ETHIO-MEREJA®


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Новости и СМИ


Addisababa, Ethiopia🇪🇹
News & Media Company®
.
USA : Washington
.
Buy ads: https://telega.io/c/ethio_mereja
.
ለጥቆማ እና ማስታወቂያ ለማሰራት
ከታች ያለውን ሊንክ ይጠቀሙ!!
👉 @ethio_merejabot

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Новости и СМИ
Статистика
Фильтр публикаций


ታስረው የሚገኙ ፖለቲከኞች እና ጋዜጠኞችን "ሶስት አመት አስራችሁ አቆዩዋቸው" ተብሎ ከፖለቲካው አካል የመጣ ትእዛዝ እንዳለ ታወቀ

ከፍርድ ቤት፣ ከስራ አስፈፃሚው አካል እንዲሁም ከጠበቆች ያሰባሰበው መረጃ እንደሚጠቁመው በተለይ ባለፉት ሁለት እና ሶስት አመታት ለእስር የተዳረጉ እነዚህ ፖለቲከኞች እና የሚድያ ሰራተኞች እስራቸው በፍርድ ሂደት ሳይሆን በፖለቲካ አመራሩ በጎ ፈቃደኝነት ብቻ ሊፈታ እንደሚችል እንደሚያምኑ ታውቋል።

ይህን የተረዱ አንዳንዶቹ ታሳሪዎች ወደ ፍርድ ቤት መመላለሱ ዋጋ እንደሌለው በመረዳት "የፍርድ ሂደቱን አንከታተልም" በማለት ወደ ፍርድ ቤቶች እየሄዱ እንዳልሆኑ ታውቋል።

በዚህ ዙርያ አስተያየት የሰጡን አንድ ጠበቃ "ይህ የሚያሳየው ታሳሪዎቹ የፖለቲካ እንጂ የህግ እስረኛ አለመሆናቸውን ነው፣ ያሰራቸው ፖለቲከኛ እንጂ በህግ ጥሰት ተጠርጥረው አይደለም" ብለዋል።

አክለውም "አሁንም እስራቸው ሊቋረጥ የሚችለው ከበላይ አካል በሚመጣ የ 'ፍቷቸው' ትእዛዝ እንጂ በዳኞች ውሳኔ አይሆንም" በማለት ሁኔታውን አስረድተዋል።(መሠረት-ሚድያ)


በአማራ ክልል 40 በመቶ የሚሆኑ ትምህርት ቤቶች ምዝገባ አልጀመሩም ተባለ፣ አንድም ትምህርት ቤት ያልተከፈተባቸው 17 ወረዳዎች መኖራቸው ተገልጿል

በአማራ ክልል አንድም ትምህርት ቤት ያልተከፈተባቸው 17 ወረዳዎች መኖራቸውን እና እንደ ክልልም 40 በመቶ ምዝገባ ያልጀመሩ ትምህርት ቤቶች መኖራቸው ተገለጸ።

የክልሉ የትምህርት ቢሮ ኀላፊ ሙሉነሽ ደሴ (ዶ.ር) የ2017 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ቅድመ ዝግጅት እና አጀማመርን አስመልክተው ባቀረቡት ሪፖርት “በአማራ ክልል 4 ነጥብ 5 ሚሊዮን በላይ ተማሪዎች ወደ ትምሕርት ቤት አልሄዱም” ብለዋል።

ከቅድመ አንደኛ እስከ ሁለተኛ ደረጃ ድረስ 7 ሚሊዮን 71 ሺህ 933 ተማሪ ለመመዝገብ ታቅዶ የተመዘገበው 2 ሚሊየን 543 ሺህ 128 መኾኑን አስታውቀዋል።

ዶክተር ሙሉነሽ በሪፖርታቸው ሁሉም ዞኖች፣ እንዲሁም ውስን ወረዳዎች እና ትምህርት ቤቶች ዓመታዊ እቅድ ማቀዳቸውን ጠቁመው ወደ ታችኛው እርከን የጸጥታ ችግሩ እንቅፋት መኾኑን ጠቅሰዋል።

5 ነጥብ 3 ሚሊዮን የአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት መጽሐፍ ወደ ደሴ እና ጎንደር የክዘና ማዕከል መግባቱን የጠቀሱት ሃላፊዋ የጸጥታ ችግሩ መጽሐፍቱን ለዝርፊያ እና ውድመት ማጋለጡን አስታውቀዋል።

