Ethiopian Digital Library


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Образование


በዚህ ቻናል ስለ
👉ትምህርት፣
👉ሥራ እና
👉ማህበራዊ ጉዳይ
መረጃ ያገኛሉ!

https://telega.io/c/Ethiopian_Digital_Library
Buy ads: https://telega.io/c/Ethiopian_Digital_Library
Contact: @ethiodlbot

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Образование
Статистика
Фильтр публикаций


በ2017 ዓ.ም ለአቅም ማሻሻያ ትምህርት (Remedial Program) ደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባችሁ ተማሪዎች ምዝገባ የካቲት 3 እና 4/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library


ድሬ ይለያል!

ሙስሊሞች ክርስቲያኖችን የሚያስተናግዱበት የድሬደዋው የጥምቀት በዓል


በድሬደዋ ከተማ የጥምቀት በዓል ሲከበር የተለየ ድባብ አለው። ሙስሊሞች ለክርስቲያኖች ጣፋጭ ምግቦችን በማዘጋጀት መንገድ ላይ ያስተናግዷቸዋል።

በዘንድሮው በዓል ላይም ታቦታቱ የሚያልፉባቸውን መንገዶች በማጽዳት፣ እንዲሁም በሞቃታማዋ ከተማ ታቦታቱን አጅበው ለሚኼዱ ምዕመናን ውሃና ልዩ ልዩ ጣፋጭ ምግቦችን አዘጋጅተው አቅርበዋል። #VoA

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library


በታቦተ ህግ ላይ ድንጋይ መወርወር

በወላይታ ቦዲቲ ከተማ በጥምቀት በዓል በታቦተ ህግ ላይ ድንጋይ በመወርወር እና የተጸለዬ ውሃ በሚል ፈሳሽ ነገር በመድፋት ሊያውኩ የሞከሩ አካላት በመለቀቃቸው ምዕመኑ ተቃውሞ እያሰማ ይገኛል

በዕለተ ጥምቀት የእናታችን የቅድስት ኪዳነ ምህረት ታቦት ህግ ወደ ማደሪያው በሚመለስብት ጊዜ እራሱን ነብይ ብሎ በሚጠራው አካል እና ጭፍሮቹ መሪነት በጉዞ ላይ በነበረ ታቦተ ህግ ላይ ጸያፍ ንግግሮች በመናገር ፣ ድንጋይ በመወርወር እና የተጸለዬበት ውሃ በሚል እንዲደፋ ለማድረግ በመሞከር የተንቀሳቀሱ አካላትን የከተማው የጸጥታ መዋቅር በመያዝ ያሰረ ቢሆንም በመፈታታቸው ምክንያት የቦዲቲ ከተማ ኦርቶዶክሳውያን ቁጣ እና ተቃውሟቸውን እያሰሙ ይገኛሉ።

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library


የዲላ ዩኒቨርስቲ ሙስሊም ተማሪዎች ኒቃብ ለብሰው እንዳይገቡ በመከልከላቸው በመስጂድ ውስጥ ለመቆየት መገደዳቸውን ተናገሩ

አርባ አራት የሚሆኑ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ሴት ተማሪዎች ኒቃብ ለብሰው ወደ ግቢው እንዳይገቡ እንደተከለከሉና አንዳንዶቹም ከአምስት ቀናት በላይ በመስጂዱ ውስጥ ለመቆየት መገደዳቸውን ለአዲስ ስታንዳርድ ገለጹ።

ከአዲስ ስታንዳርድ ጋር ቆይታ ያደረጉ ተማሪዎች፤ ቀደም ባሉት ዓመታት ኒቃብ መልበስ ይፈቀድ የነበረ ቢሆንም ዩኒቨርሲቲው በቅርቡ “የደህንነት ስጋትን” በመጥቀስ ያለቅድመ ማስጠንቀቂያ ኒቃብ መልበስን እንደከለከለ ተናግረዋል።

