ኢትዮ ቴሌኮም 114 ተጨማሪ ከተሞችን የ4ጂ ኤል.ቲ.ኢ አድቫንስድ ኔትወርክ ተጠቃሚ አደረገ! ኢትዮ ቴሌኮም በባሌ ዞን፣ አርሲ ዞን፣ ምስራቅ ባሌ ዞን፣ ምዕራብ አርሲ ዞን እና ምስራቅ ሸዋ ዞን በሚገኙ 114 ተጨማሪ ከተሞች የላቀ ፍጥነት ያለው የ4ጂ ኤል.ቲ.ኢ አድቫንስድ ሞባይል ኔትወርክ አገልግሎት ተጠቃሚ ማድረጉን በታላቅ ደስታ እንገልጻለን!
ኩባንያችን ሲያከናውን የነበረውን መጠነ ሰፊ የ4ጂ ኤል.ቲ.ኢ አድቫንስድ ኔትወርክ ማስፋፊያ ፕሮጀክት በማጠናቀቅ በደቡብ ምስራቅ ሪጂን 58 እንዲሁም በደቡብ ደቡብ ምስራቅ ሪጂን 56 በድምሩ 114 ከተሞችን የአገልግሎቱ ተጠቃሚ አድርጓል።
ይህን ያበሰረው በትላንትናው ዕለት የባሌ ሮቤና የአርሲ ከተሞች የ5ጂ ኔትወርክ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ላይ ነው፡፡ በዚህም ወቅት የ4ጂ ኤል.ቲ.ኢ አድቫንስድ ኔትወርክ የላቀ ፍጥነት ያለው የኢንተርኔት ግንኙነትን እውን በማድረግ አዳዲስ ዕድሎችን በመክፈት ለአካታች የዲጂታል ኢኮኖሚ እድገት የላቀ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ተብራርቷል።
ኢትዮ ቴሌኮም የላቀ የኢንተርኔት ፍጥነት በመላ ሀገራችን በማስፋፋት አካታች የዲጂታል ኢኮኖሚ በመገንባት ረገድ የበኩሉን ሚና መጫወቱን አጠናክሮ ይቀጥላል፡፡
ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን በማድረግ ላይ!
የከተሞቹን ዝርዝር ይመልከቱ፡
https://bit.ly/4lmShKp #RealizingDigitalEthiopia #4GLTEAdvanced #BaleRobe #Assela