ኢትዮ - ኮን ሬድዮ ፕሮግራም/Ethio con radio perogram/


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Музыка


በግንባታው ዘርፍ ላይ ትኩረት የሚያደርግ ሳምንታዊ የባለሙያዎች ፕሮግራም የኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን ሥራ ተቋራጮች ማህበር ከአሀዱ ሬድዮ 94.3 ትብብር
ዘወትር ሰኞ ምሽት ከ2፡30-3፡30 ሰዓት የሚተላለፍ ሳምንታዊ ፕሮግራም ነው።

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Музыка
Статистика
Фильтр публикаций


ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር  ተመስገን ጥሩነህ ቃሊቲ የሚገኘውን የኮርፖሬሽኑን የኢንዱስትሪ መንደር ጎበኙ

የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን ( ኢ.ኮ.ሥ.ኮ) ካነገበው ራእይ እና ተልእኮ አንጻር  በአፍሪካ ምርጥ ሦስት የኮንስትራክሽን እና ማኑፋክቸሪንግ ኩባንያዎች መካከል አንዱ ለመሆን የሚያስችሉትን ተግባራት እያከናወነ መሆኑን መመልከታቸውን  የገለጹት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኮርፖሬሽኑ  በቅርቡ የኮንስትራክሽን  ግብአት ምርቶችን በስፋት እና በጥራት በማምረት ለሀገር ውስጥ እና ለውጭ  ገበያ  እንደሚያቀርብ  ያላቸውን ተስፋ ገልጸዋል።

በጉብኝታቸው  በኮርፖሬሽኑ እየተከናወኑ   ያሉ የሪፎርም  ተግባራት     እና ያስገኙት ውጤት  እውነትም  የኢትዮጵያ  የማንሰራራት  ጊዜ መጀመርን  የሚያሳይ  መሆኑን የጠቆሙት  ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር  እና የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የቦርድ ሰብሳቢ አቶ ተመስገን ጥሩነህ የሥራ አካባቢን ጽዱ እና ምቹ ከማድረግ፣ የፕሮጀክቶች አፈጻጸምን ዘመናዊ ቴክኖሎጂን በመጠቀም  ከማስተዳደር፣ የሰው ሀይልን ምርታማነት ከማሻሻል፣  የፕሮጀክቶች አፈጻጸምን ከማላቅ እና ትርፋማነትን  ከማሳዳግ አንጻር የተከናወኑ  ተግባራት ሌሎች ተቋማት ሊማሩበት የሚገባ ነው ብለዋል።

የኢ.ኮ.ሥ.ኮ  ዋና ሥራ አስፈጻሚ   ኢንጂነር ዮናስ አያሌው የኮርፖሬሽኑን 'ከየት ወዴት' ለጎብኚዎች ገለጻ ያደረጉ ሲሆን በቀጣይ የኮርፖሬሽኑን የልህቀት ትልሞች በመተግበር  ረገድ የኮርፖሬሽኑ አመራሮች እና ሠራተኞች ለውጡን  በላቀ ሁኔታ  እንደሚያረገረጋግጡ  አብራርተዋል።

በጉብኝቱ  የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር  ጽ/ቤት ፣ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ እና የኢ.ኮ.ሥ.ኮ  አመራሮች ተገኝተዋል።


❇️የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ 4ኛ ዓመት 4ኛ መደበኛ ስብሰባ ለከተማዋ ልማት ጉልህ ፋይዳ ያላቸው አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ አፅድቋል፡፡

የጸደቁ አጀንዳዎች:-

1ኛ. የወንዝ እና የወንዝ ዳርቻ ልማት ብክለት መከላከል ረቂቅ ደንብ ላይ ተወያይቶ ለከተማዋ ነዋሪዎች ጤና፣ ፅዳት እና ውበት ወሳኝ እና ጠቃሚ መሆኑን በማረጋገጥ ደንቡን በሙሉ ድምፅ አፅድቋል፡፡

2ኛ. በከተማ ፕላን ልማት ቢሮ የተዘጋጁና የሚዘጋጁ የአካባቢ ልማት ፕላን ዝግጀት፣ አፈፃፀም ቁጥጥር እና ደንብ ማሻሽያን መርምሮ በመወያየት በሙሉ ድምፅ አፅድቋል፡፡

3ኛ. የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኤሌክትሪክ አውቶቡሶች ማቅረብ በመጀመሩ የኤሌክትሪክ አውቶቡሶች አገልግሎት አስተዳደር ረቂቅ መነሻ ሀሳብ መርምሮ በጥልቅ በመወያየት በመንግስት እና የግል አጋርነት (PPP) እንዲተዳደሩ ብሎም በከተማዋ የመንግስት እና የግል ትራንስፖርት አገልግሎት እስከ ምሽቱ 4፡00 ድረስ ግልጋሎት እንዲሰጡ እና በሁሉም የኮሪደር ልማት በሚተገበርባቸው ቦታዎች የትራንስፖርት አገልግሎት እለታዊ የጊዜ ሰሌዳ እንዲጠቀሙ እንዲደረግ

4ኛ. በሁሉም የከተማዋ ዋና ዋና መንገዶች ያሉ የንግድ እና የአገልግሎት መስጫ ተቋማት እስከ ምሽቱ 3፡30 ለህብረተሰቡ የተሟላ አገልግሎት እንዲሰጡ