ትምህርት ቤቶች በታጠቁ ኃይሎች ጉዳት እንደደረሰባቸው እና የመምህራን ግድያ መኖሩ በትምህርት ላይ ጫና አሳድሯል ነው ያሉት ቢሮ ኀላፊዋ። በሰሜኑ ጦርነት ከወደሙ 4 ሺህ ትምህርት ቤቶች መካከል የተጠገኑት ከ10 በመቶ በላይ ስላልኾኑ በጥራት ላይ ችግር እንዳለውም ገልጸዋል።

    T.me/ethio_mereja
        ኢትዮ-መረጃ


የ Graphic Design ስልጠና የሚቀጥለው ሳምንት ጠዋት ሰኞ 3 ስዓት ይጀምራል ።
የዚህን ወር ስልጠና ለሚሳተፉ የ video editing ነፃ ስልጠና እንሰጣለን።


በመራህያን የወደፊት ብሩህ ተስፋዎን የሚዘሩ ክህሎቶችን ይማራሉ !!

☎️
0989747878
0799331774

TikTok | Instagram | Facebook | LinkedIn | YouTube | Telegram

አድራሻ፦ ጀሞ ሚካኤል ጆሞ ሞል 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 226

ለበለጠ መረጃ ቻናላችንን ይቀላቀሉ : @merahyan


በቴሌ ብር ከ3 ነጥብ 25 ትሪሊየን ብር በላይ ዝውውር ተፈጸመ

በቴሌ ብር መተግበሪያ እስካሁን ከ3 ነጥብ 25 ትሪሊየን ብር በላይ ዝውውር መፈጸሙን ኢትዮ ቴሌኮም አስታውቋል፡፡

የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬሕይወት ታምሩ እንዳሉት፤ ቴሌ ብር በኢትዮጵያ ዲጂታል የገንዘብ ልውውጥን ከማሳለጥ አንጻር ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ ነው፡፡

በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ የቴሌ ብር ተጠቃሚ ደንበኞች ቁጥር ከ51 ነጥብ 3 ሚሊየን በላይ መድረሱን ገልጸው፤ መተግበሪያው ስራ ላይ ከዋለ ጀምሮ ከ3 ነጥብ 25 ትሪሊየን ብር በላይ ዝውውር ተፈጽሟል ብለዋል።

ኢትዮ ቴሌኮም ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ የተጀመረውን ጥረት ከግብ ለማድረስ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በትብብር እየሰራ መሆኑንም አስረድተዋል፡፡(ኤፍቢሲ)


💰💸ከኛ ጋር ሲጫወቱ እስከ 10 እጥፍ የማሸነፍ አድል አሎት! 💸💰

ከመቼውም ጊዜ በላይ ከፍ ባሉ ኦዶቻችን ይወራረዱ። በተመረጡ ጨዋታዎች ጊዜና ቦታ ሳይገድብዎ ባሉበት ሆነው በአፍሮስፖርት እድሎን ይሞክሩ!

እንዳያመልጥዎ አሁኑኑ ወደ👉 https://bit.ly/3XbY3o7 ይግቡና ይወራረዱ!

አፍሮስፖርት ማህበራዊ ገጾቻችንን Follow በማድረግ በየሳምንቱ የተለያዩ ሽልማቶችን ያሸንፉ፣ ቤተሰብ ይሁኑ። 👇
Telegram
Facebook
Instagram
TikTok


በካፋ ዞን ሰደበችኝ በማለት የገዛ ሚስቱን በስለት ወግቶ የገደለዉ ግለሰብ በእስራት ተቀጣ

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በካፋ ዞን የዴቻ ወረዳ ፖሊስ አዛዥ ዋና ሳጅን ሲሳይ ሰማቶ እንደገለፁት በወረዳው ዳጋ ቀበሌ ህዳር 12 ቀን 2017 ዓ.ም በባልና ሚስ በመካከላቸው በተፈጠረ አለመግባባት ባል የገዛ ሚስቱን እና የአራት ልጆቹን እናት በስለት ወግቶ በመግደሉ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ እየተጣራበት እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡

የወረዳው ፖሊስ አዛዥ አክለውም ፖሊስ በምርመራ እንዳረጋገጠው ባልና ሚስት በእለቱ በወረዳው ሺትዬ ቀበሌ ሐሙስ በሚውለው  ገበያ ውለው መመለሳቸውን እና ምሽቱን በመኖሪያ ቤታቸው ውስጥ በተፈጠረው አለመግባባት ባል ሚስቱን ሰደበችኝ በሚል በስለት የተለያዩ ቦታዎች ላይ በመውጋት ህይወቷ እንዲያልፍ ማድረጉን በሰጠው የእምነት ቃል መረጋገጡን ገልጸዋል፡፡

ሁለቱ ጥንዶች ለስድስት አመታት በትዳር ቆይታቸው አራት ልጆችን መወለዳቸውን የገለፁት አዛዡ በገበያ ውሎአቸው ከመጠጥ ቤት አብረው ጠጥቶ መመለሳቸውን እና በስካር መንፈስ የወንጀል ድርጊቱን እንደፈፀመ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር ኢንስፔክተር ደጀኔ አሰፋ ተናግረዋል፡፡

በቤተሰብ መካከል የሚፈጠርን አለመግባባት በመነጋገር መፍታት እየተገባ በተዳር አጋሩ ላይ ወንጀል መፈፀም እንደማይገባ ጠቅሰው ሌሎች ሰዎች ችግርን በመነጋገር መፍታት ይኖርባቸዋል ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

    T.me/ethio_mereja
        ኢትዮ-መረጃ


የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ከሄዝቦላህ ጋር የተጀመረውን የተኩስ አቁም ስምምነት ሀሳብ "በመርህ ደረጃ" መቀበላቸው ተሰማ!

እሁድ ምሽት ከእስራኤል ባለስልጣናት ጋር ባደረጉት የፀጥታ ምክክር ሀሳቡን በ "በመርህ ደረጃ" ማፅደቃቸውን ሲኤንኤን ጉዳዩን ያውቃሉ ያላቸውን ምንጮች ጠቅሶ ዘግቧል፡፡በዛሬው እለት ለሊባኖስ መንግስት ይተላለፋል ተብሎ በሚጠበቀው የስምምነት ሰነድ ላይ እስራኤል ያላትን የሀሳብ ልዩነቶች እንደምታንጸባርቅ ነው የተነገረው፡፡

ምንም እንኳን ቴልአቪቭ እንዲስተካከሉ የምትፈልጋቸው የሰነዱ ሀሳቦች ካልተስተካከሉ ስምምነቱን ሙሉ ለሙሉ መቀበሏን ማረጋገጫ ባይሆንም ከበርካታ ወራት በኋላ ለስምምነት የቀረበው ሰነድ ይህኛው እንደሆነ ተገልጿል፡፡የተኩስ አቁም ስምምነት ለፊርማ ከመቅረቡ በፊትም በሀገሪቱ የካቢኔ ምክር ቤት መጽደቅ ይኖርበታል፡፡

”በቀጠናው የአሜሪካ ልዩ ልዑክ አሞስ ሆይስተን ባለፈው ሳምንት በቤይሩት ባደረጉት ንግግር “በእስራኤል እና በሄዝቦላህ መካከል የተኩስ አቁም ስምምነት ተግባራዊ ለማድረግ የሚደረገው ጥረት ለፍጻሜ ቀርቧል፤ ነገር ግን ለስኬታማነቱ የሁለቱን ተደራዳሪዎች በጎ ፈቃድ ይፈልጋል” ብለዋል፡፡

በተጨማሪም የሊባኖሱ ጊዜያዊ ጠቅላይ ሚኒስትር ናጂብ ሚካቲ እና የፓርላማ አፈጉባዔው ናቢህ በሪ ከሄዝቦላህ መሪዎች ጋር ተገናኝተው ገንቢ እና ክፍተቶቹን ማጥበብ የሚያስችል ውይይት አካሄድዋል ነው ያሉት፡፡ልዩ ልኡኩ አሞስ ሆይስተን በድርድሩ የመጨረሻ ሂደቶች ዙርያ ለመምከር በመጪው ረቡዕ ወደ ሊባኖስ እንደሚያቀኑም ተዘግቧል፡፡በአሜሪካ የሚደገፈው የሰላም ስምምነት ሀሳብ ለ60 ቀናት የሚቆይ የተኩስ አቁም በማስተግበር ዘላቂ የሆነ ጦርነት ማስቆምን ተፈጻሚ ማደረግ አላማው አድርጓል፡፡(alain)