በዲላ ዩኒቨርስቲ የሙስሊም ተማሪዎች ማህበር ሊቀመንበር የሆነው ኑረዲን አብደላ በበኩሉ ጉዳዩን ከዩኒቨርስቲው የስራ ሃላፊዎች ጋር በጽሑፍም ሆነ በአካል ለመፍታት የተደረጉ ተደጋጋሚ ጥረቶች መፍትሄ አለማምጣታቸውን ለአዲስ ስታንዳርድ ተናግሯል።

አክሎም “በርካታ ሙስሊም ተማሪዎች ላለፉት አምስት ቀናት በመስጂድ ውስጥ ቆይተዋል። በዚህ ጊዜ ለፈተና መቅረብም ሆነ የሚጠበቅባቸውን አሳይመንት ለማጠናቀቅ አልቻሉም” ብሏል።

Addis Standard Amharic

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library


ከትምህርት ላይ እጃችሁን አንሱ

ይህ ያለ ዕውቀት የማይኖርበት ዘመን ነው። ትምህርት ለኢትዮጵያ ከማንኛውም አገር በላይ ያስፈልጋታል። ከዓለም አካሄድ የምንለይበት ምክንያት የለንም። ከአንደኛ ደረጃ እስከ ዩኒቨርስቲ ያለው ትምህርት እንደሚያስፈልግ ማስገንዘብ የሚያስፈልግበት ጊዜ ላይ ነን። ከሊቅ እስከ ደቂቅ ትምህርት እንደማያስፈልግ በሚናገርበት በአሁኑ ወቅት ስለ ትምህርት አስፈላጊነት መናገር ይኖርብናል። መምህራን ሆነው ሳይቀር ትምህርት ምን ይሰራል የማይሉ በርካቶች አጋጥመውኛል።

አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሲከፈት ዶክተር እጓለ ገብረዮሐንስ በሬዲዮ ስለ ዩኒቨርስቲ ምንነትና አስፈላጊነት ተናግረው ነበር። ይህም ንግግራቸው 'የከፍተኛ ትምህርት ዘይቤ' በሚል ርዕስ በመጽሐፍ መልኩ ታትሟል። ትምህርት የሚያስፈልገው ለዕውቀትና ሠናይት (መልካም ለማድረግ) መሆኑን በሰፊው ገልጸዋል። በቅርብ ዓመታት ከላይ እስከታች ትምህርትን የሚያጠፉ ተግባራት በግልጽና በረቂቅ መንገድ እየተካሄዱ ነው። ትምህርት ለዓመታት የማይማሩ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ልጆች በአገሪቱ አሉ።

በጥድፊያ የተጀመረና በቂ ዝግጅት ያልተደረገበት የትምህርት ፖሊሲ ተተግብሯል። መጽሐፍ ሳይደርስ፣ መምህር ሳይዘጋጅ ወዘተ አዲስ ፖሊሲ ተተግብሯል። መጽሐፍን ያህል ነገር በአንድ ወር አዘጋጁ ሲባል የሚጠቅምም የማይጠቅምም ነገር ማጨቅ እየተለመደ ይሄዳል። ይህ ከሚሆን ጊዜ ተሰጥቶት ቢሆን ጥሩ ነበር። ካልሆነ ትምህርት ሊባል አይችልም።

በሌላ መንገድ 12ኛ ክፍል ተፈትኖ የሚያልፈው ተማሪ ተመጥኖ አንድ ዩኒቨርስቲ ቢያስተምረው የሚበቃ ከሰላሳ ሺህ ያልበለጠ ተማሪ ዩኒቨርስቲ እንዲቀላቀል ተደረገ። በዚህ ሁኔታ መምህሩ ሥራ እንዲፈታ ተደረገ። ይህንን መሠረት አድርጎ የሠራተኛ ቅነሳ እንዲደረግ በረቂቅ መንገድ ይሠራል። ዲፓርትመንቶች እንዲዘጉ ይወሰናል።

