Fetan Sport


Гео и язык канала: Эфиопия, Амхарский
Категория: Образование


ፈጣን ስፖርት የአውሮፓን ከፍተኛ የእግር ኳስ ሊጎች የሚሸፍን የኢትዮጵያ የዜና ቻናል ነው። ይዘቱም የቡድን ዜናዎችን፣ የጨዋታ ውጤቶችን፣ የተጫዋቾች ዝውውሮችን እና ሌሎች ብዙ ነገሮችን ያካትታል።

Связанные каналы  |  Похожие каналы

Гео и язык канала
Эфиопия, Амхарский
Категория
Образование
Статистика
Фильтр публикаций


ሮድሪ መቼ ወደ ሜዳ ይመለሳል? ⚽🩹

የማንችስተር ሲቲው ወሳኝ የመሐል ሜዳ ተጨዋች ሮድሪ በጥሩ ሁኔታ ላይ መሆኑን አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ አረጋግጠዋል። ✅

" ሮድሪ በጥሩ ሁኔታ ላይ ነው " ያሉት ፔፕ ጋርዲዮላ በፍጥነት ያገግማል ብለው እንዳልጠበቁ ገልጸዋል። 🔄

ምናልባት የውድድር አመቱ ሳይጠናቀቅ ወደ ሜዳ ሊመለስ እንደሚችል ያስረዱት ጋርዲዮላ " በአለም ክለቦች ዋንጫ ከእኛ ጋር ይጫወታል " ብለዋል። 🌍🏆


" ሊጉን ለማሸነፍ ጥሩ የፋይናንስ ሁኔታ ያስፈልጋል " ሩኒ 💰

⏩ " ተጨዋች ብሆን ለዩናይትድ አልፈርምም " 😮

የቀድሞ የቀያይ ሴጣኖቹ ተጨዋች ዋይን ሩኒ ማንችስተር ዩናይትድ ሊጉን ለማሸነፍ ጥሩ ተጨዋቾች ማስፈረም እንደሚያስፈልገው ገልጿል። 🏆

" ፕርሚየር ሊጉን ማሸነፍ ከፈለግክ ምርጥ ተጨዋቾችን ማምጣት በሚያስችል የፋይናንሻል ፌር ፕሌይ ቁመና ላይ መሆን ያስፈልጋል " ሲል ሩኒ ተናግሯል። 📊

በተንታኝነት እያገለገለ የሚገኘው ሩኒ አክሎም " አሁን እኔ በሌላ ሀገር የምጫወት ምርጥ ተጨዋች ብሆን እና ዩናይትድ ሊያስፈርመኝ ቢመጣ መፈረሜን እግጠኛ አይደለሁም " ብሏል። 🌍

" በጣም ያበሳጫል በርካታ ትልቅ ቡድኖች ከኤፌ ካፑ መውጣታቸው ለማንችስተር ዩናይትድ ጥሩ እድል ሰጥቶት ነበር ሊጠቀምበት አልቻለም።" ዋይን ሩኒ 😔


⚽ ዩናይትድ ከኤፌ ካፕ ውድድር ተሰናበተ! 💔

ፉልሀም ከማንችስተር ዩናይትድ ጋር ያደረገውን የኤፌ ካፕ አምስተኛ ዙር ጨዋታ በመለያ ምት 4ለ3 በማሸነፍ ሩብ ፍፃሜውን መቀላቀል ችሎአል። 🏆

ሁለቱ ክለቦች መደበኛውን የጨዋታ ክፍለ ጊዜ 1ለ1 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቀዋል። ⚖️

ግቦችን ለማንችስተር ዩናይትድ ብሩኖ ፈርናንዴዝ እንዲሁም ለፉልሀም ካልቪን ባሴይ ማስቆጠር ችለዋል። ⚽⚽

በመለያ ምት በማንችስተር ዩናይትድ በኩል ቪክቶር ሊንድሎፍ እና ዚርኪዜ ሳይጠቀሙ ቀርተዋል። ❌

ብሩኖ ፈርናንዴዝ በውድድር ዘመኑ ከየትኛውም የማንችስተር ዩናይትድ ተጨዋች በበለጠ ሀያ አራት የግብ ተሳትፎ ማድረግ ችሏል። 🔥

የኤፌ ካፕ ሩብ ፍፃሜ ተጋጣሚዎች ከደቂቃዎች በኋላ በሚደረግ የእጣ ማውጣት ስነስርዓት የሚለዩ ይሆናል። 🎯


🚨 ዜና: ሀሪ ማጓየር ወደ እንግሊዝ ብሔራዊ ቡድን ሊመለስ ይችላል! 🏴󠁧󠁢󠁥󠁮󠁧󠁿⚽

አሰልጣኝ ሩበን አሞሪም እንደገለጹት፣ እንግሊዛዊው ተከላካይ ሀሪ ማጓየር ለብሔራዊ ቡድን መጠራት ይገባዋል። "አሁን በጥሩ ሁኔታ ላይ ነው" ብለዋል።

