Ethiopian Construction Work Professionals - ETCONp


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Карьера


🔨እጅግ ጠቃሚ የ ኮንስትራክሽን ትምህርቶች
💵የ ኮንስትራክሽን እቃዎች ሻጭ እና ገዢ ሚገናኙበት
📐ውብ ውብ የ ቤት ዲዛይናኖች
💻ሶፍትዌሮችና ሴታፖችን
📙መፅሃፍቶች
🎬ቪድዮዎቾ ምታገኙበት ቻናል
📨ሃሳብና ኣስተያየት @Philemona7 ወይ @ETCONpBOT ፃፉልን
📌ጨረታ ና ስራ @ETCONpWORK
📃 ለ መወያያ @COTMp
📍ዲጂታል ቤተ መፅሃፍ @ETCONpDigitalLibrary_Bot

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Карьера
Статистика
Фильтр публикаций


👉የግንባታ ተቆጣጣሪ መሒንዲሶች (𝐒𝐮𝐩𝐞𝐫𝐯𝐢𝐬𝐨𝐫) ዋና ዋና ሥራዎች

🏷የግንባታ ተቆጣጣሪ መሐንዲስ (𝔖𝔲𝔭𝔢𝔯𝔳𝔦𝔰𝔬𝔯) የአንድ ፕሮጀክት ግንባታ ሂደት በአስተማማኝ፣ በብቃት እና ሀገሪቷ በምትጠቀምባቸው የግንባታ መሪ ሰነዶች (𝔰𝔱𝔞𝔫𝔡𝔞𝔯𝔡𝔰) መሰረት መከናወኑን የመቆጣጠርና የማረጋገጥ ኃላፊነት አለባቸው።

ተቆጣጣሪዎች ለግንባታ ባለቤት እና ተቁቅራጭ ዋና ዋና የግንባታ ውስንነቶችን ወይም 𝔠𝔬𝔫𝔰𝔱𝔯𝔞𝔦𝔫𝔱𝔰 ተብለው የሚታወቁትን (ወጪ ገንዘብ፣ ጥራት እና ጊዜ) በአግባቡ ለመጠቀም እና ከማንኛውም ግጭት ወይም ቅሬታ ነጻ ለማድረግ የሚሰየሙ አካላት ናቸው።

⭐️ጠቅላል ሲል የሚከተሉት የሥራ ድርሻዎች አሉባቸው።

[1] የጥራት ቁጥጥር - 𝑸𝒖𝒂𝒍𝒊𝒕𝒚 𝒄𝒐𝒏𝒕𝒓𝒐𝒍፦ የግንባታ ስራዎች የተቀመጡትን ደረጃዎች (𝚜𝚝𝚊𝚗𝚍𝚊𝚛𝚍𝚜) እንዲያሟሉ እና የፕሮጀክቱን የጥራት መስፈርቶች እንዲያከብሩ የስራውን ጥራት መከታተል

[2] የጊዜ አስተዳደር - 𝑻𝒊𝒎𝒆 𝒎𝒂𝒏𝒂𝒈𝒆𝒎𝒆𝒏𝒕፦ ፕሮጀክቱን በተያዘለት የጊዜ ሰሌዳ (መርሐግብር) መሰረት እንዲጠናቀቅ የግንባታ ሂደቱን በየጊዜው መመዘንና መከታተል፣ መዘግየቶችን መለየት እና በፕሮጀክቱ የጊዜ ሰሌዳ ላይ ተጽዕኖ ሊያሳርፉ የሚችሉ ችግሮችን ለማስወገድ የእርምት እርምጃዎችን መውሰድ

[3] የሀብት አስተዳደር - 𝑹𝒆𝒔𝒐𝒖𝒓𝒄𝒆 𝑴𝒂𝒏𝒂𝒈𝒆𝒎𝒆𝒏𝒕፡ ለተገቢ ተግባራት ተገቢውን ግብአት መመደብ፣ ትክክለኛ ሰውን ለትክክለኛው ስራ በትክክለኛው ጊዜ መመደብ፣ የቁሳቁስ እና የመሳሪያ ሃብቶችን በብቃት ማስተዳደር፣ ለተያያዥ ችግሮች አስቸኳይ መፍትሔ መስጠት

[4] ደህንነትን እና ጤናን ማረጋገጥ - 𝑰𝒏𝒔𝒖𝒓𝒊𝒏𝒈 𝒔𝒂𝒇𝒆𝒕𝒚 𝒂𝒏𝒅 𝒉𝒆𝒂𝒍𝒕𝒉፦ በግንባታው ቦታ ላይ የደህንነት እርምጃዎችን በመተግበር የደህንነት ፕሮቶኮሎችን በመከተል የመከላከያ መሳሪያዎችን በመጠቀም እና አደጋዎችን እና ጉዳቶችን ለመከላከል እርምጃዎች እንዲተገበሩ ማድረግ

[5] የክፍያ ልኬቶችን ማስተዳደር - 𝑪𝒉𝒆𝒄𝒌𝒊𝒏𝒈 & 𝑨𝒑𝒑𝒓𝒐𝒗𝒊𝒏𝒈 𝑾𝒐𝒓𝒌𝒔 𝒆𝒙𝒆𝒄𝒖𝒕𝒆𝒅፦ ተቆጣጣሪዎች በኮንትራክተሩ ለክፍያ ጥያቄ የተዘጋጁትን መጠኖች የማረጋገጥ እና ትክክለኛ መጠን ከሆኑ ማሳለፍ ወይም አስተያየት በመስጠት ማስተካከያ እንዲደረግባቸው ማስደረግ

[6] ተከታታይ ሥራዎች በጊዜው እንዲከናወኑ ማዘዝ/መፍቀድ - 𝑶𝒓𝒅𝒆𝒓𝒊𝒏𝒈 𝒇𝒐𝒓 𝒑𝒓𝒐𝒄𝒆𝒆𝒅𝒊𝒏𝒈 𝒕𝒂𝒔𝒌፦ በተቋራጩ አስቀድሞ የተፈጸሙ ሥራዎችን በአግባቡ የተከናወኑ መሆናቸውን ካረጋገጡ በኋላ ተከታይ (ቀጣይ) ተግባራት እንዲቀጥል ትዕዛዝ መስጠት።

[7] ባለድርሻ አካላትና መገናኘት እና የሥራ ቅንጅትን መፍጠር - 𝑪𝒐𝒎𝒎𝒖𝒏𝒊𝒄𝒂𝒕𝒊𝒐𝒏 𝒂𝒏𝒅 𝒄𝒐𝒐𝒓𝒅𝒊𝒏𝒂𝒕𝒊𝒐𝒏፡-  ለፕሮጀክቱ ስኬታማ አፈፃፀም ያግዙ ዘንድ በተለያዩ የፕሮጀክት ባለድርሻ አካላት መካከል ለሚደረግ ንግግር ግልጽ እና ውጤታማ ግንኙነት ለመፍጠር እንደ መገናኛ/ድልድይ ማገልገል

[8] የተፈጸሙ ስራዎችን ማረጋገጥ - 𝑪𝒐𝒏𝒇𝒊𝒓𝒎𝒊𝒏𝒈 𝒆𝒙𝒆𝒄𝒖𝒕𝒆𝒅 𝒘𝒐𝒓𝒌𝒔፡- የተከናወኑ የሥራ ክፍሎችን ለእያንዳንዱ ሥራ ማረጋገጫ በሆኑ ተያያዥ የፍተሻ ዝርዝሮች (𝚝𝚊𝚜𝚔-𝚛𝚎𝚜𝚙𝚎𝚌𝚝𝚒𝚟𝚎 𝚌𝚑𝚎𝚌𝚔𝚕𝚒𝚜𝚝𝚜) መገምገም እና የተግባር ማረጋገጫ መስጠት /𝚌𝚘𝚗𝚏𝚒𝚛𝚖𝚊𝚝𝚒𝚘𝚗/ ወይም ውድቅ ማድረግ /𝚛𝚎𝚓𝚎𝚌𝚝𝚒𝚘𝚗/ ወይም የጥገና ማዘዣ መስጠት /𝚖𝚊𝚒𝚗𝚝𝚎𝚗𝚊𝚗𝚌𝚎 𝚘𝚛𝚍𝚎𝚛/ ወይም እንዲፈርሱና እና እንደገና እንዲሰሩ ማዘዝ /𝚍𝚎𝚖𝚘𝚕𝚒𝚜𝚑𝚒𝚗𝚐 𝚊𝚗𝚍 𝚛𝚎𝚠𝚘𝚛𝚔 𝚘𝚛𝚍𝚎𝚛/ ወይም አሳማኝ ማሻሻያ እንዲደረግላቸው ማድረግ /𝚖𝚘𝚍𝚒𝚏𝚒𝚌𝚊𝚝𝚒𝚘𝚗/ የመሳሰሉትን ውሳኔዎችን /𝚍𝚎𝚌𝚒𝚜𝚒𝚘𝚗𝚜/ ለኮንትራክተሩ መስጠት

[9] ችግር መፍታት - 𝑷𝒓𝒐𝒃𝒍𝒆𝒎 𝑺𝒐𝒍𝒗𝒊𝒏𝒈፦ ችግሮችን አስቀድሞ በመለየት ተግባራዊ መፍትሄዎችን በማፈላለግ ያልተጠበቁ ተግዳሮቶችን መከላከል

[10] መረጃን ሰንዶ ማስቀመጥ -   𝑫𝒐𝒄𝒖𝒎𝒆𝒏𝒕𝒂𝒕𝒊𝒐𝒏፦  የእለት ሪፖርቶችን፣ የሂደት ማሻሻያዎችን፣ እና የፕሮጀክት ምእራፎችን ለመከታተል፣ አለመግባባቶችን ለመፍታት እና ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ በመጀመሪያዎቹ እቅዶች ላይ የተደረጉ ማናቸውንም ለውጦችን ጨምሮ የግንባታ ስራዎችን ትክክለኛ ክስተት ወይም አጋጣሚዎች ወይም ሂደቶች በአግባቡ መዝግቦ መያዝ

[11] የአካባቢን ሁኔታ ታሳቢ ማድረግ  - 𝑬𝒏𝒗𝒊𝒓𝒐𝒏𝒎𝒆𝒏𝒕𝒂𝒍 𝑪𝒐𝒏𝒔𝒊𝒅𝒆𝒓𝒂𝒕𝒊𝒐𝒏𝒔፦  በግንባታ ተግባራት ላይ የሚኖረውን የአካባቢ ተፅእኖ ለመቀነስ እርምጃዎችን መተግበር፣ የአካባቢ ደንቦችን እና ምርጥ ልምዶችን ማክበር እና ማስከበር

🔰እነዚህ እና የመሳሰሉትን ጉዳዮች በዝርዝር እና በጥልቀት ይዘው ማስተዳደር ይጠበቅባቸዋል።

@etconp


👉የ "Site Diary" ጥቅምና ይዘት
{The importance and Format of Site Diary}


🚧በግንባታ ሂደት ውስጥ የምናገኛቸው የተለያየ ዓላማና ይዘት ያላቸው ሰነዶች አሉ። ለምሳሌ ያህል፦ የውል ሰነድ (contract document)፣ የሥራ ፍቃድ (Work Permit/order)፣ የግንባታ ፍቃድ (Building Permit)፣ የሥራ ምዘና መዝገብ (Checklists)፣ የዕለት ሥራ ማስታወሻ (Site Diary)፣ ንድፎች (Drawings) ... የመሳሰሉት ይገኙበታል። በሀገራችን የውል ፈጻሚዎች (አሠሪ፣ ተቋራጭ እና አማካሪ) ግጭት ውስጥ ለመግባታቸው አንዱና ዋነኛው ምክንያት እነዚህ ሰነዶች በግንባታ ሥራ አለመሟላታቸው መሆኑን የተጠኑ ጥናቶችም ጠቁመዋል።

💫ከእነዚህ ውስጥ  አንዱ የሆነውን የዕለት ሥራ ማስታወሻ (Site Diary) እንመለከታለን።

⏺ብዙ ጊዜ ስለዚህ ሰነድ ያለን ትኩረት ለዘብ ያለ ሆኖ የሚስተዋል ቢሆንም ብዙ የሥራ ተቋራጮች፣ አማካሪዎች እና አሠሪዎች ከስረውበታል።  

ክፍል አንድ  ዋና ዋና ጥቅሙ፦


1ኛ). የዕለት ተግባራትን መመዝገቢያ፡ ይህ የማስታወሻ ጥራዝ ወይም ሰነድ በየቀኑ በግንባታ ቦታው ላይ የተከናወኑ ሥራዎችን እንመዘግብበታለን። የተሰሩ ሥራዎችን፣ ግንባታው ያለበትን ደረጃ፣ በዕለቱ ያለውን የአየር ሁኔታ፣ ለግንባታ ሥራው የተሳተፉ ባለሙያዎችንና የጉልበት ሰራተኞችን ብዛት፣ የገጠሙ ችግሮችን፣ የተወሰዱ መፍትሔዎችን፣ በባለድርሻ አካላት የታዘዙ ልዩ ትእዛዞች (ካሉ) እነዚህ መረጃዎች የምንመዘግብበት የሁሉም የግንባታ ስራዎች አጠቃላይ ዕለታዊ መዝገብ ሆኖ ያገለግላል። ይህ ሰነድ የፕሮጀክቱን እድገት ለመከታተል ወሳኝ ሲሆን በዕለት ተዕለት እንቅስቃሴው ውስጥ ግልፅነትን ያረጋግጣል፣ የፕሮጀክት አስተዳዳሪዎች እና ባለድርሻ አካላት ስለቦታው ሁኔታ እንዲያውቁ ያግዛል።

2ኛ). ቅሬታ ወይም የክርክር የሚፈታበት ነው፦  በግንባታ ፕሮጀክቶች ውስጥ መጓተትን፣ የአቅም ለውጥን ወይም የሥራ ጥራትን በተመለከተ አለመግባባቶች ሊፈጠሩ ይችላሉ። በመሆኑም የዕለት ክስተት ማስታወሻው ሰነድ በቦታው ላይ ስለ ሁነቶች እና ሁኔታዎች ማስረጃ የሚያቀርብ ህጋዊ የግንባታ ሰነድ ሆኖ የሚቆጠር ስለሆነ በየትኛውም የፍትህ መንገድ ቅቡልነት አለው። ለምሳሌ ያህል፦ የጊዜ መጓተት የሚፈጥሩ ክስተቶች ካሉ (ለአብነት) ቀኑን ሙሉ ዝናብ ቢውል ወይም አካባቢው ረብሻ ቢሆን እነዚህ ክስተቶች የወሰዱትን ጊዜ (ሰዓት፣ ቀን፣ ወር) በቁጥር የምናሰላው ከ'Site Diary ላይ ለቅመን ስለሆነ ክስተቶቹ ባስተጓጎሉት የጊዜ መጠን ልክ በውሉ ላይ የነበረውን ግንባታ የሚጠናቀቅበትን ጊዜ ለማራዘም ያግዛል። በሌላም በኩል (ለምሳሌ) የግንባታ ግብአት ማቅረብ የአሠሪው (Client/employer) ድርሻ ቢሆን እና የግንባታ ጊዜ በዚህ የተነሳ ቢጓተትበት ሥራ ተቋራጩ የጊዜ ማራዘሚያ እና የሠራተኞች ያለሥራ የቆዩበትን ክፍያ አሠሪው እንዲከፍል ሊጠይቅበት የሚችለው በ'Site Diary ላይ በአግባቡ የተቀመጠ መዝገብ ካለ ነው።

3ኛ) ጥራትን ለመቆጣጠር ማረጋገጫ ይሆናል፦ site diary መያዝ የጥራት ቁጥጥር እርምጃዎችን እና ፍተሻዎችን ለመመዝገብ ያስችላል። ለምሳሌ፦ በዕለቱ የተሠራው ሥራ የፌሮ ብረት እና የአርማታ ሙሌት  ነው ብለን ብናስብ ለእያንዳንዱ ስትራክቸር የተጠቀምንው የፌሮ ብረት አይነትና ብዛት፣ የሲሚንቶ የአሸዋ እና የጠጠር ብዛት፣ የተከናወኑ የቤተሙከራ ሥራዎችና ውጤቶቻቸው እና የተስተዋሉ ያልተሟሉ ጉዳዮችን የምንመዘግብበት ስለሆነ የግንባታ ሥራ በዲዛይኑ መሰረት ዝቅተኛውን መስፈርት አሟልቶ እየተከናወነ ስለመሆኑና ስላለመሆኑ ጥራቱን እንድንቆጣጠር፣ የሚፈለገውን ደረጃና መስፈርት የሚያሟላ መሆኑን ለማረጋገጥ፣ ተጠያቂነትን ለማስፈን እና አጠቃላይ የፕሮጀክት ጥራትን ለማሻሻል ያግዛል።

ክፍል ሁለት፡ ይዘቱ ምን መምሰል አለበት


ይቀጥላል .....

@etconp


Intercon Construction Chemicals 
    
👉 Authorized agent of MC, SIMENTEK, Sika, Weber

● Concrete Admixtures
● Bonding Agents
● Waterproofings
● Concrete Repair, Grouting   
● Tile Adhesive & Tile Joint Fillers 
● Wall Putty, Prime Coat, Rush Coat
● Quartz, Contextra
● Floor hardener, Epoxy              
● Geotextiles, Geo-membranes and other construction chemicals and materials

Tel: 0961955555 or 0961955559
Address: Signal, around signal mall


survey which are carried out to provide a national grid of control for preparation of accurate maps of large areas are known
Опрос
  •   Plane survey
  •   Geodetic survey
  •   Geographical survey
  •   Topographical survey
135 голосов


Q : Which one of the following survey is used to define the property line?
Опрос
  •   A : City Survey
  •   B : Cadastral Survey
  •   C : Land Survey
  •   D : Topographical survey
142 голосов


👉HONEYCOMBS :

⏺Honeycombs are hollow spaces and cavities left in concrete mass on surface or inside the concrete mass where concrete could not reach. These look like honey bees nest.

Honeycombs which are on sides are visible to naked eyes and can be detected easily as soon shuttering is removed.

Honey combs which are inside mass of concrete can only be detected by advanced techniques like ultrasonic testing etc.

Honeycomb is due to non-reaching of concrete to all places due to which cavities and hollow pockets are created, main reasons are :

● Honeycombs are hollow spaces and cavities left in concrete mass on surface or inside the concrete mass where concrete could not reach. These look like honey bees nest.

● Honeycombs which are on sides are visible to naked eyes and can be detected easily as soon shuttering is removed. Honey combs which are inside mass of concrete can only be detected by advanced techniques like ultrasonic testing etc.

● Honeycomb is due to non-reaching of concrete to all places due to which cavities and hallow pockets are created, main reasons are:

1. Improper vibration during concrete.

2. Less cover to reinforcement bars

3. Use of very stiff concrete (this can be avoided by controlling water as per slump test).

4. Places like junction of beam to beam to column and to one or more beams are the typical spots where honey combs are observed.

This is due to jumbling of reinforcement of beams and column rods at one place; special attention is required at such place during concreting and vibrating.

5. Presence of more percentage of bigger size of aggregate in concrete also prevents concrete to fill narrow spaces between the reinforcement rods.

@etconp


👉What are bleeding & segregation of concrete?

🏷ANSWER

■ BLEEDING :

⏺It is the tendency of the water to rise to the surface of freshly laid concrete.

This results from inability of the solid material of concrete to hold the all the water mixed fro preparation of concrete and during the process of material downward settling.

If we resort to surface finish in presence of bleeding it would weaken the top surface. Type of cement used also has influence on bleeding process.

☆☆ Effects of bleeding :

● Concrete loses its homogeneity.

● Bleeding is responsible for causing permeability in concrete.

● It reduces the bond between the reinforcement and concrete when water accumulates below reinforcing bars.

● In the process of bleeding the accumulation of water creates a water voids and reduces bond between the aggregate and cement paste.

● Due to bleeding pumping ability of concrete is reduced.

● Increase in the water-cement ratio at the top.

☆☆ Ways to reduce the bleeding :

● Reduce water content. Use lower slump mix.
● Use finer cement.

● Increase amount of fines in the sand.

● Use supplementary cementitious materials.

● Use air-entraining admixtures.

● Bleeding lowers the cement strength.

■ SEGREGATION :

⏺Segregation is the “Separation of constituent materials in concrete.” In concrete technology, segregation is of three types:-

1. Separation of Coarse aggregate from the concrete mixture.

2. Separation of Cement paste from the concrete during its plastic stage.

3. Separation of water from the concrete mix (Bleeding in concrete)

⏺Concrete is a mixture of Cement, fine and coarse aggregates.

A good concrete is one which all the constituents are properly categorized to form a homogeneous mixture.

The primary cause of Segregation in concrete is the differences in specific gravities of the constituents, Specific gravity of Cement is in between 3.1-3.6g/cc, and for aggregate it lies between 2.6-2.7g/cc due to these differences, the aggregate separates from the matrix and causes segregation in concrete.

☆☆ Some other factors causing segregation in concrete:-

● Transporting concrete mixes for long distances.

● Poorly proportioned mix, where sufficient matrix is not there to bind the aggregates.

● Dropping concrete from more than 1m.

● Vibrating concrete for a long time.

☆☆ How to minimize segregation in concrete:-

1. Segregation can be controlled by maintaining proper proportioning the mix.

2. By peculiar handling, placing, transporting, compacting and finishing,

3. By using air entraining agents, admixtures and pozzolanic materials in the mix segregation controlled to some extent.

⏺In case of segregation, the heavy aggregate particles settle down leaving a sand cement mix on top affecting the quality adversely.

Fine aggregate could be used to overcome the problems.

However; design mix must be such that required strength could be achieved.

Similarly water ratio may be catered for in design mix to avoid bleeding keeping in view the local material specifications.

@etconp


#Advertising #ማስታወቂያ #MusaFide
Our Services Include:

💻 Civil 3D Full Tutorials (4K Video)

Tutorials with project files used throughout the video for hands-on learning.
📊 All Supporting Materials

Access materials, including PKT Files, Superelevation Excels, & ERA Manual XML, to streamline your design work.
🏗 Girder Bridge Working Drawing Preparation

Complete working drawings for Girder Bridges, including all materials used in the tutorial, & the 3D model created in SketchUp.
🚗 Highway Design Expertise

Professional highway design services
🛠 Template Production & PKT Development Template creation & PKT development as per your project standards.

📏 Earthwork & Pavement Quantity Preparation

Earthwork & pavement quantity preparation to ensure precise cost estimation.
🏗 Structural Working Drawing Preparation

Detailed structural working drawings Preparation
Connect with Us:
YouTube: http://www.youtube.com/@musfide
Telegram: https://t.me/musafide
WhatsApp: https://bit.ly/musfide
Call Us: +251 905 666 664


Architecture of Earthquake Resistance.pdf
23.3Мб
👉ጠቃሚ የመጽሀፍ ጥቆማ

🏷የህንጻ ቅርጽ እና ርዕደመሬት ንድፍ ለ ርዕደ መሬት ተከላካይ ኪነ ህንጻ

ለህንጻ ነዳፊዎች እጅግ የሚጠቅም በርዕደ መሬት እና በህንጻዎች  አጠቃላይ ቅርጽ ንድፍ ላይ ያተኮረ በ1981እኤአ በአሜሪካን አገር በ ናሽናል ሳይንስ ፋውንዴሽን አማካኝነት የታተመ መጽሀፍ ፒዲኤፍ ከታች ተያይዟል።

ይህ ባለ 310 ገጽ መጽሀፍ በምስሎች የበለጸገ መጽሀፍ ሲሆን ህንጻ ነዳፊዎች ህንጻዎቻቸውን ርዕደመሬት በሚያጠቃው አካባቢ  ሲነድፉ ከመጀመርያው የንድፍ እሳቤ አንስቶ የህንጻዎቻቸው አጠቃላይ ቅርጽ ውሳኔ ድረስ አትኩሮት ሊያደርጉባቸው የሚገቡ ዝርዝሮች ላይ በስፋት ትኩረት ያደርጋል።

Building Configuration and Seismic Design
The Architecture of Earthquake Resistance

Christopher Arnold and Robert Reitherman , May 1981

A study conducted by Building Systems Development, Inc.,
San Mateo, California under a grant from the National Science Foundation, Washington, D.C.

Via ethiopian architecture and urbanism

@etconp


👉የወቅቱ ሪል ስቴት ኢንቨስትመንት አደጋዎች

የሪል እስቴት ኢንቨስትመንት የሚያስገኘው ጥቅም ከፍ ያለ ቢሆንም የራሱ የሆኑ ተግዳሮቶችና አክሳሪ ሁኔታዎች ( Investment Risks) ያሉት ነው።

በዚህ ወቅትም የሀገራችን የሪል እስቴት ዘርፍ በፈታኝ አክሳሪ ሁኔታዎች እየተመታ እንደሆነ የዘርፉ ባለሙያዎች የዘርፉ የኢንቨስትመንት አደጋዎች ብለው ያቀመጧቸውና የሪል እስቴት አስተዳደርና ግብይት መጽሃፌ ላይም የተገለጹት ዝርዝር ማሳያዎች ውስጥ የእኛን ሀገር ወቅታዊ ሁኔታ ሰክቶ ለተመለከተው ያለው በግልጽ ይገነዘበዋል:-

፩) ከንግድ ስራ ጋር የተያያዘ ስጋት (Business Risk)
ይህ ከጠቅላላው የሀገር ኢኮኖሚ ውጣውረድ ጋር ተያይዞ የሚመጣ ስጋት ሲሆን ይህም በግልጽ የሚታይ ከማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው ትግበራ ጋር ምናልባት መፍትሄ  ሊያገኝ ከቻለ የሚታይ ይሆናል።

፪) ከገንዘብ አቅርቦት ጋር የተያያዘ ስጋት ( Financial Risk)
ለሪል እስቴት ኢንቨስትመንት የሚውለው ሙዓለ ነዋይ በጣም ከፍተኛ በመሆኑ የተነሳ በአልሚዎች ብቸኛ አቅም ሊሸፈን የሚችል አይደለም። አስፈላጊ የሆነውን የገንዘብ አቅርቦት ከባንክ ፣ ከደንበኞች ከሚሰበሰብ፣ አብሮ በማልማት፣ አክሲዮን በመሸጥ.. ወጪውን ለመሸፈን የሚደረጉ ጥረቶች ስኬት ሲርቃቸው እየተመለከትን ነውና ዘርፋ በዚህ ረገድም አደጋ ላይ ነው።

፫) ካለመሸጥ( ገዥ ከማጣት) ጋር የተያያዘ ( Liquidity Risk)
የሪል እስቴት ንብረት በቶሎ ተሸጦ ገንዘብ የሚገኝበት ( Liquid ) እንዳልሆነ ይታወቃል። ነገር ግን ልፕገበያ ወጥቶ በሶስት እስከ ስድስት ወራት ጊዜ ውስጥ መሸጥ ካልቻለ ችግር አለ ማለት ነው። በአሁን ወቅት ስለአንድ ቤት ሳይሆን በዘርፉ ላይ ንብረት ለገበያ  አውጥቶ ገዢ ማግኘት እየከበደ ከአንድ አመት በላይ ገዢ ያጡ ባርካታ አልሚዎች እንዳሉ እንመለከታለን ይህ ዘርፉ የ liquidity risk ውስጥ እንደገባ የሚያሳይ ነው።

፬) የግሽበት አደጋ ( Inflation Risk) እንደማንኛውም ቁስ የሪል እስቴት ግብዓቶችም ከፍተኛ ለሆነ የዋጋ ግሽበት እየተጋለጡ በመሆኑ ግንባታቸው ከተገመተው በላይ ወጪ በመጠየቅ የሚጠበቀውን ትርፍ ላያስገኝ ለኪሳራም ሊዳርግ ይችላል።

፭) የድርጅት አስተዳደር ችግር ( Management Risk)
ብዙዌች የሪል እስቴት ኢንቨስትመንት ውስጥ የሚገቡት ከተለያየ ስኬታማ  ቢዝነስ ውስጥ ተነስተው በመሆኑ ቀድመው የሚሰሩበትን የአስተዳደር ዘይቤ በሪል እስቴት ውስጥ ለማስቀጠል ሲሞክሩ ይታያል። ይህም ብዙዎችን ለኪሳራ እየዳረገ እንደሚሄድ ይጠበቃል ይታያልልም። አበባና ሰሊጥ መላክና ሪል እስቴት አይገናኙም  ኮንስትራክሽንና ሪል እስቴት ቢዝነስም ለየቅል ናቸው  ።

፮) ከብድር ወለድ ጋር የተያያዘ ( Interest Rate Risk)
ከአራጣ የማይተናነሰው በብዙ መከራና መላ አልፎ አልፎ የሚገኘው የሪል እስቴት ብድር የወለድ ምጣኔ ከፍተኛ ከመሆኑ ባሻገር በተለያዩ ጊዜያት የብድር ወለድ ምጣኔ ላይ የሚደረጉ ጭማሪዎች ያልታሰበ ወጪ በማስከተል ለኪሳራ አስተዋጽኦ እያደረጉ ነው።

፯) ከህግና መመሪያዎች ጋር የተያያዘ( Legistlative Risk)
ዘርፉ የሚመራበት ህግ በቅርቡ መጽደቁ ለዘርፉ አንድ ትልቅ አዎንታዊ አስተዋጽኦ ያለው ነው። ነገር ግን ዘርፉ ብዙ ዘርፎችን የሚያካትት በመሆኑ በሌሎች ዘርፎች ውስጥ የሚወጡ ህጎችና መመሪያዎችም ተጽዕኖ ያሳድሩበታል። ለምሳሌ የሊዝ አዋጅ ፣ የህንጻ አዋጅ እና የንብረት ማስመለስ አዋጅ በከፍተኛ ሁኔታ ተጽዕኖ ሊያሳድሩ ይችላሉ።

፰)ተፈጥሯዊ ክስተቶች (Natural Disasters)
በሪል እስቴት ግብይት ውስጥ የሚወጣው ወጪ ከፍ ማለቱ ገዢዎች በየጊዜው የሚከሰቱ ያልተጠበቁ ተፈጥራዊ አደጋዎችን ከግብይት ውሳኔ እንዲርቁ ወይም እንዲዘገዩ ሊያደርጓቸው ይችላሉ። ለምሳሌ ሰሞኑን የተከሰቱ የመሬት መንቀጥቀጥ ክስተቶች አፓርትመንት (ኮንዶሞኒየም) ቤቶች ግብይት ላይ ተጽዕኖ መፍጠሩ እየተነገረ ነው።

ከላይ የተዘረዘሩትን የኢንቨስትመንት ስጋቶች በሙሉ በሚገባ የሚያሰጉት ለሰውልጅ መሰረታዊ ፍላጎቶች ውስጥ አንዱ የሆነውን መኖሪያ ቤት እንዲያቀርብ የሚጠበቅበት  የሀገራችን የሪል እስቴት ኢንቨስትመንት ዘርፍ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት ችግሮቹ አንድ በአንድ ሊቀረፉና የሚጠበቅበትን አስተዋጽኦ እንዲያበረክት ሊደረግ ይገባል። የገበያ ስጋት ( Market Risk ) ያልተካተተው ሌሎች ችግሮች ሲፈቱ አብሮ የሚፈታ በመሆኑ ነው።

ችግሮቹን ከመፍታት አንጻር መንግስት ፣ ተጠባቂው  ካፒታል ማርኬትና አልሚዎች የየራሳቸውን ድርሻ ሊወጡ ይገባል:-

1) መንግስት በተራ ቁ. ፩፣፬ እና ፯ የሚገኙትን ትኩረት ሰጥቶ ቢፈታ
2) ካፒታል ማርኬት በተራ ቁ. ፪ እና ፮ ያሉትን መላ ቢፈጥር
3) አልሚዎች በበኩላቸው በተራ ቁ.  ፫ ፣ ፭ እና ፰ ያሉትን ትኩረት ሰጥተው ቢፈቱና የመንግስትና የካፒታል ማርኬት የሚሰጡትን መፍትሄና የሚፈጠሩ እድሎች በአግባቡ ቢጠቀሙ መልካም ይሆናል ።

Via ደሳለኝ ከበደ። የ መዋቅር መሀንዲስ፣ ገንቢ፣ ሪል ስቴት አማካሪ እና አሰልጣኝ

@etconp


👉ሀገር በቀል ህንጻ ተቋራጮች በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እንድሆኑ በትኩረት እየተሰራ ነው- የኮንስትራክሽን ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት

ሀገር በቀል ህንጻ ተቋራጮች ከሀገር አልፎ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የኮንስትራክሽን ማኔጅመንት ኢንስቲትዩት አስታወቀ።

የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ታምራት ሙሉ(ኢ/ር) ከኢዜአ ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደገለጹት የኮንስትራክሽን ዘርፉ በቴክኖሎጂ የዘመነና ተወዳዳሪ እንዲሆን ኢንስቲትዩቱ በርካታ ተግባራትን እያከናወነ ነው።

በዘርፉ ላይ ተወዳዳሪና የሰለጠነ የሰው ሀይል ለማፍራት ለዘርፉ ባለሙያዎች፣ ተቋማትና ህንጻ ተቋራጮች የተለያዩ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች እየሰጠ እንደሚገኝ አስታውቀዋል።

በተለይ በሀገር ውስጥ የሚገኙ የህንጻ ተቋራጮች በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ የክህሎት፣ የእውቀትና የቴክኖሎጂ ክፍተትን ለመሙላት እየተሰራ ያለውን ስራ ለአብነት አንስተዋል።

ይህንን ተከትሎ የሀገር ውስጥ ህንጻ ተቋራጮች በሀገር ውስጥ ህንጻዎችን ጨምሮ እየተገነቡ በሚገኙ ሜጋ ፕሮጀክቶች ላይ እየተሳተፉ መሆኑን ተናግረዋል።

በአሁኑ ወቅት ለኢንዱስትሪው ሽግግርና የቴክኖሎጂ እድገት ከፍተኛ ሚና ባለው የቢውልዲንግ ኢንፎርሜሽን ሞዴል ወይም(BIM) ላይ የህንጻ ተቋራጮች፣ የዘርፉ ምሁራንና ኢንዱስትሪዎች በቴክኖሎጂው ዙርያ ግንዛቤ እንዲኖራቸው የማድረግና የማስተዋወቅ ስራ እየተሰራ መሆኑንም ተናግረዋል
የፕሮጀክት ማኔጅመንት ፕሮፌሽናል ትሬኒንግ የተሰኘው ስልጠናም ሀገራዊ ፋይዳ ያላቸውና የሀገር ኢኮኖሚ ላይ ለውጥ የሚያመጡ እንደ ታላቁ ህዳሴ ግድብ የመሳሰሉ ፕሮጀክቶችን የሚመሩ ባለሙያዎችም ስልጠናውን እንዲወስዱ እየተደረገ ነው ብለዋል።

በዚህም ባለፉት ስድስት ወራት 89 ባለሙያዎች ስልጠናውን አጠናቀው አለም አቀፍ የፕሮጀክት ማኔጅመንት ማረጋገጫ ወረቀት መውሰዳቸውን አስታውቀዋል።

የኮንስትራክሽን ዘርፉ በቴክኖሎጂ የዘመነና ተወዳዳሪ እንዲሆን ኢንስቲትዩቱ የጥናትና ምርምር ስራዎችን እየሰራ እንደሚገኝም ገልጸዋል፡፡

Via Construction Management Institute

@etconp


👉VARIATION ORDER

🚧A Variation Order (VO) is a change to the scope of the initial construction contract that modifies the project's budget, timeline, or specifications. Here's a summary.

🛑 Types of Variation Orders

1. Additive VO: Adds new work or scope not included in the original contract.
2. Deductive VO: Removes or reduces existing scope.
3. Substitutive VO: Replaces specified materials or methods with alternatives.
4. Modification VO: Changes existing scope or specifications.

🛑 Causes of Variation Orders

1. Design changes or errors
2. Unforeseen site conditions
3. Changes in regulations or codes
4. Owner's requests or preferences
5. Errors or omissions in the original contract
6. Force majeure events (natural disasters, etc.)

🛑 Variation Order Process

1. Identification: Recognize the need for a VO.
2. Documentation: Record the change, including reasons and impact.
3. Estimation: Calculate the cost and time implications.
4. Approval: Obtain client/owner approval.
5. Implementation: Update contract documents and notify stakeholders.
6. Monitoring: Track VO progress and budget.

🛑 Key Components of a Variation Order

1. Description: Clear explanation of the change.
2. Justification: Reason for the VO.
3. Cost impact: Estimated cost variation.
4. Time impact: Revised project timeline.
5. Approval: Client/owner signature.
6. Effective date: Date of implementation.

🛑 Benefits of Variation Orders

1. Flexibility: Accommodates changes and unexpected issues.
2. Clarity: Documents scope changes and associated costs.
3. Transparency: Ensures stakeholder awareness and agreement.
4. Risk management: Minimizes disputes and potential claims.

🛑 Best Practices

1. Communicate clearly: With clients, contractors, and stakeholders.
2. Document thoroughly: Maintain detailed records.
3. Establish procedures: Standardize VO processing.
4. Monitor progress: Track changes and budget implications.
5. Negotiate fairly: Balance client needs with contractor interests.

