EFDA የኢትዮጵያ የምግብና መድኃኒት ባለስልጣን

Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Медицина

ETHIOPIAN FOOD AND DRUG AUTHORITY /EFDA/
This is EFDA'S official Telegram Channel
For more updates please visit
Free call 8482
join the Channel
t.me/ethiopianfoodanddrugauthority

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Медицина
Статистика
Фильтр публикаций

የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን ወደ ፊት ለሚወጡ የትምባሆ ማሸጊያ ፓኬት የሕብረተሰብ ጤና ማስጠንቀቂያ ፅሑፍና ባለቀለም ምስልን አገራዊ አድርጎ ለማዘጋጀት ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ጋር በትብብር ለመስራት ተስማማ፡፡

ታህሣሥ 17 /2017 ዓ.ም የተካሄደውን የመግባቢያ ስምምነት በባለስልጣኑ በኩል የሕክምና መሣሪያዎች ቁጥጥር ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሻርማርኬ ሸሪፍ ሲፈርሙ እንደተናገሩት አዋጅ ቁጥር 1112/11 ጥንካራ የትምባሆ ቁጥጥር አንቀፆች መካተታቸውን ጠቁመው ስለትምባሆ የጤና ጉዳቶች በሲጋራ ፓኬቱ ላይ 70 በመቶ የባለቀለም የጤና ማስጠንቀቂያ በማስቀመጥ ተጠቃሚዎች ማጨስ እንዲያቆሙ የሚያግዝ አንዱ ነው ብለዋል፡፡

እስካሁን የነበሩት የጤና ማስጠንቀቂያዎች ከውጭ የተወሰዱ ስለሆኑ የተፈፃሚነት ደረጃቸው አነስተኛ በመሆናቸው አዲስ ስትራቴጂ መቀየስ አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል ነው ያሉት፡፡

በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የክሊኒካል ሰርቪስ ዳይሬክተር ዶ/ር አብዱራዛቅ አህመድ በበኩላቸው የመግባቢያ ስምምነቱ በትምባሆ ማሸጊያ ፓኮዎች ላይ የሚወጡትን የምስልና የፅሑፍ የጤና ማስጠንቀቂያ መልዕክቶች ደረጃቸውን የጠበቁና የሕብረተሰብ ግንዛቤ በማሳደግ የታለመላቸውን ግብ እንዲመቱ አስፈላጊውን ጥረት ተቋማቸው እንደሚያደርግ ቃል ገብተዋል፡፡

የማቲዎስ ወንዱ የኢትዮጵያ ካንሠር ሶሳይቲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ወንዱ በቀለ በወቅቱ በአስተላለፉት መልዕክት በቀጣይነት የሚወጡ የጤና ማስጠንቀቂያዎች የሚጨሱትን ብቻ ሳይሆን ለማጨስ የሚያቅዱትን ጭምር ቆንጠጥ የሚያደርጉ ሆኖ እንዲዘጋጅ ጠይቀዋል፡፡

የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን ከምግብ አምራች እና አስመጪ ተቋማት ጋር በተዘጋጁ ረቂቅ መመሪያዎች ዙሪያ ምክክር አካሄደ፡፡

ታህሳስ 17 /2017 ዓ.ም  በተቋሙ   በተከለሱ አጠቃላይ  የምግብ   ምዝገባ መመሪያ( general food registration directive)  እና የምግብ  መልካም አመራረት ስርዓት ቁጥጥር አሰራር ረቂቅ መመሪያ ላይ ውይይት ተደርጓል። 

በወይይቱ ላይ  የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የባለስልጣኑ የምግብ ምዝገባና ፍቃድ መሪ ሥራ አስፈጻሚ አቶ  መንግስቱ አስፋው እንደተናገሩት በረቂቅ መመሪያው ላይ ውይይት ያስፈለገው  የምግብ አምራች  እና አስመጪ ተቋማት የመመሪያው ባለቤት  ከመሆናቸውም በተጨማሪ  በዘርፉ ካላቸው ክህሎት፣ ዕውቀትና ልምድ ተነስተው  በምግብ ቁጥጥር መመሪያው ጥሩ ግብዓት ማበርከት እንደሚችሉ በማመን ሲሆን አካታችነትን  ለማስፈን እና  የተሳለጠ  የቁጥጥር ስራን በጋራ ለመስራት ያስችላል ያሉ ሲሆን መመሪያዉን  በየወቅቱ  መከለስና  ማዘመን፣ ጊዜውን ያማከለ በማድረግ  እና ባለድርሻ አካላትን ማሳተፍ  የወደፊቱን የጋራ ስራ እንደሚያቀና ተናግረው ተሳታፊዎች ገንቢ ትችት እንድያቀርቡም  ጠይቀዋል፡፡

