ከመጽሐፍት ዓለም!


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Книги


Books only!
This channel is created for books sharing To widen your mind and to get books easily We have more than 2000 amharic and english books !
Join and share @Books_worldd
አስተያየት @BooksWorlddd_bot !
@books_worlddd መወያያ ግሩፕ
#share

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Книги
Статистика
Фильтр публикаций


#ስለጤናዎ

የኩላሊት ህመም ምልክቶች

የኩላሊት ህመም ምልክቶች ከሰው ወደ ሰው ይለያያሉ። መሰረታዊ የህመሙ ዓይነት እና እንደ ክብደቱ  የህመሙ ምልክት ይወሰናል። ምልክቶቹ ብዙውን ጊዜ ፣ ግልጽ ያልሆኑ እና አስደንጋጭ ያልሆኑ ናቸው። ስለሆነም በህመሙ የመጀመሪያዎቹ ደረጃዎች ህመም ስለመኖሩ ለመለየት አዳጋች ነው።
የኩላሊት ህመም በአብዛኛውን ጊዜ የሚታዩ ምልክቶች
•  የፊት እብጠት

የፊት ፣ የሆድ እና የእግር እብጠት ብዙ ጊዜ የኩላሊት ህመም ማሳያ ነው። በኩላሊት ህመም ምክንያት የሚከሰት እብጠት አንድ ባህሪይ በመጀመሪያ ከዐይን ሽፋኖቹ በታች የሚስተዋል መሆኑ ነው ፡፡ ይህም በማለዳ በጣም ጎልቶ ይታያል፡፡ ነገር ግን እብጠት የግድ የኩላሊት መጎሳቆልን እንደማያመለክት ልብ ልንለው ይገባል። በተወሰኑ የኩላሊት ህመሞች ውስጥ መደበኛ የኩላሊት ሥራ ቢኖርም እብጠት ይከሰታል (ለምሳሌ ኔፍሮቲክ ሲንድሮም)። ከዚህም ጎን ለጎን መረዳት የሚያስፈልገው ከባድ ህመም ቢከሰትም በአንዳንድ ታካሚዎች ላይ እብጠት ላይታይ እንደሚችል ነው።

•  የምግብ ፍላጎት ማጣት ፣ ማቅለሽለሽ ፣ ማስመለስ
የምግብ ፍላጎት ማጣት ፣ በአፍ ውስጥ ያልተለመደ ጣዕምና የምግብ መመገብ ደካማነት የኩላሊት ችግር ያለባቸው ሰዎች የሚያጋጥማቸው የተለመዱ ችግሮች ናቸው። የከፋ የኩላሊት ድክመት በሚኖርበት ጊዜ የማቅለሽለሽ ፣ ማስመልስ እና የአእምሮ ህመም የሚያስከትሉ መርዛማ ንጥረነገሮች መጠን እየጨመረ ይሄዳል።

•  ከፍተኛ የደም ግፊት

የኩላሊት ችግር ያለባቸው ታካሚዎች ብዙውን ጊዜ የደም ግፊት ይኖራቸዋል። የደም ግፊት ችግር በወጣትነት ዕድሜ (ከ 30 ዓመት በታች) ከተገኘ ወይም በምርመራው ወቅት የደም ግፊት በጣም ከፍተኛ ከሆነ ምክንያቱ የኩላሊት በሽታ ሊሆን እንደሚችል መጠርጠር ያስፈልጋል።