5ኛ. ሁሉም ዋና መንገድ እና መጋቢ መንገድ ላይ ያሉ ተቋማት፣ ህንፃዎች እንዲሁም የግልና የመንግስት ቢሮዎች ምሽት መብራት ማጥፋት እንዲከለከል እና ሙሉ የመብራት አገልግሎት እንዲኖር ውሳኔ አስተላልፏል፡፡

(ከፅቤ)


በግንባታ ስራ ላይ ለተሰማሩ ተቋራጮችና አማካሪዎች የተዘጋጀው የዓቅም ግንባታ ስልጠና እየተሰጠ ነው።

በአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ የተዘጋጀውና ትኩረቱን Construction Material Management እና Construction Human Resource Management ላይ ያደረገው የዓቅም ግንባታ ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል፡፡

በቢሮው በተከታታይነት እየተሰጡ ከሚገኙና የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪውን ዓቅም ከሚያጎለብቱ ስልጠናዎች ውስጥ አንዱ በሆነው በዚሀ ስልጠና በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ 250 ስራ ተቋራጮች እና አማካሪዎች  እየተሳተፉ ይገኛሉ፡፡

በቀጣይም በሁለተኛ ዙር Construction Claim and Dispute Resolution በሚል የስልጠና ርዕስ ላይ ስልጠናው አንደሚቀጥል ከቢሮው የዓቅም ግንባታ ዳይሬክቶሬት ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

ቢሮው በርካታ ግንባዎችን በጥራት በማከናወን ለአገልግሎት እያዋለ ከመሆኑ ጎንለጎን የኢንዱስትሪውን ተዋንያን ዓቅም የሚያጎለብቱ ተከታታይ ስልጠናዎችን በመስጠት የከተማው ኮንስትራክሽን ዕድገት ላይ የላቀ የድርሻ እያበረከተ ይገኛል።


(አአዲግቢ)


በፌዴራል ዋና ኦዲተር ተቋሙ ላይ ለቀረበው የኦዲት ግኝት የግብረ - መልስ ማብራሪያ ተሰጠ

የፌዴራል ኢዲተር በኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን ባካሄደው የኦዲት ግኝት ላይ ለተወካዮች ምክርቤት የመንግስት ወጪ አስተዳደር እና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ  የግብረ-መልስ ሪፖርት አቅርቧል፡፡

በተወካዮች ምክር ቤት መሰብሰቢያ አዳራሽ በተካሄደው የኦዲት ሪፖርት ግኝቱ የውይይት መድረክ ላይ ቋሚ ኮሚቴው ምላሽ የሚሰጥባቸውን ጥያቄዎች አቅርቧል፡፡

የፌዴራል ዋና ኦዲተር ግኝት በዋናነት
ከ2013  - 2015 ዓ.ም የኮንስትራክሽን ፕሮጀክቶች ክትትልና ቁጥጥር ፣ የስራ ተቋራጮች ብቃት ምዘናና ክትትል እንዲሁም የሙያ ደህንነትና ጤንነት አጠባበቅ አፈፃፀምን የተመለከተ ነው፡፡

እነዚህን የተመለከቱ ሃያ የኦዲት ግኝቶችና ተያያዥ ጥያቄዎች በቋሚ ኮሚቴው በዝርዝር ተደምጠዋል፡፡

የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ኢ/ር መስፍን ነገዎ የኦዲት ግኝቶቹን ተከትሎ  በተቋሙ  በአጭር ጊዜ የተከናወኑ የእርምትና የማስተካከያ ስራዎችን የተመለከተ ሪፖርት አቅርበዋል፡፡

ፕሮጀክቶችን አስመልክቶ ከኦዲት ግኝቱ በኋላ ማስተካከያ የተካሄደባቸው፣ በድጋሚ ለጨረታ የወጡ፣ በስምምነት ኮንትራታቸው የተቋረጡ እና በፍርድ ቤት ሂደት ያላለቁትን ሪፖርት ዋና ዳይሬክተሩ  አስደምጠዋል ፡፡

እንዲሁም ትግበራቸው የተቋረጡ የመንግስት ፕሮጀክቶች የቅድመ ክፍያን ተመላሽ በማድረግ ረገድ ተግባራዊ የተደረጉ እና በሂደት ላይ ያሉትንም ሪፖርት አቅርበዋል፡፡

የዘርፉን የመረጃ ስርዓት በአስተማማኝ ሁኔታ በማደራጅት እንዲሁም ለተቋሙ የተሰጡትን ተግባራት ውጤታማ ለማድረግ እንቅፋት የሆኑ አሰራሮችና የህግ ማዕቀፎች የሚስተካከሉበት አግባብ በመከናወን ላይ ስለመሆኑም አብራርተዋል፡፡

በዋናነትም የኮንስትራክሽን ቁጥጥር አዋጅ እና መመሪያ ፣ ከመረጃ መረብ ደህንነት አገልግሎት ጋር በጋራ በመሆን በመልማት ላይ የሚገኘው የተቀናጀ የኮንስትራክሽን ሬጉላቶሪ መረጃ አስተዳደር ስርዓት ተጠናቀው ስራ ላይ ሲዉሉ  የተቋሙን ተግባርና ኃላፊነት በውጤታማነት ለመወጣት የሚያስችል እንደሆነም ኢ/ር መስፍን ነገዎ አስረድተዋል፡፡

ከግንባታ ፕሮጀክቶች ቁጥጥር ስርዓት አንፃር ከክልሎች ጋር መኖር ስለሚገባው ግንኙነት፣ የውጭ አገር ተቋራጮች ምዝገባና ፈቃድ አሰጣጥ፣ ሕጎችና ደንቦችን ከማስከበር አንፃር መወሰድ የሚገባቸው ርምጃዎችን  እንዲሁም በዘርፉ የሴቶች ተጠቃሚነት የተመለከቱ የኦዲት ግኝቶች ላይም ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
ሪፖርቱን ተከትሎ  የፕሮጀክቶችን ጥራት ከማስጠበቅ፣ መልካም አስተዳደርን ከማስፈን ፣ ብልሹ አሰራርን ከመከላከል አንፃር ትኩረት በመስጠት በተቋሙ እየተከናወኑ ስላሉ የክትትል ስራዎች በቋሚ ኮሚቴ አባላት የማብራሪያ ጥያቄዎች ቀርበው ከተቋሙ የስራ ኃላፊዎች ግብረ - መልስ ተሰጥቷል፡፡

የፌዴራል ዋና ኦዲተር   ወ/ሮ መሰረት ዳምጤ ከኦዲት ግኝቱ ትምህርት በመቅሰም የግንባታ ፕሮጀክቶች ውጤታማ  መሆናቸውን በማረጋገጥ ረገድ ተቋሙ የተሰጡትን ስልጣንና ተግባራት በቁርጠኝነት ማከናወን እንደሚገባው ትምህርት ሊወሰድ ይገባል ሲሉ ገልጸዋል።

የመንግስት ወጪ አስተዳደር እና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ም/ሰብሳቢ የተከበሩ ወ/ሮ አራሬ ሞሲሳ በሰጡት ማጠቃለያ  በኦዲት ግኝቶቹ የተለዩና በቀጣይ መስተካከል የሚገባቸው ጉዳዮች መርሃግብር እንዲዘጋጅላቸውና በሂደት መፍትሄ ያገኙት ላይ ለባለድርሻ አካላት ሪፖርት እንዲቀርብ አሳስበዋል፡፡

(ኢኮባ)


👉 የዛሬ ምሽት ህዳር 30 ቀን 2017 ዓ.ም ኢትዮ ኮን ሳምንታዊ ፕሮግራም

🚧 👷‍♀🏢የሬድዮ ፕሮግራሙ በኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን ኢንደስትሪ የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶችን በመንቀስ የመፍትሄ አቅጣጫ የሚጠቀሙ ፕሮግራሞችን እንዲሁም የተለያዩ የኮንስትራክሽን ባለሙያዎችን በመጋበዝ ዘርፉ ላይ ያላቸውን የሙያ ክህሎታቸውና ልምዳቸውን የሚያካፍሉበት ሳምንታዊ የሬድዮ ፕሮግራም ነው፡፡

🛑 በዛሬ ፕሮግራማችን

⭕️ ወቅታዊ ፕሮግራም

🔻11ዙር ሀገር አቀፍ የጥራት ሸልማት ውድድር ስነ ስርዓት ታህሳስ 5 ቀን 2017 ዓ.ም በታላቁ ቤተ መንግስት ይከናወናል።

ይህንን በተመለከተ የኢትዮጵያ ጥራት ሽልማት ድርጅት ዋና ስራ አስፈፃሚ ከሆኑት ከአቶ ቴውድሮሰ መብራቱ ጋር ቆይታ እናደርጋለን።

⭕️ የእንግዳ ሰዓት

🔻አቶ ዮፍታሔ ዮሀንስ የዛሬ እንግዳችን ናቸው፡፡
በአይቲ እና በቴሌኮም ፕሮግራም ላይ በመስራት 17 ዓመት ልምድ ያካበቱ ባለሙያ ናቸው፡፡ ታድያ የአቶ ዮፍታሔ ከኮንስትራክሽን ዘርፍ ጋር ምን አገናኛቸው እንደምትሉ መገመት አያዳግትም፡፡ ዛሬም የምናደርገው ቆይታ ክፍል ሁለት የሚቀጥል ይሆናል።

❇️ በርካታ የሆኑ ልምዶችና ዕውቀቶችን የምታገኙበት በመሆኑ ሰዓቱን ጠብቃችሁ ፕሮግራሙን እንድትከታተሉ በድጋሚ በአክብሮት እጋብዛችኋለሁ፡፡

✍️📞☎️ የምታነሱት ሀሳብ አስተያየትና ጥያቄ ከአሁን ሰዓት ጀምሮ በዚሁ በቴሌግራም ገፃችን ላይ አድርሱን፡፡

🥍📻🕰 ምርጫችሁ አድርጋችሁ ምሽት
ከ2፡30 — 3፡30 ሰዓት በአሀዱ ሬድዮ 94.3 ላይ በቀጥታ ስርጭት ፕሮግራም ጋር ይሁን!


የሪል_ስቴት_ልማት_እና_የማይንቀሳቀስ_ንብረት_ግብይትና_ግመታ_አዋጅ.pdf
1.7Мб
የሪል ሰቴት ልማት እና የማይንቀሳቀሰ ንብረት ግብይትና ግመታ ረቂቅ አዋጅ አጭር ማብራሪያ....


