ተከታታይ መንፈሳዊ ልብወለድ
#ሁለት-ሰይፍ
ክፍል ስምንት(ሜርሲ✍️)
"ሄይ... ብዙ አትረበሽ::ቁጭ በል::"
ያልጠበቀው ስለ ነበር ግራ እንደተጋባ ቁጭ ብሎ ተመለከታት::
"ለእኔ አይደለም::ሰዎችን የተሳሳተ ነገር..."
"ሰዎችን ተዋቸው::እኔንም ጨምሮ::ስህተቷን ከመቀበል የምትሸሽ ሰው ሆና የታየችኝ::እናቷ እንዳለችው አርፋ ከሆነም የአንተ ሳይሆን የእሷ ጥፋት ነው ማለት ነው::"
"ይሄን አልጠበቅኩም ከምር::"
"ምን ተነስቼ እንድሄድ ጠብቀህ ነበር!?..እኔም ያለፍኩበት ነገር ስለሆነ እንደዚህ አይነት ሰዎችን አልስታቸውም::" አለች ፈገግ ብላ::
"ለምን እንደ እህቴ መሆን እንደምፈልግ አሁን ገባህ?" ማክቤል ነበር::
ናትናኤል ፈገግ ብሎ አንገቱን በአዎንታ ነቀነቀ::
"ዩ ጋይስ አር አሜዚንግ ከምር::"
* * *
ናትናኤል ከበሩ ቆሞ ሲመለከታት ቆይቶ በእጁ የያዘውን ጋቢ አልብሷት ከአጠገቧ ይቀመጣል::
ዞራ አይታው:-
"ኦንላይን ሥራ የለም ዛሬ?"
"ዛሬ ትንሽ ልረፍ ብዬ ነው::"
"ምን እንደምትሰራ ማወቅ እችላለሁ?"
ፈገግ ብሎ እያያት:-
"ለአጠያየቅ ትህትናሽ ስል ብቻ እመልሳለሁ::" ስቃ አይኗን ከበሩ ትመልሳለች::
"ፍሪላንሰር ነኝ::ሁለ ገብ ነኝ እዛም እዚህም::ዲጂታል ማርኬቲንግ.. ትሬድ አደርጋለሁ... ኤዲትንግ... ግራፊክስ... ኦንላይን አስተምራለሁም::"
"ርሊይ?"
"ያ.... አይ ምን ገንዘብ የሚያስገኝ ኦንላይን ላይ የሚሰራ ሁሉ ነገር እንዲያልፈኝ አልፈቅድም::"
"ኃጢያትም ቢሆን?"
"እሱን እንኳ አልሞክረውም::"
"ስቀልድህ ነው::" አለች ፈገግ ብላ::
"ኃጢያት ባይሆኑም ወደ ኃጢያት መሩኝ እንጂ::"
በዝግታ ዞራ ተመለከተችው:-
"እንዴት?"
"እረጅም ታሪክ ነው::ሌላ ጊዜ::"
"እዚህኛው ጥያቄዬ ላይ ትህትና የለበትም ማለት ነው::"
"እንደዛ ማለቴ ሳይሆን.."