    T.me/ethio_mereja
        ኢትዮ-መረጃ


🔥 ለአጭር ጊዜ የሚቆይ 30% ቅናሸ ለ10 እድለኞች ብቻ
👉በካሬ 78,000 ጀምሮ
👉50% የባንክ ብድር የተመቻቸለት
👉በ8% ቅድመ ክፍያ
📌ቦታ- ለቡ መብራት ሀይል
📌ለኢንቨስትመንት ቢሉ ለመኖሪያ ምቹ
👉ከሰቲዲዬ እሰከ ባለ 4 መኝታ የተለያዩ የቤት አማራጮች ያሉት

ስቲዲዮ -  56.5 - 57.3 ካሬ
ባለ 1መኝታ  - 69 - 90 ካሬ
ባለ 2 መኘታ -   99 - 150 ካሬ
ባለ  3 መኝታ  - 133 - 181 ካሬ
ባለ 4 መኝታ  - 177.1 - 190 ካሬ
የንግድ ሱቆች - 23 - 175 ካሬ

👉ለበለጠ መረጃ እና ለሳይት ጉብኝት ቀጠሮ ለመያዝ
የሪል እስቴት የሽያጭ አማካሪ
📱 +251911866350
📱 +251923801518


በየቀኑ በርካታ አሸናፊዎችን በሚያስተናግደው የአቪዬተር ጨዋታችን እየተዝናኑ ያሸንፉ!
በአፍሮ ስፖርት ጌሞች ለማሸነፍ ወደ👉 https://bit.ly/3M9qBIw ይሂዱ። 

አፍሮስፖርት ማህበራዊ ገጾቻችንን Follow በማድረግ በየሳምንቱ የተለያዩ ሽልማቶችን ያሸንፉ፣ ቤተሰብ ይሁኑ። 👇
Telegram
Facebook
Instagram
TikTok


"የትግራይ ፖለቲካ ወደባሰ ሁኔታ እየተጓዘ ነው" – ጌታቸው ረዳ

የጊዚያዊ አስተዳደሩ ፕሬዝዳንት ጌታቸው ረዳ፤ የህዝብን ሰላምና ደህንነት ከግምት ውስጥ ያላስገባ በወንበር ላይ የተመሰረተ ግጭትና ትርምስ እየተፈጠረ መሆኑን ገለፁ።

አቶ ጌታቸው ረዳ ዛሬ በሰጡት መግለጫ÷ "ለረጅም ጊዜ ስልጣን ላይ የቆየው ሃይል" በማለት የጠቀሱትን ቡድን “ሁሉንም ነገር አፍኖ ወደ ስልጣን ለመመለስ እየሰራ ነው ብለዋል።

ቅድሚያ የሚሰጣቸውን አጀንዳዎች ወደጎን በማለት “ወንበራችን ተነጠቅን” የሚሉ አካላት “በጉልበት እንመልሳለን” ወደሚል እንቅስቃሴ መግባታቸውን ገልፀዋል። "ጉባኤውን አከናውኛለሁ በማለት የሚንቀሳቀሰው ሃይል በጠላትነት ከፈረጀው ሀይል ጋር በመተባበርም ወንበር ለመያዝ ሌት ተቀን እየሞከረ ነው" ብለዋል አቶ ጌታቸው።

በመሆኑም የትግራይ ፖለቲካ ወደ ከፋ ሁኔታ እየተጓዘ መሆኑን ገልፀዋል። “በዞኖችና ወረዳዎች ስርዓት የሌለው ህገወጥ አሰራር እየተሰራ ነው” ብለዋል።

"የተፈናቀሉ ዜጎችን ለመመለስ እና የትግራይን ፀጥታ ከማረጋገጥ ይልቅ ወደ ሌላ የስልጣን ሽኩቻ እንድንገባ ተገድደናል" ሲሉ ገልፀዋል። አቶ ጌታቸው ረዳ እንዳሉት፤ የተካሄደው ጉባኤ በፓርቲው አሰራርም ሆነ የፌዴራል መንግስት ባወጣው መመሪያ ህገወጥ ነው ብለዋል። ልዩነቶች በዕርቅና በድርድር ለመፍታት እርሳቸውና ጓቻቸው ዝግጁ መሆናቸውም በመግለጫቸው ተናግረዋል።“እንደ ህወሐት መዳን ከፈለግን በራሳችን ውስጣዊ አቅማችን እንጂ በውጪ ሃይሎች መሆን የለበትም” ብለዋል።

