Фильтр публикаций


1.  መድኃኒት በትክክል መውሰድ ስንል ምን ማለታችን  ነው?
በትክክል ተመርምሮ ለተረጋገጠ በሽታ (በየትኛው የጀርም ዓይነት ወይም በምን ምክንያት እንደመጣ ለተረጋገጠ በሽታ) ትክክለኛው መድኃኒት ለትክክለኛው ታማሚ በትክክለኛው ጊዜና መጠን  እና ታማሚውም በባለሙያ የተሰጠውን ምክር ተግባራዊ በማደረግ መድኃኒቱን በትክክል ሲወስድ አግባባዊ የመድኃኒት አጠቃቀም (Rational Medicines Use) አለ እንላለን፡፡ ከእነዚህ ተግባራት ውጭ በሆነ መንገድ ማለትም በትክክል ተመርምሮ የትኛው ዓይነት በሽታ አምጭ ተህዋስ እንዳስከተለው ለማይታውቅ በሽታ፣ ከታዘዘው መጠን በታች ወይም በላይ ሲወሰድ፣መወሰድ ከነበረበት ሠዓት ታልፎ ሲወሰድ፣የታዘዘውን ጸረ-ተህዋስ  መድኃኒት ሙሉ በሙሉ ሳይወስድ ከቀረ (ከተቋረጠ)፣  ወዘተ አግባባዊ የመድኃኒት አጠቃቀም የለም እንላለን፡፡መድኃኒትን በአግባቡ አለመጠቀም ደግሞ  የተለያዩ ¾Ö?“'ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳቶች ሲኖሩት ከእነዚህ ችግሮች አንዱ የጸረ-ተህዋሲያን መድኃኒቶች መላመድ ነው፡፡
2.  ተህዋሲያን (ጀርሞች ) ጸረ -ተህዋሲያን መድኃኒቶችን  ይላመዳሉ ይባላል፡፡ ይህ ምን ማለት ነው?  ሕመምን የማያድነውስ  መቼ ነው ?
የጸረ-ተህዋሲያን መድኃኒቶች መላመድ ማለት ከዚህ ቀደም በበሽታ አምጭ ተህዋሲያን (ጀርሞች) አማካኝነት የሚመጡ በሽታዎችን ለማከም ሆነ ለመከላከል ሲሰጥ የነበረው አንድ ጸረ-ተህዋስ መድኃኒት ሲሰጥ በነበረው መጠን ወይም ከዚያም በላይ የሰውነታችን ሴሎች ሊቋቋሙት በሚችሉት መጠን ሁሉ ሲሰጥ ተህዋሲያኑ የማይሞቱ ወይም መራባትን የማያቆሙ እና ህመምተኛው ከህመሙ የማይፈወስ ከሆነ ተህዋሱ ከመድኃኒት ጋር ተላምዷል ስንል ሂደቱንም የጸረ-ተህዋሲያን  መድኃኒቶች መላመድ (Antimicrobial Resistance) እንላለን ፡፡ ስለሆነም መድኃኒቱን በተላመደ ተህዋስ የታመመ በሽተኛ ምንም እንኳን በሽታው በትክክል ታውቆ መድኃኒቱን እየወሰደ ቢሆንም ከበሽታው የማይፈወስ ይሆናል፡፡

3.  ከበሽታ አምጭ ተህዋሲያን ጋር የሚላመዱት የትኞቹ የመድኃኒት ዓይነት ናቸው?
እዚህ ጋር መታየት ያለበት ነገር የአንድን መድኃኒት የሚወሰደውን መጠን እየጨመርን ስንሄድ ምላሹ በዚያው መጠን ከፍ የሚል ወይም ያንን መድኃኒት ካልወሰድን ከህመማችን የምንፈወስበት ጊዜ ይኖራል፡፡ ይህ ሂደት መቋቋም (Tolerance) የምንለው ሲሆን ከጸረ-ተህዋሲያን መድኃኒቶች ጋር የተገናኘ አይደለም፡፡ ለምሳሌ የዚህ ዓይነት ባህሪ ከሚያሳዩ መድኃኒቶች የህመም ማስታገሻ መድኃኒቶች እና የአእምሮ ህመም መድኃኒቶች (የናርኮቲክ እና የሳይኮትሮፒክ መድኃኒቶ)  ተጠቃሽ ናቸው፡፡ የመድኃኒትቶች ከጀርሞች ጋር መላመድ ስንል ግን የሰውነታችን ሴሎች በሚቋቋሙት መጠን ሁሉ ሲሰጥ ከህመማችን የማንፈወስ ስንሆን ነው ማለትም መጠንን መጨመር ወይም መድኃኒቱን መውሰድ ትርጉም አይኖረውም ማለት ነው፤  መድኃኒቱ ከጥቅም ውጭ ሆኗልና፡፡ የጸረ-ተህዋሲያን መድኃኒቶች መላመድ የምንለው  ጀርሞች ከጸረ-ተህዋስያን (ጸረ- ጀርም መድኃኒቶች) ጋር በመላመድቸው ምክንያት የሚከሰት ችግርን ብቻ ነው፡፡ ሁሉም የጸረ-ተህዋሲያን መድኃኒቶች ማለትም ጸረ-ባክቴሪያ (አንቲባዮቲክ) መድኃኒቶች፣ ጸረ-ቫይረስ መድኃኒቶች፣ ጸረ-ፈንገስ መድኃኒቶች እና ጸረ-ፐሮቶዝዋ በበሽታ አምጭ ጀርሞ ይለመዳሉ፡፡

4.  ተህዋስ መድኃኒቶችን ያለ ሀኪም ትዕዛዝ ገዝተን እንጠቀማለን፣ ጉዳት ይኖረው ይሆን?

