Фильтр публикаций


የኮንስትራክሽን ባለሞያ የሚያሰለጥን የማሰልጠኛ ተቋም ተከፈተ

#FastMereja I ኤሮ አይረን ኮንስትራክሽን ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማኅበር በኮንስትራክሽኑ ዘርፍ ክህሎት ያላቸውን ባለሞያዎችን ለማፍራት ‹‹ሪቪዚት ኢንስቲቱሽን ኦፍ ዲዛይን›› የተሰኘ ማሰልጠኛ ማዕከል መክፈታቸውን ዛሬ መጋቢት 5/2017 ዓም በቤስት ዌስተርን አዲስ ሆቴል በሰጡት መግለጫ አስታውቋል።

ዓለም አቀፍ ደረጃዎችን በተከተለ መልኩ ስልጠናዎችን እንደሚሰጥ የተገለጸ ሲሆን በዚህ የሥራ መስክ በሀገራችን ብዙ ማሰልጠኛ ተቋማት ባለመኖሩ ክፍተቱን ለመሙላት አስተዋጾ ያደርጋል ተብሏል።

ሰልጣኞቹ ስልጠናቸውን ሰልጥነው ሲያጠናቅቁ ተመሳስይ የግንባታ ስራ በሚሰሩ ድርጅቶችና በዚሁ ድርጅት ተቀጥረው የሚሰሩ ከመሆኑም ሌላ ከመቀጠር ይልቅ በራሳቸው መሥራት የሚያስችላቸውን ልምዶችና እውቀቶች እንዲኖሯቸው በማድረግ ስልጠናና ትምህርቱን የሚሰጡ ይሆናል ተብሏል።

ክፍያቸዉን መፈጸም ለማይችሉ ሰልጣኞች ከዳሽን ባንክ ጋር በመሆን እስከ 1 ዓመት የሚቆይ የብድር መክፈያ መንገድ እንዳመቻቸ አስታዉቋል፡፡

ስልጠናዎቹ በቀን፣ በማታ፣ ቅዳሜ እና እሁድን ጨምሮ በኦንላይን የሚሰጡ ናቸዉ፡፡

#ቢዝነስ


የቀድሞ የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ በ13 ዓመት ፅኑ እስራት ተፈረደባቸው።

#FastMereja I የሀዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፤ ባሳለፍነው ሳምንት በሁለት ክሶች ጥፋተኛ የተባሉት የቀድሞ የሀዋሳ ከተማ ከንቲባ ረዳት ፕሮፌሰር ፀጋዬ ቱኬ ላይ 13 ዓመት ፅኑ እስራትና 21 ሺህ ብር የገንዘብ ቅጣት ፍርድ ማሳለፉን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ዘግቧል።

ፍርድ ቤቱ የቀድሞዉ ከንቲባ ካቀረቡት 8 የቅጣት ማቅለያዎች 4ቱን በመቀበል እና አራቱን ዉድቅ በማድረግ ነዉ የ13 ዓመት ፅኑ እስራት የፈረደባቸው።

በዚሁ በእሳቸው መዝገብ ተከሳሽ የነበሩት የቀድሞ የሀዋሳ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ ምክትል ኃላፊ አቶ ታርኩ ታመነ በ10 ዓመት ፅኑ እስራት እነ 41 ሺህ ብር ፤ አቶ ታፈሰ ቱናሻ በ8 ዓመት ከ5 ወር ፅኑ እስራትና 51 ሺህ ብር እንዲሁም አቶ ሰይፉ ሌሊሴ የተባሉ ግለሰብ እንደዚሁ በ8 ዓመት ከ5 ወር እና 76 ሺግ ብር የገንዘብ ቅጣት ፍርድ ተላልፎባቸዋል።

via: TIKVAH ETHIOPIA
#ችሎት


#ክብሩና ሥልጣኑ ከሰማይ ከፍታ ከፍ የሚል አባት


ዓይናችን በገለጽንበት ቅጽበት ከሚታይ ነገር ላይ እንደሚያርፈው ሁሉ አባታችን በተወለዱ ጊዜ አንደበታቸው ከምስጋና የተገኘ፣ ስለሀገራችን መቶ ዓመት ተዘቅዝቀው የጸለዩ፣ ገና በ3 ዓመታቸው በገዳም መኖር የጀመሩና ከማሕጸን ጀምሮ ለመንፈስ ቅዱስ አገልግሎት የተለዩ፣ ከተወለዱ ጀምሮ እህል ያልቀመሱ፣ በምድረ በዳ እንደመላእክት የኖሩ፣ ከጌታችን ጋር መሞት አይገባኝም ብለው የተከራከሩ ታላቅ ቋድቅ አባት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ፡፡ ትውልዳቸው ግብጽ ንሒሳ ውስጥ ነው፡፡

አባታቸው ስምዖን እናታቸው አቅሌስያ ይባላሉ፡፡ ሠላሳ ሦስት ዓመት በትዳር የቆዩት ቅዱሳን በሩካቤ ስጋ የተዋወቁት ለሦስት ቀናት ብቻ ነው፡፡ ይህም ልጅ እንዲሰጣቸው እግዚአብሔርን እየለመኑ ነው፡፡

በተጋቡ በሰላሳ ዘመናቸው አቅሌሲያ ቤተ እግዚአብሔር ገብታ ከሥላሴ ሥር ወድቃ ስትማጸን “ክብሩና ሥልጣኑ ከሰማይ ከፍታ ከፍ የሚል ንጽሕናው ከሚካኤል ከገብርኤል የሚተካከል ክህነቱ እንደ መልከጼዴቅ እንደ መጥምቁ ዮሐንስ እንደ ነቢዩ ኤልያስ የሆነ ልጅ እንቺ ተቀበይ” የሚል ድምጽ ሰማች፡፡ መጋቢት 29 ፀንሳ በታኅሣሥ 29 ደም ግባቱ እጅግ የሚያምር ወንድ ልጅ እንደወለደች መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል በሰው አምሳል መጥቶ “የዚህ ልጅሽ ስሙ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ይሁን” አላት፡፡ ወዲያውም ሕፃኑ ከእናቱ ጭን ወርዶ ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ሦስት ጊዜ ሰገዶ “ከጨለማ ወደ ብርሃን ለአወጣኸኝ ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ምስጋና ይሁን” አለ፡፡ እመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያምም ባረከችው ቅዱሳን መላዕክት ዘወትር ከእርሱ ጋር ነበሩ፡፡ ከዚህም በኋላ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ሕፃኑን አባ ዘመደ ብርሃን የተባሉ አባት ላሉበት ገዳም ሰጣቸው፡፡