በውይይቱ ላይ ከ50 በላይ የምግብ  አምራች   እና አስመጪ ተቋማት  ባለቤቶች ፣ ስራ አስፋፃሚዎች እና ተወካዮች የተገኙ ሲሆን በተካሄደውም ውይይት የተነሱ ሃሳቦችና አስተያየቶች በግብዓትነት ተወስደው  በመመሪያው ውስጥ እንደሚከታቱ  ታውቋል፡፡

በመላ ሐገሪቱ ወጥ የሆነ የቁጥጥር ስርዓት ለመዘርጋት ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸው ተገለፀ

ታህሳስ 14/2017 አዲስ አበባ፡- አዲስ በተዘጋጀው የማህበረሰብ መድኃኒት ቤትቸ ብሔራዊ ደረጃ ዙሪያ በተዘጋጀ የምክክር መድረክ ላይ በመገኘት የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሔራን ገርባ እንደተናገሩት የቁጥጥር ስርዓቱን Maturity level 3 ለማድረስ በርካታ ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸውንና ከፌዴራል ጀምሮ እስከታችኛው መዋቅር ወጥ የሆነ የቁጥጥር ስርዓት መዘርጋት አስፈላጊነትን አስረድተዋል።

የማቹሪቲ ሌቭል 3 ጉዳይ የምርጫ ጉዳይ ሳይሆን ለቁጥጥር ስርዓቱ እንደህልውና ተይዞ ሊሰራ እንደሚገባ የገለፁት ዋና ዳይሬክተሯ የቁጥጥር ስርዓቱ ለሀገር እድገት አቅም መሆን እንዳለበትና ሁሉም ክልል ሁሉም ከተማ መስተዳደር ለስኬቱ ያላሰለሰ ጥረት እንዲያደርጉ የጠየቁ ሲሆን ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ወጥ የሆነ የቁጥጥር ስርዓት ለማስፈን አደረጃጀቶችን ከማስተካከል ጀምሮ የክልሎችን አቅም ለመገንባት ከUSPQM+ ጋር በመተባበር ክልሎች የሌሎች ሀገራትን ተሞክሮ የሚያዩበትን መንገድ ማመቻቸቱን አስታውቀው ብዙውን ጊዜ የህክምና ምክርና ህክምና ለማግኘት የሚፈልጉ ዜጎች የመጀመሪያ ተደራሽ የሆኑት የማህበረሰብ መድኃኒት ቤቶች በመሆኑ የማህበረሰብ መድኃኒት ቤቶች ብሔራዊ ደረጃ እንደአዲስ መዘጋጀቱን አስረድተዋል፡፡

በመድረኩ ከጤና ሚኒስቴር፣ ከኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን፣ ከክልል ጤና ቢሮዎች፣ የክልል ተቆጣጣሪዎችና የባለስልጣን  መስሪያ ቤቱ የቅርንጫፍ ኃላፊዎች የተሳተፉ ሲሆን ከባለስልጣን መስሪያ ቤቱ፣ ከህብረተሰብ ጤና ኢንስቲቲዩትና ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተጋበዙ ፅሁፍ አቅራቢዎች ጥናቶችና ፅሁፎችን አቅርበው ሠፊ ውይይት ተደርጓል፡፡

#Join the #Ethiopian #Food and #Drug #Authority #community!
Addressed up-update regulatory information about the safety,quality,efficacy, rational use and performance of regulated health product. Follow us on all social media links below for all the latest updates.
Follow Us

Facebook:
https://web.facebook.com/p/Ethiopian-Food-and-Drug-Authority-EFDA-100064606425124/
Telegram:
https://t.me/ethiopianfoodanddrugauthority
LinkedIn:
https://www.linkedin.com/company/ethiopian-food-and-drug-authority
YouTube:
https://www.youtube.com/@FDAEthiopiaMedia
Twitter (@efda (@EfdaMedia) on X)
https://x.com/EfdaMedia?t=CLTetULx-FBOA2Ef344B-Q&s=35
Website
WWW.efda.gov.et
Online service / eRIS - Electronic Regulatory Information System/
https://eris.efda.gov.et