በሀኪም ትእዛዝ ብቻ የሚታደሉ መድኃኒቶችን በትክክል ተመርምሮ ላለተረጋገጠ በሽታ መውሰድ ከፍተኛ የጤና፣ ማህበራዊ  እና ኢኮኖሚያዊ  ጉዳት አለው፡፡ ህብረተሰቡ ያላግባብ ገንዘቡን ያባክናል፣ መድኃኒቱን በተላመደ ዓይነት በሽታ ይያዛል ፣ይህንንም ለሌሎች ጤነኞች ያስተላልፋል፡፡ ለምሳሌ መድኃኒቱን በተላመድ አይነት የቲቢ በሽታ የተያዘ አንድ ግለሰብ በቀን በመቶዎች ለሚቆጠሩ ሰዎች ባክቴሪያውን ሊያስተላልፍ ይችላል፡፡ ከህመም ለማገገም ረጅም ጊዜ ይወስዳል ፣ለረጅም ጊዜ የሆስፒታል ቆይታ ያዳርጋል፣ ከፍተኛ ወጭና የጎንዮሽ ጉዳት ያላቸው መድኃኒቶችን እንድንጠቀም ያስገድደናል፡፡ የዚህ ሁሉ ድምር ውጤት አገሪቱ ለጤና የምታወጣው ወጭ ከፍ እንዲል ያደርጋል፣ ምርትና ምርታማነት እንዲቀንስ ያደርጋል፣ ህብረተሰቡ በጤና ተቋማት አገልገሎት ላይ ያለው አመኔታ እንዲቀንስ ያደርጋል፡፡ ወዘተ፡፡


የመድኃኒት ደህንነት ማስጠንቀቂያ

የኢትዮጵያ የምግብና መድኃኒት ባለሥልጣን RELIEF የሚባል ሕገወጥ መድኃኒት (በውስጡ ዲክሎፌናክ፣ ፓራሲታሞል፣ ክሎረፊኒራሚን እና ማግኒዥየም ትራይሲሊኬት እንዳለው ይገመታል) በኢትዮጵያ ገበያ እየተዘዋወሩ መሆኑን ተደርሶበታል።

ይህ መድኃኒት በሕጋዊ መንገድ በባለስልጣን መስሪያ ቤታችን ያልተመዘገበ በመሆኑ ጥራቱ፣ ደህንነቱና ውጤታማነቱ አይታወቅም።በተጨማሪም ፣ የዚህ መድኃኒት የጎንዮሽ ጉዳቶች የምግብ ፍላጎት ማጣት ፣ ተቅማጥ ፣ የሆድ ህመም ፣ ማቅለሽለሽ ፣ ማስታወክ ፣ እንቅልፍ ማጣት ፣ ድካም፤ የእይታ መዛባት፤ መፍዘዝ ፣ ራስ ምታት ፣ የቆዳ ሽፍታ ፣ የጉበት ኢንዛይሞች መጨመርና ለረጅም ጊዜ ጥቅም ላይ ሲውል የኩላሊት ጉዳትን ያጠቃልላል። ጥናቶች እንደሚያሳዩት ይህንን መድኃኒት ለረጅም ጊዜ መጠቀም ከባድ የጉበት፣ የኩላሊት ጉዳት፣ የልብ ድካም እና ስትሮክ የመያዝ እድልን ከፍ ሊያደርግ ይችላል።


በመሆኑም ህብረተሰቡ ይህንን መድኃኒት ከመጠቀም እንዲቆጠብ እያሳሰብን መድኃኒቱን በአካባቢዎት ካገኙ በነጻ ስልክ ቁጥር 8482 ደውለው ለኢትዮጵያ የምግብና የመድኃኒት ባለስልጣን ወይም ለክልል ጤና ተቆጣጣሪ አካላት እንዲጠቁሙ በአክብሮት እንጠይቃለን።


** የወባ በሽታ ስርጭት**

የወባ በሽታ ለወባ ትንኝ መራቢያ ምቹ በሆኑ የአየር ፀባይና አካባቢዎች በቀላሉ ሊስፋፋ ይችላል፡፡  በተለይ ቆላማ በሆኑ ቦታዎች ለወባ መስፋፋት ምቹ የሆነ ሙቀትና የአየር ርጥበት ያለባቸው ሲሆን

