#ክፍል_ሁለት
መጽሃፉ የገበያ ቅቡልነት(ማረጋገጫ/ Market Validation) ለማግኘት ሶስት መሰረታዊ ደረጃዎች አሉ ፥ እነርሱም:
1) የዝግጅት (Ready!) ፣
2) የማነጣጠር (Aim!) እንዲሁም
3) የ"መተኮስ" (የድርጊት ፣ ኢላማን የመምታት፣Fire!) ናቸው።
ደራሲው #የዝግጅት ጊዜ በሚለው ውስጥ የሚከተሉትን ሶስት ዋና ነጥቦች አካትቷል።
1. 🔖 ወደ አዕምሮአችን የመጣው የቢዝነስ ሃሳብ መነሻው ምን እንደሆነ ማወቅ። ይህ ሃሳብ ጥንስሱ የስራ እና የእውቀት ልምድ ከሆነ የተሻለ የመሳካት እድል አለው ይለናል።
2. 🔖ትርፍ ያስገኛል ያልነው ገበያ ምን ያክል ተመሳሳይ ተፎካካሪዎችን አቅፎ መያዝ የሚችል ነው? እያደገ እና እየሰፋ የሚሄድ ገበያ ነው ወይ? ከሆነ የእድገት ፍጥነቱ ምን ያህል ነው? የተፈለገው ገበያ ከአጠቃላይ ኢኮኖሚው እድገት የተሻለ ፍጥነት ላይ ያለ እንደሆነ ለኢንቨስትመንት መልካም እድል ያለው ነው ሲል ይጠቁማል።
3.🔖 የገበያውን ዑደት መረዳት መቻል።
Rob Adams የገበያ ዑደት (Market Life-Cycle) ሲል እነዚህን 4 ደረጃዎች እያመላከተ ነው።
3.1.
ጀማሪ ገበያ፥ (Early Adopters / Introductory) - አዲስ ነው ፣ ጥቂት ተፎካካሪዎች ፣ ብዙ የስጋት ምጣኔ (risk) እና አቅም ያለው ነው
3.2.
በማደግ ላይ ያለ ገበያ (Early Growth) - ፍላጎት እየጨመረ ነው ፣ አዳዲስ ተፎካካሪዎች በፍጥነት እየተፈጠሩ ነው ፣ የመሰረቱ ንግዶች እያደጉ ነው ፥
3.3.
የበሰለ ገበያ (እድገቱን ያገባደደ ገበያ / Late Majority) - የገበያው የእድገት ፍጥነት የሚገታበት ፣ ከፍተኛ የተፎካካሪዎች የንግድ ሽኩቻ የሚበረታበት ደረጃ ነው።
3.4.
በማሽቆልቆል ላይ ያለ ገበያ (Laggards) - የፍላጎት መቀነስን ተከትሎ ገቢ እና ትርፍ የሚቀንስበት ፣ ተፎካካሪዎች ዋጋ በመቀነስ ከገበያው ጨርሰው ላለመውጣት ራሳቸውን ለማበርታት የሚሞክሩበት
4.🔖 ተፎካካሪዎችን በአግባቡ መገምገም እና አንዳች ጠቃሚ መደምደሚያ ላይ መድረስ
5.🔖 ገበያውን በደንብ ከሚያውቁት የዘርፉ ባለሙያዎች ጋር ግንኙነት መፍጠር
__
#BookReview
#Ethiopreneur_Recommended
Join us
@ethiopreneure