ታስረው የሚገኙ ፖለቲከኞች እና ጋዜጠኞችን "ሶስት አመት አስራችሁ አቆዩዋቸው" ተብሎ ከፖለቲካው አካል የመጣ ትእዛዝ እንዳለ ታወቀ
ከፍርድ ቤት፣ ከስራ አስፈፃሚው አካል እንዲሁም ከጠበቆች ያሰባሰበው መረጃ እንደሚጠቁመው በተለይ ባለፉት ሁለት እና ሶስት አመታት ለእስር የተዳረጉ እነዚህ ፖለቲከኞች እና የሚድያ ሰራተኞች እስራቸው በፍርድ ሂደት ሳይሆን በፖለቲካ አመራሩ በጎ ፈቃደኝነት ብቻ ሊፈታ እንደሚችል እንደሚያምኑ ታውቋል።
ይህን የተረዱ አንዳንዶቹ ታሳሪዎች ወደ ፍርድ ቤት መመላለሱ ዋጋ እንደሌለው በመረዳት "የፍርድ ሂደቱን አንከታተልም" በማለት ወደ ፍርድ ቤቶች እየሄዱ እንዳልሆኑ ታውቋል።
በዚህ ዙርያ አስተያየት የሰጡን አንድ ጠበቃ "ይህ የሚያሳየው ታሳሪዎቹ የፖለቲካ እንጂ የህግ እስረኛ አለመሆናቸውን ነው፣ ያሰራቸው ፖለቲከኛ እንጂ በህግ ጥሰት ተጠርጥረው አይደለም" ብለዋል።
አክለውም "አሁንም እስራቸው ሊቋረጥ የሚችለው ከበላይ አካል በሚመጣ የ 'ፍቷቸው' ትእዛዝ እንጂ በዳኞች ውሳኔ አይሆንም" በማለት ሁኔታውን አስረድተዋል።(መሠረት-ሚድያ)