እንማር


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Цитаты


እዚህ Channel ላይ ያስተምራሉ ያዝናናሉ ብለን የምናስባቸውን
🎯 መፅሀፎች
🎯ተከታታይ ልቦለድ
🎯ግጥም
🎯ፍልስፍና
🎯ምክር
የተለያዩ PDF መፅሐፍት እንደፍላጎቶ አሉ
    Ads - @Kiya988
https://youtube.com/channel/UCr7-LDddhyqtFUCH0OHhM2Q
Buy ads: https://telega.io/c/Enmare1988

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Цитаты
Статистика
Фильтр публикаций


✅️ምርጥ ምርጥ መጽሀፎችን በስልካችሁ ማግኘት ትችላላችሁ!
የኢትዮጵያ ዲጅታል ላይብረሪ (Ethiopian Digital Library)
በተጨማሪም
ለትምህርታዊ መፅሀፍቶች
ቴክኖሎጂ መፃሀፍቶች
የሳይንስ መጽሀፍቶች
ሪሰርቾችንና ፕሮፖዛሎች
የሳይኮሎጅ መጽሀፍት
የኮምፒውተር ቴክኖሎጂ መጽሀፍት
የመደበኛ ተማሪዎችን መጽሀፍትን፣
የሶሻልና የናቹራል መጽሀፎች
የዩኒቨርስቲ የመማሪያ ሀንዳውት፣
የቴክኒክና ሙያ ሞጁሎችን
የጥያቄና መልስ
ወርክ ሽቶች

✅የሚያገኙበት ትልቁ
የኢትዮጵያ ዲጅታል ላይብረሪ (Ethiopian Digital Library) በመግባት ማግኘት ይችላሉ።
ጊዜው የቴክኖሎጂ ነው አብረው ከቴክኖሎጂ ጋር ይጓዙ!

👇👇የቴሌግራም ቻናሉ👇👇👇👇
✈️https://t.me/EthiopiaDigitalLibrary
✈️https ://t.me/EthiopiaDigitalLibrary
https://t.me/EthiopiaDigitalLibrary


🟪🟥🟦
🔵የ አዶቤ ፎቶ ሾፕ ሙሉ ትምህርት በአማርኛ


🟡😄ማንኛውንም አይነት የህትመት ስራዎች ለመስራት ይጠቅማችሃል።
ትምህርቱ አዶቤ ፎቶሾፕ ሶፍትዌርን ይጠቀማል።


📱https://t.me/EthioLearning19/2591
📱https://t.me/EthioLearning19/2591


....የ8ኛ ክፍል ተማሪዎች እንደነበርን ነው...

አንድ ቀን የሆነ አስተማሪያችን ቀረ....በዛ ክፍት ክፍለጊዜ ሁላችንም ደስ ያለንን ስንሠራ ነበር

አብዛኞቻችን ወሬና መንጫጫት ላይ ነበርን።

...አንድ ምስጋናው የሚባል የክፍላችን ልጅ ብላክቦርድ ላይ በወዳደቀ ቾክ ሁለት ሰወችን ሳለ።

ሥዕል ስላችሁ ይሄ ዝም ብሎ የልጅ ሥዕል አይደለም፣ ባስታወስኩት ቁጥር የሚገርመኝ የግንባራቸው መስመር፣ ፊታቸው ላይ ያረፈው ጥላ ልብሳቸው ላይ ያለው ፓተርን ሳይቀር ፎቶ የሚመሳስሉ ፖርትሬቶች...

...ደግሞ የሳለው ምንም እያየ አልነበረም።

...እማሆይ ቴሬሳ ሁለት እጆቻቸውን እንደህንዶች ሰላምታ አገናኝተው ግንባራቸውን እንዳስነኩ እጃቸው መሀል መቁጠሪያ ተንጠልጥሎ፣ እንዲሁም ቀዳማዊ ኃይለስላሴ ከነ ንጉሳዊ ልብሳቸው ወደጎን ዞር ብለው።

ሁላችንም በምስጋናው የሥዕል ችሎታ ተገረምን ተደነቅን።

ቀጣዮ ክፍለግዜ ጅኦግራፊ ነበር...

