Ethiopian Electric Utility


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Карьера


EEU Official Telegram Channel
Web: www.eeu.gov.et

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Карьера
Статистика
Фильтр публикаций


የተሻለ አፈጻፀም ላስመዘገቡ ሪጅኖችና ማዕከላት የእውቀና ሽልማት ተበረከተ

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በ2016 በጀት አመት የተሻለ አፈጻፀም ላስመዘገቡ ሪጅኖችና ማዕከላት የእውቀና ሽልማት አበርክቷል፡፡

የእውቀና ሽልማቱ የተበረከተው በአጠቃላይ አፈጻፀም፣ በገቢ አሰባሰብ፣ አዳዲስ ደንበኞችን የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ በማድረግ እና በመሳሰሉ የስራ ዘርፎች ሲሆን ከምስክር ወረቀት እስከ ተሽከርካሪ የሚደርስ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡

የሐረሪ፣ ደሴና ወልዲያ ሪጅኖች በአዲስ ሃይል ማገናኘት ስራ ላይ ባስመዘገቡት የላቀ አፈጻፀም እንዲሁም ደብረ ብርሃን፣ ምሥራቅ አዲስ አበባና አርባ ምንጭ ሪጅኖች ደግሞ በኃይል ሽያጭ ስራ ላይ ባሳኩት ከፍተኛ ውጤት የምስክር ወረቀት ተሸልመዋል፡፡

በተመሳሳይ ሐረሪ ቁጥር አንድ በአጠቃላይ እቅድ አፈፀፃፀም ከደረጃ ኤ አንደኛ በመውጣት ፒካፕ መኪና የተበረከተለት ሲሆን ወለዲያ ቁጥር አንድ ማዕከል ከደረጃ ቢ 1ኛ በመውጣት ፒካፕ መኪና ተሸልሟል፡፡

መርሳ አገልግሎት መስጫ ማዕከል ከደረጃ ሲ 1ኛ በመውጣት የባጃጅ ተሸላሚ ሲሆን በወላይታ ሪጀን ስር የሚገኘው የጉሱባ አገልግሎት መስጫ ማዕከል ከደረጃ ዲ 1ኛ በመውጣት የሞተር ሳይክል ተሸላሚ ሁኗል፡፡

ወልድያ ቁጥር ሁለት፣ ጂንካ፣ ቡራዩ እና ገበዘማሪያም የአገልግሎት መስጫ ማዕከላት በአጠቃላይ እቅድ አፈፃፀም የተሻለ በማስመዝገብ የፕሪንተርና የምስክር ወረቀት ተብርክቶላቸዋል፡፡

የፍላቂት፣ አቀስታ፣ ሰሜን አዲስ አበባ ቁጥር አራት እና ደብረ ብርሃን ቁጥር ሁለት ማዕከላት ደግሞ ባስመዘገቡት አጠቃላይ አፈጻፀም የኮምፒዩተር፣ ፕሪንተርና የምስክር ወረቀት ተብርክቶላቸዋል፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት


ከብልሹ አሰራር የፀዳ ተቋም መፍጠር የሁሉም ሃላፊነት ነው

ከብልሹ አሰራር የፀዳ ተቋም መፍጠር በየደረጃው የሚገኘው አመራርና ሰራተኛ ሃላፊነት መሆኑን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋና ስራ አስፈጻሚ ሽፈራው ተሊላ (ኢ/ር) ገልፀዋል፡፡

ዋና ስራ አስፈጻሚው የምክክሩን መድረክ ማጠቃለያ ላይ ባስተላለፉት መልዕክት ተቋሙ የጀመረውን የአሰራር ስርዓት ውጤታማ በማድረግ እየጨመረ የመጣውን ሃይል ፍላጎት መመለስ እና የሃገሪቱን ኢኮኖሚ ሊሸከም የሚችል አገልግሎት መስጠት ይገባል ብለዋል፡፡

ከብልሹ አሰራር የፀዳ፣ ስልጡንና አገልጋይ አመራርና ሰራተኛ በመፍጠር ጥራት ያለውና አስተማማኝ የኤሌክትሪክ አገልግሎት መስጠት እንደሚገባ ኢ/ር ሽፈራው አሳስበዋል፡፡

