CHRIST TUBE - ETH🇪🇹


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Религия


"ለእኔ ሕይወት ክርስቶስ፥ ሞትም ጥቅም ነውና።"
(ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 1:21)
🔍 የዚህ ቻናል አላማ ኢየሱስ ክርስቶስን መስበክ ነው፡፡
📌 በተጨማሪም
◈ኢየሱስን የሚያስናፍቁ ድንቅ ዝማሬዎች
◈ስለ ክርስቶስ የሚያሳስቡ ዘመን ተሻጋሪ መልክቶች
◈መፅሐፍ ቅዱሳዊ ጥያቄዎችና
◈ተስፋ ሰጪ ሀሳቦች ይቀርብበታል
✍️ ለሀሳብ እና አስተያየት👇
📩 @Christ_Tube_Bot
Creator @Beki_MW

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Религия
Статистика
Фильтр публикаций




“ልበ ንጹሖች ብፁዓን ናቸው፥ _______ና።”  
Опрос
  •   ሀ,“የእግዚአብሔር ልጆች ይባላሉና።”
  •   ለ,“ይማራሉና።”
  •   ሐ,“የእግዚአብሔር ልጆች ይባላሉና።"
  •   መ,"እግዚአብሔርን ያዩታልና።”
  •   ሠ,የለም
129 голосов


“በኃጢአታችን ብንናዘዝ ኃጢአታችንን ይቅር ሊለን ከዓመፃም ሁሉ ሊያነጻን የታመነና ጻድቅ ነው።”  ይህ ክፍል የት ይገኛል?
Опрос
  •   ሀ, 2ኛ ዮሐንስ 1፥9
  •   ለ,ምሳሌ 4፥4
  •   ሐ, 2ኛ ጴጥሮስ 1፥2
  •   መ,1ኛ ዮሐንስ 1፥9
  •   ሠ,የለም
94 голосов


“ስለ ምን ትተኛላችሁ? ወደ ፈተና እንዳትገቡ ተነሥታችሁ ጸልዩ ”
— ሉቃስ 22፥46

 ለእኔ ሕይወት ክርስቶስ ነው
@CHRIST_TUBE
@CHRISTFAMILY


ውድ የ @CHRIST_TUBE ቤተሰቦች እንደምን አመሻችሁ 🙌
እስኪ አንድ ቆንጆ የቴሌግራም ቻናል ልጠቁማችሁ፤@RAPTURE_TUBE ይባላል...

ምፅዓት ተኮር ዜናዎችን እና ለንጥቀት የሚያዘጋጁ አዳዲስና ወቅታዊ ዜናዎችን ያገኙበታል።

@RAPTURE_TUBe

ከወደዱት Share& Join በማድረግ ይተባበሩ።
መልካም ምሽት

ለእኔ ሕይወት ክርስቶስ ነው
SHARE | @CHRIST_TUBE
SHARE | @CHRISTFAMILY


♥♥♥ ከርሞ ጥጃ♥♥♥
♥♥♥ስለ ቃሉ የተሰጡ ተስፋዎች♥♥♥
በ አገልጋይ #አሸናፊ_ከበደ
በእምነት ለሚያነቡት

1,መብራት ነው ይመራናል
፡፡


2,መድሃኒት ነው ይፈውሰናል፡(ምሳ 4፡ 22)


3,ጓደኛ ነው ይመክረናል፡፡ (መዝ 119፡ 24)

4,አጽጂ ነው ያነጻናል፡፡ (መዝ 119፡ 9)


