🌏✨በመኪና አሽከርካሪነት ወደ ውጪ ሃገራት መሰማራት ለምትፈልጉ በሙሉ!
በሥራና ክህሎት ሚኒስትር የውጪ ሃገር ሥራ ስምሪት ዜጎች በህጋዊ መንገድ ደህንነታቸው መብታቸውና ጥቅማቸው ተከብሮ መሠማራት የሚችሉበት ዕድል እንደተመቻቸ ይታወቃል።
በዚህ የውጪ ሃገር ሥራ ስምሪት በመኪና አሽከርካሪነት ሞያ መጓዝ ለምትፈልጉ ከተለያዩ ሃገራት በርካታ የሰው ሃይል ጥያቄ እየቀረበ ሲሆን በሞያው የሃገር ውስጥ መንጃ ፈቃድ ኖሯችሁ ኢንተርናሽናል ለማድረግ በኢትዮጲያ ሥራ ገበያ መረጃ ስርዓት ተመዝግባችሁ የባዮሜትሪክስ አሻራ ከሰጣችሁ በኋላ የአጭር ቀን ስልጠና መውሰድ ይጠበቅባችኋል። ሥልጠናችሁንም ስታጠናቅቁ የብቃት ማረጋገጫ ምዘና ወስዳችሁ በውጪ ሃገር የሥራ ስምሪት ዕድል መጠቀም የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።
የሥልጠና ቦታ Selam Technical and Vocational School ውስጥ ባለው ምሳሌ የመንጃ ፈቃድ ማሰልጠኛ
አድራሻ:- ኮተቤ ሃና ማርያም አካባቢ
በተጨማሪም በኢትዮ-ቻይና የተሽከርካሪ ማሰልጠኛ ተቋም
አድራሻ:- ላምበረት
ሥልጠናችሁን ካጠናቀቃችሁ በኋላ ለህጋዊ ኤጀንሲዎች ምደባ ስለሚደረግ ወደ ተመደባችሁበት ኤጀንሲ በመሄድ ፕሮሰስ መጀመር ትችላላችሁ።
የሥራ ባለቤት እርስዎ ነዎት!
ይመዝገቡ :
https://lmis.gov.ethttps://youtu.be/oZVjz3WFWCo?si=pDQRk974TyDrcdRP