የተጠያቂነት ስርዓት በመዘርጋት የመልካም አስተዳደር ችግሮችን መቅረፍ እንደሚገባ የገለፁት ዋና ስራ አስፈጻሚው የብልሹ አሰራር ችግር በሚታይባቸው አመራርና ሰራተኞች ላይ ተገቢ የሆነ እርምጃ መውሰድ እንደሚገባም ጠቁመዋል፡፡

ለደንበኞች የሃይል ጥያቄ ፈጣን ምላሽ በመስጠት፣ የቅሬታ ምንጮችን በማድረቅ እና ፈጣን ምላሽ በመስጠት የደንበኞችን የእርካታ ደረጃ ማሳደግ እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡

በተጨማሪም ኢ/ር ሽፈራው በፕሮጀክቶች አፈጻፀም ላይ ተገቢ ክትትልና ቁጥጥር በማድረግ እና የባለድርሻ አካላትን ተሳትፎ በማሳደግ የኤሌክትሪክ ተደራሽነት እውን ማድረግ እና በገጠሩ የሃገራችን ክፍሎች የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ማድረግ ይገባል፡፡

በመጨረሻም ዋና ስራ አስፈጻሚው የታዩ ጠንካራና ደካማ ጎኖችን በመለየት ችግር ፈች የሆኑ የፈጠራ ስራዎችን በማከናዎን የተቋሙን አቅም ማሳደግና በአለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ ተቋም መፍጠር ይገባል ብለዋል፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
ክቡራን ደንበኞቻችን የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ መስመሮች ከዛፎች በሶስት ሜትር መራቅ እንዳለባቸው ያውቃሉ? እንግዲያውስ ይህንን ይገንዘቡ!

ዛፎች ሲተከሉ ከኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት በሶስት ሜትር መራቅ እንዳለባቸው የተቋማችን መመሪያ ይደነግጋል፡፡ ይሁን እንጂ በአብዛኛው አካባቢዎች በመኖሪያ ቅጥር ግቢ ውስጥ እንዲሁም ከግቢ ውጭ ለኃይል መቆራረጥና ለአደጋ መንስኤ የሆኑ ዛፎችን ከመሰረተ ልማቱ በእጅጉ ተቀራርበው ይገኛሉ፡፡

ይህም አስተማማኝ የሆነ የሀይል አቅርቦት እንዳይኖር እንቅፋት በመሆኑ፤ በመመሪያው መሰረት እነዚህን ዛፎች መቁረጥ አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል፡፡ ስለሆነም ተቋማችን በቀጣይ ሁለት ተከታታይ ወራት በአዲስ አበባ ከተማና በሌሎችም አካባቢዎች ከኤሌክትሪክ መስረተ ልማት በሶስት ሜትር አቅራቢያ የሚገኙ ዛፎችን የመቁረጥና ተያያዥ የማሻሻያ ስራዎችን ያከናውናል፡፡

ውድ ደንበኞቻችን ሥራዎቹ በምናከወንበት ቀናት የኃይል አቅርቦት በታቀደ መልኩ የሚቋረጥ መሆኑን እየገለፅን፣ ሥራው እስኪጠናቀቅ ድረስ በትዕግስት እንድትጠብቁንና ለባልደረቦቻችንም አስፈላጊውን ትብብር እንድታደርጉ በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡

በዚህ አጋጣሚ ለቅድመ መከላከል ስራው ሲባል ኤሌክትሪክ በዕቅድ የሚቋረጥባቸው አካባቢዎችን በቅድሚያ በማህበራዊ ሚዲያ ገፆቻችን የምናሳውቅ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት


በአዲስ አበባ እና ፊንፊኔ ዙሪያ የመልሶ ግንባታ ሥራ ለማከናወን ሲባል በዕቅድ የሃይል አቅርቦት የሚቋረጥባቸውን አካባቢዎች ለማየት ድረ-ገፃችንን ይጎብኙ፡-
http://www.eeu.gov.et/power-interruption/detail/1039?lang=am


በብልሽት ምክንያት የተቋረጠ የኃይል አቅርቦት
****************
ከባህርዳር ዳንግላ በተዘረጋው 66 ኪሎ ቮልት የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ላይ ብልሽት በማጋጠሙ ከዛሬ ጠዋት ጀምሮ በአዊ፣ቻግኒ እና ግልገል በለስ ከተሞች የኃይል አቅርቦት ተቋርጧል፡፡
ስለሆነም ጥገና ተከናውኖ አገልግሎቱ እስኪመለስ ድረስ ክቡራን ደንበኞቻችን በትዕግስት እንድትጠብቁን በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡
#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት


26 የገጠር ከተሞችንና መንደሮችን የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ማድረግ ተቻለ

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በተጠናቀቀው የ2017 በጀት አመት የመጀመሪያ ሩብ አመት 26 የገጠር ከተሞችንና መንደሮችን የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ በማድረግ የዕቅዱን 84 በመቶ ማሳካት ችሏል፡፡

ተቋሙ 120 ሺህ አዳዲስ ደንበኞችን የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ለማድረግ አቅዶ 90 ሺህ 573 አዳዲስ ደንበኞችን የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ አድርጓል፡፡

በተመሳሳይ በተጠናቀቀው ሩብ አመት ከልዩ ልዩ የገቢ ምንጮች 11.15 ቢሊዮን ብር መሰብሰብ የቻለ ሲሆን ከኢነረጂ ሽያጭ 8.2 ቢሊዮን ብር፣ 2.77 ቢሊዮን ብር እና ከማያገለግሉ ንብረቶች ሽያጭ 183 ነጥብ 3 ሚሊየን ብር መሰብሰብ ችሏል፡፡

ተቋሙ ካሉት የድህረ ክፍያ ደንበኞች ውስጥ 87.1 በመቶ የሚሆኑ ደንበኞች በተዘረጉ ዘመናዊ የክፍያ አማራጮች ወርሃዊ የኤሌክትሪክ ፍጆታ ሂሳባቸውን እየከፈሉ ይገኛሉ፡፡

በሩብ አመቱ 40 ሺህ 634 ስማርት ቆጣሪዎችን ለመግጠም ታቅዶ 38 ሺህ 435 ስማርት ቆጣሪዎችን በመግጠም 92.56 በመቶ ማሳካት ተችሏል፡፡

የውጭ ምንዛሬ ዕጥረት፣ የሃይል ብክነት፣ የወሰን ማስከበር ችግር፣ የግብዓት እቃዎች ዋጋ መናር፣ የኤሌክትክ መሰረተ ልማት ስርቆት፣ የፕሮጀክቶች አፈጻፀም መጓተት እና የሃይል ማከፋፈያ ጣቢዎች መሙላት በሩብ አመቱ የታዩ ዋና ዋና ተግዳሮቶች ነበሩ፡፡

ጥራት ያለውና አስተማማኝ የኤሌክትሪክ አገልግሎት መስጠት፣ የሃይል ብክነትን መቀነስ፣ የደንበኛን ቁጥር መጨመር፣ የገቢ አሰባሰብ ስርዓትን ማሻሻል እና የደንበኛ እርካታ ማሳደግ በቀጣይ ትኩረት የሚደረግባቸው ጉዳዮች ናቸው፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት


በአፍዴራና ዳሎል አካባቢ ላሉ የጨውና ፖታሽ አምራች ኢንዱስትሪዎች ኤሌክትሪክ ለማቅረብ እየተሰራ ነው

በአፋር ክልል ለሚገኙ የጨውና ፖታሽ አምራች ኢንዱስትሪዎች እንዲሁም 38 የገጠር ከተሞችና መንደሮች የ24 ሰአት የኤሌክትሪክ አገልግሎት ለማቅረብ እየተሰራ ነው፡፡

ለፕሮጀክቱ ከ19 ሚሊየን በላይ የአሜሪካን ዶላርና ከ100 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የሚደረግ ሲሆን ወጪው በአፍሪካ ልማት ባንክና በኢትዮጵያ መንግስት የሚሸፈን ይሆናል፡፡

የፕሮጀክቱ ስራ ከ2014 ዓ.ም ጀምሮ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ፕሮጀክቶች ፖርትፎልዮ ማኔጅመንት አማካኝነት እየተከናወነ የሚገኝ ሲሆን እስካሁን ባለው ሂደት ለፕሮጀክቱ የሚያስፈልጉ 4,929 ፖሎች ተመርተዋል፡፡

በአፍዴራ ሳይት 469 የመካከለኛ ቮልቴጅ መስመር ምሰሶ ተከላ ተከናውኗል፡፡ በተጨማሪም ለግንባታው የሚያስፈልጉ ከውጭ ሃገር የገቡ ኮንዳክተር፣ ኢንሱሌተርና ሌሎች ግብዓቶች ፍተሻ ተከናውኗል፡፡

