ትላንት የካቲት 1 ቀን 2017 የተጀመረው የመቄዶንያ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐግብር የገንዘብ ድጋፍ ይህን ዘገባ እስካጠናቀርንበት ጊዜ ድረስ 101 ሚሊዮን ብር የተሰባሰበ መሆኑ ታውቋል ።
ይህም ድጋፍ በሃገር ውስጥ ሆነ በውጭ የሚገኙ ዜጐች እየተሳተፉበት መሆኑ ተነግሯል።
ድጋፍ ስጦታው በኢትዮጵያ ንግድ ፣ ቴሌብር ና ሌሎች ልዩ ልዩ ባንኮች በቀጥታ በማስገባት እንዲሁም በሰይፉ ዩትዩብ ቻናል ቀጥታ ስርጭት በመገኘት ቃል በመግባት እየተከናወነ ነው።
በውጭ ለሚገኙ ዜጐች በካሻ-አኘ እንዲሁም ዜል የገንዘብ ማስተላለፊያ በማሰባሰብ ላይም ይገኛል።
በመርሃ ግብሩ በርካታ ያልታሰቡ ስጦታዎች በቀጥታ ስርጭቱ ወቅት እየተለገሱ ይገኛሉ።
ይህ መርሐ ግብር በሰይፉ ዩትዩብ ቻናል ቀጥታ ስርጭት ላይ እየተከናወነ የሚገኝ ሲሆን መርሃ ግብሩ አሁንም እንደቀጠለ ነው ....
ይህንኑ ታላቅ የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም 2ኛ ቀን መርሐግብር በሰይፉ ዩቲዩብ ና በመቄዶንያን የዩትዩብ ቻናል በቀጥታ እንድትከታተሉ እና አሁንም ድጋፍ እንድታደርጉ ተጋብዛችኋል ።
#EBS
#EBSTVNEWS
#EBSTVSPORT
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews