Ministry of Education Ethiopia


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Образование


This is Ministry of Education's Official Telegram Channel.
For more updates please visit www.facebook.com/fdremoe

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Образование
Статистика
Фильтр публикаций


በሳይንስ ፣ በቴክኖሎጂና ፈጠራ የሴቶችና ልጃገረዶችን እኩል ተሳትፎና ተደራሽነት ማረጋገጥ እንደሚገባ ተመላከተ፤
--------------------------------------------

(የካቲት 05/2017 ዓ.ም) ዓለም አቀፍ የሴቶችና የልጃገረዶች ቀን ሴቶችና ልጃገረዶች “በሳይንስ፣ በምርምር፣ በቴክኖሎጂና በፈጠራ” በሚል የምርምር ኮንፍረንስ ተካሂዷል። a

የትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ኮራ ጡሹኔ በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት ሴቶችና ልጃገረዶችን በሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ፈጠራ እንዲበረቱና ችሎታቸውን እንዲያዳብሩ ማድረግ እንደሚገባ ገልጸዋል። ለሙሉ መረጃው ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://www.facebook.com/share/p/15tG9UM8Hu/


በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚካሄዱ የጥናትና የምርምር ስራዎችን ጭብጥ ተኮር ማድረግ እንደሚገባ ተጠቆመ።
-------------------------------------

(ጥር 04/2017 ዓ.ም) በጭብጥ ተኮር (Thematic) ምርምር ፈንድ አስተዳደር ትግበራ ላይ ያተኮረ ግምገማዊ ስልጠና በትምህርት ሚኒስቴር አዘጋጅነት ተካሂዷል።

የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ኮራ ጡሹኔ በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት በአገሪቱ በርካታ ምርምሮች እየተካሄዱ ቢሆንም ከውጤት ጋር ተያይዞ በርካታ ጥያቄዎች ይነሳሉ።

በተበጣጠሰ መንገድ የሚካሄዱ የጥናትና ምርምር ስራዎች የሚፈለገውን ውጤት እያመጡ አለመሆኑንም ክቡር ሚኒስትር ዴኤታው ጠቁመዋል።

በመሆኑም የፋይናንስ ሀብትን በተገቢው መንገድ ለመጠቀም የምርምር ርዕሶችን ማሰባሰብና ተጨባጭ ማድረግ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

ምርምሮችን በማሰባሰብ ተጨባጭ ለማድረግ ሚካሄደውንም ተግባር ትምህርት ሚኒስቴር ከጎናቸው መሆኑንንም አቶ ኮራ ተናግረዋል።

የምርምርና የማህበረሰብ ጉድኝት ተጠባባቂ መሪ ስራ አስፈጻሚ ሠራዊት ሀንዲሶ (ዶ/ር) በበኩላቸው የ ‘thematic’ (ጭብጥ ተኮር) የምርምር ፈንድ አስተዳደር በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ በመተግበር ላይ መሆኑን አመልክተዋል።

የሪፎርሙ ዋነኛ ዓላማም የምርምር አደረጃጀትን ተገቢነት፣ ውጤታማነት እና ዲጂታላይዜሽን በማሳለጥ የሚካሄዱ ጥናቶች ወጪ ቆጣቢና የማህበረሰቡን ችግር የሚፈቱ እንዲሆኑ ማስቻል መሆኑን ጠቁመዋል። ፈጠራን ማበረታታት የሪፎርሙ ሌላኛው ዓላማ መሆኑንም ዶ/ር ሰራዊት ጨምረው ገልጸዋል።

በግምገማዊ ስልጠናው ላይ ከሁሉም የመንግስትና የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተውጣጡ የምርምርና ማህበረሰብ ጉድኝት ምክትል ፕሬዚዳንቶች እና ዳይሬክተሮች ተገኝተዋል።


በትምህርት ቤትና አካባቢው የሚፈጸሙ ጾታዊ ጥቃቶችን በጋራ የመከላከልና ምላሽ የመስጠት ስራ እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ።

