𝙱𝚒𝚜𝚛𝚊𝚝 𝚐𝚛𝚊𝚙𝚑𝚒𝚌𝚜


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Дизайн


ትባረኩበታላችሁ 🥰🥰🥰
For any feedback @bisrsh50

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Дизайн
Статистика
Фильтр публикаций


በጣም አስቸኳይ የሚሸጥ #የTiktok  አካውንት

#18.6K Followers ያለውን እጅግ በተመጣጣኝ ዋጋ መግዛት የሚፈልግ @samazion_cj አናግሩኝ !


Day 10

ድነት የተጠናቀቀ ሥራ ስለኾነ ምንም ነገር ልንጨምርበት፣ ልንቀንስበት ወይም ልናሻሽለው አይገባም፡፡ የመዳኛው መንገድ አንድ ብቻ ነው፤ ርሱም በተጠናቀቀው የጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ሥራ ማመን ብቻ። ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ “ተፈጸመ” ብሎ ጮኸ። የጥል ግድግዳው ፈርሷል፤ ወደ እግዚአብሔር መቅረብ ተችሏል፤ የዘላለምን ሕይወት በእምነት መቀበል ተችሏል፤ የኀጢአትና የሞት ፍርሃት ተወግዷል። ይህ ኹሉ በዓለም መድኀኒት በእግዚአብሔር ልጅ በኢየሱስ ክርስቶስ ኾኗል። በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን ዐዲስ ሕይወትን ይቀበሉ።
ልናማክሮ እና ልንረዳዎ ዝግጁ ነን!

#ኑ_ወደ_ኢየሱስ 
#ያ_መሲሕ
#ኢየሱስ_የእግዚአብሔር_ልጅ

“ኢየሱስም ሖምጣጤውን ከተቀበለ በኋላ፣ “ተፈጸመ” አለ፤ ራሱን አዘንብሎ፣ መንፈሱን አሳልፎ ሰጠ” (ዮሐንስ 19፥30)።

Follow Meskerem Getu on:
Facebook | Instagram | TikTok | Threads

Follow Tesfa on:
Instagram | Facebook | Telegram | TikTok | Youtube | Threads | Pinterest


Day 9

የዳዊት ቤት ሰዎች ኹሉ ወደ ቤተልሔም ስለተጓዙ ቤተልሔም የተሠኘችው አነስተኛ ከተማ የነበሯት የእንግዳ ማረፍያ ስፍራዎች በሙሉ በእንግዶች ተይዘው ነበር፡፡ ለትንሽ ጊዜ እንኳ ማረፊያ የሚኾን ስፍራ አልነበረም፡፡ ማርያም ልጇን ልትወልድ የምትችልበት ብቸኛ ስፍራ የከብቶች በረት ነበር፡፡ በከተማዪቱ ውስጥ ለታላቁ ንጉሥ፣ ለዓለም መድኀኒት መወለጃ የሚኾን ስፍራ ጠፋ።
ዛሬስ?

ሰው ለኾነው የእግዚአብሔር ልጅ፦ ለርሱ የሚኾን ስፍራ አላችሁን? ኀጢአታችኹን ኹሉ ይቅር ማለት ለሚችለው ለመድኀኔ ዓለም የሚኾን ቦታ አላችሁን? ከአስከፊ ጉድጓድ አዘቅትና ረግረግ ማጥ ውስጥ ማውጣት ለሚችለው የዓለም ጌታ፥ ለርሱ የሚኾን ስፍራ አላችሁን? አንዴ ከመጣ ጥሏችሁ ለማይኼደው ይልቁን ልባችሁን በሰማያዊ ደስታ ለሚሞላትና እስከ ፍጻሜው ዐብሯችሁ ለሚዘልቀው አፍቃሪ አምላክ የሚኾን ስፍራ አላችሁን?