ኮስታራው አስተማሪያችን ገባና ሥዕሎቹን ዓየት አድርጎ "ማነው የሳለው?" አለ ።

በአንድ አፍ "ምስጋናው" አልን በአድናቆት ጭምር።

መምህሩ ወደምስጋናው ወንበር ተራምዶ የያዘው ልምጭ ተሰባብሮ እስከሚያልቅ ምስጋናውን ቀጠቀጠው።

እና በቁጣ "ይሄ የተከበረ የትምህርት ገበታ ነው ! ማንም እየተነሳ የሚፀዳዳበት አይደለም ደደብ" ብሎ ደነፋ።

ዳስተሩን አንስቶ አንዴ እጁን ሲያስወነጭፈው ኃይለስላሴን ለሁለት እማሆይ ቴሬሳን አናታቸውን ገመሳቸው።

አጠፋፍቶ ማስተማሩን ቀጠለ። ምስጋናው ከዛ በኋላ እንኳን ሰሌዳ ላይ ወረቀት ላይ ሲስል አላስታውስም።

...ብዙ ዓመታት አለፉ።

አንድ ቀን አዲስ አበባ ፒያሳ መርከብ የምትባል ምግብ ቤት ምሳ በልተን ስንወጣ በር ላይ አንድ የጎዳና ተዳዳሪ በፌስታል ፍርፋሪ ሲበላ ዓየሁ ምስጋናው ነበር።

ቢጎሳቆልም አልጠፋኝም ነበር።

ዛሬ በምን አስታወስኩት? አንድ አሜሪካዊ ህፃን ሰሌዳ ላይ በቾክ የሳለው ስዕል በአስተማሪዎቹ እና በትምህርት ቤቷ ርዕሰ መምህር ስለተደነቀ በቀስታ ሰሌዳውን አንስተው አንድ ቢሮ ግድግዳ ላይ እንደሰቀሉት አነበብኩ።

ሥዕሉ ለዓመታት እንዲቆይ የሆነ ነገር እናስደርጋለን ብላለች ርዕሰ መምህርቷ።

ሀገር ባከበረቻቸው ትከብራለች ባከሸፈቻቸው ትከሽፋለች።

(wegoch)
(በአሌክስ አብርሃም
)

3.2k 0 20 5 144

ይህ ደብዳቤ በ1939 በጦርነት ከሞተ ወታደር
ኪስ ውስጥ የተገኘ ነበር!💔

አንዳንድ ጊዜ ሁኔታዎች ከገባናቸው ቃላቶች ይበልጡና።
ቃለ-አባይ ያስመስሉናል 😢

ቃላችን እንዳይሳካ ያደረገው ያለአቅማችን መመኘታችን አልነበረም። የነገሩ ግዝፈት አቅማችንን ቀጭቶ እንዳይፈፀም አደረገብን እንጂ!

3.4k 0 23 86 116

"ትክክለኛው ጥያቄ :
ከሞት በሗላ ህይወት አለ ወይስ የለም የሚለው ሳይሆን ከመሞትህ በፊት እየኖርክ ነው ወይ??የሚለው ነው።"

osho

✈️@Enmare1988
✈️@Enmare1988

6.2k 0 35 23 175

አንድን ፈላስፋ
እውነተኛ ጓደኝነትን እንዴት ትገልፀዎለህ? ተብሎ ሲጠየቅ

"እውነተኛ ጓደኝነት ማለት በሁለት እና ከዚያ በላይ በሆኑ አካላት ውስጥ የሚገኙ ነፍሶች ውህደት ነው።"

'አስመሳይ ጓደኛንስ እንዴት ትገልፀዎለህ??' ተብሎ ሲጠየቅ

"አስመሳይ ጓደኛ በፀሀይ ወቅት ጥላውን ይሰጥሃል፣ዝናብ በመጣ ጊዜ ግን የሰጠህን ጥላ ይነጥቅሃል።"በማለት ነበር በአጭሩ የገለፀው።

በህይወታችን ፀሃያማ ዘመናት ውስጥ የነበሩ፣ በዝናቡም የህይዎት ጉዟችን ውስጥ ጥላቸውን ሳይነፍጉን የቀጠሉት ምን ያህሎች ይሆኑ????

6.3k 0 72 7 134

✔️ በአንድ ወቅት ትኖር የነበረች በህይወቷ ሙሉ አንድም በጎ ነገር ያልሰራች፣ በክፉ ስራዎ ብቻ የምትታወቅ ሴት ነበረች።ታዲያ ይህች ክፉ ሴት ስትሞት፣ነፋሷ ወደ አሳት ባህር ትወረወራለች።

✔️ ይህቺን ሴት ይጠብቅ የነበረ መላዓክ፣በህይወት በነበረችበት ወቅት የሰራችው በጎ ስራ ካለ በሚል ለማስታወስ ሲሞክር፣ በአንድ ወቅት ይለምን ለነበረ ሰዉ የሰጠችዉ ፣አንድ ራስ ሽንኩርት እንደነበረ ያስታዉሳል።

መልዓኩ'ም ወደ እግዜር በመቅረብ "በአንድ ወቅት ይለምን ለነበረ ሰዉ ሽንኩርት ሰጥታ ነበር...ይህ ሊያድናት አይችልምን...."ሲል ይጠይቃል።

እግዜር'ም ..."ሽንኩርቱን በመያዝ ልታወጣት ትችላለህ!!"ሲል ፈቃዱን ይሰጠዋል።

መለዓኩ'ም፣ ወደ አሳት ባህሩ ዝቅ በማለት ሽንኩረቱን ይሰጣታል።እሷም ሽንኩርቱን በመያዝ ቀስ በቀስ ከእሳቱ እየወጣች ሳለ፤የእሷን መዉጣት የተመለከቱ ሌሎች በእሳት ባህሩ ዉሰጥ የነበሩ ሃጢያተኞች፣አግሯን በመያዝ ፣ከእሷ ጋር አብረዉ ለመዉጣት ይሞክራሉ።

ሴትየዋም በቁጣ እየጮኸች..."ይህ የእኔ ሽንኩርት ነዉ!!!!የእኔ ብቻ ነዉ!!!" በማለት አሷ ላይ ተንጠላጥለው ለመወጣት የሚሞክሩትን፣ እየመታች እግሯን ለማስለቀቅ ትሞክራለች።

በዚህን ጊዜ ሽንኩርቱ ከእጇ ያመልጣትና እሳት ባህሩ ዉስጥ ይወድቃል፤እሷም ተመልሳ ወደ እሳት ባህሩ ወደቀች....

በምህረት ለመዳን የነበራትን ብቸኛ እድል፣በእራስ ወዳድነቷ ምክንያት አጣችዉ!!!!!

Brother Karamazov ከሚለዉ የዶስቶቭስኪ መፀሃፍ የተወሰደ

selfishness and lack of compassion can destroy even that chance


✈️@Enmare1988
✈️@Enmare1988

6.2k 0 31 2 162

✔️ፈገግታህ አለምን ይቀይር እንጂ ፤አለም ፈገግታህን እንዲወስድብህ አትፍቀድ።ደስታ ሁሉንም ነገር ማግኘት ሳይሆን ባለህ ነገርሮች መደሰት ነዉ።

✈️@Enmare1988
✈️@Enmare1988

6.7k 0 37 1 119

ዉሃ ያለ አሳ ዉሃነቱን አያሳጣዉም፤ አሳ ግን ያለ ዉሃ ምንም ነዉ፣አፈር ያለ ዛፍ አፈርነቱን አያሳጣዉም፤ዛፍ ያለ አፈር ግን ምንም ነዉ፣እግዚአብሔር ያለ ሰዉ ፈጣሪ መሆኑን አያሳጣዉም፤ ሰዉ ግን ያለ እግዚአብሔር ምንም ነዉ።
አሳ ከዉሀ ከወጣ እንደሚሞተዉ፣ዛፍንም ከአፈር ከለየኸዉ እንደሚሞተዉ ሁሉ፣ሰዉም በተመሳሳይ ከአምላክ ጋር ያለዉ ግንኙነት ከተቋረጠ ይሞታል።ህይወት የሚቀጥለዉ ከአምላክ ጋር ያለን ግንኙነት እስከጠበቀ ድረስ ብቻ ነዉ።

ፈጣሪን የምናመሰግንበትን አንደበት ሰዉን ለማማት፣ሰዉን ለመስደብ አንጠቀምበት!!!!!