5,መግቦ ያሳድገናል
(1ጼጥ 2፡ 2)
የእግዚአብሔር ቃል አንዲት እናት የወለደችውን ልጅ ጡቷን እያጠባች እንደምታሳድግ እግዚአብሔርም እኛ ማደጋችን በነገር ሁሉ እንዲታወቅ ልክ እንደ እናት ጡት ወተት ሁሉም ነገር ያለውን ተንኮል ግን የሌለበትን የቃሉን ወተት ተመኙ ይላል፡፡የእግዚአብሔር ቃል መግቦ ያሳድጋል፡፡ የእግዚአብሔርን ቃል በዚ ጊዜ በትጋት እያጠናን ማደግ አለብን፡፡ በቃል እውቀት ያላደገው ወጣት ምሳሌ ትዝ ይላቹሀል....✿✿✿ወጣቱ ልጅ እቤት ውስጥ ጥፋት አጠፋና አባቱ ገረፉት ፣እርሳቸው እየገረፋት እያሉ እናቱ ይደርሳሉ በዚህ ጊዜ እርሳቸውም ጥፉቱ ባይገባቸውም ባልና ሚስት አንድ ልብ መሆናቸውን በተግባር ለልጁ ለማሳየት አብረው በመተባበር ገረፉት፡፡ግርፋቱ ካበቃ በኀላ ለምን እንደተቀጣ ካስረዱትና ወደ ፊት በዚ ጥፉት ፋንታ ሌላ በጎ ነገር እንደሚያደርግ አምኖ ከተቀበለ በኀላ ምሳ ሰዓት ነውና ምሳ ተሰጠው፡፡ለምሳውም በጌታ ፊት ሲጸልይ እንዲ አ አለ ፣ እንደ ጠላት የሚላቸው ወላጆቹን ነበር፡፡ በእግዚአብሔር ቃል ብስለት ስላላደገ አልገባውምና፡፡✿✿✿ አለ ያገሬ ሰው፡፡አዎ በእግዚአብሔር ፊት ሲታይ የአብዛኛዎቻችን መንፈሳዊ እድገት ከላይ እንደተጠቀሰው ወጣት ታሪክ ይሆን ይሆናል፡፡ብዙ ዘመን በጌታ ቤት አለን ፣ ጌታን ግን ደስ የሚያሰኘው ብዙ ዘመን በቤቱ መቁጠራችን ብቻ ሳይሆን እንደ ፍቃዱ በቃሉም ማደጋችንና መብሰላችን ነውና፣ የእግዚአብሔር ቃል በሙላት እንዲኖርብን ጌታ ይርዳን፡፡አሜን!
መዝ፡ያምላኬ ቃል አያረጅም የኢየሱስ ቃል አያረጅም
ዘላለም ይኖራል እያበራ ከሚያምኑት ጋራ*4
✿ በጎ ፈቃዳችሁ ከሆነ መልዕክቱን share በማድረግ
ለሌሎች ያካፍሉ፡፡ተባረኩልኝ!!!እወዳችኀለው።

#ተስፋ_አለ
መልካም ቀን !

ለእኔ ሕይወት ክርስቶስ ነው
SHARE | @CHRIST_TUBE
SHARE | @CHRISTFAMILY


እንንቃ! ጌታ ሊመጣ በደጅ ነው።

ምፅአት ተኮር ዜናዎች የሚናቀርብበት ድንቅ ክርስቲያናዊ ቻናል።




~ ~ህብረት

የሀጥያት ጮሮቃ
ባያልኮሰኩሰው
"ሰው " የመሆን ክብሩ
የመንፈስ ልዕልናው
በእግዚአብሔር መልክ ከመፈጠራችን
ከ...ከፍታ ሰገነት
የምንዘግነው ዕሴት...
ሀዘኔታ ፥ ርህራሄ ፥ መስዋዕትነት፥
ከደመ ነፍስ በላይ
ሰው ስለሆንንበት
የሕይወት ክብርና የህላዌ ብርሃን
ነበር.....
የምንቀዳጀው ! ! !
ዛሬ ፥ዛሬ ፥ግን
ሰውነት ፥ተዋርዶ
ስብዕና ፥ ደቆ
አራጅ ፥ለወንድሙ
ካራ ፥ስሎ ፥ቆሞ
ሰው "ሰው "አረደ
እነ እንትና ስፈር
የዲያቢሎስ ፤ሆነ
የአዳም፤ ልጅ፤ ግብር

እግዚኦ ! ይታረቀን!


[በሳል ምዕመን አይሳደብም፤ አይነጫነጭም፤ ጸጋና ሠላም ከሁላችሁ ጋር ይሁን]

Prist kibru ገፅ የተወሰደ!

መልካም ቀን !

ለእኔ ሕይወት ክርስቶስ ነው
SHARE | @CHRIST_TUBE
SHARE | @CHRISTFAMILY


#ለደካማ_ምዕመናን_የተጻፈ_ደብዳቤ

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተለይ "በታዋቂ" ሰዎች የሚደረግ ካሉበት ቤተ እምነት ወደ ሌላው ቤተ እምነት የሚደረግ ዝውውር እየተለመደ መጥቷል።
ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤት የቆየ ወደ ፕሮቴስታንት ማሕበር ሲቀላቀል፤ ኦርቶዶክሱ በሐዘን፤ ፕሮቴስታንቱ ደግሞ በደስታ ይንሳፈፋል።(በተመሳሳዩ ኦርቶዶክሱም እንዲሁ)
የአንድን ቤተ እምነት ሐሰተኝነትን ታዋቂ ሰው በመውጣቱ የምንመዝን ከሆንን ጴጥሮስ ኢየሱስን በመካዱ የኢየሱስን እውነት መሆንን እንጠራጠር ነበር፣ ዴማስም ዓለምን ወድዶ በመጥፋቱ የሐዋርያ ጳውሎስን አስተምህሮ በተጠራጠርን ነበር። ነገሩ ግን እንዲያ አይደለም። እንዲሁም ደግሞ