ሕፃኑንም የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት ሁሉ እያስተማሩ አሳደጉት፡፡ ትምህርቱን በጨረሰ ጊዜ ዲቁና ሰጡት፡፡ ፍጹም የእግዚአብሔር ጸጋ አድሮበታልና ሥራው ሁሉ በዕውቀት የተመላና የተቃና ሆነ፡፡ እንደ ቅዱስ እንጦንስም አስኬማ ሰጡት፡፡ ከዚህም በኋላ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቅስናን ተቀበሉና በጾም በጸሎት ተጠምደው በታላቅ ተጋድሎ መኖር ጀመሩ፡፡ እንደ ሐዋርያትም የተአምራትና የፈውስ ሀብት ተሰጣቸውና ድውያንን የሚፈውሱ፣ ሙታንን የሚያነሡ፣ አጋንንትን የሚያወጡ ሆኑ፡፡ ወደ ሰማያት አርገው በረከትና ጸጋ የተቀበሉ፣ አጋንንትን የሚያሳድዱበት፣ ድውያንን የሚፈውሱበት ታላቅ ጸጋ ተሰጣቸው፡፡ ከሰው ተለይተው ወደ ጫካ ገብተው ከስድሳ አንበሶችና ከስድሳ ነብሮች ጋር የሚኖሩት አባታችን፣ እንስሳቱ እርሳቸውን የረገጡትን መሬት ልሰው ጠግበው ይኖራሉ፡፡

ሰውነታቸው አንድ ክንድ ከስንዝር በሚረዝም ጠጉር የተሸፈነው አባታችን ወደ ሀገራችን መጥተው ተጋድሏቸውን ቀጠሉ፡፡ የእግዚአብሔር መልአክ ቅዱስ ገብርኤልም ገዳማቶቻቸው ወዳሉባቸው ወደ ምድረ ከብድና ወደ ዝቋላ ተራራ ወሰዳቸው፡፡ በእነዚህ ገዳማት እየተመላለሱ ሲጸልዩና ሀገራችንን ሲባርኩም ኖረዋል፡፡ ሰው የገዛ ፊቱን በመስታወት እንደሚያይ በሀገራች ያለውን የኃጢአት ስራ ባዩ ጊዜ በዝቋላ ሐይቅ አንድ መቶ ዓመት ተዘቅዝቀው መላው ኢትዮጵያን እንዲምርካቸው ጸልየው ቃል ኪዳን ተቀብለዋል፡፡ የመጨረሻ እረፍታቸውም በምድረ ከብድ ገዳም ነው፡፡ ይህ እረፍታቸውም በየዓመቱ መጋቢት 5 ታስቦ ይውላል፡፡ ገዳማትንና ገዳማውያንን እያሰብን ከበረከታቸው እካፈል፡፡
     

ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት  ገዳም


ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444


የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444




44 የገበታ ጨው ምርቶች ከገበያ ታገዱ

#FastMereja I 44 የተለያዩ የገበታ ጨው ምርት ዓይነቶች ሕብረተሰቡ እንዳይጠቀማቸው የኢትዮጵያ የምግብና መድኃኒት ባለስልጣን አሳሰበ፡፡

ባለስልጣኑ በሰራው የገበያ ቅኝት ሥራዎች 44 ዓይነት የምርት መለያ ስም ያላቸው የተለያዩ በአዮዲን የበለፀጉ የምግብ ጨው በሚል ታሽገው ደህንነታቸውና ጥራታቸው ሳይረጋገጥ በተጨማሪም የሀገሪቱን አስገዳጅ ብሔራዊ ደረጃ እና የገላጭ ጽሑፍ ደረጃ ሳያሟሉና ሳይለጥፉ ሲቀርቡ የነበሩ ምርቶች መገኘታቸው ተመላክቷል፡፡

ምርቶቹም የሚከተሉት ናቸው፡-

1. አበሩሰ አዮዳይዝድ ጨው

2. ዛክ የገበታ ጨው

3. ሉሉ የገበታ ጨው

4. ሙሪዳ አዮዳይዝድ ጨው

5. እቱ የገበታ ጨው

6. እቴቴ የገበታ ጨው

7. እፍታ ጨው

8. ኤልሳ የገበታ ጨው

9. ሴፍ የገበታ ጨው

10. NS አዮዳይዝድ ሳልት

11. ማሚ የገበታ ጨው

12. ሣሊህ የገበታጨው

13. እማ የገበታ ጨው

14. አዮዲን የገበታ ጨው

15. ቃና የገበታ ጨው

16. ሀርመኒ የገበታ ጨው

17. ውዛት አዮዳይዝድ ሳልት

18. ሐበሻ ባለ አዮዲን ጨው

19. ሪል የገበታ ጨው

20. ሸጋ የገበታ ጨው

21. ጆይ አዮዳይዝድ ሳልት

22. ኮከብ የገበታ ጨው

23. ስኬት የገበታ ጨው

24. ፎር ኤም አዮዳይዝድ ሳልት

25. አዲስ የገበታ ጨው

26. ኤመሬት ጨው

27. አስቤዛ የገበታ ጨው

28. ቶም የገበታ ጨው

29. በረከት የገበታ ጨው

30. ሜናታ የገበታ ጨዉ

31. ቤስት አዮዳይዝድ ጨዉ

32. አፊአ የገበታ ጨው

33. ዋን በአዮዲን የበለፀገ የገበታ ጨዉ

34. አቢሲኒያ የገበታ ጨዉ

35. ማሩ የገበታ ጨዉ

36. ባና ኤዳይዝድ ጨው

37. ማራኪ ጨዉ

38. መክሊት የገበታ ጨዉ

39. ዳግም የገበታ ጨዉ

40. አዲስ የገበታ ጨዉ

41. አፍያ ጨዉ

42. ኦማር የገበታ ጨው

43. ገዳ የገበታ ጨው

44. NITSUH IODIZED SALT


44 የገበታ ጨው ምርቶች ከገበያ ታገዱ

#FastMereja I 44 የተለያዩ የገበታ ጨው ምርት ዓይነቶች ሕብረተሰቡ እንዳይጠቀማቸው የኢትዮጵያ የምግብና መድኃኒት ባለስልጣን አሳሰበ፡፡