✈️@Enmare1988
✈️@Enmare1988

7.6k 0 81 11 313

ህይወት እንደ ማስታወሻ ደብተር ናት።ሁለቱ ገፆች በእግዜር የተፃፉ ናቸዉ።የመጀመሪያው ገፅ የተወለድንበት ቀን ሲሆን ፤የመጨረሻው ገፅ ደግሞ የመሞቻ ቀናችን ነዉ።በመሀል ያሉትን ባዶ ገፆች በፍቅርና በመልካምነት አኛ የምንሞላቸዉ ናቸዉ።

✈️@Enmare1988
✈️@Enmare1988

8k 0 56 4 163

የመጨረሻ ጊዜ eye-contact የነበረንን ጊዜ የሚያስታውሰው አይመስለኝም። እንኳን እሱ እኔ አላስታውስም። ለትንሽ ሰከንድ ትክ ብዬ አይኑን ባየው አፌ ያላወጣውን አይኔ የሚዘረግፈው ይመስለኛል።

      "የማውቅህ ተንገብግቤ ያገባሁት ሰው አይደለህም፥ ባሌን የት አደረስከው?!" ብሎ አይኔ እንዳይለፈልፍ ነው የምሸሽው

       አንዳንዴ የአምሳል ምትኬን "አንድ ነገር ጎድሏል" የሚለውን ዘፈኗን ከፍቼ መጠበቅ የሚያምረኝ ቀን ይበዛል። ለአንድ እኔ የማይበቃ ሰው እንዴት የሁለት ሶስት ልጆች አባት ይሆናል ብዬ እብሰለሰላለሁ። ንግግሩ የሚያደርገው ነገር በሙሉ ያበሳጨኛል።

      እንዴት አይቶኝ አይረዳም ብዬ እስከመጨረሻው እንዳልናደድ ደሞ የኔንም ድክመት አየዋለሁ። ፍላጎቴን በሙሉ ከአኳኋኔ ሁሌ ሊረዳ አለመቻሉን ማወቅ አለብኝ አይደል?!

     ግን "ነገር እና ጭራ ከወደኋላ ነው" እንዲሉ የእሱም ግድ የለሽነት የኔም ራሴን አለማስረዳት ያኔ መጀመሪያ ለምን አልበጠበጠንም ነበር?! ያኔ እንቻቻል ስለነበረ ነው? ወይስ እኔን ለማስደሰት ስለሚጋጋጥ ነው ሳልነግረው የሚገባው?

    እንጃ


✍ናኒ


https://t.me/justhoughtsss


Репост из: Thoughts


አብዛኞቻችን "ወሩ ፈጥኗል፣ጊዜዉ ፈጥኗል፣ሰአቱ ይሄዳል" እንላለን።ነገር ግን የሚሄደዉ ጊዜዉ ሳይሆን የእኛ ህይወት ነዉ። ጊዜን ማባከን አይቻልም ምክኒያቱም ጊዜ ገደብ የሌለዉና እስከ አለም ፍፃሜ ድረስ የሚቆይ ነዉ፤የአንተ ህይወት ግን ገደብ አለዉ።ጊዜ አያረጅም፣አይሞትም አንተ ግን ታረጃለህ፣ ትሞታለህ።የጊዜ ገደብህ ከማለቁ በፊት ጊዜህን ለመልካም ነገሮች ተጠቀምበት።

እራስን ከሌሎች ጋር በማወዳደር ዉድ ጊዜህን አታጥፋ።የእራስህን ሩጫ ሩጥ።ጥንቸል የመዝለል፣የመሮጥ፣የፍጥነት ፀጋ ታድላለች ነገር ግን የምትኖረዉ ለ15 አመታት ነዉ።ኤሊ ጥንቸል ማድረግ ከምትችላቸው ነገሮች አንዱንም ማድረግ አትችልም።ጭራሹን አታስበዉም።ነገር ግን 150 አመት በላይ ትኖራለች።አስታዉስ ህይወት፣በፍጥነትና ዉድድር፣ሌሎች የሰሩትን ካልሰራሁ በማለት የምንመራዉ አይደለም።ህይወታችንን በእርጋታና መልካም ነገርን በማድረግ እንምራ።እራሳችንን እንሁን የተሰጠንን እናመስግን!!!!!!!