ይህ ሲደረግ ተጠንቶ ወይም በዲሞክራሲያዊ አካሄድ ባለድርሻ አካላት ተጠይቀው አይደለም። የኢትዮጵያ ህዝብ በሰላሳ ዓመት ውስጥ 200 ሚሊዮንን ያልፋል። ያን ጊዜም ሆነ አሁን ዩኒቨርስቲ ያስፈልጋል። ዕውቀት ያስፈልጋል።

ምሩቃን ባለሙያዎች ያስፈልጋሉ። ባይሆን መመረቅና ሥራ መያዝን ለመነጠል መስራት ይቻላል። የበጀትንም ጉዳይ ማስተካከል ይቻላል። የግልንም ሆነ የመንግሥትንም ዩኒቨርስቲዎችንና ኮሌጆችን በህግና መመሪያ ብዛት መዝጋትና ማስቸገር ለማንኛውም አገር አይጠቅምም። ይህንንም አስመልክቶ መጠየቅ ከሁሉም ዜጋ የሚጠበቅ ነው።

አንድ ሚኒስትር ወይም የዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት ዩኒቨርስቲ እዘጋለሁ ሲል በዝምታ ማለፍ ያልተገባ ነው። ግልጽ እንዲሆን የምፈልገው ጉዳዩ የመምህራን ሥራ ማጣት ብቻ አሳስቦኝ እንዳልሆነ ነው። መምህራን ሥራ ቢለቁ እንኳን ከዚህ የተሻለ እንጂ ያነሰ ገቢ እንደማያገኙ አስባለሁ። ሁሉም አካላት ተመካክረውና አስበውበት ለትምህርት አስፈላጊው ትኩረት እንደሚሰጥ ተስፋ አደርጋለሁ። ሐሳባችሁን ስጡኝ። እንወያይበት።

Mezemir Girma

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library


የመምህራን የመውጫ ምዘና የካቲት 1/2017 ዓ.ም ይሰጣል

በመምህርነት ሙያ ከዲፕሎማ ወደ መጀመሪያ ዲግሪ የትምህርት ደረጃ ማሻሻያ ስልጠና በክረምት መርሐግብር ስትከታታሉ ለቆይታችሁ መምህራን የመውጫ ምዘና የካቲት 1/2017 ዓ.ም ይሰጣል።

የምዘና ፈተናው በየአቅራቢያችሁ ባሉ አሰልጣኝ ዩኒቨርሲቲዎች የሚሰጥ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል። ምዘና የምትወስዱበት ተቋም/ዩኒቨርሲቲ በቀጣይ በክልል/ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮዎች በኩል ይገለፅላችኋል ተብሏል።

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library


ዲላ ዩኒቨርስቲ፣ ሙስሊም ሴት ተማሪዎች በሒጃብ ምክንያት ከትምህርት ታግደዋል ተብሎ የተሠራጨው መረጃ "መሠረተ ቢስ" ነው ሲል በፌስቡክ ገጹ ባስተላለፈው መልዕክት አስተባብሏል።

ዩኒቨርስቲው "ብዝኀነትን" አክብሮ የሚሠራ የትምህርት ተቋም መኾኑን ገልጧል።

ኾኖም ሙስሊም ሴት ተማሪዎች ካለፈው ሰኞ ጀምሮ ሒጃብ በመልበሳቸው ምክንያት ወደ ዩንቨርስቲው ቅጥር ግቢ እንዳይገቡ ታግደው በመስጂዶች ለማደር እንደተገደዱ መናገራቸውን ዶይቸቨለ ዘግቧል።

ሰኞ'ለት 44 ሴት ሙስሊም ተማሪዎች ከስግደት ሲመለሱ፣ የግቢው ጸጥታ አካላት ሒጃባችኹን ካላወለቃችኹ አትገቡም እንዳሏቸው ተማሪዎቹ መግለጣቸውንም ዘገባው ጠቅሷል።

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ ከማል ሐሩን፣ ምክር ቤቱ በጉዳዩ ላይ ከትምህርት ሚንስቴር ሃላፊዎች ጋር በመነጋገር ለችግሩ ዘላቂ መፍትሄ ለማስገኘት እንዲቻል አንድ የጋራ መድረክ ለማካሄድ ቀጠሮ እንደተያዘ ተናግረዋል ተብሏል። #DW

