_ወሊድን በተመለከተ__
ልጅን መውለድ ብዙ ተባዙ ያለውን አምላካዊ ቃል መፈጸም ስለሆነ ትልቅ ክብር ነው። ወላድ እናቶቻችንም ክቡራት ናቸው። ባለማወቅ (ላለዝበው ብየ ነው እንጂ በድንቁርና ልል ነበር) የወለደች ሴት እስላም ናት፣ ርኵስ ናት የሚሉ ሰዎች ከእውቀት ጋር የተጣሉ ሰዎች ናቸው። ወንድ ከወለደች በኋላ ለ40 ቀን ቤተክርስቲያን አትገባም። የማትገባበት ምክንያት ግን እስከዚያ ድረስ ደም ስለሚፈሳት ነው። ደም የሚፈሰው ሰው ደግሞ ቤተክርስቲያን አይገባም። ይህ ለወላድ ሴት ብቻ የተወሰነ ሳይሆን ወንዱም ቢሆን እንቅፋት መትቶት አካሉ ቢደማ ቤተክርስቲያን አይገባም። አፍንጫው ቢነስር ብቻ ከመድማት ወገን በአንዱ ቢደማ ቤተክርስቲያን አይገባም። ርስሐት (ዝንየት) ካገኘውም 24 ሰዓት ጠብቆ ይገባል እንጂ ከዚያ በፊት እንዲገባ ሥርዐት አልተሠራም። ሴት ልጅ የወለደች እናትም እስከ 80 ቀን ቤተክርስቲያን አትገባም። ይኽውም ደም ስለሚፈሳት ነው። በወር አበባ ያለች ሴትም ቤተክርስቲያን አትገባም ይኽም ደም ስለሚፈሳት ነው። ቤተክርስቲያን መፍሰስ ያለበት የክርስቶስ ደም ብቻ ነው። የፍጡር ደም መፍሰስ የለበትም። ይህ ሥርዐት የተሠራውም ለቤተክርስቲያን ክብር ተብሎ እንጂ የወር አበባ፣ በወሊድ ጊዜ የሚፈሰው ደም ርኵሰት ሆኖ አይደለም። ክቡራት ወላድ እናቶቻችንን እንደ ርኵስ ማሰብ የርኵስ ሰዎች እሳቤ ነው። እናቶችን ልጅ ስለወለዱ እናከብራቸዋለን እንጂ ርኵስ ናቸው አንልም። የወለዱ እናቶችን በወለዱ ቀን በሌላ ቀንም ሄዶ "እንኳን ማርያም ማረችሽ" ማለት የክርስቲያን ሥራ ነው። ከቤተክርስቲያን መግባት፣ ሥጋውን ደሙን ከመቀበል አይከለክልም።
።
።
ፍትሐ ነገሥት አንቀጸ ቀሳውስት ላይ ቁጥር ፪፻፴፯ (237) ላይ፣ በደስ ፰ (8)፣ አቡሊዲስ በጻፈው መጽሐፍ በስምንተኛው አንቀጽ ቄስ ሚስቱ ብትወልድ ከአገልግሎት አይከልከል ይላል። ቀሲስ ሶበ ወለደት ብእሲቱ ኢይትከላእ እንዲል። አንዳንድ ቦታ ላይ ገጠር የወለደችን ሴት በአሥረኛው ቀን ጸበል የሚረጩ ቄሶች አሉ። ጸበል በረከት ያለው ስለሆነ መረጨቷ ጉዳት የለውም። ነገር ግን ርኵሰቷን ስለሚያስለቅቅ ተብሎ ከሆነ የሚረጨው ነውር ነው። መጀመሪያም ልጅ በመውለዷ ርኵስት አልሆነችምና። ይሄ ከትምህርቷ ገፋ ያለማድረግ ችግር ነው። ጸበል ተረጨችም አልተረጨችም ምንም ዓይነት ነውር የለባትም። ያ ብቻ ሳይሆን በማየ ገቦ (ሕጻኑ በተጠመቀበት ማይ) እናቲቱንና ክርስትና የሚያነሱ ሰዎችን መርጨት ትልቅ ውንብድና ነው። ማየ ገቦ ልጅነት የሚያሰጥ ስለሆነ ሕጻኑ ብቻ ይጠመቅበታል እንጂ ለሌላ ሰው አይረጭም።
።
ስለ አዋላጆች (መወልዳት) በፍትሐ ነገሥት ተነግሯል። ይኽውም ሴት ያዋለዱ አዋላጆች እስከ ፵ ቀን ቤተክርስቲያን እንዳይገቡ፣ ወንድ ያዋለዱ አዋላጆች ደግሞ እስከ ፳ ቀን እንዳይገቡ ሥርዓት ተሠርቷል። በዘመናችን ደግሞ አዋላጅ ነርሶች (Midwives) አሉ። ሥራቸው ማዋለድ ነው። ለእነርሱ ዘለዓለም ቤተክርስቲያን አይግቡ የሚል ትምህርት የለንም። ሥርዓቱ ሲሠራ በነበረው ዘመን የነበሩ አዋላጆች እና አሁን ያሉ አዋላጆች ሚናቸው የተለያየ ስለሆነ ለአሁን ዘመን አዋላጆች የሚመጥን ሥርዓት እንዲሠራልን በዚሁ አጋጣሚ ለቅዱስ ሲኖዶስ የምናሳስበው ይሆናል ማለት ነው። ምክንያቱም የአሁን አዋላጆች ያለምንም ደም ንክኪ ሊያዋልዱ የሚችሉበት መንገድ ስለሚኖርና ጥንቃቄያቸው ከቀድሞው ከፍ ያለ ስለሆነ ነው። ሕክምናን በተመለከተ የቀዶ ሕክምና ሐኪሞችን ሁሉ ያካተተ ሥርዓት ቢሠራ መልካም ነው።
።
ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን።