በብፁዕ አቡነ ፊልጶስ የደቡብ ኦሞና አሪ ዞኖች ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት በቡስካ ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም እና አቡነ ሙሴ ጸሊም ገዳም የልማት ሥራዎችን ጎበኙ።
ዘጋቢ መ/ር አቤል አሰፋ
(#EOTCTV ጥር 4 ቀን 2017 ዓ.ም ቡስካ)
➕➕➕➕➕➕➕➕➕➕➕➕➕➕➕➕➕
በሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ላስታ ወረዳ ከሚገኘው ኃይላ ለጥበብ ተከዜ ሐዋርያ ክርስቶስ አንድነት ገዳም አካል የሆኑትና በደቡብ ኦሞና አሪ ዞኖች ሀገረ ስብከት የሚገኙት የቡስካ ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም እና አቡነ ሙሴ ጸሊም ገዳም እና የኦሞ ብሔረ ብፁዓን አቡነ ዜናማርቆስ እና አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ አንድነት ገዳም የልማት ሥራዎች ተጎብኝተዋል።
ብፁዕነታቸው በኦሞ ወንዝ ላይ በጀልባ ተጉዘው በደቡብ ኦሞ ዞን በዳሰነች ወረዳ የሚገኘውንና ከኦሞ ወንዝ በተጠለፈ መስኖ በ500 ሄክታር ላይ የሚለማውን ሜካይዝድ እርሻ ጎብኝተዋል።
ገዳሙ የኦሞን ወንዝ በመጥለፍ ለመስኖ የሚሆን ከአንድ ኪሎ ሜትር በላይ የውሃ ካናል ግንባታ ያጠናቀቀ ሲሆን ከዋናው ካናል ወደ እርሻ የሚያስገቡ የውሃ መፋሰሻዎች ሥራ ያለበተትን ደረጃ ተመልክተዋል።
ከፍተኛ አቅም ያላቸው ለውሃ መሣቢያ ሞተሮች በገዳሙ የደረሱ ሲሆን 120 ሄክታር የሚሆነውን የእርሻ መሬት ለዘር የማዘጋጀቱ ሥራ መጠናቀቁን ገዳሙ አስታውቋል ።
ከዋናው እርሻ ጎን ለጎን የለማውን የሙዝ እርሻም በጉብኝቱ ተመልክቷል ።
ብፁዕነታቸው በደቡብ ኦሞ ዞን ሐመር ወረዳ የሚገኘውን የቡስካ ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም እና አቡነ ሙሴ ጸሊም ገዳም የልማት ሥራዎችንም ተመልክተዋል።
በደቡብ ኦሞ ሀገረ ስብከት በሁለቱ ገዳማት ከ400 በላይ መነኮሳት እና መነኮሳይያት የሚገኙ መሆኑን የገለጹት የገዳሙ አፈ መምህር አባ ወልደኪዳን ሐዋርያክርስቶስ ገዳማቱ በአንድ አበምኔትና በአንድ አፈ መምህር በአንድ መዋቅር የሚተዳደሩ አንድነት ገዳማት መሆናቸውን ገልጸዋል።
የቡስካ ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም እና አቡነ ሙሴ ጸሊም ገዳም መነኮሳት እና መነኮሳይያት ከገዳማዊ ሕይወት ጎን ለጎን በስልብስ ስፌት ሹራብ ሥራና አልባሳት ልማት ዘርፍ እንዲሁም በማር ምርት ውጤታማ ሥራ በማከናወን ላይ እንደሚገኙ በጉብኝቱ ተገልጿል ።
ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ የደቡብ ኦሞና አሪ ዞኖች ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት በገዳማቱ ለሚገኙ መናንያን ትምሕርተ ወንጌል እና የሥራ መመሪያ ሰጥተዋል።
በጉብኙቱ ላይ መጋቤ ካህናት አባ ሀብተጊዮርጊስ አሥራት የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት የገዳማት አስተዳደር መምሪያ ሓላፊ ፣ መልአከ ሰላም አባ ገብረመስቀል ካሳሁን የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ የአስተዳደር የተማሪዎች ዲን; የደቡብ ኦሞ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ መልአከ መንክራት ቆሞስ አባ ሥምረተአብ እሸቱ የገዳማቱ አበምኔት ባሕታዊ አባ ኪዳነ ማርያም ገብረ እግዚአብሔር ተገኝተዋል ።
#የቤተ ክርስቲያን የሆነውን ብቻ!
+++++++++++++++++++++++++++++++++++++
https://youtu.be/Wqgq1KebrOo 🇪🇹 "የቤተክርስቲያን የሆነውን ብቻ" 🇪🇹
ተቋሙን በገንዘብ ለማገዝ፡-
የመገናኛ ብዙኃን ሥርጭት አገልግሎት ድርጅት EOTC(BSA)
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1000165122406
ዓባይ ባንክ 1462319237132015 🎥
📱 የዲጂታል ሚዲያ ገጾች💻
ለመረጃ 📞 +251985585858
➽ የዩቲዮብ ገጻችን
http://www.youtube.com/c/eotctv➽ የፌስ ቡክ ገጻችንን
https://www.facebook.com/eotctvchannel➽የቴሌግራም ገጻችን
https://t.me/eotctvchannel➽ የቲክ ቶክ ገጻችን
https://vm.tiktok.com/ZMFSxXdUf/➽ የዩቲዮብ ገጻችን Eotc tv 2
https://youtu.be/Wqgq1KebrOo➽የትዊተር ገጻችን
https://twitter.com/EotcT/➽የኢንስታግራም ገጻችን
https://www.instagram.com/p/CknRF0MtB77/?igshid=MDJmNzVkMjY=