አዲሱ አሰልጣኝ ቶማስ ቱሄል በሚቀጥለው ሳምንት የተጫዋቾችን ዝርዝር ይፋ ሊያደርግ ነው።

ማጓየር ባለፈው አመት በጉዳት ምክንያት ከሶስቱ አናብስት የአውሮፓ ዋንጫ ቡድን ውጪ ነበር።

እንግሊዝ በሚቀጥለው ወር ከአልባንያ እና ላቲቪያ ጋር የአለም ዋንጫ ማጣሪያ ጨዋታዎችን ታደርጋለች። 🌍🏆


⚽️ "የኤፌ ካፕ ኳስ ጥሩ አይደለም" - ጋርዲዮላ

የማንችስተር ሲቲው አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ የኤፌ ካፕ መጫወቻ ኳስ ለተጨዋቾች ምቹ አለመሆኑን ገልጸዋል። 🏆

"ስለ ኳሱ ጥራት ለአመታት አውርተናል። ኳሱ ጥሩ አይደለም፣ በሚመቱ ኳሶች ትክክለኛነት ላይ ተፅዕኖ አለው" ሲሉ ፔፕ ጋርዲዮላ ተናግረዋል።

ይህንን ሀሳብ ብዙ ተጨዋቾች እና አሰልጣኞች እንደሚጋሩት ያስረዱት ፔፕ ጋርዲዮላ "የሊጉ እና የሻምፒየንስ ሊግ ኳሶች በጣም አሪፍ ናቸው፣ ይሄኛው ግን ጥሩ አይደለም" ብለዋል። 🔵

በቅርቡ የአርሰናሉ አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ በተመሳሳይ የመጫወቻ ኳሱ ላይ ተቃውሞ ሲያቀርቡ ነበር። 🔴


💪 "አንቶኒ በፕርሚየር ሊጉ የተቸገረው ከጥንካሬ ጋር በተያያዘ ነው" - አሞሪም

የማንችስተር ዩናይትድ ዋና አሰልጣኝ ሩበን አሞሪም አንቶኒ በእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ የተቸገረው ከአካል ጥንካሬ ጋር በተያያዘ መሆኑን ገልጸዋል። 🔴

"አካላዊ ጥንካሬህ ጥሩ ካልሆነ በእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ አስቸጋሪ ሁኔታ ይገጥምሀል" ሲሉ አሰልጣኝ ሩበን አሞሪም ተናግረዋል።

"አንቶኒ ስፔን ውስጥ ከዚህ የተሻለ ነገር እያሳየ ነው" ያሉት አሰልጣኙ "ነገርግን ለዚህ ዋናው ምክንያቱ አካላዊ ጥንካሬ መሆኑን አረጋግጥላችኋለሁ" ብለዋል። ⚽️


ሮድሪ በመስከረም ወር ከደረሰበት የACl ጉዳት በኋላ ወደ የግል ልምምድ ተመልሷል 🥶🥶🥶


🔵 ጉንዶጋን በማንችስተር ሲቲ ይቀጥላል!

የማንችስተር ሲቲው ጀርመናዊ የመሀል ሜዳ ተጨዋች ኢልካይ ጉንዶጋን ኮንትራት ለተጨማሪ አንድ አመት ለማራዘም ማሰባቸው ተገልጿል። ⚽️

ጉንዶጋን ባሳለፍነው ክረምት ለአንድ ተጨማሪ አመት የማራዘም አማራጭ ባካተተ የአንድ አመት ውል ማንችስተር ሲቲን በነፃ መቀላቀሉ አይዘነጋም። 🇩🇪

ማንችስተር ሲቲ አሁን ላይ የኢልካይ ጉንዶጋንን ለአንድ አመት እስከ 2026 የመቆየት አማራጭ ለመጠቀም ማሰቡን አሰልጣኝ ፔፕ ጋርዲዮላ ገልጸዋል። 📝


ሞሃመድ ሳላህ ለሊቨርፑል አሻራውን ቀጥሏል! 🔥

⚽️ ከሊል ላይ
⚽️ ከኢፕስዊች ላይ
⚽️⚽️ ከቦርንማውዝ ላይ
⚽️🎯 ከቶተንሃም ላይ
⚽️🎯 ከኤቨርተን ላይ
⚽️ ከዎልቭስ ላይ
⚽️🎯 ከአስቶን ቪላ ላይ
⚽️🎯 ከማን ሲቲ ላይ
🎯 ከኒውካስል ላይ

ግብ ጠባቂዎችን ማሸነፉን አያቋርጥም! 👑


🔮 ጥያቄ: ሩቤን አሞሪም የስሜው መጨረሻ ከመድረሱ በፊት ይሰናበታሉ?