    T.me/ethio_mereja
        ኢትዮ-መረጃ


ሂዝቦላህ በሚሳኤሎችና ድሮኖች በመታገዝ እስራኤል ላይ ጥቃት ፈጸመ

ሂዝቦላህ በመቶዎች በሚቆጠሩ ሚሳኤሎችና ድሮኖች በመታገዝ እስራኤል ላይ ጥቃት መፈጸሙን የእስራኤል መከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

በእስራኤል እና በሊባኖሱ ታጣቂ ቡድን ሂዝቦህ መካከል እየተደረገ ያለው ጦርነት ተባብሶ መቀጠሉ ተመላክቷል፡፡ ከሰሞኑ እስራኤል በሊባኖስ መዲና ቤሩት የተለያዩ አቅጣጫዎች በተመረጡ የሂዝቦላህ ይዞታዎች ላይ ጥቃት መፈጸሟን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

በጥቃቱ እየደረሰ ያለውን ውድመት ተከትሎም በቤሩት እስከ ቀጣዩ ጥር ወር ድረስ ት/ቤት መዘጋቱን የሊባኖስ ትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡ ለጥቃቱ አጸፋም ሂዝቦላህ 340 በሚሆኑ ሚሳኤሎች እና ድሮኖች በእስራኤል ላይ ጥቃት መፈጸሙ ነው የተገለጸው፡፡

በጥቃቱም በሰሜንና ማዕከላዊ እስራኤል በርካታ ሰዎች የተጎዱ ሲሆን÷ ህንጻዎችና መኖሪያ ቤቶች መውደማቸውም ተጠቁሟል፡፡ እስካሁን ድረስ በ11 ሰዎች ላይ ከቀላል እስከ ከባድ ጉዳት መድረሱን የእስራኤል መከላከያ ሚኒስቴር ይፋ አድርጓል፡፡

በጥቃቱ ከደረሰው ውድመት ባሻገር በሚሊየን የሚቆጠሩ እስራኤላውያን ከጥቃቱ ሽሽት ወደ ምሽግ መግባታቸው ተጠቁሟል፡፡

    T.me/ethio_mereja
        ኢትዮ-መረጃ


ዩክሬን በኩርስክ ግዛት ከተቆጣጠረቻቸው ቦታዎች ውስጥ 40 በመቶውን በሩሲያ መነጠቋን አመነች፡፡

የሩሲያ ዩክሬን ጦርነት መልኩን እየቀያየረ ሲሆን በምስራቅ ዩክሬን ባለው የውጊያ ግምባር የሩሲያ ጦር በየዕለቱ ወደ ፕሮቭስካ ከተማ እየተቃረበ ይገኛል፡፡ዩክሬን ቁልፍ የሎጅስቲክስ ማዕከል የሆነችው ፐሮቭስካ ከተማን በሩሲያ እንዳትያዝ በሚል በድንገት ሳይታሰብ ወደ ሩሲያዋ ኩርስክ ግዛት ጥቃት ከፍታ ነበር፡፡

ባሳለፍነው ነሀሴ ላይ በተጀመረው የኩርስክ ግዛት ጦርነት ዩክሬን ከ 1 ሺህ 200 በላይ ስፋት ያለው አካባቢን ተቆጣጥራለች፡፡የዩክሬን ያልታሰበ የኩርስክ ጥቃት በርካታ ሩሲያዊንን ያስደነገጠ እንደነበር በወቅቱ ተገልጾ ነበር፡፡ይሁንና ሩሲያ እንደታሰበው በምስራቅ ዩክሬን በኩል የሰማራችውን ጦር ወደ ኋላ እንዲያፈገፍግ ከማድረግ ይልቅ ወደ ፊት እንዲገፋ አድርጋለች፡፡

ዩክሬንም የኩርስክ ግምባር ዓለማው መክሸፉን በወቅቱ ገልጻ የነበረ ሲሆን ቦታውን እስከቻለችው ድረስ ተቆጣጥራ የመቆየት እቅድ እንዳላት አስታውቃለች፡፡