    👉 በዝናብ ምክንያትና አንዳንዴም በድርቅ ወቅት ወንዞች በመቆራረጣቸው የተነሳ
    👉 በየአካባቢው ውሀ ያቋቱ ስፍራዎች መበራከትና
    👉 በአግባቡ ያልተያዙ ረግረግ  መሬቶች መፈጠር እንዲሁም ከደጋማው ለወባ ተጋላጭ ካልሆኑ አካባቢ ወደነዚህ ቆላማ ስፍራዎች የህብረተሰብ እንቅስቃሴ መጨመር ለወባ መስፋፋት ምቹ ሁኔታዎች ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ 

👉 የወባ በሽታ መከላከያ መንገዶች

    👉 ውሃ ያቆሩ ቦታዎችን የማፋሰስና የማዳፈን ስራዎችን መስራት

    👉 የጸረ ትንኝም ሆነ የጸረ ዕጭ ኬሚካል መጠቀም
    👉 በኬሚካል የተነከረ አጎበር  ሁል ጊዜ መጠቀም

👉 የወባ በሽታ ምልክቶች

በትንኝ ንክሻ ወቅት ተሀዋሲው  ወደ ደም ዘልቆ በመግባት የደም ሴሎችን በማጥቃትና በሌሎች የውስጥ አካላት ላይ ጉዳት በማድረስ በሽተኛውን ለከፋ ጉዳት ብሎም ለሞት ይዳርጋል፡፡
አንድ ሰው የወባ በሽታ አምጭ ተህዋሲውን በያዘች ትንኝ ከተነከሰና የበሽታ ተሃዋሲ በደሙ ውሰጥ ከገባ በኋላ በሽታው በደም ዝውውር አማካይነት በጉበቱ ውስጥ ይገባል፡፡ ጉበት ውስጥ ገበቶ ተራብቶ አስፈላጊውን ሁኔታዎችን ባሟላ ከ7- 14 ባሉት ቀናት ውስጥ አንድ ሰው የበሽታውን ምልክቶች ሊያሳይ ይችላል፡፡ ከእነዚህም ምልክቶች ውስጥ
   👉  ከፍተኛ ትኩሳት፣
   👉 ብርድ ብርድ ማለት፣
   👉  ማንቀጥቀጥ፣
   👉 የመገጣጠሚያ አካላት ህመም፣
   👉 ቁርጥማት፣
   👉 የራስ ምታት፣
   👉 የምግብ ፍላጎት መቀነስና 
   👉 ማስታወክ ሊጠቀሱ ይችላሉ፡፡ 
ምልክቶቹ በየ2 ቀኑ እየተመላለሱ የሚያሰቃዩ ሲሆን በተለይም ህመሙ ኘላዝሞዲየም ፋልሲፓረም በተባለው የበሽታ አምጭ ተህዋሲ የመጣ ከሆነና በቂ ህክምና ካልተገኘ ከዚህ በከፋ ሁኔታ ማለትም እንደ ራስን መሳት፣ እንደሚጥል በሽታ አይነት መንፈራገጥ፣ እንዲሁም በከፋ ደም ማነስና የጉበት፣ የኩላሊትና የሳንባ ጉዳት ሊያደርስና ለሞት ሊዳርግም ይችላል፡፡

እነዚህን ምልክቶች ካዩ አቅራቢያዎ ወደሚገኝ ጤና ተቋም በመሄድ ምርመራ ያድርጉ!

አላማችን በደጋግ እጆች ህይወትን ማዳን ነው።

ዶክተር ሎምባሞ መካከለኛ ክሊኒክ

አድራሻ - ሆሳዕና - ጎምቦራ ከታክሲ ማዞርያ ወደ ጎፈር ሜዳ በሚወስደው መንገድ 50ሜትር ገባ ብሎ ያገኙናል ።

ስልክ ፦ 0911512338
Email ፦ babeshoy@gmail.com
telegram ፦ https://t.me/DRLOMBAMOCLINIC


የወባ በሽታ ወረርሽኝ

👉 የወባ በሽታ ምንነት

የወባ በሽታ ኘላዝሞዲየም በሚባል የደም ውስጥ ጥገኛ ተህዋሲ አማካይነት የሚመጣ አደገኛ በሽታ ነው፡፡ሌሎች እንስሳትን የሚያጠቁ  ዝርዎችም እንዳሉ ቢታወቅም የሰውን ዘር የሚያጠቃው ኘላዝሞዲየም ፉልሲፓረም፣ኘላዝሞዲየም ቫይቫክስ፣ ኘላዝሞዲየም ኦቫሌ እና ኘላዝሞዲየም ማለሪዬ በተባሉ አራት አይነት ዝርያዎቹ ነው፡፡

👉 የወባ በሽታ መተላላፊያ መንገዶቹ

የወባ በሽታ አኖፌለስ በተባሉ የትንኝ ዝርያዎች እንደሚተላለፍ የሚታወቅ ሲሆን በሴቷ ትንኝ ንክሻ አማካይነትም ከህመምተኛ ወደ ጤነኛ ሰው ይተላለፍል፡፡ የወባ በሽታን የሚያስላልፉት አራት አይነት ብቻ ናቸው፡፡