6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት በ4ኛ ዓመት የስራ ዘመኑ ባካሄደው 9ኛ መደበኛ ስብሰባው በየዘርፉ ያሉ ችግሮችን ይፈታሉ የተባሉ ሶስት ረቂቅ አዋጆችን መርምሮ አፅድቋል

የመጀመሪያው የኢትዮጵያ ሕንፃዎች ረቂቅ አዋጅ ሲሆን፤ የከተማ መሰረተ ልማትና ትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ የተከበሩ እሸቱ ተመስገን (ዶ/ር) የረቂቅ አዋጅን አስመልክቶ በቋሚ ኮሚቴው የተዘጋጀውን ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ አቅርበዋል፡፡

ረቂቅ አዋጁ በነባሩ ሕግ በአፈፃፀም የተለዩ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን የሚፈታ፣ የአካል ጉዳተኞችን ተደራሽነት የሚያረጋግጥ፣ የግንባታ ጥራትና የሀብት ብክነት ችግሮች የሚቀርፍ፣ ግልፅና ለአተገባበር ምቹ የሆነ የአሰራር ስርዓት መዘርጋት የሚያስችል መሆኑን ባቀረቡት የውሳኔ ሀሳብ ገልጸዋል፡፡

ምክር ቤቱም በቀረበው ረቂቅ አዋጅ ላይ በስፋት ከተወያየ በኋላ የኢትዮጵያ ሕንፃዎች አዋጅን፤ አዋጅ ቁጥር 1356/2017 አድርጎ በሙሉ ድምጽ አፅድቆታል፡፡ 

በተመሳሳይም የተከበሩ እሸቱ ተመስገን
(ዶ/ር) የሪል እስቴት ልማት እና የማይንቀሳቀስ ንብረት ግብይትና ግመታ ረቂቅ አዋጅን አስመልክቶ የተዘጋጀውን ሪፖርትና የውሳኔ በዝርዝር አቅርበዋል፡፡

የሪል እስቴት ልማቱ አቅርቦት እጅግ ወደኋላ የቀረና የህዝቡን ፍላጎት የማያሟላ በመሆኑ፣ የማይንቀሳቀስ ንብረት ግመታ ስርዓቱ ዘመናዊና በመረጃ በተደገፈ መልኩ ተገማች ዋጋ እንዲኖረው ማድረግ በማስፈለጉ እና በማይንቀሳቀስ ንብረት ገበያው ግልጽነት መጓደሉ የኢኮኖሚ መዛባት እያስከተለና የመንግስትን ጥቅም የሚያሳጣ እንዳይሆን ለማድረግ የሚያስችል ረቂቅ አዋጅ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ምክር ቤቱም በቀረበው ረቂቅ አዋጅ ላይ በስፋት ከተወያየ በኋላ ረቂቅ አዋጁ፤ አዋጅ ቁጥር 1357/2017 ሆኖ በሁለት ተቃውሞና በአንድ ድምፀ ተዓቅቦ በአብላጫ ድምጽ ፀድቋል፡፡ 

በመቀጠልም ምክር ቤቱ በውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ በተከበሩ ዲማ ኖጎ (ዶ/ር) የኤሌክትሮኒክስ ፊርማ አዋጅ ቁጥር 1072/2010 ማሻሻያ አዋጅ ለማፅደቅ የቀረበው ሪፖርትና የውሳኔ ሀሳብ አዳምጧል፡፡

የተከበሩ ዶ/ር ዲማ ባቀረቡት የውሳኔ ሀሳብ ኤሌክትሮኒክ ፊርማ አዋጅ ቁጥር 1072/2010 ለመተግበር የሚያስፈልጉ ደንብና መመሪያዎችን አውጥቶ ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችል ውክልና ለሚኒስትሮች ምክር ቤት እና ለኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር አለመስጠቱ አዋጅ ቁጥር 1072/2ዐ10 ተፈፃሚ ለማድረግ ተቋሙ መቸገሩንና የተቋሙ ሥራ መጓተቱን ቋሚ ኮሚቴው ተገንዝቧል ብለዋል፡፡

በመሆኑም ቋሚ ኮሚቴው ረቂቅ አዋጁን ከመረመረ በኋላ አስፈላጊነቱን በሙሉ ድምፅ የተቀበለው መሆኑን ጠቁመው፤ የተከበረው ምክር ቤት ረቂቅ አዋጁን እንዲያፀድቀው ጠይቀዋል፡፡

ምክር ቤቱም በቀረበው የረቂቅ አዋጅ ማሻሻያ ላይ በስፋት ከተወያየ በኋላ የኤሌክትሮኒክስ ፊርማ አዋጅ ቁጥር 1072/2010 ማሻሻያ አዋጅ፤ አዋጅ ቁጥር 1358/2017 አድርጎ በሙሉ ድምጽ አፅድቆታል፡፡

(ፖርላማ)


🔷በመዲናዋ የግንባታ ተረፈ ምርት አያያዝና አወጋገድን ስርዓት የሚያሲዝ አሰራር ከነገ ጀምሮ ሊተገበር ነው

ከአዲስ አበባ ከተማ ውበትና ፅዳት ጋር የሚጣጣም የግንባታ ተረፈ ምርት አያያዝና አወጋገድን ስርዓት የሚያሲዝ አሰራር ከነገ ጀምሮ ተግባራዊ ሊደረግ መሆኑን የከተማ አስተዳደሩ አስታወቀ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ሁለተኛው ምዕራፍ የኮሪደር ልማት የስራ አፈጻጸም ሪፖርት በተገመገመበት ወቅት በኮሪደር ልማቱ የተገነቡ መሰረተ ልማቶችን በአግባቡ ማስተዳደር እንደሚገባ ገልጸው ነበር።