ሩሲያ የኩርስክ ግዛትን መልሳ ለመቆጣጠር አዲስ ዘመቻ ጀምራለች የተባለ ሲሆን እስካሁን በዩክሬን ጦር ተይዘው ከነበሩ ቦታዎች ውስጥ 40 በመቶውን መልሳ መቆጣጠሯን ዩክሬን ገልጻለች፡፡ስማቸው ያልተጠቀሰ አንድ የዩክሬን ጀነራል ለሮይተርስ እንዳሉት ሩሲያ ኩርስክን ለመቆጣጠር 11 ሺህ የሰሜን ኮሪያ ወታደሮችን ጨምሮ 60 ሺህ ገደማ ወታደሮችን አሰማርታለች፡፡ ዩክሬን የኩርስክን ግምባር ለመበታተን የአየር ላይ ጥቃቶችን በማድረስ ላይ እንደሆነች የተናገሩት አዛዡ በተለይም የሎጅስቲክስ ማዕከላትን እና የትራንስፖርት መስመሮችን ኢላማ አድርጋለችም ብለዋል፡፡

    T.me/ethio_mereja
        ኢትዮ-መረጃ


🎁🎁የተለያዩ አዝናኝ እና አሸናፊ የሚያደርጓችሁን ውድድሮች በአፍሮስፖርት ይዘንላችሁ መጥተናል!🎁🎁

ከዛሬ ጀምራችሁ የማህበራዊ ገጾቻችንን follow በማድረግ በየቀኑ አሸናፊ ሁኑ❗️

ውርርድዎን ዛሬውኑ https://bit.ly/3XbY3o7 ላይ ያስቀምጡ!

አፍሮስፖርት ማህበራዊ ገጾቻችንን Follow በማድረግ በየሳምንቱ የተለያዩ ሽልማቶችን ያሸንፉ፣ ቤተሰብ ይሁኑ። 👇
Telegram
Facebook
Instagram
TikTok


ማንቺስተር ሲቲ በሜዳው በቶተንሃም 4 ለ 0 ተሸነፈ!

በ12ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ምሽት 2፡30 ላይ በተደረገ ጨዋታ ማንቺስተር ሲቲ በሜዳውና በደጋፊው ፊት በቶተንሃም ሆትስፐር 4 ለ 0 ተሸንፏል፡፡

በጨዋታው የቶተንሃም ሆትስፐርን የማሸነፊያ ግቦች ጀምስ ማዲሰን በ 13ኛው እና በ20ኛው ደቂቃ፣ ፔድሮ ፖሮው በ52ኛው ደቂቃ እንዲሁም ቤናን ጆንሰን በ94ኛው ደቂቃ አስቆጥረዋል፡፡

ማንቺስተር ሲቲ ይህን ጨዋታ መሸነፉን ተከትሎ በሁሉም ውድድር 5ኛ ተከታታይ ሽንፈቱ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

    T.me/ethio_mereja
        ኢትዮ-መረጃ


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
🌺Spa Gel Socks

🔰ለእግር ልስላሴ
🔰ለሚሰነጣጠቅ እግር
🔰ድርቀትን የሚያለሰልስ
🔰የሚታጠብ

✅በቀን ከ20-30 ደቂቃ ብንጠቀመው የእግራችንን ልስላሴ ሙሉ በሙሉ መመለስ ይቻላል


⭕️ዋጋና ተጨማሪ እቃዎችን👇 ለማየት ሊንኩን ይጫኑ!
   🌞 https://t.me/AddisEka1 Join us!
   🌞 https://t.me/AddisEka1 Join us!

አድራሻ፣ መገናኛ ሲሳይ ፕላዛ 1ኛ ፎቅ 1-010ቁ


“ለማንችስተር ዩናይትድ ትክክለኛው ሰው ነኝ ብየ አስባለሁ”- ሩብን አሞሪም

አዲሱ የማንቸስተር ዩናይትድ ዋና አሰልጣኝ ሩብን አሞሪም ለመጀመርያ ጊዜ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ “በኦልድ ትራፎርድ የሚጠብቀኝን ፈተና ብገነዘብም ክለቡን ማሻሻል እና መለወጥ እንደሚቻል አምናለሁ” ብሏል፡፡