ወንድሜና እኅቴ ሆይ ለንጉሡ ኤየሱስ የሚኾን ስፍራ በልባችሁ ውስጥ ካለ ዛሬ በነፍሳችሁ ውስጥ እንዲወለድ
ፍቀዱለት፡፡ “ዛሬ ድምጹን ብትሰሙ ፤ በምድረበዳ በፈተና ቀን እንዳደረጋችሁት ፤ ልባችሁን አታደንድኑ” (ዕብራውያን 3፥7-8)፤ “ዕንኾ፤ ትክክለኛው ሰዓት አኹን ነው የመዳንም ቀን አኹን ነው” (2 ቆሮንቶስ 6፥2)
በልባችሁ በረት እንዲወለድ ለኢየሱስ ስፍራ ስጡት! አሁኑኑ ለኢየሱስ ስፍራ ስጡት!
ልናማክሮ እና ልንረዳዎ ዝግጁ ነን!

#ኑ_ወደ_ኢየሱስ 
#ያ_መሲሕ
#ኢየሱስ_የእግዚአብሔር_ልጅ

Follow Meskerem Getu on:
Facebook | Instagram | TikTok | Threads

Follow Tesfa on:
Instagram | Facebook | Telegram | TikTok | Youtube | Threads | Pinterest


Day 8

ከምድራዊ ግዛት በላይ የሆነው እና እሱን የሚመስል ንጉስ የሌለው ታላቁ የይሁዳ ንጉስ ቀድሞ እንደተለመደው መንግስታዊ አመጣጥ በሃይል እና በጦር ታጅቦ ሳይሆን በታላቅ ትህትና እና በዝቅታ ፣ ያ መሲሕ ባልተጠበቀ መንገድ በበረት ተወለደ ። የሰላሙ ትሁት ንጉስ በተአምራዊ መንገድ ግርግም በጨርቅ የተጠቀለለ ህፃን ሆኖ መምጣቱ የእግዚአብሔርን ትህትና እና ወደ ሰው ልጅ ሁኔታ እጅግ በሚያስገርም መንገድ ለመቅረብ መምረጡን የሚያሳይ ነው። እግዚአብሔር የገባውን የተስፋ ቃል ፍጻሜ ለማቀናጀት ይህን ኢምንት የሚመስለውን ክስተት መረጠ ። የእግዚአብሔር የመቤዠት እቅድ እንዲደርሶዎ ፣ የመሲሑ መወለድ ከርሶ ሕይዎት ጋር ያለውን ቀጥኛ ግንኙነት ችላ አይበሉ ። ስለአእርሶ የመጣውን የሰላም መልእክተኛ ኢየሱስን አሁኑኑ በማመን ይዳኑ

#ኑ_ወደ_ኢየሱስ 
#ያ_መሲሕ
#ኢየሱስ_የእግዚአብሔር_ልጅ

የበኵር ልጅዋንም ወለደች፥ በመጠቅለያም ጠቀለለችው፤ በእንግዶችም ማደሪያ ስፍራ ስላልነበራቸው በግርግም አስተኛችው።(ሉቃስ 2፡7)

Follow Meskerem Getu on:
Facebook | Instagram | TikTok | Threads

Follow Tesfa on:
Instagram | Facebook | Telegram | TikTok | Youtube | Threads | Pinterest


የዳንበትን ወንጌል በማሰራጨት ይህንን challenge እንቀላቀል

daily ሚለቀቁ photo instagram, facebook... or telegram ላይ story ማድረግ አይረሳ

ተባረኩ!!