የግንባታ ተረፈ ምርት አያያዝና አወጋገድ በተለይም ተረፈ ምርት በተሽከርካሪ ሲጓጓዝ ስርዓት የከተማዋን ገፅታና መሰረተ ልማት በማያበላሽ መልኩ መሆን እንደሚገባ አሳስበዋል።

በከተማዋ የሕገ ወጥ የግንባታ ተረፈ ምርቶች እና ግብዓቶችን ስርዓት ለማስያዝ የተዘጋጀው ማስፈፀሚያ ዕቅድ ዙሪያ የባለድርሻ አካላት የንቅናቄ መድረክ ዛሬ ተካሂዷል።

በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር ወንድሙ ሴታ በዚሁ ወቅት፤ ባለፉት ጥቂት ዓመታት ከተማ አቀፍ የልማት ስራዎች የሀገር ገፅታ እየለወጡ መሆኑን ተናግረዋል።

ከተማዋን ውብና ጽዱ ለማድረግ ከሚደረገው ጥረት ጋር የሚጣጣም ለግንባታ ተረፈ ምርቶች አያያዝና አወጋገድ ስርዓት ማበጀት እንደሚጠይቅ ገልፀዋል።

በዚህም የግንባታ ተረፈ ምርት የሚያንቀሳቅሱ የጭነት ተሽከርካሪዎች የከተማዋን ውበትና ጽዳት በማይጎዳ መልኩ እንዲከውኑ የሚያስገድድ አሰራር ከነገ ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚደረግ ተናግረዋል።

ይህ አሰራር የመንገድና ሌሎች መሰረተ ልማቶችን ከጉዳት ለመጠበቅ፣ የተሳለጠ እንቅስቃሴና ጤናማ ከባቢ መፍጠር እንደሚያስችል ጠቁመው፤ አሰራሩ ሳይሸራረፍ መተግበር ይገባዋል ነው ያሉት።

የከተማ አስተዳደሩ ፅዳት ኤጀንሲ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ሙላት ተገኝ በበኩላቸው፤ ከህዝብ ቁጥር፣ ከከተማው መስፋፋትና የኢንዱስትሪ ዕድገትን ተከትሎ የቆሻሻ መጠንና አይነት እየጨመረ ነው ብለዋል።

ኤጀንሲው ቆሻሻን በወቅቱና በተደራጀ መልኩ የመሰብሰብ፣ የማስወገድና መልሶ ጥቅም ላይ እንዲውል በትኩረት እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

በግንባታ ሂደት የሚመነጩ ተረፈ ምርቶችና ግብዓት አያያዝና አወጋገድ ስርዓት የጎደለው በመሆኑ ለከተማ ውበት፣ ለእንቅስቃሴ እንዲሁም ለማህበረሰቡ የጤና ጠንቅ እንደሆነ አንስተዋል።

በመዲናዋ በ66 ወረዳዎች ሕገ ወጥ የግንባታ ተረፈ ምርት መከማቸቱን ያነሱት አቶ ሙላት፤ አዲሱ አሰራር እንዲህ ዓይነት ሕገ ወጥ የግንባታ ተረፈ ምርት አያያዝ ላይ ህጋዊ እርምጃ መውሰድ እንደሚያስቸል መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል።


❇️የሲሚንቶ ዋጋ በሲሚንቶ አምራች ፋብሪካዎች እንዲወሰን ተደረገ

🔷የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ለሲሚንቶ ፋብሪካ ድርጅቶች በጻፈው ደብዳቤ ከጥቅምት 29 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ  ምርታቸውን በፍትሃዊ ዋጋ  እንዲያቀርቡ መወሰኑን አስታውቋል፡፡

🔷ከዚህ ቀደም የሲሚንቶ ምርት የፋብሪካ መሸጫ ዋጋ በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እየተወሰነ ለገበያ ሲሰራጭ የቆየ ቢሆንም በአዲሱ የአሰራር ሂደት ግን አምራች ፋብሪካዎች ሙሉ ሀላፊነቱን በመውሰድ በነጻነት ምርታቸውን ለገበያ እንዲያቀርቡ እና ገበያውን እንዲያረጋጉ ሃላፊነት መስጠቱን ሚኒስቴሩ እውቁልኝ ብሏል፡፡

🔷የሲሚንቶ ፋብሪካዎቹ የተሰጣቸውን ሀላፊነት በተጠያቂነት ስሜት እና በፍትሃዊ የዋጋ ተመን ማህበረሰቡን እንዲያገለግሉም መወሰኑን ገልጾ ከዚህ ቀደም አገልግሎት ላይ ይውል የነበረውን መመሪያ 940/2015 ማንሳቱን ይፋ አድርጓል፡፡


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
ኢትዮ ኮን ህዳር 23፤ 2017


👉 የዛሬ ምሽት ህዳር 23 ቀን 2017 ዓ.ም ኢትዮ ኮን ሳምንታዊ ፕሮግራም

🚧የሬድዮ ፕሮግራሙ በኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን ኢንደስትሪ የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶችን በመንቀስ የመፍትሄ አቅጣጫ የሚጠቀሙ ፕሮግራሞችን እንዲሁም የተለያዩ የኮንስትራክሽን ባለሙያዎችን በመጋበዝ ዘርፉ ላይ ያላቸውን የሙያ ክህሎታቸውንና ልምዳቸውን የሚያካፍሉበት ሳምንታዊ የሬድዮ ፕሮግራም ነው፡፡