የወባ በሽታ አስተላላፊ ትንኝ የምትራባው በአብዛኛው በጊዜያዊነት ባቆሩ ውሃዎች ላይ  ሲሆን አልፎ አልፎ ዕጮቿ በወንዞችና በሀይቆች ዳርቻ ሊገኙ ይችላሉ፡፡  በተጨማሪ በመኖሪያ አከባቢ በሚገኙ ዉሃ መያዝ በሚችሉ ቁሳቁሶች ላይ በቀላሉ ትራባለች፡፡

ትንኟ ዕቁላሏን ለማኩረት የሚጠቅማትን ደም ለማግኘት ስትል  በሰዎች ጠረን፣ ሙቀትና ትንፋሽ በመሳብና ወደ ሰዎች አካል በመቅረብ ትናከሳለች፡፡ ንክሻው በአብዛኛው በምሽትና (ከምሽት እስከ ንጋት ባለው ጊዜ ውስጥ) በቤት ውስጥ ሲሆን ከቤት ውጭም ይከናወናል፡፤ አኖፊለስ  አረቢየንሲስ የተሰኘችው ዋናዋ የወባ አስተላላፊ ትንኝ ቤትም ተመገበች ውጭ በአብዛኛው የምታርፈው በቤት ውስጥ ነው፡፡

**ይቀጥላል**




Vacancy Announcement

Dr Lombamo Medium Clinic, located at Hossana, wants to hire a General practitioner who has Graduated from recognized medical institution

Number: 1
Work experience: 0 years
Gender:  Male/ Female
Salary : negotiable
Employment form : full time
Hadiyisa language proficiency is preferable

How to apply : All interested applicants can apply in person at Dr Lombamo Medium Clinic, Hosanna, Gombora, 50meters on the way from taxi marozia to Gofermeda or using our telegram

Tel: 0911512338 or via our email Address- babeshoy@gmail.com

Application deadline : October 9 to 14,  2024


እንኳን ለመውሊድ በዓል በሰላም አደረሰዎ!! እያልን በዓሉ የሠላምና የጤና እንዲሆንልዎ እንመኛለን።

ክሊኒካችን በሞያቸው አንቱታን ባተረፉ እስፔሻሊስት ሀኪሞች ከተሟላ የላቦራቶሪ ምርመራ ጋር አገልግሎት በመስጠት ላይ መሆኑን ስንገልፅ በታላቅ ደስታ ነው ፡፡

ዶክተር ሎምባሞ መካከለኛ ክሊኒክ

አድራሻ - ሆሳዕና - ጎምቦራ ከታክሲ ማዞርያ ወደ ጎፈር ሜዳ በሚወስደው መንገድ 50ሜትር ገባ ብሎ ያገኙናል ።

ስልክ ፦ 0911512338/0913762936
Email ፦ babeshoy@gmail.com
telegram ፦ https://t.me/DRLOMBAMOCLINIC

አላማችን በደጋግ እጆች ህይወትን ማዳን ነው።


እንኳን ለ2017ዓ.ም የዘመን መለወጫ በዓል በሰላም አደረሰዎ እያልን አዲሱ ዓመት የሠላምና የጤና እንዲሆንልዎ እንመኛለን።

ክሊኒካችን በሞያቸው አንቱታን ባተረፉ እስፔሻሊስት ሀኪሞች ከተሟላ የላቦራቶሪ ምርመራ ጋር አገልግሎት በመስጠት ላይ መሆኑን ስንገልፅ በታላቅ ደስታ ነው ፡፡

ዶክተር ሎምባሞ መካከለኛ ክሊኒክ

አድራሻ - ሆሳዕና - ጎምቦራ ከታክሲ ማዞርያ ወደ ጎፈር ሜዳ በሚወስደው መንገድ 50ሜትር ገባ ብሎ ያገኙናል ።

ስልክ ፦ 0911512338/0913762936
Email ፦ babeshoy@gmail.com
telegram ፦ https://t.me/DRLOMBAMOCLINIC

አላማችን በደጋግ እጆች ህይወትን ማዳን ነው።


ዶክተር ሎምባሞ መካከለኛ ክሊኒክ አዲሱን ዓመት ምክንያት በማድረግ ከዻጉሜ 1-5 የሚቆይ ነፃ የጤና ምርመራ እና የማማከር አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል ።

እርሶም በስራ ሰዓት በክሊኒካችን በመገኘት የእድሉ ተጠቃሚ እንዲሆኑ በአክብሮት ጋብዘኖታል።

ዶክተር ሎምባሞ መካከለኛ ክሊኒክ

አድራሻ - ሆሳዕና - ጎምቦራ ከታክሲ ማዞርያ ወደ ጎፈር ሜዳ በሚወስደው መንገድ 50ሜትር ገባ ብሎ ያገኙናል ።
ስልክ ፦ 0911512338
Email ፦ babeshoy@gmail.com telegram ፦https://t.me/DRLOMBAMOCLINIC

አላማችን በደጋግ እጆች ህይወትን ማዳን ነው !!!!