የአንድን ቤተ እምነት ትክክለኛነትን ታዋቂ ሰው ወደዛ በመቀላቀሉ የምንመዝን ከሆነ ለወንጌል ብዙ ዋጋ የከፈለው ቱርቱሊያን የተቀላቀለበትን "የሞንታኒስ እንቅስቃሴን" እውነት ነው ብለን በተቀላቀልን ነበር።

የአንድን ቤተ እምነት ትክክለኝነት ሆነ ሐሰተኛነት እንደ pendulum በሚዘዋወሩ(በልጅነታቸው ዥዋዥዌ ባልተጫወቱ) ሰዎች አንመዝን።
ታዋቂ ሰው ከኦርቶዶክስ ወደ ፕሮቴስታንት ስለተቀላቀለ ብቻ ኦርቶዶክስን አናውግዝ፤ እንዲሁም ደግሞ ኦርቶዶክሶችም ታዋቂ ሰው ከፕሮቴስታንት ወደ ኦርቶዶክስ ስለሄድ አታውግዙን/ልክነታችሁንም አታረጋግጡልን።

መለኪያችን ግለሰቦች ሳይሆኑ፤ የቤተ እምነቱ አስተምህሮ ነው። አስተምሮ ላይ መነጋገር የአዋቂ ነው።
ዛሬ መጣ ያሉት ነገ ሊወጣ ይችላል፤ ፕሮቴስታንቱም ዛሬ መጣ ያሉት ነገ ሊወጣ ይችላል። በመውጣት እና መግባታቸው ደማችሁ ዝቅ እና ከፍ የሚል ከሆነ በሽተኛ ናችሁ እና ታከሙ።
የወጣው ምን አጥቶ ነው የወጣው የሚለው እና ምን አግኝቶ ነው የተመለሰው የሚለው የሁለቱም ጎራዎች የቤት ሥራ ነው።

ደግሞ ወደ እኛ ከመጣ በኌላ በገንዘብ አልደገፍነውም ብር ስላጣ ነው የተመለሰው እያላችሁ ምክንያት የምትደረድሩ ሆይ፤ ለእናንተም ፈራሁ፤(ነገ ምዕመን አልደገፈኝም ብለህ ልትክድ ያለኸው አንተ ነህና) የገባን ነገር እውነት ነው ብለን ካመንን እንኳን ማጣትን እንኳን መራብን ለጌታ መሞትን መምረጥ የለብንም እንዴ? ወይስ አሁን ምናገለግል በጣም ደልቶን እያገለገልን ነው። (ሰዎቹ ከኦርቶዳክስ ሲወጡ ብር ፈልገው ነው ይባላል፤ ወደ ኦርቶዶክስ ሲመለሱ ግን እኛ ጋር ብር ስላጡ ነው ይባላሉ።) ብቻ እኛ ያለንን ጥለን የምንከተለውን አምላክ እንጂ የሌለን እንዲሰጠን የምንከተለው አምላክ የለንም።
[ልብ አድርጉልኝ ስለ ዲያቆን ሐዋዝ እየተናገርኩኝ አይደለም። ምክንያቱም እሱ ፕሮቴስታንት እንደሆነ አላውቅምና]

ብቻ እንደ እኔ አንድ ሰው ኤቲስት ከሚሆን ሙስሊም፤ ሙስሊም ከሚሆን ደግሞ ጆቫ ዊትነስ/ሐዋርያት ቢሆን፤ ጆቫ ዊትነስ/ ሐዋርያት ከሚሆን ደግሞ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ/ ካቶሊክ ቢሆ፣ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ/ ካቶሊክ ከሚሆን ኦርቶዶክ ተሐድሶ ቢሆን፤ ኦርቶዶክስ ተሐድሶ ከሚሆን ፕሮቴስታንት ቢሆን የተሻለ ነው እላለሁ።

[በሳል ምዕመን አይሳደብም፤ አይነጫነጭም፤ ጸጋና ሠላም ከሁላችሁ ጋር ይሁን]

Prist kibru ገፅ የተወሰደ!