በግንባታ ሂደት ያጋጠሙ ችግሮችን ለመፍታት ከአፋር ክልል ውሃና ኢነርጂ ቢሮ ኃላፊዎች ጋር ምክክር በማድረግ መዋቅራዊ አሰራር ማስቀመጥ መቻሉን ለማወቅ ተችሏል፡፡

ፕሮጀክቱን በዚህ ዓመት ለማጠናቀቅ ዕቅድ ተይዞ እየተሰራ ይገኛል፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት


የጥገና ሥራ ለማከናወን ሲባል የሚቋረጥ የኃይል አቅርቦት

እሑድ ህዳር 15 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 12፡00 እስከ ቀኑ 7፡00 ሰዓት ድረስ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በቃሊቲ 2 የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ላይ የጥገና ስራ ስለሚያከናውን በሃና ማርያም፣በብሄረ ፅጌ፣ በአዲስ ጎማ ፋብሪካ፣ በሳሪስ፣ በቦሌ ቡልቡላ፣ በአዋሽ ቆዳ ፋብሪካ፣ በአዲስ ሰፈር፣ በኦሳካ ብረታ ብረት ፋብሪካ የኤሌክትሪክ አቅርቦት ተቋርጦ ይቆያል፡፡
ስለሆነም በተጠቀሱት አካባቢዎች የምትገኙ ክቡራን ደንበኞቻችን ይህንን ተገንዝባችሁ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት እንድታደርጉ በአክብሮት እናሳስባለን፡፡
#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት


አዲሱን የአሰራር ስርዓት በአግባቡ ተግባራዊ በማድረግ የአገልግሎት አሰጣጡን ማሻሻል ይገባል

አዲሱን የአሰራር ስርዓት በአግባቡ ተግባራዊ በማድረግ የተቋሙን አገልግሎት አሰጣጥ ማሻሻል እንደሚገባ ዛሬ በተጀመረው 5ኛው ዙር ዓመታዊ የሥራ መሪዎች የምክክር መድረክ ላይ ተገልጿል፡፡

በዕለቱ በአዲሱ የአሰራር ስርዓት ትግበራ ዙሪያ ገለፃና ማብራሪያ የተሰጠ ሲሆን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣውን የሃይል ፍላጎት መመለስ፣ ጥራት ያለውና አስተማማኝ የኤሌክትሪክ አገልግሎት መስጠት እንዲሁም የኤሌክትሪክ ተደረሽነትን እውን ይገባል ተብሏል፡፡

የአገልግሎት አሰጣጥን ማሻሻል፣ የደንበኞችን የእርካታ ደረጃ ማሳደግ እና የመልካም አስተዳደርና ብልሹ አሰራር ችግሮችን መቅረፍ እና የመሳሰሉት ወቅቱ የሚጠይቃቸው ጉዳዮች በመሆናቸው በየደረጃው የሚገኘው አመራርና ሰራተኛ በትኩረት ሊሰራ እንደሚገባ በመድረኩ ተገልጿል ፡፡

በተጨማሪም ተቋማዊ የስራ ባህልን ማሻሻል፣ የደንበኛ ቁጥር መጨመር፣ እና የሃይል መቆራረጥ ድግግሞሽን መቀነስ ፣ የሃይል ብክነትን መቀነስ፣ የደንበኛ ቅሬታ መፍታት እንዲሁም የመረጃ አያያዝ ስርዓትን ማዘመን እንደሚገባ ተጠቁሟል፡፡

በአዳማ ከተማ እየተካሄደ በሚገኘው ዓመታዊ የሥራ መሪዎች የምክክር መድረክ የተቋሙ ስራ አስፈጻሚዎች፣ የሪጅን ማስተባበሪየሳ ፅ/ቤት ሃላፊዎች፣ የመሰረታዊ ሰራተኛ ማህበር አመራሮች፣ የሪጅን ዳይሬክተሮች እና የአገልግሎት መስጫ ማዕከል ስራ አስኪያጆች እየተሳተፉ ይገኛሉ፡፡

#የኢትዮጵያኤሌክትሪክአገልግሎት

6.1k 0 33 10 68


Показано 10 последних публикаций.