ወደ ፊት መሄድህን ቀጥል፤ግብህ ለመድረስ ምን ያህል ርቀት እንደቀረህ አታዉቅም!!!!!!!!!!!!

7.1k 0 39 1 142

" በፈጣሪ ልጄን አድኑልኝ😭😭😭"     #አበት

ይህ ቆንጅዬ ህፃን #አሚር የሱፍ  ይባላል!በተወለደ 4ኛ ወሩ ህመም ሲያሰቃየውና እንቅልፍ ሲከለክለው እናትና አባት ወደ ጥቁርአንበሳ ሆስፒታል ይዘውት ይሄዳሉ!
ህፃን አሚር አንድ ወር አልጋ ይዞ ክትትል ካደረገ በኋላ ዶክተሮች "የልብ ክፍተት  ችግር አለበት፣ አስቸኳይ ቀዶ ጥገና ያስፈልገዋል"ተባሉ!

ልጁን ለማሳከም የተጠየቁት 1500000 ብር ነው ከአቅም በላይ ስለሆነ ልጃቸውን ለማዳን እናንተን እየተማፀኑ ነው😭 እባካችሁ #እንድረስላቸው🙏  #በዱአ #ሼር እናግዛቸው🙏
                "ለመልካም ስራ ረፍዶ አያውቅም"
#አካውንት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
1000304310937-ዩሱፍ ሀምደለ (አባት)
#ስልክ
0705740135

☞አድራሻ ካራ ቆሬ ወታደር ሰፈር

☞ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል

8.4k 1 28 10 192

ፈላስፋ 'እዉነትና ዉሸት' ሲገልፅ እንዲህ ነበር ያለዉ.....

"እዉነት እንደ ቀዶ ጥገና ነዉ።ለጊዜዉ ይጎዳሀል ግን ይድናል።ዉሸት ደግሞ እንደ ህመም ማስታገሻ ነዉ ለጊዜዉ እረፍት ይሰጥሃል ነገር ግን ችግሩ እስከ ህይወት ፍፃሜ ይቀጥላል።"


✈️@Enmare1988
✈️@Enmare1988

7.9k 0 59 1 144

1. ህይወትህ ትርጉም እንዲኖራት ዓላማ ይኑርህ፡፡

2. የአንተነትህ ትልቁ ምዕራፍ ከእውቀትህ በላይ ስራህ መሆኑን አትርሳ፡፡

3. ፈጣሪ ካልፈታው ገንዘብ ችግርህን አይፈታውም ፈጣሪ ካልሞላው ሰው ጎንህን አይሞላውም ፈጣሪ ካልገለጸ እውቀት ጥበብ አይሆንም

4. ይቺ ዓለም ለሁሉም እኩል ናት፡፡ ዛሬ ብታገኝ ነገ ታጣለህ ዛሬ ብታሸንፍ ነገ ትሸነፋለህ፡፡ ለሁሉም ጊዜ አለው የሚባል መዶሻ አለ፡፡ መልካምነት ዋጋ ያስከፍልሃልና ሁሌም ፍጹም መልካም ሰው ሁን

5. ንጹህ ልብ ልክ እንደ አበባ ናት! ፍሬ ባናገኝባትም ውበቷ ግን እጅግ ማራኪ ነው፡፡

6. የውድቀት መጀመሪያው ራስህን አዋቂና ብቸኛ አድርጎ ማሰብ ነው

6. ፍጻሜህ እንዲያምር ራስህን አታመጻድቅ ሁሌም ከስህተትህ ለመታረም ፈቃደኛ ሁን ጥፋትህን አሜን ብለህ መቀበልህ ክብርህን የሚጎዳብህ አይምሰልህ፡፡