ባለስልጣኑ በሰራው የገበያ ቅኝት ሥራዎች 44 ዓይነት የምርት መለያ ስም ያላቸው የተለያዩ በአዮዲን የበለፀጉ የምግብ ጨው በሚል ታሽገው ደህንነታቸውና ጥራታቸው ሳይረጋገጥ በተጨማሪም የሀገሪቱን አስገዳጅ ብሔራዊ ደረጃ እና የገላጭ ጽሑፍ ደረጃ ሳያሟሉና ሳይለጥፉ ሲቀርቡ የነበሩ ምርቶች መገኘታቸው ተመላክቷል፡፡

ምርቶቹም የሚከተሉት ናቸው፡-

1. አበሩሰ አዮዳይዝድ ጨው

2. ዛክ የገበታ ጨው

3. ሉሉ የገበታ ጨው

4. ሙሪዳ አዮዳይዝድ ጨው

5. እቱ የገበታ ጨው

6. እቴቴ የገበታ ጨው

7. እፍታ ጨው

8. ኤልሳ የገበታ ጨው

9. ሴፍ  የገበታ ጨው

10. NS አዮዳይዝድ ሳልት

11. ማሚ የገበታ ጨው

12. ሣሊህ  የገበታጨው

13. እማ የገበታ ጨው

14. አዮዲን የገበታ ጨው

15. ቃና የገበታ ጨው

16. ሀርመኒ የገበታ ጨው

17. ውዛት አዮዳይዝድ ሳልት

18. ሐበሻ ባለ አዮዲን ጨው

19. ሪል የገበታ ጨው

20. ሸጋ የገበታ ጨው

21. ጆይ አዮዳይዝድ ሳልት

22. ኮከብ የገበታ ጨው

23. ስኬት የገበታ ጨው

24. ፎር ኤም አዮዳይዝድ ሳልት

25. አዲስ የገበታ ጨው

26. ኤመሬት ጨው

27. አስቤዛ የገበታ ጨው

28. ቶም የገበታ ጨው

29. በረከት የገበታ ጨው

30. ሜናታ የገበታ ጨዉ

31. ቤስት አዮዳይዝድ  ጨዉ

32. አፊአ  የገበታ ጨው

33. ዋን በአዮዲን የበለፀገ የገበታ ጨዉ

34. አቢሲኒያ የገበታ ጨዉ

35. ማሩ የገበታ ጨዉ

36. ባና ኤዳይዝድ ጨው

37. ማራኪ ጨዉ

38. መክሊት የገበታ ጨዉ

39. ዳግም የገበታ ጨዉ

40. አዲስ የገበታ ጨዉ

41. አፍያ ጨዉ

42. ኦማር የገበታ ጨው

43. ገዳ የገበታ ጨው

44. NITSUH IODIZED SALT




የሙዚቃ አቀናባሪው ካሙዙ ካሳ የጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ ያለውን አድናቆት ገለፀ። በማህበራዊ ትስስር ገፁ ባሰፈረው የአድናቆት መልዕክት "ክቡር ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ ሆይ ፈጣሪ ካንተ ጋር ነውና ሀገር ወዳድ ልበቀና በሳል እና ጥበበኛ መሪ እንደሆንክ ገና አለም ይመሰክርልሀል እየመሰከርልህም ነው የሀገሬ የኢትዮጵያ መሪ በመሆንህ እኮራብሃለሁ" ብሏል።

በመጨረሻም እውነት ካንተ ጋር ነው ሲል ገልጿል።

3.7k 0 11 14 172

#ስለሃይማኖታቸው ክብር ንጉሱን ያልፈሩት ጻድቅ


በአጼ ሱስንዮስ ዘመነ መንግሥት በአሥራ ሰባተኛው መቶ ክፍለ ዘመን የነበሩ ድንቅ ሥራ የሰሩ፣ ተአምረኛና ገዳማዊ አባት ናቸው። እኒህ ታላቅ ጻድቅ ሐዋርያዊ አባት አቡነ ዓምደ ሥላሴ የካቲት 27 ጎጃም ውስጥ ነው የተወለዱት።

የካቲት 17 ቀን መንኩሰው ወደ ተጋድሎ ገብተዋል። በተለያዩ ገዳማት በነበራቸው ቆይታም እመቤታችን ቅድስት ኪዳነ ምሕረት የካቲት 16 ቀን በነበራቸው ፍቅር ይታወቃሉ። ጻድቁ በበርካታ ገዳማት የነበሩ ሲሆን በገዳማዊ ሕይወታቸው በትህርምት፣ በጸሎታቸውና በተጋድሏቸው ዛሬም ድረስ ከሚታወቁ አባቶች አንዱ ናቸው። ጻድቁ አባታችን ዓምደ ሥላሴ ከሚነገሩላቸው ታሪኮች ቅድሚያውን የሚይዘው የተዋሕዶ ጠበቃነታቸው ነው።