Day 7

ሰዎች የቤት፣ የተሽከርካሪ፣ የሕይወት፣ ወዘተ. . . ዋስትና በመግዛት ለሚደርስባቸው አደጋ ተመጣጣኝ ካሳ ለማግኘት ይሞክራሉ። በተለይ የሕይወት ዋስትና የገዙ ሰዎች አደጋ አጋጥሟቸው ሕይወታቸው ሲያልፍ፥ ይህ የገዙት ዋስትና ከሞት በኋላ ሊያግዛቸው ስለማይችል፥ ካሳው ለቤተሰባቸው ይከፈላል። ከዚህ የተሻለ የሕይወት ዋስትና እንዳለ ያውቁ ኖሯል? ከሞት ስለሚሻገረውና ለዘላለም ዘላቂ ስለሆነው ዋስትና ሰምተዋል? ይህንን ዋስትና የያዘ ሰው ለዘላለም ከአምላኩ ጋር በደስታ መኖር ይችላል። ይህ የሕይወት ዋስትና በከብቶች በረት የተወለደው፣ ፍጹም ሰው፡ ፍጹም አምላክ የኾነው፣ ስለ ሰው ልጆች ኹሉ ኃጢአት በመስቀል ላይ የሞተው፥ በሦስተኛውም ቀን ሞትን ድል አድርጎ የተነሳው፣ ወደ ሰማይ ያረገው፣ ዳግመኛም ተመልሶ የሚመጣው ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ዘላለማዊ የሕይወት ዋስትና የሚገኘው ርሱን በማመን ብቻ ነው። ሌሎች ዋስትናዎች በሙሉ እስከሞት ድረስ ተጎጂውን ለማገዝ ይጥራሉ። ኢየሱስ ክርስቶስን በማመን የሚገኘው ዘላለማዊ ዋስትና ግን አሁንም ከሞት በኋላም ለዘላለም አስተማማኝ ነው። ዛሬውኑ ፈጥነው ይህንን ዋስትና ይያዙ። ልናማክሮ እና ልንረዳዎ ዝግጁ ነን!

#ኑ_ወደ_ኢየሱስ
#ያ_መሲሕ
#ኢየሱስ_የእግዚአብሔር_ልጅ

“እውነት፥ እውነት እላችኋለሁ፤ ቃሌን የሚሰማና በላከኝም የሚያምን የዘለዓለም ሕይወት አለው፤ እርሱ ከሞት ወደ ሕይወት የተሻገረ ስለ ሆነ አይፈረድበትም።” (የዮሐንስ ወንጌል 5:24)

Follow Meskerem Getu on:
Facebook | Instagram | TikTok | Threads

Follow Tesfa on:
Instagram | Facebook | Telegram | TikTok | Youtube | Threads | Pinterest


ነቃ ነቃ ኧረ active members የታላቹ react ይደረግ ካርድ ልንለቅ ነው❤




Day 6

በምድራችን ላይ ሰዎች በተለያዩ በሽታዎች ይያዛሉ። ብዙዎቹ በሽታዎች በሐኪም እርዳታ እና በመድኃኒት ሊድኑ የሚችሉ ቢኾኑም፥ አንዳንድ እስካሁን መድኃኒት ያልተገኘላቸው በሽታዎች አሉ። እነዚህ በሽታዎች “ገዳይ በሽታዎች” ይባላሉ። ነገር ግን ከእነዚህ ሁሉ በሽታዎች የሚበልጥ እና የሰው ልጆችን ሁሉ ያጠቃ አንድ ገዳይ በሽታ አለ። ይህ በሽታ ኃጢአት ይባላል። ገዳይነቱም ለዘለዓለም ነው። በሰው ልጆች ታሪክ ውስጥ የዚህን ገዳይ በሽታ መድኃኒት ያገኝ ሐኪም የለም። ነገር ግን ከዛሬ ሁለት ሺህ ዓመታት በፊት ለኃጢአት በሽታ መድኃኒቱ ከሰማይ ተገኝቷል። ይህ መድኃኒት ኢየሱስ ክርስቶስ ይባላል። ከድንግል ማርያም የተወለደው ያ መሲሕ ብቸኛው የኃጢአት መድኃኒት ነው። በርሱ ያመኑ ሁሉ ከዚህ በሽታ ይድናሉ። እግዚአብሔር ዛሬም “በዚህ መድኃኒት በማመን ከኃጢአታችሁ ዳኑ” በማለት ለሰዎች ጥሪ ያቀርባል። ርስዎም በዚህ መድኃኒት አምነው እንዲድኑ ተጋብዘዋል። ልናማክሮ እና ልንረዳዎ ዝግጁ ነን!

