የሚኒስትሮች ምክር ቤት በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎችን አሳለፈ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 10፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 42ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ፡፡
ውሳኔዎቹ እንደሚከተለው ቀርበዋል፡-
በቅድሚያ ምክር ቤቱ የተወያየው የኢትዮጵያ የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ረቂቅ አዋጅ ላይ ነው፡፡ አዋጁ በተቋሙ የተጀመረውን የሪፎርም ስርዓት ወደ ተግባር በመለወጥ በኢትዮጵያ የህዝቡን የእርስ በእርስ መረዳዳት ባህል የማጎልበትና ተረጂነትን በዘላቂነት በሀገር አቅም መወጣትን ማዕከል በማድረግ የአደጋ ጉዳት ሰለባ ለሆኑ ዜጎች ከሰብአዊ ድጋፍ መርሆዎች፣ ከዘላቂ የልማት ፕሮግራሞችና ከሰላም መስፈን ጋር በማስተሳሰር ማህበራዊ፤ ኢኮኖሚያዊና ሞራላዊ ጉዳቱን ለመቀነስ የሚያስችል ነው፡፡ ምክር ቤቱም በጉዳዩ ላይ በሰፊው ከተወያየበት በኋላ ግብአቶችን በማከል ወደ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዲተላለፍ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡
https://www.fanabc.com/archives/282983