ባዶ እኮ ነች።
(የሞገሤ ልጅ)
መጀመርያ፣
ኑ እንፍጠር በመባባል አምላክ ራሱን ሳያማክር፣
ዘረጋግቶ፣
እውን ሆነው እስኪታዩ እስኪኖሩ ምድር ጠፈር፤
ለባዶነት፣
ያጨው ነገር ለመኖሩ ስለማናውቅ ምንም ባንል፣
ምድራችን ግን፣
ከአካሏ ተቀናንሰው ሳር ቅጠሉን እስክታበቅል፤
አሁን ጠባ፣
በቤት ላይ ቤት እንዲሰራ ሠው ወገኗን ያስገደደች፣
ዛሬ ሳንደርስ፣
ጅማሮዋን ብቸኝነት ያካረማት ባዶ እኮ ነች።
ልክ እንደሷ፣
ሃ ማለቴን አፍ ሳይሆነው ጅማሮዬን አብሮት ሳይቆም፣
አሁን መቶ፣
ሄደሽ መቶ ባዶነቴ መከበቤ ቢደመደም፤
ባዶነቴ፣
አዲሥ ሕይወት አዲሥ መንገድ እንዲያመጣ ምድር ሆኜለት፣
መከፋቴን፣
መቀየሩ ስለማይቀር ባዶነቴን ገጠምኩበት።
ገጠምኩበት..
አልወደኩም፣
ሆኖ ሲታይ ባልጣለው ፊት ላልወደቁት ሲመሰክር፣
ያሳምናል፣
የአይን አዋጅ ለሆነበት ዝናን ማድመቅ ቀሪን መቅበር።
አንድ አንዴ ግን፣
ግዳጅ ጥሎ ፎካሪ ላይ ተሽመድምዶም መዘባበት፣
ቀን ያወጣል፣
ወድያ ወዲህ ተንጎራዳጅ አምላክ ፈቅዶ ከዞረበት።
ያን እለት ግን..
ራሱን ሆኖ ከጣለው እጅ ተፍገምግሞ የተነሳ፣
ባዶነቱን፣
ምርኩዝ ስጡኝ ባላለ አፍ መተኛቱን እስኪረሳ፤
ተመርኩዞ፣
ሲደጋግፍ ቆሞ ሊታይ የራሱ ቀኝ ራሱ ሆኖ፣
ባዶነቱ፣
ኃይል ይወልዳል ብርቱ ጉልበት ከድካሙ ተሰናስኖ።
ባዶ አረግሺኝ?
እንኳንም ሆንኩ!
አንቺን ይድላሽ፣
ግን ጨርሰሽ አትራቂው ብቸኝነት ከሚጠላሽ!
ለምን አልሺኝ?
ካልሺኝ እማ..
ምንም መሆን ምንም ነው፣
ለባዶነት ልኩ ያንሳል፣
አለመኖር ካጣ ፍጥረት ጉድለት ሞልቶት በዝቅታው ሺ ይብሳል።
ባዶነት ግን..
እርቃን መሆን ሸክሙ ከብዶ፣
ቋጠሮውን ለማላላት፣
አዲስ መንገድ ይፈልጋል፣
አዲሥ ነገር ለማሳየት።
By
@eyadermoges1@getem@getem@paappii