በተጨማሪም "ከቡድኑ አስተዳደር ጋር አንድ አይነት ሀሳብ ያለን ይመስለኛል ፤ይህ ደግሞ የቡድኑን አቅም ለመጨመር የሚረዳ ነው” ሲል ተናግሯል፡፡ብዙዎች በተጫዎቹ እምነት እንደሌላቸው ያነሳው አሞሪም በተጨዋቾቹ አቅም እንደሚተማመን እና አዳዲስ ነገሮችን መሞከር እንደሚፈልግ ለዚህ ደግሞ ትክክለኛው ሰው መሆኑን አስታውቋል። ከአራት አመታት የስፖርቲንግ ሊዝበን ቆይታ በኋላ ዩናይትድን የተቀላቀለው ፖርቹጋላዊ ማንችስተር ዩናይትድን ለዋንጫ ክብር ለማብቃት ጠንክሮ እንደሚሰራም ገልጿል፡፡
 
“ሊጉ በርካታ ጠንካራ ክለቦች የሚሳተፉበት ቢሆንም ጨዋታዎችን ማሸነፍ እንዳለብን አውቃለሁ፤ ነገር ግን ሊግ ከባድ ስለሆነ ብዙ ጊዜ እንፈልጋለን። በዚህ ሂደት ውስጥም ወደ ዋንጫ አሸናፊነት የምንቀርብ ይሆናል” ነው ያለው፡፡

3-4-3 ወይም 3-4-2-1 በማጥቃት እና በኳስ ቁጥጥር ላይ ላይ የተመሰረተ ጨዋታ የሚከተለው አሞሪም ወጣቶችን በማብቃት እና አቅማቸውን በማጎልበት ልዩ ችሎታ እንዳለው ይነገርለታል፡፡ከ2021 ጀምሮ ስፖርቲንግ ሊዝበንን ተረክቦ ማሰልጠን የጀመረ ሲሆን ቡድኑ አምስት ዋንጫዎችን ሲያነሳ በአማካይ 71.7 በመቶ ወይም ከአስር ጨዋታዎች 7 ጨዋታዎችን የማሸነፍ ምጣኔ ያለው ቡድን መገንባትም ችሏል፡፡

    T.me/ethio_mereja
        ኢትዮ-መረጃ


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
🎁ከአፍሮ ስፖርት ትልልቅ ሽልማቶች ያሉት ቻሌንጅ ይዘንላችሁ መጥተናል!🎁

ለመሳተፍ 2 ቀላል ነገሮችን ብቻ ነው የሚጠበቅባችሁ!

1. በዚህ ቻሌንጅ ለመሳተፍ በመጀመርያ በአፍሮ ስፖርት ወብሲተ ረጂስተር አድርገው ደፖዚት ማድረግ እንዲሁም

2. የአፍሮስፖርት ማህበራዊ ገፆችን ማለትም Facebook , Instagram, Telegram እና Tiktok ገጾች መከተል

ቻሌንጁ ለ 1 ሳምንት ብቻ ስለሚቆይ እንዳያመልጣችሁ!

💸🏆🥇ይሳተፉ ያሸንፉ!💸🏆🥇

Website
Telegram
Facebook
Instagram
TikTok


#Update

ዛሬ በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን አለልቱ ወረዳ በደረሰው የትራፊክ አደጋ የ11 ሰዎች ሕይወት ማለፉ ታውቋል።

አደጋው ከአዲስ አበባ ወደ ደሴ የሚጓዝ የሕዝብ ማመላለሻ በተቃራኒ አቅጣጫ ሲጓዝ ከነበረ ሲኖ ትራክ ተሽከርካሪ ጋር በመጋጨቱ ነው የተከሰተው።

የዞኑ ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ሥራ ሒደት ሃላፊ አቶ ሰለሞን ዘውዴ በአደጋው እስካሁን የ11 ሰዎች ሕይወት አልፏል ብለዋል።

በተጨማሪም በ40 ሰዎች ላይ ከባድ እና 11 ሰዎች ላይ ደግሞ ቀላል ጉዳት መድረሱን ተናግረዋል።

ዛሬ ጠዋት 2:30 ላይ በተከሰተው አደጋ የተጎዱ ሰዎች በሰንዳፋ ሆስፒታል ሕክምና እተከታተሉ እንደሚገኙም አመልክተዋል ሲል ፋና መረጃውን አጋርቶ ተመልክተናል።

