በቴሌ ብር ከ3 ነጥብ 25 ትሪሊየን ብር በላይ ዝውውር ተፈጸመ
በቴሌ ብር መተግበሪያ እስካሁን ከ3 ነጥብ 25 ትሪሊየን ብር በላይ ዝውውር መፈጸሙን ኢትዮ ቴሌኮም አስታውቋል፡፡
የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሬሕይወት ታምሩ እንዳሉት፤ ቴሌ ብር በኢትዮጵያ ዲጂታል የገንዘብ ልውውጥን ከማሳለጥ አንጻር ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ ነው፡፡
በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ የቴሌ ብር ተጠቃሚ ደንበኞች ቁጥር ከ51 ነጥብ 3 ሚሊየን በላይ መድረሱን ገልጸው፤ መተግበሪያው ስራ ላይ ከዋለ ጀምሮ ከ3 ነጥብ 25 ትሪሊየን ብር በላይ ዝውውር ተፈጽሟል ብለዋል።
ኢትዮ ቴሌኮም ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ የተጀመረውን ጥረት ከግብ ለማድረስ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በትብብር እየሰራ መሆኑንም አስረድተዋል፡፡(ኤፍቢሲ)