If Interested ......
ቀን 17/12/2015 ዓ.ም
ማስታወቂያ
በ4ኛ ዙር የጉምሩክ አስተላላፊነት ስልጠና ለወሰዳችሁ፤
በ4ኛ ዙር የአዳዲስ የጉምሩክ አስተላላፊነት ስልጠና ከወሰዳችሁ ሰልጣኞች ውስጥ ከዚህ በታች ስም ዝርዝራችሁ የተጠቀሳችሁ የተሰጣችሁን የምዘና ፈተና 75 በመቶና ከዚያ በላይ በማምጣት ያለፋችሁ በመሆኑ የሙያ ማረጋገጫ ሰርተፍኬት የተዘጋጀላችሁ ሲሆን
- ማንነታችሁን የሚገልጽ መታወቂያ
- ውክልና ከሆነ በውልና ማስረጃ የተረጋገጠ ህጋዊ የውክልና ማስረጃ እንዲሁም
- ስም ዝርዝራችሁ ያለበትን ተራ ቁጥር በመያዝ
ከመስቀል አደባባይ ወደ ሳሪስ በሚወስደው መንገድ መሻለኪያ ድልድዩ ፊት ለፊት በሚገኘው የጉምሩክ ኮሚሽን ዋና መ/ቤት 8ኛ ፎቅ የደንበኞች ትምህርትና ድጋፍ ዳይሬክቶሬት በመምጣት ሰርተፍኬት መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
ስም ዝርዝራችሁ የሌለ ሰልጣኞች በዚሁ የቴሌግራም ገጽ የሚለቀቁ የተለያዩ ማስታወቂያዎችን እንድትከታተሉ እናሳስባለን፡፡
በተጨማሪም በ3ኛ ዙር የጉምሩክ አስተላላፊነት ስልጠና ተሳተፋችሁ ድጋሚ ፈተና (Re-Exam) ወስዳችሁ የማለፊያ ነጥብ ያስመዘገባችሁትን ሰልጣኞች ስም ዝርዝር በቅርብ
በደንበኞች ትምህርትና ድጋፍ ዳይሬክቶሬት የቴሌግራም ገጽ የምናሳውቅ መሆኑን አውቃችሁ ማስታወቂያ እንድትከታተሉ እናሳስባለን፡፡
በጉምሩክ ኮሚሽን
የደንበኞች ትምህርትና ድጋፍ ዳይሬክቶሬት