------------------------------
(የካቲት 3/2017 ዓ.ም) በትምህርት ሚኒስቴር የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች አካቶ ትግበራ ሥራ አስፈጻሚ በትምህርት ቤትና አካባቢው የሚፈጸሙ ጾታዊ ጥቃቶችን የመከላከልና ምላሽ የመስጠት አቅምን ለማጎልበት እንዲቻል ለባለድርሻ አካላት የአሰልጣኞች ስልጠና ሰጥቷል።

በመድረኩ የተገኙት የስራ ክፍሉ ሃላፊ ወ/ሮ ምህረተክርስቶስ ታምሩ በትምህርት ቤትና አካባቢው የሚፈጸሙ ጾታዊ ጥቃቶችን በጋራ የመከላከልና ምላሽ የመስጠት ስራ እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰው ይህንን ስራ ከፍ ለማድረግ የባለድርሻ አካላትን የነቃ ተሳትፎ ጠይቀዋል።።


የሥልጠናው ዓላማ ትምህርት ቤቶች ውስጣቸውንና አካባቢያቸውን ከጾታዊ ጥቃቶች ነጻ በማድረግ ሴቶችና ህጻናት ትምህርታቸውን በውጤታማነት የሚከታተሉበትን ምቹ ሁኔታ ለመፍጠርና ለሚከሰቱ ጾታዊ ጥቃቶችም አፋጣኝ ምላሽ መስጠት የሚያስችል አቅም ለመፍጠር መሆኑ ተገልጿል።

ወ/ሮ ምህርተክርስቶስ ጨምረውም ሥልጠናው ሴቶችና ህጻናት ከትምህርት ቤት እንዳይቀሩ፣ሳይሽማቀቁ ትምህርታቸውን እንዲማሩ፣ያለእድሜ ጋብቻና ለሌሎች ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችም እንዳይጋለጡ የባለድርሻ አካላትን ግንዛቤ በማሳደግ የድርሻቸውን እንዲወጡ የሚያግዝ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በሥልጠናው ከትምህርት ሚኒስቴር፣ከክልልና ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮዎች የሚመለከታቸው የሥራ ክፍሎች እና በአገር አቀፍ ደረጃ በናሙናነት ከተመረጡ ትምህርት ቤቶች የተውጣጡ የሥርዓተ ጾታ አስተባባሪዎችና ርእሳነ መምህራን ተሳታፊዎች ሆነዋል፡፡

=====///====


የኢትዮጵያ ዩኒቨርሰቲ ተማሪዎች ስፖርት ፌስቲቫል በመካሄድ ላይ ይገኛል ፤ በወርልድ ቴኳንዶ 12 ተወዳዳሪዎች ወርቅ አግኝተዋል ፡
----------------------------------------------
በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጁ ዩኒቨርስቲ አዘጋጅነት ጥር 17/2017 ዓ.ም የተከፈተው የኢትዮጵያ ዩኒቨርስቲዎች ስፖርት ውድድር ቀጥሎ በመካሄድ ላይ ነው።

በወርልድ ቴኳንዶ በወንዶች በተደረጉ ውድድሮች በ80 ኪ.ግ ምድብ ፋሲል ላቀው ከደብረብርሃን ፣ በ74 ኪ.ግ ግዛቸው ደምሴ ከወልቂጤ ፣ በ68 ኪ.ግ አማኑኤል ዳንኤል ከባህር ዳር፣ በ63 ኪ.ግ. ፍቃዱ ዳንኤል ከሀዋሳ ፣ በ58 ኪ.ግ ተከታይ አደራው ከወላይታ ሶዶ ፣ በ54 ኪ.ግ ድሪባ ደበላ ከጅማ ዩኒቨርስቲ የወርቅ ሜዳሊያ አግኝተዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፤ https://www.facebook.com/share/p/1CKojKRhZ9/


ትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲን ጎበኙ።
---------------------------------------
(ጥር 21/2017 ዓ.ም) የትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮች የኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲን በመጎብኘት ከተቋሙ አመራሮች ጋር ውይይት አድርገዋል።

በጉብኝቱ ወቅትም ዩኒቨርሲቲው ከተቋቋመ ጀምሮ በአካዳሚክ፣ በምርምርና በማህበረሰብ አቀፍ አገልግሎቶች የሰራቸውን ሥራዎች እና ድጋፍ የሚሹ ጉዳዮችን ለአመራሮቹ ገለጻ ተደርጎላቸዋል። ሙሉ መረጃውን ለማግኘት ይህንን ሊንክ ይጫኑ፣ https://www.facebook.com/share/p/18DdMBQaXC/


