የትግራይ ህዝብ ቁስሉ ሳይሽር በፍራቻ ውስጥ ገብቶ በጦርነት ወሬ ተከቦ እየኖረ ይገኛል - ጠቅላይ ሚኒስተር ዶ/ር አብይ አህመድ
ጠቅላይ ሚኒስተር ዶ/ር አብይ አህመድ በዛሬው ዕለት በተለይ ለትግራይ ህዝብና ለትግራይ ልሂቃን የተፃፈ ደብዳቤ አሰራጭተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስተሩ 'ምክር ለትግራይ ህዝብና ልሂቃን' በሚል ርእስ ባሰራጩት ዘለግ ያለ ፅሑፍ በተለያዩ አጋጣሚዎች እንደገለፅኩት የትግራይ መሬትና ህዝብ የስልጣኔ መሰረት ብሎም የሀገር ዋልታና መከታ ናቸው ከዚህ በላይ ግን ትግራይ በርካታ ሀገራቸውን የሚጠቅሙ ሊቆች፣ የሀይማኖት መሪዎች፣ ፖለቲከኞችና የሀገር ሽማግሌዎች ያፈራ ህዝብ ነው ብለዋል።
ዶ/ር አብይ በመግለጫቸው መጥፎ አጋጣሚ ሆኖ ባለፉት መቶ ዓመታት በተለያዩ አጋጣሚና ምክንያቶች በተለይ ደግሞ ከማእከላዊ መንግስት ጋር በሚፈጠሩ አለመግባባቶች ትግራይ የጦርነት አውድማ፣ የትግራይ ህዝብ ደግሞ የጦርነት ገፈጥ ቀማሽ ሆነዋል ብለዋል።
ምክንያቱ ምንም ይሁን ምን መነሳት ያለበት ጥያቄ ባለፉት 100 ዓመታት የተደረጉ ጦርነቶች ለትግራይ ህዝብ ምን አይነት ማህበራዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖምያዊና የፀጥታ ትርፍ አስገኙለት ምንስ አከሰሩት ብለን መጠየቅና ማስላት ይገባል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስተር ዶ/ር አብይ በዚህ ሰዓት አንድ ልባም የትግራይ ልሂቅ ትግራይና ህዝቧ ከጦርነቶቹ ያገኙት ወይስ ያጦት ይበዛል ብሎ መጠየቅና መልስ ማግኘነት ይገባዋል ብለዋል። አክለውም ሁሉም የተደረጉ ጦርነቶች ብቸኛ የመፍትሄ አማራጮች ነበሩ ወይ ብሎም መጠየቅ ከዚህ በኃላስ ተመሳሳይ ጦርነት ውስጥ ላለመግባት ምን መደረግ አለበት የሚል ጥያቄ ተነስቶ ምላሽ መፈለግ ይገባል ብለዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ አክለው አሳዛኙ ነገር የትግራይ ህዝብ የትላንት ቁስሉ ሳይሽር አሁንም ሰላም አግኝቶ ሰርቶ እንዳይኖርና እንዳይለማ በፍራቻ ውስጥ ገብቶ በጦርነት ወሬ ተከቦ እየኖረ ይገኛል ያሉ ሲሆን ይህንን አይነቱ አደጋ እንዴት ማስቀረት እንደሚቻል ላይ በተረጋጋ መንፈስ መመካከር የሚገባው ጉዳይ ስለመሆኑ ግልፅ ነው ብለዋል።
ስለሆነም በትግራይ ፖለቲካ፣ ንግድ፣ ፀጥታ፣ አካዳሚና ሚድያ ብሎም በሌሎች ዘርፎች የምትሰሩ የትግራይ ልሂቃንና መላው የትግራይ ህዝብ የትግራይ ህዝብ እስካሁን የከፈለው ዋጋ ይበቃል፣ ከጦርነት የሚገኝ ትርፍ የለም በማለት በመጀመርያ ደረጃ በውስጣቹ ያለውን ክፍፍል ተነጋግራቹ ጉዳያቹ በሰላምና የትግራይን ህዝብ አንድነት በሚያረጋግጥ መንገድ እንድትፈቱ እጠይቃለው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስተር ዶ/ር አብይ አህመድ ጥሪ አቅርበዋል።
ከዚህ በተጨማሪ ከፌደራል መንግስትም ሆነ ከሌሎች ሀይሎች ጋር ያላቹን ልዩነት በሀገሪቱ ህገ መንግስትና በዴሞክራስያዊ መንገድ ለመፍታት ዝግጁ እንደትሆኑ መልእክቴን አስታልፋለው ሲሉ አክለዋል። ጠቅላይ ሚኒስተሩ በመጨረሻም ለትግራይ ህዝብ ሰላም የተመኙ ሲሆን ቅራኔና ጦርነት ይበቃናል ሲሉ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።
ትርጉም በሚሊዮን ሙሴ
@sheger_press@sheger_press