ዶክተር ሎምባሞ መካከለኛ ክሊኒክ አዲሱን ዓመት ምክንያት በማድረግ ከዻጉሜ 1-5 የሚቆይ ነፃ የጤና ምርመራ እና የማማከር አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል ።

እርሶም በስራ ሰዓት በክሊኒካችን በመገኘት የእድሉ ተጠቃሚ እንዲሆኑ በአክብሮት ጋብዘኖታል።

ዶክተር ሎምባሞ መካከለኛ ክሊኒክ

አድራሻ - ሆሳዕና - ጎምቦራ ከታክሲ ማዞርያ ወደ ጎፈር ሜዳ በሚወስደው መንገድ 50ሜትር ገባ ብሎ ያገኙናል ።
ስልክ ፦ 0911512338
Email ፦ babeshoy@gmail.com telegram ፦https://t.me/DRLOMBAMOCLINIC

አላማችን በደጋግ እጆች ህይወትን ማዳን ነው !!!!


አስደሳች ዜና ለሆሳዕና እና አከባቢዋ ነዋሪዎች በሙሉ

ዶክተር ሎምባሞ መካከለኛ ክሊኒክ አዲሱን ዓመት ምክንያት በማድረግ ከዻጉሜ 1-5 የሚቆይ ነፃ የጤና ምርመራ እና የማማከር አገልግሎት እንደሚሰጥ ስናበስር በታላቅ ደስታ ነው።

እርሶም በስራ ሰዓት በክሊኒካችን በመገኘት የእድሉ ተጠቃሚ እንዲሆኑ በአክብሮት ጋብዘኖታል።

ዶክተር ሎምባሞ መካከለኛ ክሊኒክ

አድራሻ - ሆሳዕና - ጎምቦራ ከታክሲ ማዞርያ ወደ ጎፈር ሜዳ በሚወስደው መንገድ 50ሜትር ገባ ብሎ ያገኙናል ።

ስልክ ፦ 0911512338
Email ፦ babeshoy@gmail.com
telegram ፦https://t.me/DRLOMBAMOCLINIC

አላማችን በደጋግ እጆች ህይወትን ማዳን ነው !!!!


ካለፈው የቀጠለ ፨፨፨፨፨፨

ከዚህ በተጨማሪ አደንዛዥ ዕፅ መጠቀም፣ አልኮል መጠጥ መጠጣት፣ ሲጋራ ማጨስ እንዲሁም ከመጠን በላይ የሆነ ውፍረት የዘር ፍሬን መጠን ሊቀንስ ይችላል።


ወንዶችን ለመካንነት የሚያጋልጡ ነገሮች ምን ምንድን ናቸው?


ሲጋራ ማጨስ
አልኮል መጠጥ መጠጣት
አደንዛዥ ዕፅ መጠቀም
ከመጠን ያለፈ ውፍረት
ጭንቀት
የአባለዘር በሽታ
በዘር ፍሬ ላይ የሚደርስ የኬሚካል፣ የጨረር እና የከፍተኛ ሙቀት አደጋ፤
በወንድ የመራቢያ አካል ላይ የሚሠራ የቀዶ ጥገና፤
በቤተሰብ ውስጥ ተመሳሳይ ችግር ከአለ ወይም ከነበረ፤


የወንዶች መካንነት እንዴት ይታከማል?

በወንዶች ላይ መካንነትን የሚያስከትሉ ምክንያቶች እንደሚለያዩ ሁሉ ሕክምናውም ይለያያል።
ጥንዶች ቢያንስ ለ 12 ወራት ያለ ወሊድ መቆጣጠሪያ በቂ ግብረ ሥጋ ግንኙነት እየፈፀሙ ልጅ ካላገኙ ወደ ሐኪም ቤት በመምጣት የሕክምና ክትትል ማድረግ ይጠበቅባቸዋል።
ሐኪም ቤት ከመጡ በኋላ ሁለቱም የተለያዩ ምርመራዎች ይደረግላቸዋል።

ለወንዱ ከሚደረግለት ምርመራዎች ውስጥ ዋንኛው የዘር ፍሬውን መለካት እና በቂነቱን ማረጋገጥ ሲሆን ይህም ምርመራ ሴመን አናሊሲስ (semen analysis) ይባላል።