በ1603 ዓ.ም ጴጥሮስ ወይም ፔድሮ ፓኤዝ የሚባል ካቶሊካዊ ከሀዲ ወደ ሃገራችን ገብቶ ነበር መኖር ጀመረ፡፡ ከዚያም  ውስጥ ለውስጥ ሲሰብክ ቆይቶ በ1609 ዓ.ም ነገሩ በመገለጡ እነ ራስ ዮልዮስ ለሃይማኖታቸው ጠዳ ላይ ተዋግተው ግንቦት 6 ቀን ተሰው። በ1622 ዓ.ም አጼ ሱስኒዮስ ከነቤተሰባቸው ተጠምቀው ካቶሊክ ሆኑ፡፡ ይህ ነገር ሲሰማ ወንድ ሴት፣ ትልቅ ትንሽ ሳይመረጥ በገጠሩም፣ በከተማውም፣ በገዳሙም ያሉት ሁሉ የተዋሕዶ ልጆች መንቀሳቀስ ጀመሩ። በ1626 ዓ.ም ካቶሊክ የኢትዮጵያ እምነት ነው ብለው ሲያውጁ ግጭቱ በይፋ ተጀመረ። "ተዋሕዶን ካልካዳችሁ" በሚል በቀን እስከ ስምንት ሺህ ሰው በሰይፍ ታረደ። ይህን ያደረጉት ደግሞ አልፎንሱ ሜንዴዝ፣ ንጉሡ ሱስንዮስና ጀሌዎቻቸው ነበሩ።

በጊዜውም ከቤተ መንግሥት የሱስንዮስ ሚስት እነ ንግሥት ወልድ ሰዓላ፣ ከጻድቃን አበው ዘርዓ ቡሩክ ዘግሸን፣ ሐራ ድንግል ዘደራ፣ ምዕመነ ድንግል ዘጩጊ፣ ዓምደ ሥላሴ ዘማኅበረ ሥላሴ፣..... ከቅዱሳት እነ ፍቅርተ ክርስቶስ፣ ወለተ ጴጥሮስ፣ ወለተ ጳውሎስ፣ እኅተ ጴጥሮስ፣..... ለሃይማኖታቸው ተዋሕዶ ጥብቅና ቆመው ሕዝቡን አስተማሩ፤ መከራም ተቀበሉ። ብዙ ኢትዮጵያውያን የመከራ ጽዋን ተጐንጭተው በክብር ሰማእትነት ከተቀበሉ በኋላ የእግዚአብሔር ፍርድ ተገለጠ። በጻድቃኑ በእነ አባ ዓምደ ሥላሴ ሐዘን ንጉሡ ታመሙ ከዚያም ምላሳቸው ተጐልጉሎ ወጣ። በዚህ ጊዜ አቤቶ ፋሲለደስ ለአባ ዓምደ ሥላሴና ለሌሎቹ ቅዱሳን "አባቴን አድኑልኝ! ተዋሕዶም ትመለስ።" አላቸው።

ጻድቁም ከባልንጀሮቻቸው ጋር ጸልየው ንጉሡን አዳኗቸው። እርሳቸውም "ፋሲል ይንገሥ! ተዋሕዶ ሃይማኖት ይመለስ! የሮም ሃይማኖት ይፍለስ!" ብለው አሳወጁ። ከዚህ በኋላ አጼ ፋሲል ሲነግሡ አባ ዓምደ ሥላሴ ለገዳማቸው ብዙ ቦታ አስከልለው በተጋድሎ ኑረው የካቲት 27 ዐርፈዋል።

ገዳማውያን ሃይማኖት ሲነካ አንገታቸውን አሳልፈው እስከ መስጠት መስዋዕትነት ይከፍላሉ፡፡ ሕዝቡን ለማጽናናትና ለማስተማር ከገዳማቸው ይወጣሉ እንጂ በተጋድሎ ጸንተው፣ በትህርምት ረግተው፣ በጸሎት ተግተው ከዓለም ርቀው ነው የሚኖሩት፡፡ በዓለም ላለነው ለኛና ለቅድስት ቤተክርስቲያን ለሀገራችንም ይጸልያሉ፡፡ ገዳማቸውን በመርዳት፣ በዓታቸውን በማጽናት ከበረከታቸው እንሳተፍ፡፡ 


ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት  ገዳም


ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444


የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444




#ሐዋርያው ቅዱስ እንድርያስ...


የስሙ ትርጓሜ “ጽኑ በኩር” ማለት ነው፡፡ የቅዱስ ጴጥሮስ ወንድም ሲሆን በመጀመሪያ የተጠራ ሐዋርያ ነው፡፡ በመጀመሪያ የመጥምቁ ዮሐንስ ደቀ መዝሙር የነበረ ቢሆንም መጥምቁ የጌታችንን መንገድ ሲጠርግና ስለ ክርስቶስም ሲሰብክ ስለሰማው በዚያው የጌታችን ደቀ መዝሙር ሆኗል፡፡ ከሰው ጋር ፈጥኖ የመግባባት ችሎታ ስለነበረው በሐዋርያትም ዘንድ እንደ አስተባባሪ ይቆጠር ነበር፡፡ ጌታችን 5 እንጀራና ሁለቱን ዓሣ አበርክቶ ሕዝቡን ሲመግብ እንጀራውንና ዓሣዎቹን የያዘውን ወጣት ወደ ጌታችን ወስዶ እንዲባረክ ያደረገው እንድርያስ ነው፡፡ በዚህም የወጣቶች ሐዋርያ ይባላል፤ ሐዋርያው ቅዱስ እንድርያስ፡፡ ሐዋርያው በሩሲያ፣ በቢታንያ፣ በገላቲያና በሩማንያ ወንጌልን ሰብኮ ብዙ ክርስቲያኖችን አፍርቷል፡፡

የአስቆሮቱ ይሁዳን ተክቶ ሐዋርያው ቅዱስ ማትያስ ከ12ቱ ሐዋርያት ጋር ከተቆጠረ በኋላ ሰውን የሚበሉ ሰዎች ወዳሉባት “እስኩቴስ" ወደተባለች የሩሲያ ክፍል ሄዶ ወንጌልን ይሰብክ ዘንድ ዕጣ ደረሰው፡፡ ቅዱስ ማትያስም አገራቸው እንደደረሰ ዐይኑን አውልቀው አሠሩት፡፡ ምግባቸውም የእንግዳ ሰው ሥጋ ነው፡፡ በልማዳቸው መሠረት ገና እንደያዙት ዐይኖቹን ዐውልቀው እሥር ቤት ይጥሉታል፡፡ እስከ 30 ቀን ድረስም ሳር እያበሉ ያስቀምጡትና በ30ኛው ቀን ከእሥር ቤታቸው አውጥተው አርደው ይበሉታል፡፡ሐዋርያው ቅዱስ እንድርያስ ወንጌልን እየሰበከ በግሪክ አገር ሳለ ክብር ይጋበውና ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተገለጠለትና “ሰውን የሚበሉ ሰዎች ማትያስን ይዘው አሥረውታል፣ ከሦስት ቀንም በኋላ ሊበሉት ከእሥር ቤታቸው ያወጡታልና አንተ አሁን ወደ እነዚያ ሰውን ወደሚበሉት ሰዎች አገር ሂድ” አለው፡፡