📷በዛሬ ፕሮግራማችን፡-

👷የእንግዳ ሰዓት

አቶ ዮፍታሔ ዩሀንስ የዛሬ እንግዳችን ናቸው፡፡
በአይቲ እና በቴሌኮም ፕሮግራም ላይ በመስራት 17 ዓመት ልምድ ያካበቱ ባለሙያ ናቸው፡፡ ታድያ የአቶ ዮፍታሔ ከኮንስትራክሽን ዘርፍ ጋር ምን አገናኛቸው እንደምትሉ መገመት አያዳግትም፡፡ ለዚህ ምላሽ ምሽት በሚኖረን የቀጥታ ስርጭት ፕሮግራማችንን ጠብቃችሁ ትከታተሉን ዘንድ ከወዲሁ በአክብሮት ነው የምጋብዘው፡፡

❇️ በርካታ የሆኑ ልምዶችና ዕውቀቶችን የምታገኙበት በመሆኑ ሰዓቱን ጠብቃችሁ ፕሮግራሙን እንድትከታተሉ በድጋሚ በአክብሮት እጋብዛችኋለሁ፡፡

✍️📞☎️ የምታነሱት ሀሳብ አስተያየትና ጥያቄ ከአሁን ሰዓት ጀምሮ በዚሁ በቴሌግራም ገፃችን ላይ አድርሱን፡፡

🥍📻🕰 ምርጫችሁ አድርጋችሁ ምሽት
ከ2፡30 — 3፡30 ሰዓት በአሀዱ ሬድዮ 94.3 ላይ በቀጥታ ስርጭት ፕሮግራም ጋር ይሁን!


የኢትዮጵያ አየር መንገድ በ5 ቢሊየን ፓውንድ በቢሾፍቱ ከተማ የሚገነባው "ሜጋ ኤርፖርት ከተማ" ፕሮጀክት ይፋ ተደረገ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በ5 ቢሊየን ፓውንድ በቢሾፍቱ ከተማ የሚገነባው "ሜጋ ኤርፖርት ከተማ" ፕሮጀክት ይፋ ሆኗል።

ከአዲስ አበባ በ25 ማይል ርቀት ላይ በምትገኘው ቢሾፍቱ አቅራቢያ የሚገኘው ይህ የወደፊት አየር ማረፊያ በ2029 ሲጠናቀቅ እስከ 110 ሚሊዮን መንገደኞችን በዓመት የሚያስተናግድ ትልቅ ተርሚናል እና አራት ማኮብኮቢያዎችን ይይዛል ተብሏል።

በኢትዮጵያ አየር መንገድ ከዳር አል ሀንዳሳ አማካሪዎች ጋር በመተባበር የሚመራው ይህ የ5 ቢሊዮን ፓውንድ ፕሮጀክት ኢትዮጵያን በአለም አቀፍ ንግድና ቱሪዝም ዋና ተዋናይ ለማድረግ ያለመ እንደሆነ ተመላክቷል።

በአሁኑ ወቅት የአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት መጨናነቅ ቢያጋጥመውም "ሜጋ ኤርፖርት ከተማ" ይህን ችግር በመቅረፍ የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ ያሳድጋልም ተብሎለታል።

(አማ)


ከአርክቴክቶች ማህበር የተሰጠ መግለጫ


3⃣ ቀናት ብቻ ቀሩት

በስልጠናው ለመሳተፍ የሚያስችሎትን ፎርም  በትክክል መሙላትዎን እርግጠኛ ይሁኑ

☑️ለመመዝገብ ከታች በተያያዘው ሊንክ በመግባት ፎርሙ የሚጠይቀውን የግል መረጃዎችዎን በትክክል ይሙሉ
👇👇👇👇👇👇👇👇

https://forms.gle/J4ktYcejEXcKJsV8A


በዶሮ ቅርፅ የተሰራው የዓለማችን ትልቁ ሕንፃ

በፊሊፒንስ የሚገኘው በዶሮ ቅርፅ የተሰራ የዓለማችን ትልቁ ሕንፃ ለሆቴል አገልግሎት የተገነባ ነው፡፡

ይህ ግዙፉ ሆቴል 6 ፎቆች ያሉት ሲሆን ቁመቱ ከ114 ሜትር በላይ ሆኖ በውስጡ 15 ክፍሎች መያዙም ተነግሯል፡፡

በኔግሮስ ኦክሲደንታል ደሴት ላይ በሚገኘው ካምፑስቶሃን ሃይላንድ ሪዞርት ኮረብቶች አናት ላይ የሚገኘው ሆቴሉ ሌላ ለየት የሚያደርገው ነገር የሆቴሎቹ ክፍሎች መስኮት አልባ መሆናቸው ነው፡፡

ሆቴሉ የዶሮ ቅርጽ ያለው ትልቁ ሕንፃ በመባልም በዓለም ድንቃድንቅ መዝገብ ላይ መስፈር ችሏል።

የሆቴሉ ባለቤት ታን ሲናገር" ይህን ሕንጻ የሰራሁት በሺዎች የሚቆጠሩ ሰራተኞችን ለመቅጠር እና የወፍ ዘር ለኔግሮስ ሕዝብ ያለውን ጠቀሜታ ለማክበር እና ለማሳየት ነው" ብሏል፡፡