የተለያዩ ምርመራዎች ከተደረጉ እና ችግሩ ከተለየ በኋላ እንደ ችግሩ የተለያዩ የሕክምና አማራጭች ይቀርባሉ።

ለምሳሌ
የዘር ፍሬ ፈሳሽ እንዳይወጣ የሚያግድ ጠባሳ ካለ በቀዶ ጥገና ማስተካከል ይቻላል።

በተመሳሳይ ቫሪኮሴሌ የሚባለው መካንነትን የሚያመጣው የጤና እክልም በቀዶ ጥገና መስተካከል የሚችል ነው።

በተጨምሪም የወንዱን የዘር ፍሬ ሕዋስ በማውጣት ላብራቶሪ ውስጥ የሴቷ ዕንቁላል ጋር ይደባልቁታል።

የተለያዩ መንገዶች ተሞክረው ልጅ መረገዝ ካልተቻል እንደ ጉዲፈቻ ያሉ አማራጮችን መጠቀም ይቻላል።

ምንጭ - wecare


ዶክተር ሎምባሞ መካከለኛ ክሊኒክ

አላማችን በደጋግ እጆች ህይወትን ማዳን ነው።

አድራሻ - ሆሳዕና - ጎምቦራ ከታክሲ ማዞርያ ወደ ጎፈር ሜዳ በሚወስደው መንገድ 50ሜትር ገባ ብሎ ያገኙናል ።

ስልክ ፦ 0911512338/0913762936

https://t.me/DRLOMBAMOCLINIC


ካለፈው የቀጠለ ፨፨፨፨፨፨

ከእነዚህ በሽታዎች ውስጥ ጥቂቶቹ
አንድ አንድ ጊዜ የዘር ፍሬ ከረጢትን የሚመግበው የደም መልስ ቧንቧ ሊያብጥ ይችላል።

ይህም ቫሪኮሴሌ (varicocele) ይባላል። ይኽንን በሽታ አክሞ ማዳን የሚቻል ቢሆንም የወንዶች መካንነትን ከሚያስከትሉ ምክንያቶች መካከል ዋንኛው ነው።

ከዚህ በተጨማሪም እንደ ጨብጥ ያሉ በልቅ የግብረ ሥጋ ግንኙነት የሚተላለፉ በሽታዎች የዘር ፍሬ የሚታልፍበትን መንገድ በጠባሳ ሊዘጉ ይችላሉ። አንዳንድ ኢንፌክሽኖች ደግሞ የዘር ፍሬ ሕዋሳት እንዳይመረቱ ሊያደርጉ ይችላሉ።

ስንፈተ ወሲብን ጨምሮ የተለያዩ ከግብረ ሥጋ ጋር ተያይዘው የሚመጡ ችግሮች ለመካንነት ምክንያት ሆነው ይጠቀሳሉ።

ሌላው ምክንያት የዘር ፍሬ ፈሳሽ ወደ ውጭ መውጣቱን ትቶ በተቃራኒው ወደ ሽንት ፊኛ ሲገባ ነው። ይህም ሬትሮግሬድ ኢጃኩሌሽን (retrograde ejaculation) ይባላል።

ይህም ሁኔታ በስኳር በሽታ፣ በተለያዩ መድኃኒቶች አማካኝነት፣ ኅብለ ሰረሰር ላይ በሚደርስ አደጋ እንዲሁም በፊኛ ቀዶ ጥገና አማካኝነት ሊፈጠር ይችላል።

አንዲሴንድድ ቴስቲስ (Undescended testicles) በፅንስ ዕድገት ጊዜ የወንድ የዘር ፍሬ ከረጢት ከፅንሱ ሆድ ውስጥ ወጥቶ ወደ ታች ይወርዳል።

አንድ አንድ ሕፃናት ላይ ግን ይህ አይፈጠርም።
በዚህ ጊዜ የዘር ፍሬን የሚያመነጨው አካል በሆድ ውስጥ ስለሚቀር እና ለከፍተኛ የሰውነት ሙቀት ስለሚጋለጥ የዘር ፍሬ ማምረቱን ይቀንሳል ወይም ያቆማል።

ይህም ለመካንነትን የመጋለጥ ዕድልን ይጨምራል።

አነስተኛ የቴስቴስትሮን ሆርሞን መጠን፤
መካንነትን የሚያመጡ በዘር የሚወረሱ የተለያዩ የጤና ችግሮች አሉ።
ለምሳሌ ክሌንፌልተርስ ሲንድረም (Klinefelter's syndrome) የሚባል በሽታ የወንድ መራቢያ አካል በትክክለኛ መልኩ እንዳይሠራ የሚያደርግ በሽታ ነው።

በወንዱ መራቢያ አካል ላይ የሚሠሩ የተለያዩ የቀዶ ጥገና ዓይነቶች ጠባሳን በመፍጠር የዘር ፍሬ ወደ ውጭ እንዳይወጣ ሊያግዱ ይችላሉ።

ከላይ ከተጠቀሱት በተጨማሪ ለተለያዩ ጎጂ ኬሚካሎች፣ ጨረር እና ለከፍተኛ ሙቀት መጋለጥ የዘር ፍሬ ምርትን ሊቀንስ ይችላል።

አንዲሴንድድ ቴስቲስ (Undescended testicles) በፅንስ ዕድገት ጊዜ የወንድ የዘር ፍሬ ከረጢት ከፅንሱ ሆድ ውስጥ ወጥቶ ወደ ታች ይወርዳል።
አንድ አንድ ሕፃናት ላይ ግን ይህ አይፈጠርም።