እንድርያስም “ጌታዬ ፈጣሪዬ የቀረው ሦስት ቀን ከሆነ እንዴት እደርሳለሁ? ባይሆን ፈጥኖ የሚያወጣው መልአክ ላክለት” አለው፡፡ ጌታችንም “እኔ ሀገሪቱን ነይ ካልኳት በውስጧ ከሚኖሩት ሁሉ ጋር ትመጣለች፤ ፈቃዴ ግን አንተና ደቀ መዝሙሮችህ እንድትሄዱ ነውና ነገ በጠዋት ተነሥታችሁ ወደ ባሕሩ ሂዱ፣ የተዘጋጀች መርከብም ታገኛላችሁ” ብሎት በክብር ዐረገ፡፡ በነጋው ወደ ወደቡ ሲደርሱ ጥሩ የተዘጋጀች መርከብንም አገኙ፡፡ ጌታችንም በሊቀ ሐመር አምሳል ተገለጠለት ነገር ግን እንድርያስ አላወቀውም ነበር፡፡ በመርከቡ ሲጓዙም እንቅልፍ ጣላቸውና መላእክት ወስደው በባሕሩ ዳርቻ አስቀመጧቸው፤ መርከቡ ግን አልነበረም፡፡ እንድርያስም የመርከቡ ቀዛፊ ጌታችን መሆኑን አሁን ዐወቆ ሲጸልይ ጌታችን ተገለጠለትና ማትያስንና አብረውት ያሉትን ከወህኒ ሳይፈራ እንዲያወጣቸው ነገረው፡፡

ቅዱስ እንድርያስና ደቀ መዛሙርቱም መትያስንና እስረኞቹን ሁሉ ነጻ አወጧቸው፡፡ ሰው የሚበሉትን የከተማዋ ሕዝቦችም በድንቅ ተአምራት መልሰው ወንጌል ሰብከው አጠመቋቸው፡፡ ቅዱስ እንድርያስ የቍስጥንጥንያ የመጀመሪያው ሊቀ ጳጳስም ነው፡፡ በግሪክ ሲያስተምር ከሃዲያን ይዘው በ60 ዓ.ም ታኅሣሥ 4 ቀን ሰቅለው ገድለውታል፡፡ ሊሰቅሉት ሲወስዱትም “ጌታዬ በተሰቀለበት ዓይነት መስቀል አትስቀሉኝ” በማለት ሲለምናቸው እነርሱም ፍቃዱን ፈጽመውለት የእንግሊዝኛው ኤክስ (X) ፊደል ቅርጽ ባለው መስቀል ላይ ሰቅለውታል፡፡ ስኮትላንዶች የቀኝ የእጆቹን ጣቶች በአንድ መነኩሴ አማካኝነት ስላገኙ ሐዋርያው እንድርያስን ‹‹ጠባቂያችን›› ነው እያሉ ይመኩበታል፡፡ በረከቱ ትደርብ አሜን፡፡  


በገዳማዊ ኑሮ ያሉትን እየረዳንና በዓታቸውን እያጸናን የበረከታቸው ተሳታፊ እንሁን፡፡


ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት  ገዳም


ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444


የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444




“ሴቶችን በሙያ ማክበር!” በሚል ርዕስ የፓናል ውይይት ተካሄደ።

#FastMereja I “ሴቶችን በሙያ ማክበር!” በሚል ርዕስ ኢንጀንደር ሄልዝ በተለያየ ዘርፍ ውስጥ ያሉ የሴቶች የሙያ ማህበራት በተገኙበት የፓናል ውይይት ዛሬ መጋቢት 4/2017 ዓም በስካይላይት ሆቴል አካሄዷል።

ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀንን አስመልክቶ የተካሄደው የፓናል ውይይት በጤና፣ በትምህርት፣ ሳይንስና ቴክኖሎጂ፣ በፍትህ፣ በሲቪል ሶሳይቲ ዘርፍ ውስጥ ባሉ የሴቶች የሙያ ማህበራት ተሳታፊ ሆኗል።

በመድረኩ ላይ ስኬታማ ሴቶች ተሞክሮቸውን ያካፈሉ ሲሆን ከተሳታፊዎች ጥያቄ ቀርቦ ምላሽ ተሰጥቷል።

ኢንጀንደር ሄልዝ ኢትዮጵያ በስነ-ተዋልዶ ጤና፤ በእናቶች እና ጨቅላ ህፃናት ጤና፣ ወጣቶችንና ሴቶችን በማብቃት፣ የስርዓተ-ፆታ እኩልነትና ፍትሃዊነት ማረጋገጥ ላይ ፆታዊ-ጥቃትን መከላከል እና ምላሽ መስጠት ላይ እየሰራ ያለ አለም አቀፍ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት ነው፡፡


አርቲስት አንዱአለም ጎሳ በቀነኒ ሞት ተጠርጥሮ ፍርድ ቤት ቀረበ

#FastMereja I አርቲስት አንዱአለም ጎሳ በእጮኛው ቀነኒ አዱኛ ሞት ተጠርጥሮ ከታሰረ ከሁለት ቀናት በኋላ ፍርድ ቤት መቅረቡን ጠበቃው ለቢቢሲ አፋን ኦሮሞ ገልጿል።

ፖሊስ እስካሁን አሻራ ማንሳቱን፣ አስከሬኑን ወደ ሆስፒታል በመላክ፣ የአስከሬን ምርመራ ማድረጉን ገልጾ የሰው ማስረጃዎችን በማሰባሰብ ላይ እንደሚገኝ ተናግሯል።

“አሁን ፎቶግራፎችን ከመዝገቡ ጋር ለማያያዝ፣ የሰዎች ምስክርነት ለመስጠት እና የአስከሬን ምርመራው እስኪመጣ ድረስ ለማጣራት 14 ቀናት ያስፈልገኛል ብሏል።