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library


ባለቤቱን ገድሎ ስጋዋን ከትፎ መጸዳጃ ቤት ዉስጥ የከተተዉ ተከሳሽ በሞት እንዲቀጣ ተወሰነበት

ፀሃዬ ቦጋለ በየነ የተባለ ተከሳሽ ከነሐሴ 27 ቀን 2014 ዓ.ም በግምት ከቀኑ 5፡00 እስከ ነሐሴ 28 ቀን 2014 ዓ.ም ከምሽቱ 12፡30 ድረስ ባለው ጊዜ በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 04 አርሴማ ፀበል አከባቢ ባለቤቱ የነበረችውን ሟች ወንበር ላይ ተቀምጣ እያለ ሳታየው ከኋላዋ በመምጣት በሊጥ ማዳመጫ ዱላ ማጅራትዋን በመምታት ህይወቷ እንዲጠፋ አድርጓል መባሉን ዳጉ ጆርናል ከፍትሕ ሚኒስቴር ሰምቷል።

ግለሰቡ ባለቤቱን እራሷን እንድትስት ካደረገ በኋላ እዛው ትቷት ከቤት ወጥቶ በመሄድና ከተወሰነ ሰዓታት በኋላ ተመልሶ በመምጣት ሟች እራሷን ስታ ከወደቀችበት መሬት ለመሬት በመጎተት እቤት ውስጥ ወደሚገኘው መታጠቢያ ቤት በማስገባት አንድ እግሯን ከዳሌዋ ጀምሮ በመቁረጥና ሙሉ የእግሯን ስጋ አጥንቷ ባዶ እስኪሆን ድረስ መልምሎ በማውጣት ስጋዋን አድቅቆ በመክተፍና በመቆራረጥ መጸዳጃ ቤት ውስጥ ጨምሯል።

ወንጀለኛዉ የቆረጠውን እግሯን ለሁለት በመስበርና በፌስታል በመቋጠር ፀጉሯን በመቀስ በመቁረጥ ቀሪ አስከሬንዋ ላይ ጨርቅና የተለያየ መዘፍዘፊያ በመጫን እዛው መታጠቢያ ቤት ውስጥ በማስቀመጥ እስከ ነሃሴ 30/2014 ዓ.ም ድረስ ምንም እንዳልተፈጠረ እቤት ውስጥ እያደረ ከቆየ በኋላ ከጷግሜ 1/2014 ዓ.ም ጀምሮ እስከ መስከረም 16/2015 ዓ.ም ድረስ ቤቱን ዘግቶ ተሰዉሮ ነበር ብሏል።

በዚህም ምክያንት በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ምርመራ ተጣርቶ በፍትህ ሚኒስቴር የጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዘርፍ በሴቶችና ህጻናት ላይ ሚፈፀሙ ወንጀሎች ዐቃቤ ሕግ ዳይሬክቶሬት በወ/ሕ/አ539/1/ሀ/ መሰረት በፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 2ኛ የሰው ግድያና ከባድ ውንብድና ወንጀል ችሎት ክስ ቀርቦበት ክርክር ሲደረግ ቆይቷል፡፡

በክርክሩ ሒደትም የዐቃቤ ሕግ ማስረጃ ከተሰማ በኋላ ተከሳሽ እንዲከላከል ብይን ቢሰጥም የመከላከያ ማስረጃ አቅርቦ የቀረበበትን ክስ ሊከላከል ባለመቻሉ ፍ/ቤቱ በተከሳሽ ላይ የጥፋተኛነት ፍርድ በመስጠት በዕድሜ ልክ ፅኑ እስራት እንዲቀጣ የወሰነ የነበረ ቢሆንም ዐቃቤ ሕግ ባቀረበው ይግባኝ መሰረት የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የፌዴራል ከፍተኛ ፍ/ቤት የወሰነውን የእድሜ ልክ ጽኑ እስራት ውሳኔ በመሻር ተከሳሹ በሞት እንዲቀጣ ወስኖበታል፡፡