🛑 Common Challenges

1. Scope creep: Uncontrolled changes.
2. Cost overruns: Unbudgeted expenses.
3. Delays: Timeline extensions.
4. Disputes: Stakeholder disagreements.
5. Administrative burdens: Increased paperwork.

@etconp


ታምራት  ፕሌት እና ጄቦልት አቅራቢ

👉ከ አባይ ግድብ እስከ ኮሪደር ልማት

ከግለሰብ ቤቶች እስከ ተቋማት እና

መጋዘኖች በሁሉም የኢትዮጽያ ክፍል

አሻራችንን አሳርፈናል

🔰ምን ይፈልጋሉ?

✂️ላሜራ መቁረጫ ÷ ማጠፊያ እና መብሻ ማሽኖች አሉን

🔗ፌሮ (ቶንዲኖ) ጥርስ ማስበጀት ወይንም ማሳጠፍ ካሰቡ ለሱም ማሽኑ በጃችን ነዉ

📐ማንኛዉንም የሞደፊክ ስራዎችን የሚሰሩ ብቁ ባለሙያዎችም አሉን

☎️ይደዉሉልን ያማክሩን

📍ኢትዮጵያ ዉስጥ የትም እንልክሎታለን

አድራሻችን፦
                    ቁ.1 መርካቶ
                    ቁ.2 ተክለሀይማኖት
                     ቁ.3 አየር ጤና

0904040477
0911016833


Intercon Construction Chemicals 
    
👉 Authorized agent of MC, SIMENTEK, Sika, Weber

● Concrete Admixtures
● Bonding Agents
● Waterproofings
● Concrete Repair, Grouting   
● Tile Adhesive & Tile Joint Fillers 
● Wall Putty, Prime Coat, Rush Coat
● Quartz, Contextra
● Floor hardener, Epoxy              
● Geotextiles, Geo-membranes and other construction chemicals and materials

Tel: 0961955555 or 0961955559
Address: Signal, around signal mall


👉በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት የተደረገው የቦሌ አራብሳ ዘመናዊ  የፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያ:-

በቀን 30 ሚሊዮን ሊትር ፍሳሽ የማጣራት አቅም ያለው የቦሌ አራብሳ ዘመናዊ የፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያ

ይህ ዘመናዊ የፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያ  የከተማችንን የፍሳሽ ማጣራት አቅም ከአምስት ዓመት በፊት ከነበረበት በቀን 48 ሺሕ ሜትር ኪዮብ ወደ በቀን233 ሺሕ ሜትር ኪዮብ ከፍ ማድረግ አስችሎናል::

የቦሌ አራብሳ ፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያ  ከ240 ሺህ በላይ የሚሆኑ የአካባቢውን ነዋሪዎች የዘመናዊ ፍሳሽ ማጣሪያ ፣ስርዓት ተጠቃሚ የሚያደርግ ነዉ። 

Via AAWSA

@etconp


👉ኦቪድ ሪል እስቴት በ 21 ቢሊዬን ብር ወጪ የሚገነባዉ የጫካ ፕሮጀክት ግንባታዉን በይፋ አስጀመረ፡፡

ኦቪድ ሪል እስቴት ለሚያስገነባው የጫካ ፕሮጀክት የኮንኩሪት ሙሌት ማስጀመሪያ እና የሽያጭ ቢሮ ማስመረቂያ ፕሮግራም አካሂዷል፡፡

ግንባታዉ በ 9 ነጥብ 4 ሄክታር መሬት ላይ የሚያርፍ ሲሆን ባለ 18 ወለል 26 ህንፃዎች የሚኖሩት ይሆናል ተብሎል ፡፡

የኦቪድ ሪል እስቴት ዋና ስራ አሰፈፃሚ ኢንጂነር ሙሉቀን ምትኩ በፕሮጀክቱ ማስጀመሪያ ላይ እንዳስታወቁት ግንባታዉ 2 ሺህ 1 መቶ 32 አባዎራዎችን መያዝ የሚችል ሲሆን የስፖርት ማዘውተሪያ ፤ሱፐር ማርኬትእንዲሁም አስፈላጊ መሰረተ ልማቶችን ያካተተ ነው ሲሉ ገልፀዋል

ግንባታዉ በሁለት ምእራፍ የሚካሄድ ሲሆን ከ ከሁለት እስከ አምስት አመታት የሚዘልቅ ቆይታ ይኖረዋል ተብሏል

የጨካ ፕሮጀክቱን ኦቪድ ሪል እስቴት ከጠቅላይ ሚኒስተር ቢሮ ጋር በጋራ የሚለማው ይሆናል ፡፡

ኦቪድ እሪል እስቴት መካከለኛ እና ዝቅተኛ ገቢ ያላቸዉ የህብረተሰብ ክፍሎች ታሳቢ ያደረጉ ቤቶች በመገንባት የሚታወቅ ሲሆን ቅንጡ እና ዉድ ቤቶችን በአማራጭነት የተካተቱበት መሆኑ ተገልጿል፡፡

Via Ethio FM

@etconp


👉ከመንግሥት ጋር ከተያያዙ ተግዳሮቶች ባሻገር ተቋራጮች በራሳቸው ደካማ የሆነ የውል አስተዳደር (Contract Administration) ትግበራ እንዳላቸውም ተጠቅሷል።

ሳሙኤል (ኢንጂነር)፣ ‹‹ለምሳሌ የዋጋ ማስተካከያ ይፈቀድልን በሚል ገንዘብ ሚኒስቴር ሲጠየቅ፣ ‹ማን ከለከላችሁ?› የሚል ጥያቄ ሲያነሳ፣ የከለከለን አማካሪው በልዩ ሁኔታ (Special Condition) በማስፈረም መሆኑን ሲገልጹ፣ ገንዘብ ሚኒስቴር እንደዚህ ያለ ውል ማን ፈርሙ አላችሁ? ብሎናል። የእኛንም ችግር ራሳችን መውሰድ መቻል አለብን። ግን ፍፁም የተከለከለ አይደለም። በፊት የ12 ወር ተባለ አሁን የ18 ወር ሆነ፣ ከዚያ ውጪ ግን ሙሉ ለሙሉ ይህ ፕሮጀክት ይህንን አያካትትም ብሎ መከልከልን ያመጣው በደካማ ውል አስተዳደር ትግበራችን ችግር ነው፤›› ብለዋል። 