ሩቤን አሞሪም የማን ዩናይትድ አዲሱ አሰልጣኝ በዚህ የውድድር ዘመን ከሚመሩት የክለብ ሥራ ይባረራሉ? እርስዎ ምን ይላሉ? 🤔⚽️

በመጪው ጊዜ ውስጥ የማን ዩናይትድ አሰልጣኝ ሩቤን አሞሪም ዕጣ ፈንታ ምን ይሆን? ያለዎትን ሐሳብ ይጋሩን! 🔴


🚨 አሌክሳንደር ኢሳክ በአነስተኛ የብሽሽት ችግር የሊቨርፑል ጨዋታን ያመልጣል! ⚽️

የኒውካስል ዩናይትድ ተጨዋች አሌክሳንደር ኢሳክ በአነስተኛ የብሽሽት ችግር ምክንያት በፕሪሚየር ሊግ ከሊቨርፑል ጋር የሚደረገውን ጨዋታ እንደሚያመልጥ ተገልጿል። 🏥


⚽️ "ይህንንም እኛ በመሆናችን ነው" - አርቴታ

የአርሰናል ዋና አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ ቡድናቸው በዚህ የውድድር አመት ባደረገው ነገር ትችት እንደማይገባው ገልጸዋል። 🔴⚪

"በዚህም ደረጃ ያለነው እኛ በመሆናችን ነው" የሚሉት ሚኬል አርቴታ "በዚህ አመት እንደተፈጠሩብን ችግሮች በደረጃ ሰንጠረዡ ግማሽ መሆን ነበረብን" ብለዋል።

"በአመቱ ውስጥ አምስት ቀይ ካርድ ተመዝግቦበት ይህን ያህል የጉዳት ችግር ገጥሞት እኛ ባለንበት ደረጃ ላይ ያለ በታሪክ ታይቶ አይታወቅም" ሲሉ አሰልጣኙ አክለው ተናግረዋል። 💪


🟥 አሰልጣኝ አርኔ ስሎት ቅጣት ተጣለባቸው!

የሊቨርፑሉ ዋና አሰልጣኝ አርኔ ስሎት ከመርሲሳይድ ደርቢ በኋላ ባሳዩት ያልተገባ ባህሪ ምክንያት ቅጣት ተጥሎባቸዋል። 🚫

አሰልጣኙ ከደርቢው በኋላ ቀይ ካርድ የተመለከቱ ሲሆን ከእንግሊዝ ኤፍኤ የቀረበባቸውን ክስ አምነው መቀበላቸው ይታወሳል። ⚽️

አሁን ላይ አሰልጣኝ አርኔ ስሎት የሁለት ጨዋታዎች ቅጣት እንደተጣለባቸው ይፋ ተደርጓል። 📢

አሰልጣኝ አርኔ ስሎት በቀጣይ የኒውካስል ዩናይትድ እና ሳውዝሀምፕተን ጨዋታዎች የሚያመልጧቸው ይሆናል። 🔜


⚽️ "ሚላን የሄድኩት ለፎንሴካ ብዬ ነው" - ሞራታ

ስፔናዊው የፊት መስመር ተጨዋች አልቫሮ ሞራታ ኤሲ ሚላንን ተቀላቅሎ የነበረው አሰልጣኝ ፓውሎ ፎንሴካን ብሎ እንደነበር ገልጿል። 🔴⚫

"ወደ ኤሲ ሚላን ያቀናሁት ለፎንሴካ ስል ነበር" ያለው አልቫሮ ሞራታ "ነገርግን ከጥቂት ወራት በኋላ እቅዳቸው ተቀይሯል" ብሏል።

