የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬሕይወት ታምሩ እና የቱሪዝም ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ሰላማዊት ካሳ የኢትዮ ቴሌኮምን ግዙፍ የኮሙኒኬሽን እና የዲጂታል መሠረተ ልማት በመጠቀም የኢትዮጵያን ቱሪዝም ዘርፍ ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ በሚቻልበት ስትራቴጂዎች ላይ ፍሬያማ ውይይት አድርገዋል፡፡
ውይይቱ በመከናወን ላይ ያለውን የቨርቹዋል ቱሪዝም ፕሮጀክት ከማጠናቀቅ በተጨማሪ በመላ ሀገሪቱ ቁልፍ በሆኑ የቱሪስት መዳረሻዎች ላይ ዘመኑ የደረሰበትን ኔትወርክ በመጠቀም እና ዘመናዊ የዲጂታል ቴክኖሎጂዎችን ተግባራዊ በማድረግ የጎብኚዎችን ተሞክሮ በከፍተኛ ደረጃ ለማሳደግ የታለሙ አዳዲስ ቴክኖሎጂ-ተኮር መፍትሄዎች ላይ ጠንካራ መሰረት ለመጣል ላይ ያተኮረ ነው።
የቱሪዝም ኢንዱስትሪውን ለማዘመን እንደ ኦግመንትድ ሪያሊቲ (AR) እና ቨርቹዋል ሪያሊቲ (VR) ያሉ የዲጂታል ቴክኖሎጂዎችን ሥራ ላይ ለማዋል ሲሆን፣ የእነዚህ ቴክኖሎጂዎች ተግበራዊ መደረግ ጎብኚዎች የኢትዮጵያን እምቅ ባህላዊና ተፈጥሯዊ ቅርሶች መስተጋብራዊ በሆነ መንገድ ለመረዳት ያስችላቸዋል። ይህም ጎብኚዎች የቱሪዝም መዳረሻዎችን በአካል ተገኝተው የላቀ ተሞክሮ እንዲያገኙ ከማስቻል ባሻገር በቨርቹዋል ቱሪዝም የሀገራችንን የቱሪስት መዳረሻዎች ለዓለም በማስተዋወቅ ረገድ ከፍተኛ ፋይዳ ይኖረዋል፡፡
በተጨማሪም ትብብሩ የቱሪዝም አገልግሎቶችን ለማዘመን የሚያስችል የጥሪ ማዕከል ማቋቋምን ያካተተ ሲሆን አስፈላጊ መረጃዎችን በቀላሉ ለማግኘት፣ የክፍያ ሂደቶችን ለማቀላጠፍ እንዲሁም በቴክኖሎጂ የተደገፈ አገልግሎት ለማቅረብ ያስችላል፡፡
የኩባንያችን ዋና ሥራ አስፈጻሚ እና ክብርት ሚኒስትሯ የኢትዮጵያ የቱሪዝም ዘርፍ በዲጂታል የማዘመን ራዕይ እውን ለማድረግ የሚያስችል የፕሮጀክት ቡድኖች በማቋቋም ወደትግበራ ለመግባት ስምምነት ላይ ደርሰዋል።