በዚህ ጊዜ የዘር ፍሬን የሚያመነጨው አካል በሆድ ውስጥ ስለሚቀር እና ለከፍተኛ የሰውነት ሙቀት ስለሚጋለጥ የዘር ፍሬ ማምረቱን ይቀንሳል ወይም ያቆማል።

ይህም ለመካንነትን የመጋለጥ ዕድልን ይጨምራል።
አነስተኛ የቴስቴስትሮን ሆርሞን መጠን፤

ይቀጥላል
ምንጭ - wecare


ዶክተር ሎምባሞ መካከለኛ ክሊኒክ

አላማችን በደጋግ እጆች ህይወትን ማዳን ነው።

አድራሻ - ሆሳዕና - ጎምቦራ ከታክሲ ማዞርያ ወደ ጎፈር ሜዳ በሚወስደው መንገድ 50ሜትር ገባ ብሎ ያገኙናል ።

ስልክ ፦ 0911512338/0913762936

https://t.me/DRLOMBAMOCLINIC


መካንነት በወንዶች ላይ ሊከሰት ይችላል ?????

መካንነት በወንዶች ላይ ( Male Infertility )

መካንነት የሚባለው ጥንዶች ቢያንስ ለ አንድ ዓመት ያህል ሞክረው (ቢያንስ በሳምንት 3 ጊዜ ያለወሊድ መቆጣጠሪያ) ልጅ መውለድ (ማርገዝ) ካልቻሉ ነው። ነገር ግን ሴቷ ከ 35 ዓመት በላይ ከሆነች በ6 ወር ብቻ ምርመራ ሊጀመርላት ይችላል።
በተደረገው ጥናት መሠረት 85% የሚሆኑ ጥንዶች በመጀመሪያው 12 ወር ውስጥ ሴቷ ትፀንሳለች። የተቀሩት 10% የሚሆኑት ጥንዶች ደግሞ በቀጣዩ አንድ ዓመት ውስጥ ይሳካላቸዋል።
መካንነት የተለያዩ ምክንያቶች ሊኖሩት ይችላሉ። ከእነዚህ ውስጥ፤
አንድ ሦስተኛ የሚሆኑት ላይ የሴቷ ችግር፤
አንድ ሦስተኛ የሚሆኑት ላይ ደግሞ የወንዱ ችግር ሲሆን፤የተቀሩት አንድ ሦስተኞቹ ላይ በሴቷም በወንዱም ላይ ችግር ተገኝቷል።

መካንነትን በወንዶች ላይ የሚያመጡ ነገሮች ምን ምንድን ናቸው?
የተለያዩ የጤና ችግሮች በወንዶች ላይ መካንነትን ያመጣሉ። እነዚህ የጤና እክሎች እንዴት መካንነት እንደሚያመጡ ለመረዳት በመጀመሪያ ትክክለኛው የዘር ፍሬ እንዴት እንደሚሠራ እና መጠኑን መረዳት ያስፈልጋል።
የወንድ የዘር ፍሬ የሚመረተው የዘር ከረጢት ውስጥ ነው፡፡ ወንዱ ለዐቅመ አዳም ከደረሰ ጊዜ አንሥቶ በየቀኑ በሚሊዮን የሚቆጠሩ የዘር ፍሬዎች ይመረታሉ። እነዚህ የዘር ፍሬ ሕዋሳት እንዲመረቱ ቴስቴስትሮን (Testosterone) የሚባል ሆርሞን ዋነኛውን ሚና ይጫወታል። እነዚህ የዘር ፍሬ ሕዋሳት ከተመረቱ በኃላ በአምስት ሳምንታት ጊዜ ውስጥ ሙሉ በሙሉ ያድጋሉ። ቀጥሎም በግብረ ሥጋ ግንኙነት ጊዜ ሴሚናል ፈሳሽ ከሚባል ጋር በመደባለቅ በሽንት ቧንቧ አማካኝነት ወደ ሴቷ መራቢያ ክፍል ይገባሉ።
በአማካኝ
በአንድ ግዜ የሚፈስው የዘር ፈሳሽ 1.5 - 5 ሚሊ ሊትር ሲሆን
በአንድ ሚሊ ሊትር ውስጥ የሚኖረው የዘር ፍሬ ብዛት ከ15 ሚሊዮን ይበልጣል፡፡ በጠቅላላው ከ39 ሚሊዮን የሚበልጥ የዘር ፍሬ ሕዋሳትን በውስጡ ይይዛል።
በመጨረሻም ከቁጥሩ በተጨማሪ የዘር ፍሬ ሕዋሶቹ መጠናቸው እና ቅርፃቸው እንዲሁም የሚንቀሳቀሱበት ፍጥነት አስተዋጽዖ አለው።
ከላይ ከተጠቀሰው ሂደት ውስጥ አንዱ ላይ ችግር ከአለ መካንነት ሊከሠት ይችላል። በዚህ ምክንያት የወንዶች መካንነት በተለያዩ ምክንያቶች ሊመጣ ይችላል ማለት ነው። ከ 30 እስከ 40 በመቶ የሚሆነው የመካንነት ችግር የሚፈጠረው ቆለጥ ላይ በሚደርስ ችግር ነው፡፡ ከ 10 እስከ 20 በመቶ የሚሆነው ደግሞ ከ ዘር ፍሬ ከረጢት ተነሥቶ የሴቷ የመራቢያ አካል እስኪደርስ ባለው መተላለፊያ ቱቦ ላይ በሚደርስ ችግር ምክንያት የሚከሠት ነው።
ይቀጥላል
ምንጭ - wecare