•  የደም ማነስ እና ድክመት

ቶሎ መድከም ፣ ማተኮር አለመቻል እና የቆዳ መገርጣት የደም ማነስ ችግር ያለበት ሰው የተለመዱ ምልክቶች ናቸው። አንዳንድ ጊዜ ሥር የሰደደ የኩላሊት መድከም የመጀመሪያ ደረጃዎች ላይ አንድ ሰው የሚያሳያቸው ብቸኛ ምልክቶች ሊሆኑ ይችላሉ። የደም ማነስ ያለበት ሰው በመደበኛ ህክምና በተለምዶ በሚሰጡ መድኃቶች ካልዳነ፣ የኩላሊት ህመም እንዳለበት መጠርጠር ያስፈልጋል።
ከዚህም ተጨማሪ ምልክቶች -ዝቅተኛ የጀርባ ህመም ፣ አጠቃላይ የሰውነት ህመም ፣ እና የእግር ማሳከክ እና ህመም በኩላሊት ህመም ውስጥ ተደጋጋሚ የሚታዩ ምልክቶች ናቸው። በደንብ አለማደግ ፣የቁመት ማጠር እና የግር አጥንት ቀጥ አለማለት በልጆች ላይ የኩላሊት ህመም የሚያሳይ ነው።
የተለመዱ ምልክቶች

1.  በሽንት መጠን መቀነስ ፣ በተለያዩ የኩላሊት ህመሞች ውስጥ በጣም የተለመደ ነው።

2.  ሽንት በሚወገድበት ወቅት የሚያቃጥል ስሜት ፣ በተከታታይ መሽናት (ያልተለመደ ድግግሞሽ) እንዲሁም ደም ወይም መግል በሽንት ውስጥ ማየት የሽንት ቧንቧ ህመም የሚያሳዩ ምልክቶች ናቸው።

3.  የሽንት ፍሰት መዘጋት ሽንትን ለማስተላለፍ ችግር ያስከትላል።

ምንም እንኳን አንድ ሰው ከላይ ከተዘረዘሩት ምልክቶች መካከል የተወሰኑት ሊያሳይ ቢችልም የግድ ሰውዬው በኩላሊት ህመም ተይዟል ማለት ግን አይደለም። ሆኖም እንደዚህ አይነት ምልክቶች ባሉበት ሁኔታ ሀኪምን ማማከር እና የኩላሊት ህመም እና ሌሎች ህመሞች መኖር ወይም አለመኖራቸውን በደም እና በሽንት ናሙና ምርመራዎች ማረጋገጥ የግድ ይላል።

ምንጭ:-- SPHMMC


ማዘን ለኛ ነው ፣በባከነ ደቂቃ በራሳችን ግብን ለምናስቆጥር ፣ በህፃናቱ ሞት ላልደነገጥን ፣
ሞት በእርጅና መስሎን በንስሃ ላልጠበቅን
፣በስፍር እድሜ ለቀለድን፣
ነግ ለኔ ላላልን፣ሳንኖር ለሞትን፣
ሳይነጋ ለመሸብን፣
ብልጭልጩ እያታለለ ያጎደለን፣
ጠብ በሚል ስኳር፣እንደ በግ በአሞሌ ለተነዳን፣
ለኛ ነዉ ማዘን:-ሞት አፋፍ ላይ
ለምንጨፍር
ከእድሜ ቁጥር ላልተማርን
ክንደ ብርቱን እያየነዉ ሞት ሲነጥቀዉ:
ባለሀብቱን በገንዘቡ መችአፈረዉ:ዘረብዙን ከሰዉ መንጋ ሲነጥለዉ:ታዋቂዉን ስለ እዉቅናዉ አዋቂዉን ስለ እዉቀቱ መቼ ተወዉ:ባለ ስልጣን ለስልጣኑ አትለወጥ ሞት ከቀኑ
#ማልቀስ ለራስ ነዉ : ከዚህ ሁሉ ከአለም እዉነት ላልተማረ #ማዘን ለራስ ነዉ:ለማይቀር ሞት ተዘጋጅቶ ላልጠበቀ.....
                      ነ
                      ብ
                       ስ
           ይ ማ ር...
         
                          ለነ ብ ሴ 😢


#ሼር #share
@Books_worldd




Atomic Habits
Author - James Clear
Published Date - 2018
Page - 290
Audio Length - 05:35:19

@books_worldd




ኦሮማይ - Oromay (በዓሉ ግርማ).pdf
9.3Мб
ኦሮማይ
ድርሰት - በአሉ ግርማ
የመጀመሪያ ዕትም - ፲፱፻፸፭ 1975 ዓ.ም
የገፅ ብዛት - 375
@books_worldd

64k 0 469 151

ዶክተር ዳዊት አሰፋ _የአእምሮ ሐኪም ናቸው_የአገር ውስጥ መፈናቀል ጦርነት መደፈር ወዘተ የፈጠረው ማሕበራዊ ድባቴ ይታከም ይሆን ?