#ኑ_ወደ_ኢየሱስ
#ያ_መሲሕ
#ኢየሱስ_የእግዚአብሔር_ልጅ

“እነሆ! ዛሬ በዳዊት ከተማ አዳኝ ተወልዶላችኋል፤ እርሱም ጌታ ክርስቶስ ነው።” (የሉቃስ ወንጌል 2:11)

Follow Meskerem Getu on:
Facebook | Instagram | TikTok | Threads

Follow Tesfa on:
Instagram | Facebook | Telegram | TikTok | Youtube | Threads | Pinterest


Day 5

እነዚያ ጠቢባን በኮከብ እየተመሩ ሲመጡ ሕፃኑን ንጉሥ ተራ ስፍራ ግርግም ውስጥ እንጂ ቤተ መንግሥት ውስጥ አላገኙትም። ንግሥናውንና ማንነቱን አምነው በሕፃኑ ፊት ሰገዱለት። ነገር ግን ይህ ትእይንት ስለ አምልኮ ብቻ አይደለም። ርሱ ከተወለደ በኋላ ስላለው ጥልቅ ዐላማም እንጂ። በበረት ውስጥ የተወለደው ያ መሲሕ፥ በሰው ልጆችና በእግዚአብሔር መካከል ድልድይ ኾኖ የሚጫወተው ሚና እጅግ ታላቅ ነው። ለእኛ ሲል የታገሠውን ሞት አስታውሱ። ሕይወቱ ከልደት እስከ ሞቱ ድረስ የኀጢአትንና የሞትን ኀይል ለማሸነፍ፣ ለሚያምኑ ኹሉ የዘላለም ጥያቄ መልስ ኾኖ የተገኘ ብቸኛ መፍትሒ ነው። ከእኛ ፈጽሞ ሩቅ የኾነው አምላክ እንደኛ ኾኖ በመካከላችን ተገኘ ። በርሱ የሚያምኑ የሰው ልጆች ኹሉ አምላክ ወደሚኖርበት ከተማ መድረሻ ብቸኛው መግቢያ በር ኾኖልን መጥቷል። ዛሬም ርሱን እንዲያገኙትና ሕይወትዎን ለርሱ በመስጠት ውስጥ ያለውን ጥልቅ ደስታ እንዲለማመዱ ተጋብዘዋል። ርስዎን ፍለጋ ከሰማይ ድረስ ወደመጣው አዳኝ አኹኑኑ በመምጣት ከዘላለም ቅጣት ይትረፉ። ልናማክሮ እና ልንረዳዎ ዝግጁ ነን!

#ኑ_ወደ_ኢየሱስ 
#ያ_መሲሕ
#ኢየሱስ_የእግዚአብሔር_ልጅ

“ ወደ ቤትም ገብተው ሕፃኑን ከእናቱ ከማርያም ጋራ አዩት ወድቀውም ሰገዱለት ሣጥኖቻቸውንም ከፍተው እጅ መንሻ ወርቅና እጣን ከርቤም አቀረቡለት” (ማቴዎስ 2፥11 )
Follow Meskerem Getu on:
Facebook | Instagram | TikTok | Threads

Follow Tesfa on:
Instagram | Facebook | Telegram | TikTok | Youtube | Threads | Pinterest


D1
D2
D3
D4


#ያ_መሲሕ በሚል እርዕስ የተዘጋጀውን የdigital outreach, Blood Donation እና street outreach ይህን ፕሮፋይል ፒክቸር በመቀየር ቻሌንጁን ይቀላቀሉን!