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library

10.1k 0 39 18 173

ኢትዮጵያ የጥናት እና ምርምር ውጤቶችን በመኮረጅ በዓለም ቀዳሚዋ ሀገር ተብላለች።

መቀመጫውን ሕንድ ያደረገው ዓለም አቀፍ ሪሰርች ዋች እንዳለው ከሆነ ኢትዮጵያ በሌሎች ሀገራት የተሰሩ ጥናቶችን ቀጥታ ትቀዳለች።

ሳውዲ አረቢያ፣ ፓኪስታን፣ ቻይና እና ግብጽ ከኢትዮጵያ በመቀጠል የጥናት ውጤቶችን የሚኮርጁ ሀገራት ናቸው።

እነዚህ ሀገራት የሌሎች ሰዎችን ጥናት ሲኮርጁ የሚቀጣ ህግ የላቸውም ብሏል። #Plagiarism

Credit: አዩ ዘሀበሻ

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library


100 ሺህ በላይ ምሩቃን - ጎንደር ዩኒቨርሲቲ 70ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን ማክበር ጀምሯል

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ 70ኛ ዓመት እና የዩኒቨርሲቲው አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ማስተማሪያ ሆስፒታል 100ኛ ዓመት ክብረ-በዓል የመክፈቻ ሩጫ ውድድር በጎንደር ከተማ ተካሒዷል።

ዩኒቨርሲቲው በህክምናና ጤና ሳይንስ ዘርፍ ዕውቀትን የተካኑ ባለሙያዎችን በማፍራት ለሀገሪቱ የላቀ አስተዋፅኦ በማበርከት ላይ እንደሚገኝ በኹነቱ ላይ የተገኙት የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ተናግረዋል።

በቀጣይ ሁለት ዓመታት ራስ-ገዝ ከሚሆኑ 10 የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች መካከል ጎንደር ዩኒቨርሲቲ አንዱ ነው።

ኢትዮጵያውያን ሐኪሞች እንዲኖሩ ታስቦ በ1947 ዓ.ም የተመሰረው ዩኒቨርሲቲው፤ ከ100 ሺህ በላይ ምሩቃንን ማፍራቱን የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት አስራት አፀጸወይን (ዶ/ር) ገልፀዋል።

የምስረታ በዓሉ እስከ ሰኔ 30/2017 ዓ.ም ድረስ የሚከበር ሲሆን፤ ለተቋሙ ጉልህ አስተዋፅኦ ያበረከቱ ግለሰቦች ዕውቅና መስጠትን ጨምሮ ከ20 በላይ ኹነቶች እንደሚከናወኑ ይጠበቃል።

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library


ሲዳማ ክልል መምህራን ደሞዝ ይከፈለን እያሉ አደባባይ ወጥተው ተቃውሞ አሰምተዋል።

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library


ኢትዮጵያን ቀዳሚውን ደረጃ ይዛለች - በ2025 ከፍተኛ የኑሮ ውድነት የታየባቸው የአፍሪካ ሀገራት

ዜጎች ለምግብ፣ መጠለያ፣ ትራንስፖርት፣ ጤና እና ሌሎችም መሰረታዊ ፍላጎቶች የሚጠየቁት ወጪ መናር ፈታኝ ሆኗል::

በብዙ የአፍሪካ አገሮች የተሻለ ገቢ ያላቸው ሰዎች እያደገ ከሚሄደው ወጪ ጋር ተላምደው ሲቀጥሉ፤ ዝቅተኛ እና መካከለኛ ገቢ ያላቸው ቤተሰቦች ደግሞ የችግሩን ጫና ይጋፈጣሉ።

በመሰረታዊ ሸቀጥ እና አገልግሎቶች እየጨመረ የሚገኘው ዋጋ ከሚያባብሰው ድህነት ባለፈ ማህበራዊ ቀውስ እና ወንጀልን ሊያባበስ እንደሚችል ተገልጿል፡፡