#የልጆቻችን_ኢትዮጲያ!


ያዲሱ ዘመን አስተምሕሮት በአነቃቂዎች አንድምታና የመንግት ተቋማዊ አሰራር _በዶክተር ኤርሲዶና በኢንጅነር ጌታሁን ሔራሞ

@books_wOrldd #ሼር


የታላላቅ_ሰዎች_እውነተኛ_የፍቅር_ታሪክ_@OLDBOOKSPDF.pdf
15.6Мб
የፍቅር ጀርባው @OLDBOOKSPDF.pdf
58.1Мб
አንድ_ሺህ_አንድ_ሌሊት_ቅፅ_2_@OLDBOOKSPDF.pdf
19.7Мб
የታላላቅ ሰዎች እውነተኛ የፍቅር ታሪክ
ድርሰት - Unknown
ትረጉም - ሰለሞን ሀይለማርያም
ይዘት - ታሪክ
የመጀመሪያ ዕትም - 1990 ዓ.ም
የገፅ ብዛት - 173
@books_worldd #ሼር


ሰምና ወርቁ ተሰማ እሸቴ @OLDBOOKSPDF.pdf
15.3Мб
ሰምና ወርቁ ተሰማ እሸቴ
ድርሰት-ይድነቃቸው ተሰማ
ይዘት-ታሪክ
@books_worldd #ሼር




ኪም ኢል ሱንግ @OLDBOOKSPDF.pdf
38.0Мб
ኪም ኢል ሱንግ
ታላቁ የኮሬያ ህዝብ መሪ ኪም ኢል የሞቱበትን 5ኛ አመት መታሰቢያ በማድረግ!
@books_worldd #ሼር


የጣፈለግ @OLDBOOKSPDF.pdf
40.9Мб
የጣፈለግ
ሲድኒ ሸልደን
ልብወለድ
@books_worldd #ሼር

74k 1 299 2 92



The_art_of_fearless_mindset,_John_Ward_$_@meet_book_storage.pdf
2.1Мб
ያለ አግባብ መፍርሃት ትልቁ እንቅፋታችን ነው ይላል የዚህ መፅሀፍ ፀሀፊ ጆን ዋርድ።

ለመለወጥ እንፈልጋለን አዲስ ነገር ለመሞከር እንፈራለን ።

በይሉኝታ በፍርሃት ብዙ ነገር እናደርጋለን ያ ደግሞ ሲጎዳን ይታያል ይላል ፀሀፊው።

የለውጥ ፍርሃትን እንዴት ማሸነፍ እንደሚቻል እና በመንገድዎ የሚመጡትን ሁሉንም አጋጣሚዎች እንዴት መያዝ እንዳለበዎት መፅሀፉ ያስተምራል።

ለምንድነው የማያውቁትን መፍራት አዳዲስ ጠቃሚ ልምዶችን ለመጋፈጥ ኋላ የሚያፈገፍጎት በማለት መፅሀፉ ይሞግታል ትችት እና መፍትሄ ሀሳቦች ያቀርባል።

@books_worldd #ሼር

72.3k 1 563 1 157









#መደመጥ ያለበት 🤔

ሰይፋ በኢቢኤስ ላይ ልጄን በትራስ አፍና ገደለችና በ3 ኛው ወር ተለቀቀች ስለተባለችው የቤት ሰራተኛ አቃቢ ሕግ የሰጠው ምላሽ  በሀኪም ምርመራ የተደገፈ ማስረጃ ነው ልጆቻችንን ምን ያሕል እናውቃቸዋለን? #የቸገረን_ነገር ከተሰኘ ፕሮግራም የተወሰደ ።

@books_worldd #ሼር

Показано 20 последних публикаций.