For report any suspicious, substandard, or falsified medicinal products:
Email pharmacovigilance@efda.gov.et
Calling the
Toll-free 8482

#የኢትዮጵያን #ምግብ እና #መድኃኒት #ባለስልጣን #ማህበረሰብን ይቀላቀሉ! ስለ ምግበና  የጤና ግብዓት ቁጥጥር ፣ደህንነት፣ጥራት፣ውጤታማነት፣አግባባዊ አጠቃቀም እና አፈጻጸም ወቅታዊ የቁጥጥር መረጃ ምላሽ ለማግኘት፤ለምግብና የጤና ግብዓት ቁጥጥር ትክክለኛ መረጃ በሁሉም የተቋሙ የማህበራዊ ሚዲያ እና ድህረ ገጽ ላይ ይከተሉን።

ህገወጥ የምግብና የጤና ግብዓቶችን ንግድና ዝውውር ለመቆጣጠር በቅንጅት የተሰሩ ስራዎች በቀጣይ ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው ተገለፀ

11/04/2017 ጅማ:- የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር በጅማ የጎምሩክ ኮሚሽን ፅህፈት ቤት በመገኘት ከዚህ ቀደም ባለስልጣን መስሪያ ቤቱና ኮሚሽኑ በጋራ በሰሩት የሰርቬይላንስና የኦፕሬሽን ስራዎች እንዲሁም በጉምሩክ የቁጥጥር ጣቢያዎች በተያዙ ህገወጥ መድኃኒቶችን ለማስወገድ የሚያስችል ውይይት ከጅማ ዞን የጉምሩክ ኮሚሽን ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ መርጋ ቶሌራ ጋር አድርገዋል።

በውይይቱ ወቅት ዋና ዳይሬክተሯ እንደተናገሩት ባለስልጣን መስሪያ ቤቱና ኮሚሽኑ በጋራ በመስራታቸው ብዙ ውጤቶች መገኘታቸውን በመግለፅ ህገወጥ የመድኃኒት ዝውውር የህብረተሰብ ጤናን አደጋ ላይ የሚጥልና የሁሉንም አካላት ትብብር የሚጠይቅ መሆኑን ተናገረው ህገወጥ መድኃኒቶቹን የማስወገድ ስራ በቅርቡ እንደሚሰራ አስታውቀዋል።

የጅማ ዞን የጉምሩክ ኮሚሽን ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ መርጋ ቶሌራ በበኩላቸው የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሔራን ገርባ የኮሚሽኑ መጋዘን በመምጣት መድኃኒቶቹ በሚወገዱበት መንገድ ዙሪያ ለመወያየት ወደኮሚሽኑ በመምጣታቸውና ባለስልጣኑ በየጊዜው ለሚያደርገው የባለሙያ ድጋፍና የጋራ ኦፕሬሽኖች ምስጋና አቅርበው ይህ ትብብር ቀጣይነት እንዲኖረው ጠይቀዋል።

በምግብና ጤና ግብዓቶች ቁጥጥር ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር ሲካሄድ የነበረው ውይይት ተጠናቀቀ።

ታህሳስ 10/2017 ጅማ፡- በኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን አዘጋጅነት በጅማ ከተማ በተካሄደው የባለድርሻ አካላት የውይይት መድረክ የተሰሩ ስራዎች፣ህጓችና አሰራሮች እና በቅንጅት የሚሰሩ ስራዎች የቀረቡ ሲሆን ፤የምግብና የጤና ግብአቶች ደህንነት ማስጠበቅ የሁሉም ጉዳይ በመሆኑ በቀጣይ ባለድርሻ አካላት በትብብርና በቅንጅት የሚሰሩ ስራዎችን አጠናክሮ በመቀጠል  ህብረተሰባችን ላይ በህገወጥና ደህንነታቸው በተጓደሉ ምርቶች በጤናው ላይ ሊያደርሱ  የሚችለውን ጉዳትግንዛቤ በመጨበጥ የጋራ ስራዎችን በማጠናከር መከላከል እንደሚገባ የባለስልጣን መመስሪያቤቱ  ዋና ዳይሬክተር  ወ/ሪት ሄራን ገርባ አስታውቀዋል።