የአንዱአለም ጠበቃ በበኩሉ የዋስ መብት ይሰጥ ብሎ ቢጠይቅም ፍርድ ቤት የአስክሬን ምርመራ እንስኪደርስ በማለት 13 ቀናት ድምፃዊው በማረሚያ ቤት እንዲቆይ ወስኗል።

#FastMereja #ሾውቢዝ


3ኛው የአፍሪካን ሮቦቲክስ ሻምፒየንሺፕ ውድድር ተጀመረ

#FastMereja I 3ኛው ዙር የአፍሪካን ሮቦቲክስ ሻምፒየንሺፕ ውድድር የመጀመሪያ ደረጃ፤ የሁለተኛ ደረጃ፣ የኮሌጅና የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ተሳታፊ ናቸው።

ውድድሩ በዲዛይኒንግ፤ በኢንጂነሪንግና በአውቶነመስ ኮዲንግ ላይ እንደሚያተኩር ተገልጿል።

ውድድሩ ከመጋቢት 4 እስከ 6 ቀን 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ ሳይንስ ሙዚየም የሚካሄደው ኢትዮ ሮቦቲክስ አስታውቋል።

በውድድሩ አሸናፊ የሚሆኑ ተማሪዎች የዋንጫ ሽልማቶችን የሚያገኙ ሲሆን፤ በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የተፈረመ ሰርተፊኬትም ይበረከትላቸዋል ተብሏል፡፡

በዚህ ውድድር በአዲስ አበባ የሚኖሩ አፍሪካውያንም የሚካፈሉ ሲሆን፤ ለፍጻሜ የሚበቁ ተማሪዎች አገራቸውን ወክለው በአሜሪካ በሚካሄደው ዓለምአቀፍ የሮቦቲክስ ውድድር ላይ እንደሚሳተፉ የኢትዮ ሮቦቲክስ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ሰናይክረም መኮንን ገልጸዋል።

ባለፈው ዓመት በቻይና ሻንጋይ በተካሄደው ኢንጆይ ኤአይ ዓለምአቀፍ የሮቦቲክስ ውድድር ላይ 21 ኢትዮጵያውያን ታዳጊዎች ሀገራቸውን ወክለው የተወዳደሩ ሲሆን፤ በውድድሩ ከተሳተፉ 27 የዓለም አገራት 3ኛ ደረጃን ይዘው ማጠናቀቃቸው ይታወሳል፡፡

#ሳይ_ቴክ


በዛሬው እለት ከ24 ድርጅቶች እና 3 ግለሰቦች በድምሩ 6,700,000 ብር መቅጣቱን ገለፀ።

#FastMereja I የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ከአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ጋር በመተባበር ፍሳሽ ቆሻሻ ወደ ወንዝ የለቀቁ ድርጅቶችና ግለሰቦችን በደንብ ቁጥር 180/2017 መሰረት የገንዘብ ቅጣቶች በመቅጣት አስተዳደራዊ እርምጃ መውሰዱ ገለጸ፡፡

ባለስልጣኑ በዛሬው እለት በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ 1,800,000 ብር፣ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ 1,750,000 ብር፣ በአራዳ ክፍለ ከተማ 1,200,000 ብር፣በጉለሌ ክፍለ ከተማ 600,000 ብር ፣ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ 400,000 ብር በመቅጣት አስተዳደራዊ እርምጃ ወስዷል።

በተያያዘ ዜና በቦሌ ክ/ከተማ 450,000 ብር በኮልፌ ክ/ከተማ 400,000 ብር ፤በልደታ ክፍለ ከተማ 100,000 ብር በመቅጣት አስተዳደራዊ እርምጃ በመውሰድ ለመንግስት ገቢ አድርጓል።

ባለስልጣኑ በአጠቃላይ በዛሬው እለት 24 ጅርጅቶች እና 3 ግለሰቦች በድምሩ 6,700,000/ስድስት ሚሊየን ሰባት መቶ ሺህ/ ብር መቅጣቱ ገልጿል።

መረጃው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን


#ዓለም ላይ እርሱን የመሰለ ጠቢብ ፈጽሞ አይነሳም 

እስከ ዓለም ፍጻሜ በተሰጠው ጥበብ እርሱን የሚመስል ከሰው ልጅ ወገን እንደማይነሳ ይነገርለታል፡፡ መፍቀሬ ጥበብ፣ ጠቢበ ጠቢባን፣ ንጉሠ እሥራኤል፣ የጽድቅ ነቢየ፣ ሰላማዊው ንጉስ እየተባለ ይጠራል፡፡ አባቱ ታላቁ ነቢይና ንጉሥ ልበ አምላክ ቅዱስ_ዳዊት ነው፡፡ እናቱ ደግሞ ቤርሳቤህ ወይም ቤትስባ ትባላለች፡፡ ከ3ሺ ዓመታት በፊት የተወለደው ቅዱስ ሰሎሞን እስከ 12 ዓመቱ ድረስ በቤተ መንግሥት ከአባቱ ጋር አድጓል፡፡ ቅዱስ ዳዊት 70 ዘመን በሞላው ጊዜ የአካሉን መድከም አይቶ አዶንያስ በጉልበት እነግሣለሁ ቢልም አልተሳካለትም:: እግዚአብሔር ሰሎሞንን መርጧልና ገና በ12 ዓመቱ ነገሠ:: ልበ አምላክ አባቱ ዳዊት ነፍሱ ከሥጋው ከመለየቷ በፊት መከረው:: "ልጄ ሆይ! ልብህን ስጠኝ:: ፈጣሪህንም አምልክ" አለው::

