገህ መሞከር ትችላለህ?” መሞከር መሳሪያ ነው፡፡ መሞከር ሽወዳ ነው፡፡ አንድን ነገር ማድረግ ሳትፈልግ ስትቀር ትሞክራለህ፡፡ አንድን ነገር ማድረግ ስትፈልግ ግን ታደርገዋለህ፡፡

📓የመኖር ጥበብ
📚@Bemnet_Library

12.3k 0 103 4 183
Показано 20 последних публикаций.