Фильтр публикаций






ላፎንቴ "ጓደኛ"
በ1997 ዓ.ም የተሰራ አልበም ነበር:: ይህ አልበም እንዲህ ምርጥ እንዲሆን ያደረገው የተሳተፉበት ድምፃውያን ናቸው ማለት ይቻላል:: በዋና ድምፃዊነት ታደለ ሮባ እና ብርሀኑ ተዘራ ሲሆኑ በተጨማሪ ድምፃዊነት ስለሺ ደምሴ : ኢህሳን አብዱልሰላም : ዘሪቱ ከበደ እና ሳምቮድ ተሳትፈዋል:: ቅንብሩ ላይ ኤልያስ መልካ እና ዳግማዊ አሊ ተራቀውበታል:: ግጥም እና ዜማ ላይ ሙሉ መረጃ ባይኖረንም ስለሺ ደምሴ : ብስራት ጋረደው እንደተሳተፉ መረጃው አለን:: 90ዎቹን ምርጥ ካደረጉ የሙዚቃ አልበሞች ውስጥ አንዱ ይህ ስራ ነበር::

ዛሬ ምሽት ይህን ስራ ለማዳመጥ ዝግጁ ናችሁ ቤተሰቦቻችን? ኮመንት ላይ አሳውቁን ❤️🙌

@cassettemusiq






ፀደኒያ ገብረማርቆስ "ቢሰጠኝ"
በ1996 ዓ.ም ነበር ፀደኒያ ይህን አልበም ለህዝብ ያደረሰችው:: ግጥም እና ዜማ እራሷ ፀደኒያ ገብረማርቆስ እና ይልማ ገብረአብ ሰርተውታል:: ሙሉ አልበም ቅንብር በዳግማዊ አሊ ምርጥ ብቃት ተሰርቷል:: በተለያዩ አፍሪካዊያን ሽልማቶች በእጩነት ደረጃ የደረሰ ምርጥ አልበም ነበር::

ዛሬ ምሽት በካሴት ሙዚቃ የቴሌግራም ቻናል ይጠብቁን ❤️🙌

@cassettemusiq





Показано 8 последних публикаций.