በሆቴሉ የመኝታ ዋጋ ለአራት ሰዎች የሚሆን አንድ ክፍል ከ80 የአሜሪካ ዶላር በታች ሲሆን እስከ ሰባት ለሚደርሱ ሰዎች የሚበቃው ክፍል ደግሞ 120 ዶላር ገደማ ወጪ ይጠይቃል ተብሏል።

ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ አካባቢው ለመዝናኛ ተመራጭ እየሆነ የመጣ ሲሆን፤ በዶሮ ቅርጽ የተሰራውን ግዙፍ ሕንፃ ለመመልከትም በርካቶች ወደ ስፍራው እያቀኑ መሆኑን ሲኤንኤን ዘግቧል፡፡

(Ebc)


ባለ 13 ወለሉ የልደታ ክፍለከተማ አስተዳደር ሕንፃ ግንባታ ሙሉ ለሙሉ ተጠናቆ ለአገልግሎት ዝግጁ ተደረገ።

በከተማ አስተዳደሩ ስር የሚገነቡ የመንግስት አገልግሎት መስጫ ተቋማትን በባለቤትነት የማከናወን ኃላፊነት የተሰጠው የአዲስ አበባ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ በርካታ ቁጥር ያላቸው ግንባታዎችን በጥራትና በፍጥነት በማከናወን ለአገልግሎት እያበቃ ይገኛል።

ከነዚህ ፕሮጀክቶች ውስጥ አንዱ የሆነውና በስራ ተቋራጭ አፈፃፀም ውስንነት ተገምግሞና የቀደመ ውሉ ተቋርጦ ዳግም ከቆመበት እንዲቀጥል የተደረገው የልደታ ክፍለከተማ አስተዳደር 2B+G+11 ሕንፃ ግንባታ ሙሉ በሙሉ ተጠናቋል።

ከ1.1 ቢሊየን ብር በላይ ተመድቦለት በ 3000 ካ.ሜ. ቦታ ላይ የተገነባው ይህ የክፍለከተማ አስተዳደር ሕንፃ ለተለያዩ ፅ/ቤቶች የሚውሉ ቢሮዎችን ጨምሮ እያንዳንዳቸው 1,224 እና 459 ሰዎችን ማስተናገድ የሚችሉ ሁለት የመሰብሰቢያ አዳራሾች ፣ 30 ተሽከርካሪዎችን በቤዝመንት እንዲሁም 65 ተሽከርካሪዎችን በውጪ የማስተናገድ ዓቅም ያላቸው ፓርኪንጎች ፣ ጂምናዚየም ፣ የሕፃናት ማቆያና መጫወቻ ፣ ሬስቶራንት ፣ የመረጃ ክፍል ተሟልተውለታል።

ከዚህ በተጨማሪ አቅመ ደካማ እና የአካል ጉዳት ያለባቸው የሕብረተሰብ ክፍሎችን ከግምት ያስገቡ 4 ዘመናዊ ሊፍቶች የተገጠሙለት ሲሆን ለአገልግሎት ሰጪውና ለአገልግሎት ፈላጊው ምቹ እና ሳቢ ከባቢን የሚፈጥር የአረንጓዴ ስፍራዎች የፕሮጀክቱ አካል ተደርገዋል።

ይህ ሕንፃ ከቀደሙት የክፍለከተማ አስተዳደር ሕንፃዎች ልምድ የተወሰደበትና የመዲናዋን የዕድገት ደረጃ እንዲሁም የስማርት ሲቲ ትልም ከግምት አስገብቶ ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን በማካተት የተከናወነ ሲሆን በግንባታ ስራው ባማኮን ኢንጂነሪንግ በስራ ተቋራጭነት እንዲሁም ኔማድ ኢንጂነሮችና አርክቴክቶች ኃ/የተ/የግ/ማ በአማካሪነት ተሳትፈውበታል።

የዚህ ህንፃ መገንባት የበርካታ ፋይናንስ ተቋማት መቀመጫ ለሆነው የልደታ ክፍለከተማ አስተዳደር አገልግሎት ትልቅ ዓቅም መፍጠር ከማስቻሉም ባለፈ አስተዳደሩ ለህንፃ ኪራይ የሚያወጣውን ከፍተኛ መዋለ ንዋይ በማስቀረት ረገድ ትልቅ ፋይዳ የሚኖረው ይሆናል።

(አግስቢ)


የኢትዮጵያ የህንጻ አዋጅ.pdf
2.4Мб
🏢🚧የህንጻ አዋጁ መሻሪያ ረቂቅ ሰነድ ማብራሪያ እስቲ ሀሳብ አስተያየታችሁን አካፍሉን.....




ማስታወቂያ

ለአስራ አንዱም ክ/ከተሞች ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት  ኃላፊዎች በሙሉ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ከፕሮጀክት ማኔጅመንት ኢኒስቲትዩት ጋር በመተባበር በተለያዩ የምህንድስና ዘርፎች ለ10 ተከታታይ ቀናት በሁለተኛ ዙር ስልጠና ይሰጣል።

ስለሆነም ስልጠናው የፊታችን ህዳር  16/2017  ዓ.ም የሚጀምር መሆኑን እየገለፅን ሁሉም የክ/ከተማ ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት ኃላፊዎች ይህን አውቃችሁ ባለሙያዎች በስልጠናው እንዲሳተፉ እንድታደርጉ ስንል ጥሪ እናስተላልፋለን።


ዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ
ሕዳር 13/2017


የአዲስ አበባ ከተማ የአፍሪካ ስማርት ከተሞች አዋርድ ተሸላሚ ሆናለች!

