እሱን ነበር የፈለኩት........አንድ እሱን ብቻ
እንዲወደኝ፣እንዲያፈቅረኝ፣እንዲመኘኝ አልጠበቅኩም።በየትኛውም ነገር ላይ እንዲያገን እንዲጎዳ አልፈለኩም
ሳቀርበው ስወደው ላፈቅረው ስነሳ ከቶም ከሱ አንዳች ምላሽ አልጠበቅኩም።
"እወድሃለሁ" አልኩት አላንገራገረም "እሺ"ነበር ያለኝ።
"ታስፈልገኛለህ"ስለው መጥቀሙን ያለምንም ስስት አሳይቶኛል።
መውደዴ ብሶ ድንገት ተሳስቼ ማፍቀሬን ባሳየው የልብ ምኞት አይቀር እሱም ቢያፈቅረኝ የሚል ትልቅ ምኞት መሰነቅ አይቀርም።
አልሆነም እንደማይሆንም አውቅ ነበር።በሱ በኩል አንዳች ስሜት እንደሌለ በስንት ጉዳጉድ ታጥሮ አንዳች እስርቤት ውስጥ መኖሩን አውቄ ሁሉን ልተውለት ከቶ ላላነሳ ራሴን አሳምኜ.......ልክ እንደ ጓደኛ የራስ ሰው እንደምንለው የሱን ደህንነት አስቀደምኩኝ
አንድ ነገር አውቃለሁ.....
ስሜቶቻችን ከእኛ በታች መሆናቸውን.....ምንም ከሱ አልጠበቅኩም ምክንያቱም ታሳሪ ምንም አያደርግምና፤መልስም አልጠበቅኩም ግን ሁሉም ቀርቶ ጓ-ደኝነቱ ይቅር የሚል አንዳች ሀይል ሀሳቤን መና አስቀረው.....አውላላ ሜዳ ላይ እንደ ጉድ ተሰጣሁ.........ብቻ ስሙኝማ የሱ ነገር ይለያል አንዳች ተዐምር ተፈጥሮ ደህንነቱ ቢመለስ ለኔ ደስታዬ ነው ምንም አልጎደለኝ እሱ ስለነበር አሁን ግን መሄዱን ስረዳ መጉደሌን አመንኩኝ
.......መጉደል.......
.......ይከታል ከገደል........ ✨ቃል ነበርኩኝ✨
🙌ሰናይ ቀን ተመኘሁ🙌
@betagitim@zemenenbegetem