በሰፊው የሚታወቀው ልክ እንደ አባቱ እስራኤልን ለአርባ ዓመት በማስተዳደሩና ታላቁን ቤተ መውደስ በመገንባቱ ነው፡፡ እንደ ነገሠም በገባዖን ለእግዚአብሔር መስዋዕትን አቀረበ፡፡ ጌታም ተገልጾ "ምን ትፈልጋለህ?" አለው፡፡ ሰሎሞንም እንደ አባቱ ማስተዋልን፣ ልቡናን ለመነ፡፡ ጌታም ደስ ስለተሰኘ "ከአንተ በፊትም ሆነ ከአንተም በኋላ እንዳንተ ያለ ጠቢብና ባለጸጋ ሰው አይኖርም" ብሎታል፡፡ ግሩም በሆነ ፍርዱ፣ በልዩ ጥበቡ ስለርሱ የሰማው ዓለም ሁሉ ተገዛለት፡፡ የእኛዋ ታላቅ ንግስተ ሳባ /ማክዳም/ ትፈትነው ዘንድ ሒዳ ምኒልክን ጸንሳ መምጣቷ በሁዋላም ለታቦተ ጽዮንና ሥርዓተ ኦሪት መምጣት ምክንያት ሆኗል፡፡ ቅዱስ ሰሎሞን በተለይ ስለ ድንግል ማርያም የጻፈው ምስጋና እንደ አባቱ ቅዱስ ዳዊት ዛሬም ድረስ በቅድስት ቤተክርስቲያንችን ጥቅም ላይ ይውላል፡፡

ንጉስ ሰሎሞን ድንግል ማርያም ከእርሱ ዘር እንደምትወለድ ሲነገረው፣ አንድም ሥጋ ለባሽ ሰው ነውና ሁለተኛም ከብዙ ሴቶች መካከል ከአንዷ እመ ብርሃን ትገኛለች መስሎት መፍቀሬ አንስት ሆነ፡፡ ከአሕዛብ ወገን ከፈርዖን ልጅ ጋር በመወዳጀቱም ለጣዖት ሰግዶ እግዚአብሔርን ቢያሳዝንም በራዕይ ተገልጦ "ስለ ወዳጄ ስለ ዳዊት ስል በአንተ ላይ ክፉን አላደርግም" አለው፡፡ ታላቁ ነቢይ ሰሎሞን ይህንን ሲሰማ ወደ ልቡ በመመለስ ማቅ ለብሶ፣ አመድ ነስንሶ በፍጹም ልቡ ንስሃ በመግባቱ ጌታችን ንስሃውን ተቀበለው፡፡ አሁን ድረስ ድንቅ ጥበብ የያዙትን መኃልየ መኃልይ ዘሰሎሞን፣ መጽሐፈ ጥበብ፣ መጽሐፈ ምሳሌ፣ መጽሐፈ ተግሣጽ፣ መጽሐፈ መክብብ የተባሉ አምስት መጻሕፍት ገለጸለት፡፡

“ወዳጄ ሆይ፥ እነሆ ውብ ነሽ፤ እነሆ አንቺ ውብ ነሽ፤ ዓይኖችሽም እንደ ርግቦች ናቸው።” ናቸው ሲል ቅድስት ድንግል ማርያምን አመስግኗታል፡፡ ዘመናትን መዋጀት እንደሚገባ ሲነግረንም በተለይ ትልቁን የወጣትነት ጊዜ በጥበብ ቃላት ሲገልጸው “የጭንቀት ቀን ሳይመጣ በጉብዝናህ ወራት ፈጣሪህን አስብ፡፡ ደስ አያሰኙም የምትላቸውም ዓመታት ሳይደርሱ፤ ፀሐይ፣ ጨረቃና ከዋክብትም ሳይጨልሙ፤ አፈርም ወደ ነበረበት ምድር ሳይመለስ፤ ነፍስም ወደ ሰጠው ወደ እግዚአብሔር ሳይመለስ ፈጣሪህን አስብ፡፡” ይለናል፡፡ በመጽሐፈ ምክብብም በዚህ ዓለም ምንም ብንሰበስብ እግዚአብሔር ከሌለበት እንደማይረባ ሲነግረን "ከንቱ፣ ከንቱ፣ ሁሉ ከንቱ ነው" ይላል:: ጠቢብ፣ ነቢይና ንጉስ ሰሎሞን በዚህች ዕለት በ52 ዓመቱ ዐርፎ ወደ ፈጣሪው መሔዱን “ድርሳነ መስቀል” ላይ ሰፍሮ ይገኛል፡፡


በገዳማዊ ኑሮ ያሉትን እየረዳንና በዓታቸውን እያጸናን የበረከታቸው ተሳታፊ እንሁን፡፡


ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት  ገዳም


ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444


የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444




በወ/ሮ ሙሉ ግርማይ የተመሰረተው ላይፍ ሴንተር ነገ የገቢ ማሰባሰብያ ሊያካሄድ ነው

#FastMereja I ላይፍ ሴንተር ኢትዮጵያ የድርጅቱ መስራች ወ/ሮ ሙሉ ግርማይ በስደት ከሚኖሩበት አሜሪካን ሀገር ወደ ኢትዮጵያ ቤተሰብ ለመጠየቅ በመጡበት ወቅት የወላጅ አልባ ህፃናትንና የችግረኛ እናቶችን አስቸጋሪ ህይወት በመመልከት እራሳቸው ያለፉበትን የህይወት ፈተና በማስታወስ ወገኖቻችንን ለመርዳት በ2005 ዓ/ም የተመሰረተ የበጎ አድራጎት ድርጅት ሲሆን ላለፉት 12 ዓመታት ወላጅ አልባ ህፃናትንና መበለቶችን እየረዳ የቀጥለ ድርጅት ነው::

በጥቂት ህጻናት ብቻ የጀመሩት የስፖንሰርሺፕ እርዳታ ፕሮግራም አሁን ከ345 የሚበልጡ ወላጅ አልባ ህፃናትን የተመጣጠነ ምግብ፣ ልብስ፣ የትምህርት መርጃ መሣሪያዎችንና የመሳሰሉትን እያቀረበ የህይወት ክህሎት ስልጠና እና የምክር አገልግሎት እየሰጠ መልካም ዜጋን ለማፍራት አስተዋፅኦ እያደረገ ያለ ድርጅት መሆኑ ተገልጿል።

እንዲሁም ከ919 ለሚበልጡ መበለቶች የቢዝነስ ክህሎት ስልጠና በመስጠት: የአነስተኛ ብድር አገልግሎት ተጠቃሚ በማድረግ ላይ ይገኛል::