    T.me/ethio_mereja
        ኢትዮ-መረጃ


አሳዛኝ አደጋ🕯🕯

ከአዲስ አበባ ወደ ደሴ የሚጓዝ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ከሲኖ ትራክ ተጋጭቶ የበርካቶ ህይወት ማለፉ ተሰምቷል

በዛሬው ዕለት በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን አለልቱ መንገድ ላይ ከባድ የትራፊክ አደጋ ደረሰ አደጋው አለልቱ አቅራቢያ ጮሌ ጸበል ጋር የተከሰተ ሲሆን፤ ከአዲስ አበባ ወደ ደሴ የሚጓዝ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ከሲኖ ትራክ ተሸከርካሪ ጋር በመጋጨቱ መከሰቱን በስፍራው ያሉ ነዋሪዎች ገልፀዋል።

በአደጋው በርካታ ሰዎች መጎዳታቸውን እንዲሁም ለጊዜው ቁጥራቸው ያልታወቀ ሰዎች ሕይወት ማለፉን የተናገሩት ነዋሪዎቹ፤ የሲኖ ትራክ ተሸከርካሪው ረዳት መኪና ውስጥ ተቀርቅሮ በመቅረቱ እርሱን ለማውጣት ከአንድ ሰዓት በላይ ጥረት ቢደረግም ሕይወቱን ማትረፍ አለመቻሉን ተናግረዋል፡፡

በዚህም ምክንያት መንገዱ ለረጅም ሰዓት መዘጋቱ የተነገረ ሲሆን፤ በአደጋው ጉዳት የደረሰባቸውን ሰዎች ወደሆስፒታል የማድረስ ሥራ እየተሰራ መሆኑን ከአሐዱ ሬዲዮ ዘገባ ሰምተናል።(አሀዱራዲዮ)

    T.me/ethio_mereja
        ኢትዮ-መረጃ

17.5k 0 30 16 201

የጥንቃቄ መልእክት!

ወደ አውሮፓና አሜሪካ ዜጎችን ለማሰማራት ለየትኛውም አካል ውክልና አልተሰጠም - የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር

በውጭ ሀገር ስራ ስምሪቱ ወደ አውሮፓና አሜሪካ ዜጎችን ለሥራ ለማሰማራት ለየትኛውም አካል ውክልና አለመስጠቱን የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር አስታወቀ።

ለሥራ ዜጎችን እንልካለን በማለት የማጭበርበር ድርጊት የሚፈጽሙ አካላትን የሕግ ተጠያቂ ለማድረግ እየሰራ እንደሚገኝም ገልጿል።

ካናዳን ጨምሮ በተለያዩ የአውሮፓ ሀገራት ለሥራ ዜጎችን እንልካለን፤ ለዚህም ከሚመለከታቸው አካላት ፍቃድ አግኝተናል በሚል በተለያዩ የማህበራዊ ትስስር ገጾች ህገ-ወጥ ማስታወቂያዎችን በማሰራጨት ህብረተሰቡን ለአላስፈላጊ ወጪና እንግልት እየዳረጉ መሆኑን ሚኒስቴሩ አስታውቋል።

መሰል የማጭበርበር ተግባር እየፈፀሙ የሚገኙ አካላትን በህግ ተጠያቂ ለማድረግ በትኩረት እየሰራ እንደሚገኝ ገልጿል።

ዜጎች በስምሪቱ ተጠቃሚ ለመሆን ህጋዊ አማራጮችን ብቻ በመጠቀም ካላስፈላጊ ወጪ፣ እንግልትና ከሌሎች አስከፊ አደጋዎች ራሳቸውን እንዲጠብቁ አሳስቧል።

ሚኒስቴሩ ዜጎች የሁለትዮሽ ስምምነት በተፈረመባቸው መዳረሻ ሀገራት የሥራ ዕድል ለማግኘት (lmis.gov.et) የተሰኘውን ማስፈንጠሪያ በመጠቀም የኢትዮጵያ የሥራ ገበያ መረጃ ስርዓት ላይ በመመዝገብ ደህንነቱ የተረጋገጠ የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት ተጠቃሚ መሆን እንደሚችሉ ጠቁሟል።

    T.me/ethio_mereja
        ኢትዮ-መረጃ

Показано 20 последних публикаций.