7. ጠቢብ ሰው እንኳን ከራሱ ከሰው ስህተት ተምሮ ራሱን ይጠብቃል ይመለሳልና፡፡

8. በህይወት ውስጥ አንዱ ሲታወር አንዱ መሪ መሆን አለበት

9. እውነትነ የሚናገር ሰው አፉ ክፉ ይመስላል ልቡ ግን ንጹህ ነው

10. ህይወት በመደጋገፍ የተሞላች ናትና ወንድምህን ከመርዳት ወደሗላ አትበል!

✈️@Enmare1988
✈️@Enmare1988

7.4k 0 95 4 113

ቅጠሎች
አንዳንድ በህይወት የሚገጥሙን ሰዎች ልክ እንደ ዛፍ ቅጠሎች ናቸዉ።ለጥቂት ወቅቶች ብቻ አብረዉን የሚቆዩ፣እንደ ዛፍ ቅጠል ሁሉ ከእኛ የሚፈልጉትን ከአገኙ በኋላ በሚገጥሙን ቀላል የህይወት ነፋስና ወጀብ ወቅት አብረዉን የማይዘልቁ፤ ጊዜያዊ ጥላ ለመሆን ብቻ ወደ ህይወታችን የመጡ፣ ልንተማመንባቸዉ የማንችል በቀላሉ የሚረግፉ ደካሞች ናቸዉ።

ቅርንጫፎች
አንዳንዶች ደግሞ በዛፍ ቅርንጫፍ ይመሰላሉ።እነዚህ አይነት ሰዎች ከቅጠሎችን የታሻሉና ጠንካሮች ናቸዉ። እንደ ዛፍ ቅርንጫፎች ሁሉ ጫናዎችን ተቋቁመዉ አብረዉን ሊመዝለቅ የሚሞክሩ ቢሆንም፣ነገር ግን ሙሉ በሙሉ እምነታችንን የማንጥልባቸዉና ከባድ የህይወት ወጀብ በገጠመን ሰአት ተገንጥለዉ የሚቀሩ አይነት ሰዎች ናቸዉ።

ስሮች
ጥቂት እንደ ዛፍ ስሮች የሆኑ ሰዎች ልናገኝ እንችላለን።እነዚህ ሰዎች ስር ለዛፉ ጥንካሬና ጤንነት እንደሚታትር ሁሉ የእኛንም ህይወት በደስታና በጥንካሬ እንድንመራና ቀጥ ብለን እንድንቆም የሚረዱን ፣ልክ እንደ ዛፍ ስር ሁሉ በህይወት የሚገጥሙንን ወጀቦች እንድንቋቋም የሚያደርጉን፣ የሚመግቡን፣የሚያጠጡን ልዩ የሆኑ ሰዎች ናቸዉ።

ዛፎች ብዙ ቅጠሎች፣ ቅርንጫፎችና ጥቂት ስሮች አሏቸው።የአንተን/ቺን ህይወት ተመልከቱ ምን ያህል ቅጠሎች፣ቅርንጫፎችና ስሮች አሏችሁ?እናንተስ በሌሎች ህይወት ዉስጥ የቱኛዉን ናችሁ?


"እናቴ በልጅነቴ የምትነግረኝን ሁሌም አስታዉሰዋለሁ 'የሰዉ ልጅ ሽልማት ይሸልምሀል፤አምላክ ግን ስጦታ ይሰጥሃል!!' እያለች ትነግረኝ ነበር።

ዝናብ እንዲዘንብልህ ከፀለይክ፣ጭቃዉን ለመጋፈጥ መዘጋጀት አለብህ!!!!!!"