ቢዝነስ ኢንሳይደር በ2025 መጀመሪያ በአፍሪካ ከፍተኛ የኑሮ ውድነት ያስመዘገቡ ሀገራትን ዝርዝር ባወጣበት መረጃው ኢትዮጵያን ቀዳሚ አድርጓታል፡፡

በባለፈው አመት መለኪያ አራተኛ ደረጃ ላይ የነበረችው ኢትዮጵያ በዚህ አመት ወደ አንደኛ ደረጃ ከፍ ያለችው ሞዛምቢክ ፣ ሴኔጋል እና አይቮሪኮስት በዚህኛው አመት መጠነኛ ማሻሻያዎችን አስመዝግበዋል፡፡

በ2025 መጀመሪያ በኑሮ ውድነት ቦትስዋና ፣ ሞዛምቢክ እና አይቪሪኮስት ኢትዮጵን በመከተል ከሁለተኛ እስከ አራተኛ ያለውን ደረጃ ይዘዋል፡፡#ALAIN

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
ህፃናት

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library


አፋን ኦሮሞ ማስተማር ጀመረ

ሚኒሶታ ዩኒቨርሲቲ በCollege of Liberal Arts አፋን ኦሮሞ ቋንቋን ማስተማር ጀመረ።

በዩኒቨርሲቲው የመጀመሪያው የአፋን ኦሮሞ መምህር በመሆን የቀድሞ የኦፌኮ ፓርቲ አመራር አቶ በቀለ ገርባ ተቀጥሯል።

የመጀመሪያዎቹ ተማሪዎች በመሆን 25 ተማሪዎች የተመዘገቡ ሲሆን 5 ተማሪዎች በተጠባባቂነት ተይዟል። #Fast_Mereja

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library


በአማራ ክልል ያለው የመምህራን ደመወዝ አለመከፈል መምህራንን የጉልበት ሥራ እንዲሰሩ ማስገደዱ ተገለጸ

በአማራ ክልል ከመስከረም እስከ ታሕሳስ ወር ደመወዝ ያልተከፈላቸው መምህራን፤ ከኑሮ ውድነቱ ጋር ተዳምሮ የጉልበት ሥራ ለመስራት ተገደዋል ሲል የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር አስታወቀ፡፡

በክልሉ ያሉ መምህራን ለተማሪዎቻቸው ሲሉ ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ ተቋቁመው እየሰሩ ነበር ያለው ማህበሩ፤ "አሁን ላይ ግን ያለው ሁኔታ ካቅማቸው በላይ እየሆነ ነው" ብሏል፡፡

"ለወራት ደመወዝ ያልተከፈሉ መምህራን ወደ ቤተሰቦቻቸው መመለስ ባለመቻላቸው የጉልበት ሥራ የሚሰሩ አሉ" ያሉት፤ የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር ምክትል ፕሬዝደንት አቶ ሽመልስ አበበ ናቸው፡፡

"በዚህም ቀጣዩ የመምህራኑ እጣ ፋንታ ምን እንደሆነ አይታወቅም" ያሉት የማህበሩ ምክትል ፕሬዝደንት የትምህርት ሥራውንም ወደ ኋላ ጎትቶታል ብለዋል፡፡

በተጨማሪም ትምህርት ባልተጀመረባቸው አካባቢዎች ያሉ ተማሪዎች ትምህርት ወደሚሰጥባቸው ቦታዎች ሄደው ለመማር ሲሞክሩ በተፈጠረ የቦታ ጥበት፤ በአንድ ክፍል ውስጥ 90 የሚሆኑ ተማሪዎች እንዲቀመጡ አስገድዷል ነው የተባለው፡፡

በአጠቃላይ በኢትዮጵያ ያሉ መምህራንን የተመለከቱ ችግሮች በሁሉም አካባቢ አይነት እና መጠናቸውን እየቀያየሩ መቀጠላቸውም ነው የተገለጸው፡፡#አሐዱ

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library


በኦርቶዶክስ ተዋህዶ ታቦተ ህጉ ላይ ሲያላግጡ የሚያሳዩ ከ20 በላይ ቪዲዮ ተስርቶ አይተናል።

ሰሪዎቹ የፕሮቴስታንት እምነት ተከታዮች እንደሆኑ ሌሎች ቪዲዮቻቸው ያሳያሉ።

ብዙ መልካም የሆኑ የፕሮቴስታንት እምነት ተከታይ ሰዎችን እናውቃለን!