ዶክተር ሎምባሞ መካከለኛ ክሊኒክ

አላማችን በደጋግ እጆች ህይወትን ማዳን ነው።

አድራሻ - ሆሳዕና - ጎምቦራ ከታክሲ ማዞርያ ወደ ጎፈር ሜዳ በሚወስደው መንገድ 50ሜትር ገባ ብሎ ያገኙናል ።

ስልክ ፦ 0911512338/0913762936

https://t.me/DRLOMBAMOCLINIC


መካንነት በወንዶች ላይ


Habayyi 2016HD Yesuus kiristoos leh kich ugudina xumine afisukko

እንኳን ለ2016ዓ.ም ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የትንሣኤ በዓል በሰላም  አደረሰን የሚለን ዶክተር ሎምባሞ መካከለኛ ክሊኒክ በዓሉ የሰላም፣ የፍቅር፣ የደስታ እንዲሆን ይመኛል ።

       መልካም የትንሣኤ በዓል
ዶክተር ሎምባሞ መካከለኛ ክሊኒክ

አላማችን በደጋግ እጆች ህይወትን ማዳን ነው።

አድራሻ - ሆሳዕና - ጎምቦራ ከታክሲ ማዞርያ ወደ ጎፈር ሜዳ በሚወስደው መንገድ 50ሜትር ገባ ብሎ ያገኙናል ።

ስልክ ፦ 0911512338/0913762936

https://t.me/DRLOMBAMOCLINIC


ወንዶች ልጆቻችንን መቼ ነው ማስገረዝ ያለብን?

ብዙ ቤተሰቦች ልጃቸውን ለማስገረዝ ተመራጩን  ዕድሜ ይጠይቃሉ፡፡ ልጅ ለማስገረዝ በጣም ተመራጩ ዕድሜ ከተወለደ ከ 8 ኛው ቀን ጀምሮ እስከ ሦስተኛው ወር መጨረሻ ድረስ ነው፡፡ ምክንያቱም ፤

1. ህጻናት በዚህ እድሜ ትንሽ ህመም ይሰማቸዋል

2. በግርዛት ወቅት ብዙ ስለማይንቀሳቀሱ  አያስቸግሩም

3. ወደፊት የዚህን ግርዛት (የቀዶ ጥገናውን) ምንም ትውስታ አይኖራቸውም

ከአዋቂዎች ግርዛት ጋር ሲነጻጸር፤ የሕፃናት ግርዛት ቀላል በሆኑ ዘዴዎች ይከናወናል እንድሁም ለመዳን አጭር ጊዜ ይወስዳል፡፡በልጅነት ጊዜ የተገረዙ ወንዶች የቁስሉ ቦታ በጊዜ ሂደት በትክክል ስለሚድን የተሻለ (የማይታይ) ጠባሳ ይኖራቸዋል።

ካለን ልምድ የቀለበት የግርዛት ዘዴ አንድ ልጅ ከአራት ወር በታች ሲገረዝ የተሻለ ይሰራል። ይህ እድሜ ለእናቲቱም ሆነ ለህፃኑ በጣም ተስማሚ ነው፡፡

ዶ/ር ደሳለኝ አብዲሳ
የቀዶ ህክምና ስፔሻልስት

በዶክተር ሎምባሞ መካከለኛ ክሊኒክ ዘወትር በስራ ሰዓት በቀዶ ጥገና እስፔሻሊስት ሀኪም

አላማችን በደጋግ እጆች ህይወትን ማዳን ነው።
አድራሻ - ሆሳዕና - ጎምቦራ ከታክሲ ማዞርያ ወደ ጎፈር ሜዳ በሚወስደው መንገድ 50ሜትር ገባ ብሎ ያገኙናል ።
ስልክ ፦ 0911512338/0913762936


የኩፍኝ በሽታ


የኩፍኝ በሽታ


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
እንኳን ለብርሃነ ልደቱ በሠላም አደረሰዎ!
በዓሉ የሠላም፣ የደስታ፣ የፍቅርና የአብሮነት እንዲሆንልዎ ከልብ እንመኛለን!
ዶክተር ሎምባሞ መካከለኛ ክሊኒክ
አላማችን በደጋግ እጆች ህይወትን ማዳን ነው
መልካም የገና በዓል!

Показано 20 последних публикаций.