ዴንዝል ዋሽንግተን(actor)

✈️@Enmare1988
✈️@Enmare1988

7.7k 0 54 6 183

ለአሸናፊነት_መገዛት_ትርጉም_ማኅሌት_ጥላሁን_እና_ዳኜ.pdf
2.8Мб
📚ርዕስ :-ለአሸናፊነት መገዛት

😀ደራሲ: ቪቭ ኬራ

👤ተርጓሚዎች:- ማህሌት ጥላሁንና ዳኜ መላኩ

✔️ዘውግ:- ስነ ልቦና

📖የገጽ ብዛት:-256



በጥያቄያችሁ መሰረት በመላው አለም በ8 ቋንቋዎች ተተርጉሞ ከ1,000,000 ቅጂዎች በላይ የተሸጠውን ለአሸናፊነት መገዛት የተሰኘውን ድንቅ መፅሀፍ  እነሆ አልናችሁ ...

"
#ከሁሉም_ከሁሉም_በፊት_ማድረግ_ያለብህ

✔️ማንንም ከመፍራትህ በፊት
ፈጣሪህን ፍራ❗️

✔️ማንንም ሰው ከማገዝህ በፊት
ራስህን አግዝ

✔️ ማንንም ከማድመጥህ በፊት
ትክክል እንደሆነ ህሊናህ የሚነግርህን እውነት አድምጥ!

✔️ስለማንም ሰው ሁኔታ ከሌሎች ሰዎች ጋር ከማውራትህ በፊት
ስለራስህ ጉዳይ ከራስህ ጋር አውራ

✔️ያልሆነልህንና የሆነብህን ሁን ከማሰላሰልህ በፊት
የሆነልህንና ያልሆነብህን አሰላሰል!

ሁሉም ደህና ይሆናል!

🥇አሸናፊዎች የተለዩ ነገሮችን የሚያደርጉ ሳይሆኑ፣
ነገሮችን በተለየ መንገድ ሚያደርጉ ናቸው!!!
🏆

🎀🎀🎀
                 ከመፅሀፉ የተቀነጨበ


✈️@Enmare1988
✈️@Enmare1988


✔️#በሕይወት_አሸናፊ_ለመሆን_ለአሸናፊነት_ተገዛ!!



እነሆ የመጽሐፉ የጀርባ መልዕክት
👇👇👇

💠ሕይወት ትግል ናት።

ሕይወት እንድትታገላትና እንድታሸንፋት ሜዳ አዘጋጅታ የምትጠብቅ ቆንጆ ትግል ናት። ለአሸናፊነት ተገዝተህና የማሸነፊያ መሳሪያህን ታጥቀህ ስታሸንፋት ደግሞ ስኬትን እንደ ካባ ታለብስሃለች፤ በአደባባይም ታነግስሃለች።

በሕይወት፦

#ስኬት ጥረት ነው፤ መንገዱንና ሂደቱን እየቀያየርክ እንድታሳካው ይፈልጋል።

#ጤና ሕይወት ነው፤ እንድትጠብቀው፣ እንድትንከባከበው ይፈልጋል።

#ደስታ ምርጫ ነው፤ በየቀኑ የሚገጥሙህን ሀዘኖች በማሸነፍ ፈገግ እንድትል ይፈልጋል።

ታዲያ የተሰማራህበት ዘርፍ፣ የዕለት ተዕለት መንገድህ፣ ሕልምህ፣ ራእይህ፣ ሰላምህና ደስታህ፣ በአጠቃላይ ሕይወትህ በስኬት የተሞላ ይሆን ዘንድ ለአሸናፊነት መገዛት አለብህ።

✔️#ለአሸናፊነት_ተገዛ- አሸናፊነት ስኬታማነት ነውና!
✔️#ለአሸናፊነት_ተገዛ- ጤናህ የየዕለት ክትትልህ ውጤት ነውና!
✔️#ለአሸናፊነት_ተገዛ- ሰውነትህ የየዕለት ስፖርትህ ውጤት ነውና!
✔️#ለአሸናፊነት_ተገዛ-ስምህ በየዕለቱ የገነባኸው ምግባርህ ነውና!
✔️#ለአሸናፊነት_ተገዛ- ሀብትህ የዕለት ጥረትህና ቢዝነስህ ውጤት ነውና!
✔️#ለአሸናፊነት_ተገዛ- ስኬትህ የልፋትህ፣ የትግልህና የጥረትህ ውጤት ነውና!


✈️@Enmare1988
✈️@Enmare1988

Показано 20 последних публикаций.