📆
በግንባታ ግዥ ዘርፍ ስራ ልምድ ወይንም ዓመታዊ ተርን ኦቨር አላሟላም ብለው ከጨረታ ተሳትፎ ለመውጣት ከመወሰኖ በፊት ይህንን ይንብቡ?
በፌደራል መንግስት እና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ግዥ መመሪያዎች ላይ ከተቀመጡ መሰረታዊ ጉዳዮች መካከል በግንባታ ግዥ ጨረታ ውድድር ላይ የስራ ልምዱ እና ዓመታዊ ተርን ኦቨር ላይ በዶላር ምንዛሬ ለውጥ መሰረት የሚደረግ ማስተካከያ መኖሩ ሲሆን ይህም እንደሚከተለው ይሰላል።
1) ለጨረታ ግምገማ ዓላማ የሥራ ተቋራጩ በስራ ልምድነት እንዲያዝለት በሚያቀርበው የግንባታ ውለታ ዋጋ ላይ ማስተካከያ የሚደረግለት ሲሆን ይህም የሚሰላው ጨረታ ከሚቀርብበት የመጨረሻ ቀን 28 ቀናት በፊት የነበረው የምንዛሪ ምጣኔን ውሉ በተፈረመበት ጊዜ በነበረው የምንዛሪ ምጣኔ በማካፈል ከተሰላ በኋላ በሚገኘው ውጤት በማባዛት ነው።
2)በተመሳሳይም በጨረታ ግምገማ ጊዜ ለሚደረግ ማስተካከያ አላማ ለተርን ኦቨር ስሌት የሚወስደው ሥራ ተቋራጩ ያቀረበው አመታዊ የግንባታ ሥራ ተርን ኦቨር መጠን' ጨረታ ከሚቀርብበት የመጨረሻ ቀን 28 ቀን በፊት የነበረውን የምንዛሪ መጠን በእያንዳንዱ በጀት አመት የመጨረሻ ቀን ላይ ባለው የምንዛሪ መጠን በማካፈል ነው።
3) ሁለቱም ማስተካከያዎች የሚሰሉት የኢትዮዽያ ብሔራዊ ባንክ የሚሰጠውን የውጭ አገር ገንዘብ መሸጫ ዋጋ መረጃ መሠረት በማድረግ ይሆናል።
Join Us:
https://t.me/procinsightet