በአሁኑ ጊዜ እርዳታ የሚፈልጉ ወገኖቻችን ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ በመሄዱ፣ ላይፍ ሴንተር የአገልግሎቱን አድማስ በማስፋት ለብዙዎች ተደራሽ መሆን ይፈልጋል ያሉ ሲሆን ይህንን የተቀደስ ህልማችንን እውን ለማድረግ የወገኖቻችን ዕርዳታ ለመጠየቅ ዓመታዊ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃግብር ነገ መጋቢት 4 ቀን 2017 በሂልተን ሆቴል መዘጋጀቱ ተገልጿል።

በዛሬው እለትም አርቲስት ልያት ስዩም የላይፍ ሴንተር የበጎ ፍቃድ አምባሳደር ተደርጋ ተሹማለች።

የላይፍ ሴንተር የበጎ ፍቃድ አምባሳደር ሆና የተሾመችው አርቲስት ልያት ስዩም የበጎ ፍቃድ አምባሳደርነቱ ለሁለት አመታት የሚቆይ ሲሆን ተቋሙን በተለያዩ ስራዎች የምታገለግል ይሆናል።


የፍቅር ጥያቄዬ ምላሽ አላገኘም ያለው ሁለት ሰዎችን ገድሎ ራሱን አጠፋ

በአዲስ አበባ ልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ ስድስት ካርል አደባባይ አካባቢ በሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ አንድ ግለሰብ ሁለት ሰዎችን ገድሎ ራሱን እንዳጠፋ የአዲስ አበባ ፖሊስ ለቢቢሲ ተናገረ።

ክስተቱ ያጋጠመው ትናንት ማክሰኞ መጋቢት 02/2017 ዓ.ም. ሲሆን፤ ለሦስት ሰዎች ሞት ምክንያት የሆነው ሁኔታ የተፈጠረው 'የፍቅር ጥያቄዬ ምላሽ አላገኘም' በሚል ምክንያት መሆኑን ፖሊስ ገልጿል።

አቶ ሽፈራው ረጋሳ የተባለ የባንኩ የጥበቃ ሠራተኛ ለሥራ ባልደረባው የፍቅር ጥያቄ አቅርቦላት ምላሽ ባለማግኘቱ ግለሰቧን እና ከግለሰቧ ጋር የፍቅር ግንኙነት አለው በሚል የጠረጠረውን ሌላ ባልደረባውን በመግደል ራሱን እንዳጠፋ አዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል።

ግለሰቡ የፍቅር ጥያቄ ያቀረበላት ወይዘሪት ሃና ተስፋዬ የተባለች 32 ዓመት ወጣት እና አቶ ንጉሤ ብርሃኑ የተባለ የሥራ ባልደረቦቹን በጥይት ተኩሶ የገደለው።

የአዲስ አበባ ፖሊስ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ ለቢቢሲ እንደገለጹት ወንጀሉን የፈፀመው የጥበቃ ሠራተኛ ካልተራው ሌላ ሠራተኛን ተክቶ በመግባት እና ከምሽት የጥበቃ ሠራተኞች የጦር መሳሪያ በመቀበል ግድያውን ፈፅሟል።

ግለሰቡ ግድያውን የፈጸመው ተጠርጣሪው ወደ ዕለታዊ ሥራቸው እስኪገቡ ድረስ በመጠበቅ መጀመሪያ አቶ ንጉሤ ብርሃኑ የተባለውን ግለሰብ በሁለት ጥይት መትቶ መግደሉን ኮማንደር ማርቆስ ገልጸዋል።

ግድያው ማክሰኞ መጋቢት 2/2017 ዓ.ም. ጠዋት ከአንድ ሰዓት ተኩል እስከ ለሁለት ሰዓት ሩብ ጉዳይ ድረስ ባላው ጊዜ ውስጥ መፈፀሙን የተናገሩት የአዲስ አበባ ፖሊስ ቃል አቀባይ፤ በሁለቱ ግድያዎች መካከል እስከ 15 ደቂቃ የሚሆን የጊዜ ክፍተት እንደነበረ አመለክተዋል።

ግድያውን የፈጸመው ግለሰብ ባልደረባውን ተኩሶ ከገደ በኋላ ሌላኛዋን የጥቃቱ ሰለባን ከመግደሉ በፊት ከድርጊቱ እንዲቆጠብ መጠየቁን ነገር ግን ፈቃደኛ እንዳልነበረ ተገልጿል።

ግለሰቡ መሳሪያውን እንዲያስቀምጥ እና እጁን እንዲሰጥ በተደጋጋሚ በተደጋጋሚ ጥያቄ ቀርቦለት የነበረ ሲሆን፣ በዚህ መካከልም ወደ ባንኩ አንደኛ ፎቅ በማምራት የፍቅር ጥያቄውን አልተቀበለችም ያላትን በተመሳሳይ ሁኔታ በጥይት መትቶ መግደሉን ፖሊስ ገልጿል።

ግለሰቡ ሁለቱን ባልደረቦቹን ከገደለ በኋላ በያዘው መሳሪያ የእራሱንም ሕይወት እንዳጠፋ የአዲስ አበባ ፖሊስ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ ለቢቢሲ ገልጸው በክስተቱ በአጠቃላይ የሦስት ሰዎች ሕይወት ጠፍቷል።

ሁለቱ ሟቾች ወ/ሪት ሃና ተስፋዬ እና አቶ ንጉሤ ብርሃኑ የፍቅር ግንኙነት እንደነበራቸው የሚጠቁም ፎቶግራፎች መገኘታቸውን የጠቆሙት ኃላፊው፤ ፖሊስ በምርመራው ስለግንኙነታቸው እንደሚያጣራ ገልፀዋል።

ከዚሁ ክስተት ጋር በተያያዘ ፖሊስ እያካሄደ ያለውን የምርመራ ሂደት እንደሚቀጥል አስታውቋል።

ቢቢሲ ስለ ግድያው ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ኃላፊዎችን ለማነጋገር ያደረገው ጥረት አልተሳካም።

ዘገባው የቢቢሲ ነው።

Показано 20 последних публикаций.