#የማለዳ_ቃል 🌤☀️

2ኛ ቆሮ 12
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁹ እርሱም፦ ጸጋዬ ይበቃሃል፥ ኃይሌ በድካም ይፈጸማልና አለኝ። እንግዲህ የክርስቶስ ኃይል ያድርብኝ ዘንድ በብዙ ደስታ በድካሜ ልመካ እወዳለሁ።
¹⁰ ስለዚህ ስለ ክርስቶስ በድካም በመንገላታትም በችግርም በስደትም በጭንቀትም ደስ ይለኛል፤ ስደክም ያን ጊዜ ኃይለኛ ነኝና።

መልካም ቀን !

ለእኔ ሕይወት ክርስቶስ ነው
SHARE | @CHRIST_TUBE
SHARE | @CHRISTFAMILY


አትጨነቁ!

"ለእግዚአብሔር መኖርን ከመረጥህ የሚያስፈልግህን እርሱ ይሰጥሃል"

“የመለኮቱ ኃይል፥ በገዛ ክብሩና በበጎነቱ የጠራንን በማወቅ፥ ለሕይወትና እግዚአብሔርን ለመምሰል የሚሆነውን ነገር ሁሉ ስለ ሰጠን፥
  — 2ኛ ጴጥሮስ 1፥2-3

 ለእኔ ሕይወት ክርስቶስ ነው
@CHRIST_TUBE
@CHRISTFAMILY


#Spiritual speech

🗣 ❝ ለጠላት(ዲያብሎስ) ስንዝር ስትሰጠው ክንድህን ይወስድብሃል በፍጹም እድልን አትስጥ❝

 ለእኔ ሕይወት ክርስቶስ ነው
@CHRIST_TUBE
@CHRISTFAMILY
ሼር በማድረግ ለሌሎች ያድርሱ!


#የማለዳ_ቃል

“ለድሃ አደጉና ለመበለቲቱ ይፈርዳል፥ መብልና ልብስም ይሰጠው ዘንድ ስደተኛውን ይወድዳል።”
— ዘዳግም 10፥18

መልካም ቀን !

ለእኔ ሕይወት ክርስቶስ ነው
Join us Telegram
SHARE | @CHRIST_TUBE
SHARE | @CHRISTFAMILY


Good morning 🌄
#የማለዳ_ቃል

ፊልጵስዩስ 3
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²⁰ እኛ አገራችን በሰማይ ነውና፥ ከዚያም ደግሞ የሚመጣ መድኃኒትን እርሱንም ጌታን ኢየሱስ ክርስቶስን እንጠባበቃለን፤
²¹ እርሱም ሁሉን እንኳ ለራሱ ሊያስገዛ እንደሚችልበት አሠራር፥ ክቡር ሥጋውን እንዲመስል የተዋረደውን ሥጋችንን ይለውጣል።

ይህ #CHRIST_TUBE ነው ።
Join us Telegram💯☎️
መልካም ቀን 🌞🌄

#CHRIST_TUBE
#CHRIST_family


#የማለዳ_ቃል 🌤☀️

“ያስተምረኝም ነበር እንዲህም ይለኝ ነበር፦ ልብህ ቃሌን ይቀበል፤ ትእዛዜን ጠብቅ በሕይወትም ትኖራለህ።”
  — ምሳሌ 4፥4

መልካም ቀን !

ለእኔ ሕይወት ክርስቶስ ነው
SHARE | @CHRIST_TUBE
SHARE | @CHRISTFAMILY


ማንም እይሟገትላቹ እግዚአብሔር ይሟገትላቹ!
በማንም አትታዩ በእግዚአብሔር ታዩ!

መልካም ምሽት !

ለእኔ ሕይወት ክርስቶስ ነው
SHARE | @CHRIST_TUBE
SHARE | @CHRISTFAMILY


አስታውስ!!!

ፀሎቴን ቶሎ አልሰማኝም ያልከው እግዚአብሔር... ስታጠፋም ቶሎ ያልቀጣህ እግዚአብሔር ነው!


እሱ እግዚአብሔር ሉዓላዊ ነው!!

@CHRIST_TUBE
@CHRIST_TUBE


#የማለዳ_ቃል ✨🌤

መዝሙር 91
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁴ በእኔ ተማምኖአልና አስጥለዋለሁ፤ ስሜንም አውቆአልና እጋርደዋለሁ።
¹⁵ ይጠራኛል እመልስለትማለሁ፥ በመከራውም ጊዜ ከእርሱ ጋራ እሆናለሁ፤ አድነዋለሁ አከብረውማለሁ።
¹⁶ ረጅምን ዕድሜ አጠግበዋለሁ፥ ማዳኔንም አሳየዋለሁ።

መልካም ቀን !

ለእኔ ሕይወት ክርስቶስ ነው
SHARE | @CHRIST_TUBE
SHARE | @CHRISTFAMILY

Показано 20 последних публикаций.