ዳይሬክተሰሯ እንደተናገሩት ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ከክልሎች ጋር ብቻ ሳይሆን የጤና ጉዳይ የሁሉም የጋራ ጉዳይ በመሆኑ  ድንበር ተሻጋሪ ህገወጥ የምግብና ጤና ግብዓቶች ቁጥጥር  ዙሪያ ከጎረቤት ሀገራትም ጋር ያለው ግንኙነት ከጊዜ ወደጊዜ እየተጠናከረ መምጣቱን ገልፀው ከክልሎችም ጋር በየጊዜው የግመገማና የሪፖርት ስርዓት በመዘርጋት ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸውን እና በቀጣይነትም እንደሚካሄድ  ገልጸዋል፡፡

በምግብና ጤና ግብዓቶች ቁጥጥር ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት እየተካሄደ ነው፡፡

ታህሳስ 10/2017 ጅማ፡- በጅማ ከተማ እየተካሄደ ባለው የባለድርሻ አካላት የምግብና የጤና ግብዓቶች ቁጥጥር የውይይት መድረክ ላይ በመገኘት የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ወ/ሪት ሄራን ገርባ እንደተናገሩት ጤናው ሴክተር ላይ ብዙ ሪፎርም መሰራቱን ገልፀው የጤና ፖሊሲያችን ትኩረቱ እንደቀድሞው መከላከል ላይ ብቻ ሳይሆን አክሞ ማዳንን እንደሚጨምር አስታውቀው በአካባቢው የሚገኙ የጉምሩክ ኃላፊዎችና ሠራተኞች የፌዴራል ፖሊስ አባላትና ሌሎች ተቆጣጣሪዎች ሀገርና ህዝብን ከህገወጥ ምግብና የጤና ግብዓት ለመከላከል የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ አድንቀው ህገወጥ የጤና ግብዓቶች የጤና ብቻ ሳይሆን የሀገር ደህንነት አደጋም ስለሆኑ የጋራ ስራ እንደሚያስፈልግ ገልፀው ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በምግብና ጤና ግብዓቶች ቁጥጥር ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር በጋራ ስራዎችን ሲሰራ መቆየቱንና በዚህም በርካታ ውጤቶች መመዝገባቸውን አስታውቀዋል፡፡

በውይይት መድረኩ ላይ በመገኘት መልክት ያስተላለፉት የጅማ ከተማ የጉምሩክ ኮሚሽን ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ መርጋ ቶሌራ እንደተናገሩት የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን ህገወጥ ምግብና የጤና ግብዓቶች ዝውውርን ለመከላከል ከጉምሩክ ኮሚሽንና ከፌዴራል ፖሊሰ ጋር በጋራ እየሰራ ላለው ስራ ምስጋና ያቀረቡ ሲሆን ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ይህንን መድረክ ማዘጋጀቱ ለቁጥጥር ስራው ትልቅ አቅም ይኖረዋል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ባዘጋጀው በወይይት መድረኩ የጉምሩክ ኮሚሽን፣ የፌዴራል ፖሊስ፣ የጅማ ዞን ንግድ ቢሮና ጤና ቢሮ እየተሳተፉ የሚገኙ ሲሆን ፅሁፎች ቀርበው ውይይቶች የሚካሄዱ ይሆናል።