"በመጨረሻም እዛ ምቾት አልተሰማኝም ነበር ምክንያቱም እዛ የነበርኩበት ምክንያት ፎንሴካ ነው" ሲል ሞራታ ተናግሯል። 🇪🇸

አልቫሮ ሞራት በጥር የተጨዋቾች የዝውውር መስኮት ኤሲ ሚላንን በመልቀቅ የቱርኩን ክለብ ጋላታሳራይ መቀላቀሉ አይዘነጋም! 🦁


💪 "ከቡድኑ ጠንካራው ፓልመር ነው" - ማሬስካ

የቼልሲው አሰልጣኝ ኢንዞ ማሬስካ ኮል ፓልመር አስቸጋሪ ወቅቶች ሲገጥሙት የበለጠ ፍጹምነት እንደሚያሳይ ተናግሯል! 🔵

"ፓልመር ነገሮች ባልተመቹበት ጊዜ የበለጠ ጠንክሮ ይሰራል፤ ይህንን ነገር በጣም እወደዋለሁ" ሲሉ ማሬስካ አድናቆታቸውን ገልጸዋል።

"በወራት ልዩነት ለተጨዋቾቻችን የአካል ብቃት ምዘና እናደርጋለን። ባለፈው ሳምንት በተደረገው ፓልመር ከቡድኑ ሁሉ የበለጠ ጠንካራው ነበር!" 👑

"ኮል ፓልመር እና የሚያሳየው አቋም ፈጽሞ አያስጨንቀኝም። ከጅምሩ ቡድኑ በራሱ ላይ መመካት እንዳለበት ተናግሬያለሁ" ሲሉ አሰልጣኙ አክለው ተናግረዋል።


🏃‍♂️🇪🇹 ሲቪያ የኢትዮጵያውያን አትሌቶችን ድል ያከብራል!

በ2025 የሲቪያ ማራቶን አሸናፊዎች ሰለሞን ባረጋ እና አንቺናሉ ደሴ ዛሬ በራሞን ሳንቼዝ ፒዥዋን ስታዲየም ልዩ እውቅና ይሰጣቸዋል። 🏆

ክብሩ የሚሰጠው ሲቪያ ከማዮርካ ጋር በሚያደርገው ጨዋታ በፊት ሲሆን፣ ጨዋታው ዛሬ ምሽት 5:00 ሰዓት ይጀመራል! ⚽️


😢 ሞይስ ኪን በከባድ ጉዳት ተጎድቷል!

የፊዮሬንቲናው አጥቂ ሞይስ ኪን ዛሬ በሄላስ ቬሮና ጨዋታ ከባድ የጭንቅላት ጉዳት አጋጥሞታል። ተጨዋቹ ከተቃራኒ ተጨዋች ጋር በነበረው ግጭት ቆስሎ ነበር፣ ሆኖም ወደ ጨዋታው ተመልሷል። 🏥

በድጋሚ ወደ ሜዳ ከገባ በኋላ ግን ራሱን ስቶ ወድቋል። ክለቡ በይፋዊ መግለጫው ተጨዋቹ በጭንቅላቱ ላይ ጉዳት መድረሱን አረጋግጧል። ⚠️

ሞይስ ኪን በአሁኑ ሰዓት በሆስፒታል ህክምና እየተደረገለት ይገኛል። 🏟️


Predictions?
Опрос
  •   🔵 Man City Win
  •   🤝 Draw
  •   🔴 Liverpool Win
37 голосов


🔵🔴 ባርሴሎና መሪነቱን አጠናክሯል!

በላሊጋ የዛሬው ጨዋታ ባርሴሎና ላስ ፓልማስን 2-0 አሸንፏል። ሁለቱን ግቦች ዳኒ ኦልሞ እና ፌራን ቶሬስ አስቆጥረዋል! ⚽️

የሊግ ደረጃ:
1️⃣ ባርሴሎና - 54 ነጥብ
1️⃣7️⃣ ላስ ፓልማስ - 23 ነጥብ

ቀጣይ ጨዋታዎች:
📅 አርብ: ሪያል ቫላዶለሊድ vs ላስ ፓልማስ
📅 እሁድ: ባርሴሎና vs ሪያል ሶሴዳድ


⚽️ ሰማያዊዎቹ ተከታታይ ሽንፈት አስተናገዱ! 🔵

አስቶን ቪላ በቼልሲ ሜዳ 2-1 አሸንፈዋል። የቪላ ጀግና ማርኮ አሴንሲዮ ባስቆጠራቸው 2 ግቦች ሲሆን፣ ለቼልሲ ኢንዞ ፈርናንዴዝ ነበር ያስቆጠረው።

ማርከስ ራሽፎርድ 2 ለግብ የሆኑ ኳሶችን አመቻችቷል! 🎯

መደብ:
6️⃣ ቼልሲ - 43 ነጥብ
7️⃣ አስቶን ቪላ - 42 ነጥብ

ማክሰኞ የሚጫወቱት:
🔵 ቼልሲ vs ሳውዝሀምፕተን
🦁 ክሪስታል ፓላስ vs አስቶን ቪላ

Показано 20 последних публикаций.