ሁለቱም ይስቃሉ... ሳቃቸውን የሚያቁአርጥ ድምፅ ሲሰሙ ሳራ ብድግ አለች::
"ማክ.." እየሮጠች ወደ ውስጥ ስትገባ ናትናኤልም እየተከተላት ገባ::
ማክቤል ከመኝታ ክፍል ወደ ሳሎን ባለው ደረጃ በባዶ እግሩ እየተንደረደረ የእናቱን እና የአባቱን ስም እየጠራ ሲወርድ ተመለከቱት::
ሳራ እየተንደረደረች ሄዳ ከስር ተቀብላው አቀፈችው::
"ማክ.. እኔ.. ነኝ... እኔ.. አለሁልህ.... እኔ.. አለሁልህ.. ቅዘት ነው::" እያገላበጠችው እየሳመችው እና እያቀፈችው ናትናኤል የሚሆነውን በዝምታ ይመለከታል::ማክቤል መጥራቱን አቁሞ ሲረጋጋ ወደ ሶፋው በመሄድ ስትቀመጥ እሱ ከሶፋው ወጥቶ ከእግሯ ጭንቅላቱን አስደግፎ አይኖቹን ይጨፍናል::ጋቢውን ከጀርባዋ አንስታ እሱን በማልበስ ፀጉሩን እያሻሸች ወደ ናትናኤል እንባ ባቀረሩ አይኖችዋ ተመለከተች::በዓይኑ ደሕና መሆኗን ሲጠይቃት አፀፋውን ትመልሳለች::
"ሂድ ተኛ::እኔ እጠብቃታለሁ::" አለችው ዝግ ባለ ድምፀት::አንገቱን በአዎንታ በመነቅነቅ በሩን ገርበብ አድርጎ በመውጣት ወደ ክፍሉ ገብቶ ከሶፋው በመቀመጥ በእረጅሙ ይተነፍሳል::
በር ሲንኳኳ ብድግ ይል እና ሲወጣ ሳራንም ከበሩ ያገኛታል::በመገረም እያያት:-
"አንቺ ከማክቤል ጋር ሁኚ::ጥለሽው መውጣትም አልነበረብሽም::እኔ አወራታለሁ::"
"ናቲ.."
"ፕሊስ... ወደ ውስጥ ግቢ::"
እሷ ስትገባ እሱ ወደ በሩ በፍጥነት በመሄድ ይከፍተዋል::ያደረሳት መኪና ሲሄድ ተመልክቶ ወደ እሷ ይዞራል::
"ሄይ ቆንጆው ልጅ.... ክልስ ነህ አይደለ?"
"በአያቴ::"
"ጠርጥሬ ነበር::" አለች በእጇ እያጨበጨበች ድምፁአን ከፍ አድርጋ::
"ሄይ ድምፅሽን ቀንሺ::ማክ ተኝቷል::"
"ኦውው... እኔን ወንድሜን... እሺሺሺ... አልረብሽም::"
ልትገባ ስትል በሩ አደናቅፉአት ልትወድቅ ስትል ደግፎ ይዙአት በሩን በአንድ እጁ ይዘጋዋል::
"ሂሂሂ.... ይሄን ፊልም ላይ ብቻ ነው የማውቀው የነበረው::"
"እባክሽን ዮሃና..."
"ኦውው... ማክ... እሺሺሺሺ...." አንድ ጣቷን በአፉአ በማድረግ ድምፅ ሳታሰማ ትስቃለች::
ወደ በር ሲደርሱ ቆም ይልና :-
"ዛሬ እኔ ጋር ታድሪያለሽ::"
"ህ?" ቀና ብላ ስካር ባጨናበሰው አይኖችዋ ትመለከተዋለች::
"ማክቤል ደህና አይደለም::"
"ኦውው... ከቆንጆው ልጅ ጋር ላድር ነው::"
"እንደዛ አይደለም::" ደንገጥ ብሎ::
"ገብቶኛል ባክህን...." ወደ እሱ ክፍል ይገባሉ::
* * *
አይኖችዋን በግድ ስትገልጥ ከፊቷ ናትናኤል ተቀምጦ ስትመለከት በርግጋ ትነሳለች::የተኛችበትን ሶፋ ትመለከታለች::
"እዚህ ምን እሰራለሁ!?"
"ምንም ነገር አታስታውሺም?"
"በፍፁም::"
"ሰው እንዴት እራሱን በዚህን ያህል ልክ ይበቀላል!?... ፍትፍት ላዘጋጅልሽ::"
በዓይኗ ሸኝታው ቤቱን ግራ በመጋባት ትቃኛለች::
Like🥰 Comment📩 Share💫ቀጣዩ እንድለቀቅ
ይቀጥላል...
ግጥሜን ለኢየሱስ
💙እወዳችኋለሁ 💙
---------------------------------------------------------
SHARE
|
@GITIM_ALEM |
|
@GITIM_ALEM |
--------------------------------------------------------
SHARE
Contact me
@abu_ND8