የትምህርት ሚኒስቴር የሚያከናውናቸውን አዳዲስ የለውጥ ስራዎች የሚደግፍ የመግባቢያ ስምምነት ተፈረመ፡፡
--------------------------------------
(ጥር 20/2017 ዓ.ም) በትምህርት ሚኒስቴር እና በኢንፎ ማይንድ ሶሊሽን መካከል የተፈረመው የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ በትምህርት ሚኒስቴር እየተተገበሩ ያሉ አዳዲስ የለውጥ ስራዎችን በመደገፍ ተቋማትና ተማሪዎች በየጊዜው አቅማቸውን እንዲገነቡ የሚያደርግ መሆኑ ተገልጿል።

የኢፊዲሪ ትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚንስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ኮራ ጡሽኔ በፊሪማ ስነስርዓቱ ላይ እንደገለጹት ስምምነቱ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ ማዕከላትን በማቋቋም እንዲሁም የተለያዩ የአቅም ግንባታ ስራዎች ላይ በመሳተፍ ተማሪዎች የተሻለ አቅም እንዲፈጥሩ የሚያግዝ በመሆኑ ለተግባራዊነቱ ቁርጠኛ መሆን ይገባል ብለዋል።

ስምምነቱ ተማሪዎች በህይወት ጉዞአቸው ወዴትና እንዴት መሄድ እንዳለባቸው የሚያመላክት ስራዎችን ከማከናወን ባለፈ ትምህርታቸውን ጨርሰው ወደ ስራው አለም በሚቀላቀሉበት ወቅት የሚያጋጥሟቸውን ችግሮች ከወዲሁ ለመቅረፍ የሚያስችል መሆኑን ሚንስትር ዴኤታው አያይዘው ገልጸዋል፡፡

የኢንፎ ማይንድ ሶሊሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ የሱፍ ረጃ በበኩላቸው በሰጡት ማብራሪያ የስምምነቱ መፈረም የተማሪዎችን አቅም ከመገንባት ባለፈ ሚኒስቴር መስያ ቤቱ በቀጣይ ለሚያከናወናቸው የጥናትና ምርምር ስራዎች መረጃዎችንም ጭምር ለማግኘት የሚያስችል ነው ብለዋል ፡፡




የከፍተኛ ትምህርትና ስልጠና ጥራትን ለማስጠበቅ በተዘጋጀው የጥራት ኦዲት መመሪያ እና ስታንዳርድ ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ተደረገ።
----------------------------------------------
(ጥር 18/2017 ዓ.ም) በትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ኮራ ጡሽኔ በውይይቱ መክፈቻ ላይ በመገኘት ባስተላለፉት ቁልፍ መልእክት የትምህርት ስርዓቱ ፍትሃዊ፣ አካታች፣ ተደራሽነት ያለውና ችግር ፈቺ ለማድረግ በሚደረጉ ጥረቶች ውስጥ የባለድርሻ አካላትና አጋር ድርጅቶች ሚናቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ አቅርበዋል።

የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ ቀጣይነት ያለውና እየተሻሻለ የሚሄድ የውስጥ ጥራት አጠባበቅ ስርዓት የመዘርጋት፣ ስታንደርዶችን የማውጣትና ተግባራዊነታቸውን የማረጋገጥ ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ሚንስትር ዴኤታው አያይዘው ገልጸዋል።

በዚህም ዜጎች የሀገሪቱን ልማትና ዕድገት ለማሳለጥ የሚያስችል ዕውቀት፤ ክህሎት እና አመለካከት ይዘው እንዲወጡና ከዘመኑ ጋር የሚሄድ የትምህርትና ስልጠና ጥራት ኦዲት መመሪያ እና ስታንዳርዶች የተዘጋጁ መሆኑ ተገልጿል።

የትምህርት ተቋማቱ በቀጣይ መመሪያው ከጸደቀ በኋላ በአዲሱ የስልጠና ጥራት ኦዲት መመሪያ እና ስታንዳርድ መሠረት የሚመዘኑ መሆኑ ተጠቁሟል



Показано 9 последних публикаций.