#Meskeremgetu


Репост из: 𝙱𝚒𝚜𝚛𝚊𝚝 𝚐𝚛𝚊𝚙𝚑𝚒𝚌𝚜
1️⃣🔠🔠🔠🔠🅱️➕5️⃣0️⃣
የውድድር አይነት

🔹ግጥም
መስፈርት

🔻15-25 ስንኝ የያዘ
🔹ስለ ኢየሱስ መወለድ የሚያወራ
🔺ይህን ቻናል join ማረግ
ነጥብ አሰጣጥ

🔻ብዙ like ያገኘ(50%)
🔺ሙያዊ እይታ(ጭብጥ, ቀለም,... 50%)
እስከ መቼ መሳተፍ ይቻላል

እስከ ቀጣይ ሳምንት(ታህሳስ 23)

🔻ግጥሞን ከዚ post ስር ባለው comment መስጫ ላይ ያስቀምጡ

መሳተፍ ለሚችሉ ወዳጆቾ ያጋሩ🔻🔻

@bisrat_graphics
@bisrat_graphics


🚩Verse
🚩🚩🚩🚩🚩🚩🚩🚩🚩
🌐🌐🌐🌐

ኤፌሶን 4:17-32
(አ.መ.ትርጉም)

share for freinds🌐
join us🔸
@bisrat_graphics
@bisrat_graphics


1️⃣🔠🔠🔠🔠🅱️➕5️⃣0️⃣
የውድድር አይነት

🔹ግጥም
መስፈርት

🔻15-25 ስንኝ የያዘ
🔹ስለ ኢየሱስ መወለድ የሚያወራ
🔺ይህን ቻናል join ማረግ
ነጥብ አሰጣጥ

🔻ብዙ like ያገኘ(50%)
🔺ሙያዊ እይታ(ጭብጥ, ቀለም,... 50%)
እስከ መቼ መሳተፍ ይቻላል

እስከ ቀጣይ ሳምንት(ታህሳስ 23)

🔻ግጥሞን ከዚ post ስር ባለው comment መስጫ ላይ ያስቀምጡ

መሳተፍ ለሚችሉ ወዳጆቾ ያጋሩ🔻🔻

@bisrat_graphics
@bisrat_graphics




ሰዎችን ከላይ አይቼ ስገምት ምን ገጠመኝ ???
ይሄን ተጋበዙልኝ😁😁
ፈርጠም ፈርጠም ያለ ሎጋ ነው ቁመቱ
ትንሽ ብትጠጉት ያስብላል አቤቱ
ከላይ አየውና እሱን ስገምተው
ይህን ውበት ሰቶት አይቻልም ጉራው
ብሩሹን አንስቶ ሲስለው የውስጡን
እጅጉን ያስንቃል ከላይ ሚታየውን
ካልኩት ተቃራኒ ሆኖ ባገኘውስ
እሱ ሰው መሆኑን ገልጦ ቢያሳየኝስ
አወይ የኔ ነገር የውስጡንሳላውቅ ከቶ ሳልረዳው
ሰውነቱን አየው ብዬ ብገምተው
በግምቴ አጣው


እኔ ብቻ ነኝ 😳


መንፈሳዊ
🔺ግጥም
🔻ወግ
😃ትረካ
🔻ድርሰት (ልብወለድ ወይም ኢ-ልብወለድ)

ይቻላል😀


🔊🔊🔊
የተለያየ ፀጋና ችሎታ አለኝ ምትሉ⚡️

📚የእግ/ር ቃል በማስተማር

🎵በዝማሬ

📱📱Graphics& photo editing

📱📱Video editing& motion graphics

እንዲሁም በሌሎች ነገሮች admin ሆነው ከኛ ጋር መስራት ምትፈልጉ comment መስጫው ጋር⬇️ "አለው" በሉን❗️

❗️❗️❗️❗️❗️💚


Poster design

If you want poster design for any program dm @bisrsh50

@bisrat_graphics
@bisrat_graphics

Показано 20 последних публикаций.