Ethio Lawyers Insight


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Право


የቻናሉ አላማ ህግ እና ህግ ነክ በሆኑ ጉዳዮች ላይ የተሸለ እዉቀትን ለማዳበር የተከፈተ ቻናል እና ግሩፕ ሲሆን፣ የሀገር ዉስጥ እና አለም አቀፍ የህግ መፅሀፍትንና የተለያዩ የህግ የምርምር ስራዎችን ያገኙበታል።
Ethiopia

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Право
Статистика
Фильтр публикаций






ሰ/መ/ቁ 252231 ጥቅምት 2016 ዓ.ም

ፍርድ ቤት እስከ 15 ቀን ድረስ ዐቃቤ ሕግ ክስ እንዲመሰርት በወ/መ/ሥ/ሥ/ሕግ ቁጥር 109/1 መሰረት የሰጠዉ ጊዜ ከአለቀ በኋላ በተጠርጣሪዉ ላይ ክስ ሳይመሰርት ተጠርጣሪዉን በእስር ላይ ማቆየት በኢፌዲሪ ሕገ መንግሥት እና በተባበሩት መንግሥታት የሲቪልና የፖለቲካ መብቶች ቃል ኪዳን መሠረት  በዘፈቀደ አስሮ እንደማቆየት ተገቢነት የለውም።

# ተጠርጣሪው የዋስትና መብት እንዲጠበቅለት ጥያቄ አቅርቦ ጥያቄዉ ውድቅ ከሆነ በኋላ
ዐቃቤ ሕግ ክስ እንዲመሰርት የተሰጠዉ የ15 ቀን ጊዜ ክስ ሳይመሰርት ያለቀ ከሆነ ተጠርጣሪው በድጋሚ ዋስትና ለመጠየቅ ይችላል።

Shakkamaan galmeen himannaa guyyaa 15  kessatti irratti akka banamu mana murtiin ajajamee yoo himannaan guyyoota jedhame kana keessatti yoo banamuu baate ykn ol'iyyataan ajajni hin geeddaramne shakkamaan mirga wabii irra deebi'ee gaafachuun gadi lakkifamuu danda'a jechuun,

Dhaddachi Ijibbaataa MMWF lakk.galmee 252231 ta'e irratti gaafa guyyaa 12/2/2016 murtii dirqisiisaa kenneera.

https://t.me/ethiolawreview
Credit Binimos


በውጭ_ሀገር_የተሰጠ_ፍርድ_ወይም_የግልግል_ዳኝነት_ውሳኔ_የሚፈፀምበት_ሁኔታ.pdf
122.8Кб
በውጭ ሃገር የተሰጠ ፍርድ ወይም የግልግል ዳኝነት ውሳኔ የሚፈፀምበት ሁኔታ

በፍትሕ ሚኒስቴር ንቃተ ህግ ትምህርት እና የስልጠና ዳይሬክቶሬት የተዘጋጀ
https://t.me/ethiolawreviews

https://t.me/ethiolawreview


አንድ ተጠርጣሪ በምርመራ ሂደት ላይ የዋስትና መብቱ ተነፍጎ /ውድቅ ሆኖበት/ የጊዜ ቀጠሮ የሚያየው ፍ/ቤት ዐ/ህግ በ15 ቀን ውስጥ ክስ እንዲያቀርብ በማለት የጊዜ ቀጠሮ መዝገብ ቢዘጋውና በ15 ቀኑ ክስ ባይቀርብ ተጠርጣሪው አዲስ ነገር ተከስቷል በማለት ድጋሚ ለ2ኛ ዙር የዋስትና ጥያቄ ማቅረብ ይችላልን? ይህን ጉዳይ በተመለከተ ፍ/ቤት ምን ማድረግ አለበት?


1002-2024.pdf
404.1Кб
Directive on monitoring, control, and investigation of civil society organization No.1002/2024

ስለሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ክትትል፣ ቁጥጥር እናምርመራ የወጣ መመሪያ ቁጥር 1002/2016

https://t.me/ethiolawreview


አንድ ድርጅት ባልተከፋፈለ ትርፍ ላይ ግብር እንዲከፍል የማይጠየቀው ድርጅቱ በአንድ የሂሳብ ጊዜ(የበጀት ዓመት) ውስጥ የተገኘውን ያልተከፋፈለ ትርፍ የሂሳብ ጊዜው በተጠናቀቀ በ12 ወራት ጊዜ ውስጥ የአባላቱን የአክስዮን ድርሻ መጠን እና የድርጅቱን ካፒታል በተገኘው ትርፍ መጠን ያሳደገ እንደሆነ ነው፡፡
ድርጅቱ ያልተከፋፈለ ትርፍ የሌለው መሆኑን የሚያስረዳው በአንድ የሂሳብ ጊዜ(የበጀት ዓመት) ውስጥ የተገኘው የተጣራ ትርፍ የባለአክስዮኖችን የአክስዮን ድርሻ መጠን እና የድርጅቱን ካፒታል ለማሳደግ የዋለ መሆኑን በሰነዶች ምዝገባና ማረጋገጫ ኤጀንሲ የፀደቀ ቃለ-ጉባኤ እና ከንግድ ሚኒስቴር ወይም አግባብነት ካለው የክልል/የከተማ አስተዳደር ቢሮ የድርጅቱ ካፒታል ማደጉን የሚገልጽ ሰነድ በጣምራ በማቅረብ ነው በማለት የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት አስገዳጅ የሕግ ትርጉም ሰጥቷል፡፡

https://t.me/ethiolawreview


አዲሱ ተግባራዊ የሚሆነው ውልና ማስረጃ ለሚሰጣቸው አገልግሎቶች የሚከፈል የአገልግሎት ክፍያን ለመወሰን በወጣው የሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 543/2016 መሰረት የአገልግሎት ክፍያ ማሻሻያ ደንብ
ከላይ ይመልከቱ

https://t.me/ethiolawreview


1002-2024.pdf
404.1Кб
Directive on monitoring, control, and investigation of civil society organization No. 1002/2024-ስለሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ክትትል፣ ቁጥጥር እናምርመራ የወጣ መመሪያ ቁጥር 1002/2016

https://t.me/ethiolawreview

Показано 9 последних публикаций.