መንግስት ጤናማ ባልሆኑ ምግቦች ምክንያት የሚከሰቱ በሽታዎችን ለመቀነስ ብሎም ለማጥፋት የሚያስችሉ ዘርፈ ብዙ ጥረቶችን በማካሄድ ላይ መሆኑ ተገለፀ፡፡
ታህሣሥ 3/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ በኢንዱስትሪ የሚመረቱ ትራንስ ፋቲ አሲድ ያለባቸውን ምግቦች ለመመርመር የሚያስችል አገር አቀፍ የላቦራቶሪ አቅም ለመፈተሽ የተካሄደውን ጥናት ይፋ ለማድረግ የተዘጋጀውን አውደጥናት የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ሄራን ገርባ ሲከፍቱ እንደተናገሩት በአገር ውስጥም ይሁን ከውጭ ወደ አገር  የሚገቡ በኢንዱስትሪ  የተመረቱ ምግቦች  የትራንስ ፋቲ አሲ መጠናቸውን ለመለካት የሚያስችል አገር አቀፍ የላቦራቶሪ  አቅም ፍተሻ ጥናት ማካሄድ  በቀጣይ  በዘርፉ ላይ ለሚደረገው ቁጥጥር አቅም የሚፈጥር ነው፡፡
በኢንዱስትሪ የሚመረቱ ምግቦች ውስጥ ያለውን የትራንስ ፋቲ አሲድ መጠን የመቀንስ ብሎም የማጥፋት ስራ የምግብ ደህንነት ለማረጋገጥ ከሚሠሩ ስራዎች መካከል አንዱ መሆኑን የጠቀሱት ዋና ዳይሬክተሯ መንግስት የህብረተሰብ ጤና ለመጠበቅ የምግብና የምግብ ስር-ዓተ ፖሊሲ ከማውጣት ጀምሮ የአምስት ዓመት የምግብ ደህንነት ፍኖተ ካርታ አውጥቶ ተግባራዊ በማድረግ ላይ ይገኛል ብለዋል፡፡
በጥናቱ የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን፣የሕብረተሰብ ጤና አጠባበቅ ኢንስቲትዩትና የኢትዮጵያ ተስማሚነት ምዘና ድርጅት፣ አዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ስነ-ምግብ ማዕከል እንዲሁም የኬሚስትሪ ላቦራቶሪዎች፣ ፣ጅማ ዩንቨርስቲ፣ አሮማያ ዩኒቨርስቲ እንዲሁም ብሌስ አግሮ ላቦታሮሪ ና ጄጄ ላቦ ላቦራቶሪዎች በጥናቱ ተዳሰዋል፡፡
በቀጣይ ሁሉም ላቦራቶሪዎች ወደ ተፈለገው የላቦራቶሪ ምርመራ ስራ መግባት እንዲችሉ ያሉባቸውን ክፍተት በመሸፈንና የጋራ የትብብርና የቅንጅት ስራ በማጠናከር አጋር ድርጅቶች እገዛ መጨመር ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ ተግባር እንደሆነ ተመልክቷል፡፡

Видео недоступно для предпросмотра
Смотреть в Telegram
https://youtu.be/howauTWVGl0

“ሀገራዊ መግባባት ለኅብረብሔራዊ አንድነት”

እንኳን ለ19ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል በሰላም አደረሳችሁ!
#ኢትዮጵያ

Facebook:
https://web.facebook.com/p/Ethiopian-Food-and-Drug-Authority-EFDA-100064606425124/
Telegram:
https://t.me/ethiopianfoodanddrugauthority
LinkedIn:
https://www.linkedin.com/company/ethiopian-food-and-drug-authority
YouTube:
https://www.youtube.com/@FDAEthiopiaMedia
Twitter (@efda (@EfdaMedia) on X)
https://x.com/EfdaMedia?t=CLTetULx-FBOA2Ef344B-Q&s=35

አገር አቀፍ የትምባሆ ቁጥጥር አስተባባሪ ኮሚቴ አባላት ወደ ክልል ወርደው የተሰሩ የትምባሆ ቁጥጥር ስራዎችን የመገምገም ተግባር ቀጣይነት ባለው መልኩ መስራት እንዳለባቸው ተገለፀ፡
ህዳር 26/2017 ዓ.ም ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ አገር አቀፍ የትምባሆ ቁጥጥር አስተባባሪ ኮሚቴ አባላትን እንደገና ለማደራጀትና በቀጣይ ሊሰሩ ስለታቀዱ ስራዎች ለተለያዩ የፌደራል የመንግስትና መንግስታዊ ያልሆኑ ባለድርሻ አካላት የአስተዋወቀበትን መድረክ የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ሄራን ገርባ ሲከፍቱ እንደተናገሩት አገር አቀፍ የትምባሆ ቁጥጥር አስተባባሪ ኮሚቴ አባላት በጋራ የሚሰሩ የትምባሆ ቁጥጥር ስራዎችን ክልል ድረስ ወርደው መጎብኘት እንዳለባቸው ጠቁመው ይህም ትኩረት ተሰጥቶ በቀጣይነት ሊሰራ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡
የመንግስት ተቋማት በተለያዩ አደረጃጀቶች ምክንያት በመቀያየራቸውና ሰራተኞችም በተለያየ ምክንያት ስራቸውን ሲቀይሩ ከአስተባባሪ ኮሚቴው ሲወጡ በመቆየታቸው እንደገና ኮሚቴውን አዋቅሮና አጠናክሮ ማስቀጠል በማስፈለጉ መደረኩ መዘጋጀቱን አስታውቀዋል፡፡
በቀጣይነት ኮሚቴው በጋራ በሚሰሩ ስራዎች ላይ መግባባት በመፍጠር አባላቱ ከባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ጋር በተናጥል የጋራ መግባቢያ ሰነድ እንደሚፈራረሙ እንደሚጠበቅ ከመድረኩ ለማወቅ ተችሏል፡፡

Показано 15 последних публикаций.