ጥቂቶች አጥፊዎች ግን ሃይ ሊባሉ ይገባል!

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library


Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
በሆሳዕና ከተማ የሚኖሩት ግለሰቦች የኢ/ኦ/ተ/ቤ የምትጠቀመውን ታቦተ ህግ ላይ "ሚካኤል በሆሳዕና" በሚል በመዘባበት የጥላቻ እና የንቀት ቪዲያ ሰርተው በቲክታክ የለቀቁ ሲሆን ከሰዓታት በኃላ ቪዲዮውን አንስተው ይቅርታ ጠይቀዋል።

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library


🚀 Your Future Starts Here! Don’t Miss the First Pathway Info Session of 2025! 🎓🌍

This is your chance to take the next big step toward earning an international degree and unlocking exclusive scholarships!

🔹 Expert Guidance: Learn how to access top global universities and secure life-changing scholarships!
🔹 Hands-on Application Support: Get 1-on-1 help to complete your application, bring your friends along!
🔹 In-Person Q&A: Have all your questions answered by our expert team!

📅 Date: Friday, January 24 & Saturday,
        January 25, 2025 (ጥር 16 ና 17, 2017)
⏰ Time: 9:00 AM - 5:00 PM (ከ3፡00 - 11፡00 ሰአት)
📍 Location: Capstone ALX Tech Hub, Mexico/Lideta

📌 Limited Spots Available! RSVP Now:
https://bit.ly/PathwayInfoSessionV7

This is your first and best opportunity in 2025 to secure your spot in the Pathway Program.

Don’t wait, your future starts now! 🚀💡


በተያያዘ ዜና

ሆሳዕና ከተማም ተመሳሳይ ነገር ተፈፅሟል።

በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታዮች ዘንድ በድምቀት ከሚከበረው የጥምቀት በዓል ጋር ተያይዞ በታቦት እና በሃይማኖቱ ላይ ሲሳለቁ የሚያሳይ ቪዲዮ ደርሶናል።

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library


በቁጥጥር ስር አውለናቸዋል - የአምቦ ከተማ አስተዳደር

የአምቦ ከተማ አስተዳደር ከጸጥታ ኃይሉ ጋር በመተባበር በአንቦ ዩኒቨርስቲ ተማሪ የነበሩና የሃይማኖት ስም በማጥፋት ወንጀል የተጠረጠሩ 3 ተማሪዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን ገልጿል።

ተማሪዎቹ በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት ተከታዮች ዘንድ በድምቀት ከሚከበረው የጥምቀት በዓል ጋር ተያይዞ በታቦት እና በሃይማኖቱ ላይ ሲሳለቁ የሚያሳይ ቪዲዮ #ቲክቶክ በተባለው የማህበራዊ ሚዲያ ከለቀቁ በኋላ እጅግ በርካታ ሰዎች ጋር ደርሶ ቁጣን ፈጥሯል።

የአምቦ ከተማ አስተዳደር በድርጊቱ የተሳተፉ እና በማህበራዊ ገጾች ላይ የለጠፉ 3 ተማሪዎች በቁጥጥር ስር እንደዋሉ (እንደታሰሩ) ገልጾ የአምቦ ዩኒቨርሲቲም የዲሲፕሊን ቅጣት ለማስተላለፍ አቅጣጫ ማስቀመጡን አስተውቋል።

Credit: Tikvah

@Ethiopian_Digital_Library
@Ethiopian_Digital_Library

Показано 20 последних публикаций.