ከዚህ ባሻገር የአገር ውስጥ የሥራ ተቋራጮች የግንባታ ጥሬ ዕቃ ከውጭ አገሮች ለማስመጣት፣ ከፕሮጀክቱ አጠቃላይ ወጪ ከ40 እስከ 60 በመቶ የሚሆነውን ያህል ገንዘብ የሚያወጡ ቢሆንም፣ ግዥ ለመፈጸም የሚዋዋሉት አገር ውስጥ ካለ አስመጪ ድርጅት ጋር በመሆኑ፣ ዕቃዎቹ ወደ አገር ውስጥ የሚገባበት ጊዜ ፍጥነት አስተማማኝ አለመሆኑን ጥናቶቹን ያቀረቡት ባለሙያዎች አስረድተዋል።

Via ሪፖርተር

@etconp


👉የሲሚንቶ ቤተሙከራዎች »
  { Cement Tests }

A) የመኮማተር ጥንካሬ (Compressive Strength)፡- ይህ ምዘን ሲሚንቶ ከደረቀ በኋላ ያለምንም መኮማተር  ወይም መፈረካከስ የሚተገበርበትን ክብደት የመሸከም አቅሙን የምንለይበት ነው።

በመሆኑም ሲሚንቶው ምን ያህል ክብደትን ወይን ጭነትን (loads) የመቋቋም አቅም እንዳለው የምንለይበት ነው።

B) የመለጠጥ ጥንካሬ (Tensile strength)፡ ይህ ሙከራ የሲሚንቶን የመለጠጥ ጥንካሬን የምንመዝንበት ሲሆን ለጭንቀት ሊጋለጥ ለሚችልበትን የጭነት ትግበራ ለማወቅ ጠቃሚ ነው።

C) ጤናማነት ፍተሻ (Soundness):  ይህ የምዘና ሥራ ሲሚንቶ ከውሃ ጋር ሲዋሃድ የሚኖረውን የመጠን ለውጥ እና መሰነጣጠቅን ለመቋቋም ያለውን ክህሎት (ጥንካሬ) የምናይበት ነው።

D) የመጠንከሪያ ሰዓት (Setting Time)፡ ይህ ሙከራ ሲሚንቶ የሚጠበቅበትን ጥንካሬ  የሚይዝበትን ወይን የሚደርቅበትን የሰዓት መጠን (ለማጠንከር የሚፈጀውን ጊዜ) ለማወቅ የሚደረግ ምዘና ነው።

ይህ ሂደት የቀረበው የሲሚንቶ አይነት ልንጠቀምበት ላቀድነው የሥራ ክፍል (application to intended works) ተስማሚ የሆነ የመጠንከሪያ ጊዜ መሆኑን ለመለየት ይጠቅማል።

E) ጥቃቅንነት ወይም ልመት (Fineness):  ይህ የሲሚንቶ ቤተሙከራዊ ምዘና የሲሚንቶውን ቅንጣት መጠን (particle size) ለመወሰን የምንሰራው ሲሆን ከውሃ ጋር የመዋሐድ (hydration) ምጣኔን እና በውኅደት ሂደት የሚኖረውን ጥንካሬ እድገት የምንለካበት ነው።

F) ከውሃ ጋር የሚዋሃድበትን የሙቀት መጠን (Heat of Hydration)፡ ይህ የምዘና ሂደት ሲሚንቶ ከእርጥበት ወይም ከውሃ ጋር ለሚያደርገው አጸግብሮት የሚያስፈልገውን የሙቀት መጠን ለማወቅ ይጠቅማል። ይህ ፍተሻ በእርጥበት ሂደት ውስጥ የሚፈጠረው ሙቀት በሲሚንቶው ላይ ስንጥቅ ወይም ሌላ ጉዳት እንዳይደርስበት መጠኑን ለመወሰን ወይም ለማረጋገጥ ጠቃሚ ነው።

G) የኬሚካል ይዘት (Chemical Analysis)፡ ይህ ሙከራ ሲሚንቶው የተመረተበትን የኬሚካል ስብጥር ለማወቅ የሚጠቅም ሲሆን በውስጡ ያሉ ኬሚካሎችና መጠናቸው ለሚፈለገው ሥራ ተስማሚ መሆኑንና አለመሆኑን ወይም የኬሚካል መመዘኛዎች የሚያሟላ መሆኑን እና ምንም ዓይነት ጎጂ ንጥረ ነገሮችን እንደሌለው ለማረጋገጥ ጠቃሚ ነው።

@etconp


#Advertising #ማስታወቂያ #MusaFide
Our Services Include:

💻 Civil 3D Full Tutorials (4K Video)

Tutorials with project files used throughout the video for hands-on learning.
📊 All Supporting Materials

Access materials, including PKT Files, Superelevation Excels, & ERA Manual XML, to streamline your design work.
🏗 Girder Bridge Working Drawing Preparation

Complete working drawings for Girder Bridges, including all materials used in the tutorial, & the 3D model created in SketchUp.
🚗 Highway Design Expertise

Professional highway design services
🛠 Template Production & PKT Development Template creation & PKT development as per your project standards.

📏 Earthwork & Pavement Quantity Preparation

Earthwork & pavement quantity preparation to ensure precise cost estimation.
🏗 Structural Working Drawing Preparation

Detailed structural working drawings Preparation
Connect with Us:
YouTube: http://www.youtube.com/@musfide
Telegram: https://t.me/musafide
WhatsApp: https://bit.ly/musfide
Call Us: +251 905 666 664


@etconp 2017 2nd Quarter Direct Cost.pdf
20.0Мб
🏷በ2017 ዓ.ም ሁለተኛ ሩብ ዓመት ተግባራዊ የሚደረግ የግንባታ ሥራዎች ይፋዊ ቀጥተኛ ዋጋ ተመን (2nd Quarter Construction Works of Direct Cost)

🔑በተለይ የዋጋ ተመን (BOQ - Priced bill of Quantities) ለምታወጡ የዲዛይን አማካሪዎች እና የፕሮጀክት መሐንዲሶች ይጠማችኋል።

💫በሌሎች የሀገሪቱ ክፍሎች የምትገኙ የኮንስትራክሽን ባለሙያዎችም እንደመነሻ ሀሳብ ይጠቅማችኋል።


@etconp

6.1k 0 141 4 23
Показано 20 последних публикаций.