ከተማ አስተዳደሩ ሽልማቱን ያገኘነው በከተማችን እየተስራ ባለው የኮሪደር ልማት እና ተያያዥ የመሠረተ ልማት ግንባታዎች ፣ ከተማችንን ለነዋሪዎቿ ለመኖሪያ ምቹ በማድረግ እና ተያይዞም በተተገበረው የአረንጓዴ አሻራ ትግበራ ፤ ቴክኖሎጂ ተኮር የመሠረተ ልማት ዝርጋታ እና አቅርቦት ለነዋሪዎች ያለውን አስተዋፅዖ ጭምር በመለየት የተሰጠ ነው ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባስመዘገባቸው አመርቂ ውጤቶች በናይሮቢ በመካሄድ ላይ ባለዉ የአፍሪካ ስማርት ከተሞች የኢንቨስትመንት ጉባኤ ላይ ተሸላሚ መሆን ችላለች።

የአዲስ አበባ ከተማ ከሌሎች ስማርት የአፍሪካ ከተሞች ጋር ተወዳድራ ሽልማቱን ከሚወስዱ ሶስት ከተሞች መካካል አንዷ መሆን የቻለች ሲሆን ፤ ክብርት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባን በመዋክል የተላከው የልኡኳን ቡድን ሽልማቱን ተቀብለዋል።

ይህ አዋርድ ለአዲስ አበባ ከተማ ሊሰጥ የቻለበት ዋነኛ ምክንያት በኮሪደር ልማት ከተማይቱን ለነዋሪዎቿ ምቹ እና ተስማሚ ለማድረግ የተገኘውን አመርቂና ውጤታማ ተግባር መሰረት በማድረግ መሆኑን እና በአርንጓዴ አሻራ የአየር ለውጥ ተጽዕኖን ለመቀነስ እየተተገበረ ያለውን ተምሳሌታዊ ተግባር በማስመልከት እንደሆነ ተገልጿል ። በተጨማሪም ሰው ተኮር ስማርት ከተሞች ለትውልድ መገንባት የሚለውን የከተማነት ሀሳብ በከተማይቱ ተግባራዊ በመደረጉ ነው። እንዲሁም ዘመናዊ እና ምቹ ከተማን ለመፍጠር ለአብንትም የእግረኞች መሄጃ እና የሞተር አልባ ተሸከርካሪዎች መንገድ ደረጃውን በጠበቃ ቴክኖሎጂ መገንባታቸውን መሰረት በማድረግ መሆኑን በሽልማት ስነስርዓቱ ላይ ተገልጿል።

ከዚህም በተጨማሪ በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ስማርት በቴክኖሎጂ የተደገፉ አገልግሎት እና የዘመኑን ቴክኖሎጂ ታሳቢ ያደረጉ መሠረተልማት ዝርጋታዎች እንዲሁም ስማርት የነዋሪዎች እና የዜጐች ተኮር ከባቢዎች መገንባታቸው፤ ተያይዘው የተፈጠሩ ሰፊ የሥራ ዕድል ፈጠራ ፤ እና ብቁ እና አመቺ ልማት ቴክኖሎጂን የተደገፍ አገልግሎት አሰጣጥ ሂደታቶች በመተግበራቸው ከተማይቱ ይህንን ሽልማት እንድታገኝ አድርጓታል ተብሏል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ተሸላሚ መደረጉ ለሀገራችን የገጽታ ግንባታ የሚያበረክተው አስተዋጽዖ ትልቅ ትርጉም የሚሰጠው መሆኑን በመድረኩ ላይ ተገልጿል።

በአፍሪካ አህጉር ለሚገኙ መሰል ዋና ከተሞች ተምሳሌት የሚሆን ተብሏል።

ይህ የአፍሪካ ስማርት ከተሞች የኢንቨስትመንት ጉባኤ በዋናነት በኬንያ መንግስት፣ በናይሮቢ ካውንቲ እና ናይሮቢ በሚገኘው በተመድ የሰዎች ሰፋራ (UN-Habitat) እና ሌሎች አጋር አካላት በትብብር የተዘጋጀ መሆኑ ታውቋል።

በዝግጅቱ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አመራሮች ልዑካን ቡድን እየተሳተፉበት የሚገኙ ሲሆን በተመሳሳይ ሁኔታ ከተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የተወጣጡ ሚነስትሮች፣ ከንቲባዎች፣ የተለያዩ አህጉራዊ እና አለም አቀፍ ድርጅቶች ተወካዮች ተሳታፊ መሆን ችለዋል።

በናይሮቢ የሚገኘውን የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ኤምባሲን በመወከል ክቡር አምባሳደር ደመቀ አጥናፉ በሽልማት ስነ ስርአቱ ላይ ተገኝተዋል ።

የቀጣዩን 2025 ጉባኤም አዲስ አበባ የምታስተናግድ መመረጧም ተገልጿል።

(አኮቢ)

Показано 20 последних публикаций.